ከሩሲያ ጎን ሆነው በዩክሬኑ ጦርነት ለመሣተፍ ዛሬ በሩሲያ ኤምባሲ የተሰለፉ ወጣቶች

April 18, 2022
278645274 10159200243354915 2329566138872678746 n
በወጣቶቹ ውስጥ የሚታየው የመጨረሻ አማራጫቸው ሄዶ ወይ መሞት ወይ መለወጥ ነው። በሃገርህና በመንግስትህ ተስፋ ስትቆርጥ እንኳን ይሄ ሌላም ይደረጋል። አይዞን ወገኔ!

እያደሩ ማነስ

በምስሉ ላይ የሚታዩት ኢትዮጵያውያን በሩስያ ኤምባሲ ደጅ የተሰለፉት ለሩስያ ለመዋጋት /ለመመዝገብ/ ነው እየተባለ ነው! ሩስያ በበኩሏ (ኤምባሲው ለአል አይን እንደገለጸው) ‘እኔ ወታደር እየመዘገብኩ አይደለም :ለእኛ ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት ነው የተሰበሰቡት ‘ብላለች! በሃገሪቷ ባለው የኢኮኖሚ ሁኔታ (ስራ አጥነት) እንኳንስ ሩስያ የትም ድረስ ለመሄድ የሚነሳ ወጣት መመልከት አይገርምም!
እየገረመኝ ያለው የመንግስት ነገር ነው።
በአለምአቀፍ ህግ ሰዎች ለሃገራቸው ካልሆነ በስተቀር ለሌላ ሃገር ተቀጥረው መዋጋት አይችሉም!(መርሲናሪዝም በየትኛውም ቦታ የተወገዘ ነው) ኢትዮጵያ ራሷ ፈራሚ በሆነችበት ‘መርሲናሪዝምን ከአፍሪካ ምድር ለማስወገድ የተደረገ ስምምነት’ (ሊብረቪል 1977) ሃገራት ዜጎቻቸው ለሌላ ሃገር ተቀጥረው እንዳይዋጉ የሚችሉትን ሁሉ ማድረግ እንዳለባቸው የተደነገገ ሲሆን በዚሁ ስምምነት አንቀጽ 7 ላይ ፈራሚ ሃገራት ይህን ድርጊት በሃገራቸው የውስጥ ህግ ‘እስከ ሞት ድረስ የሚያስቀጣ ወንጀል ‘ ማድረግ እንዳለባቸው ይገልጻል!
እንግዲህ ኢትዮጵያም በዚሁ ተስማምታ ፈርማለች ።መፈረምም ብቻ ሳይሆን እኤአ በ1982 በሃገር ውስጥ አጽድቃለች! ይህን በፎቶው ላይ የሚታየውን ድርጊት አንዳንዶች ሊዘባበቱበት ቢችሉም የጸጥታ አካላት ግን ዝም ብሎ ማየት የለባቸውም! በአንድ ወቅት በአፍሪካም ሆነ በአለም አለም አቀፍ ህግን በማስከበርም ሆነ በማክበር ምሳሌ በነበረች ሃገር ይህን አይነቱን ነገር ማየት ያማል!
እስከአሁን ባለማወቅ ዝም ተብሎ እንኳን ቢሆን ከነገ ጀምሮ ግን ይህን አይነቱ ነገር ሊቆም ይገባል!

Andualem Buketo FB የተገኘ

2 Comments

  1. አንዱ አለም ቡኬቶ የጻፍከው በነጻው አለም በነጻነት ይሆናል ወይም ቤተ መንግስት አካባቢም ልትሆን ትችላለህ። የምታያቸው ወጣቶች ባለው መንግስት ተስፋ የቆረጡ ወደፊት የማይታያቸው ድህነታቸውንና ረሃባቸውን ችለው እንዳይኖሩ የሺመልስ፤የጁዋር፤የታየ ደንዳ፤የዳውድ ኢብሳ፤የአህመዲን ጀበል፤የቄሮ መንግስት በተኙበት ያርዳቸዋል ከዚህ የተሻለ መፍትሄ ልትጠቁማቸው ትችላለህ?

  2. የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች። ወራዳ ሁሉ። ለማን ለመሞት ነው ራሺያ ድረስ የሚጓዙት? ለነጩ ዓለም? ጉዳዪ ትክክል ከሆነ ይህ ወርደት እንጂ ጀግንነት አይደለም። ዛሬ ሩሲያ በዪክሬን ላይ የምትፈጽመው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እንኳን ከሩሲያ ጎን ተሰልፎ ለመዋጋት ቀርቶ ሩሲያዊያንን በስም መጥራት ይከብዳል። ግን ሩሲያና ወያኔ አንድ ናቸው። በጅምላ መጨፍጨፍ። የራሳቸው ያለሆነ መሬትን የእኔ ነው ማለት፤ በሃገራቸው ላይ ሰውንና ነጻ ሚዲያን ማፈን። ፕሬዝደንት ፕቱን መውደቂያውን እያመቻቸ እንደሆነ ተግባሩ አስረግጦ ያሳያል፡፤ ከ 20 ዓመታት አስረሽ ምቺው የአፍጋንስታን ፓለቲካ በህዋላ እግሬ አውጭኝ ብለው ከፈረጠጡት ከአሜሪካኖች እንዴት ሰው አይማርም? ግራም ነፈሰ ቀኝ የሃበሻው አፍቃሪ ራሺያ መሆን መሰረት የለሽ ነው። አልፎ ተርፎም ሩሲያ ሂዶ ለመዋጋት መመኘት ለእንጀራ ነው ወይስ ለፍትህ? ሃገርህ ለውትድርና ትፈልግሃለች ሲሉት የሚደበቀው አይደል እንዴ አሁን ራሺያ ሄጄ እዋጋለሁ የሚለው። ሂድና እንደ ጧፍ ተንቀልቀል። ሞዛዛ ሁሉ!
    አሁን ራሺያ የምትፈጽመውን አይነት መሬትና ንብረትን የማቃጠል የፓለቲካ ትኩሳት ቻይና በቅርብ እንደምትጀምረው የታወቀ ነው። ዓለም አብዳለች። የአሜሪካና የአውሮፓ እሳት ለዪክሬን ማቀበል የእብደቱን ከፍታ የሚያሳይ ነው። እኛ መሞት አንፈልግም እናንተ ግን ተገዳደሉ። አይ ዲሞክራሲ። የውሻ ዲሞክራሲ!
    የቻይና አለሁ አለሁ ማለትም ምዕራቡ ዓለም ኩባኒያውን በዚያችው ሃገር በማስፋፋቱ እንጂ የቻይናው ኢኮኖሚ ብቻውን ዘመን አይሻገርም። አለሙ ሁሉ የተጠላለፈ ነው። ለዚህም ነው የሃገሮች የብቻ ፓለቲካና ኢኮኖሚ አያዋጣም የምንለው። ቻይና የዓለም ጸር እየሆነች ነው። በቅርቡ በሩዋንዳ እስራት የተፈረደበት ቻይናዊ የሃገሬውን ተወላጅ አስሮ ሲደበድብ ቪዲዪ ተነስቶ እንደ መረጃ በመቅረቡ ነው። ስንት ቻይናዊያን በሃገራችን ላይ ሰቆቃ እየፈጸሙ በነጻነት ይኖራሉ? ቻይናዎች ከሰው ባህሪ የወጡ፤ ያዪትን የሚበሉ፤ በጥቁር ላይ ጭፍን የሆነ ጭካኔና እይታ ያላቸው ናቸው። አሁን በአፍሪቃ ያለ ቅጥ የተንሰራፉት ለመዝረፍና ለማዘረፍ እንዲመቻቸው ነው። በሌላ መልኩ እንግሊዞች በምድራቸው ጥገኝነት የጠየቁ ጥቁሮችን ወደ ሩዋንዳ ለማጓጓዝ ስትዘጋጅ፤ ከምሥራቁ የመጡ የነጭ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለምን በሃገሯ እንዲቆዪ ፈቀደች የሚለውን መጠየቅ ያስፈልጋል። ግን በተተራመሰው ዓለም የራስን ቤት በእሳት እየለኮሱና የሌሎችን እያቃጠሉ ስደተኛ ነኝ ማለት የፓለቲካ ሽፋን ሆኗል። ዛሬ በሱዳን የሚኖሩት እልፍ የትግራይ ስደተኞች አንዴ ታጣቂ፤ ሌላ ጊዜ ስደተኛ፤ ሲሆኑ ማየት ምን ያህል ልብን ያደማል? ቢቻልና አብሮ መኖር ቢመረጥ ሰው በሃገሩና በወንዙ ላይ ተቸግሮ መኖር ይሻል ነበር። ይህ ግን አልሆነም። ሁሉም መሰደድን እንደ ትልቅ ተንቦላ እየቆጠረ አሁን ደግሞ ይባስ ተብሎ ከራሺያ ጎን እንዋጋለን ማለት ምን የሚሉት እብደት ነው። የራሺያ ኤምባሲ ነገሩ ትክክል ቢሆንም ነው ብሎ አይናገርም። ስለሆነም የሰልፉ ሚስጢር እንደተሰላፊዎቹ ዓላማ ሁሉ ድብቅ ነው። ቆይተን እንይ። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

278576930 354685613364179 8688840986409169848 n
Previous Story

በጦርነትና ግጭት ውስጥ ሆነው የተፈተኑና የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ2014 ዓ.ም መደበኛ ተፈታኞች ጋር እንዲፈተኑ ውሳኔ ተላለፈ

abiy 2 1
Next Story

አቢቹ ፦ ነቄ ተብለሀል! (እውነቱ ቢሆን)

Latest from Blog

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የሚደነግግ አዋጅ ቀረበ

ዮሐንስ አንበርብር በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ ንብረት የመውረስ ድንጋጌም በአዋጁ ተካቷል አዋጁ የሚፀድቅ ከሆነ 10 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ተፈጻሚ ይሆናል ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ሰው ወይም ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሀብት አፍርቶ ምንጩ ሕጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ያልቻለ ሰው፣ ንብረት በመንግሥት እንዲወረስ የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ
Go toTop