አቢቹ ፦ ነቄ ተብለሀል! (እውነቱ ቢሆን)

ሳናውቅህ ሙሴ ብለንሀል፡፡ ፎቶህን በቲሸርት አሰርተን ለብሰናል፡፤ደግፈንህም ቆመናል፡፡አሁን አወቅንህ፡፡ ተራ አታላይ ብቻ ሳትሆን እውቀትም ችሎታም የለህም፡ ይህንን የዋህ ህዝብና ይህችን ታላቅ ጥንታዊት አገር ቁማር ተጫወትክባቸው፡፤

በተለይ በኦሮሙማ ታውረህና በአማራ ጠልነት ሰክረህ ከአማራ ጠላቶች ጋር አብረህ አማራውን በየአቅጣጫው አስጨረስከው፡፡ በህይወት የተረፈውንም እንዳያንሰራራ አደረግሀው ፤ በኩሩው ኢትዮጵያዊ በአፋር ህዝብም ላይ እንደሁ አደረግህ፡፤ በትግራይም በወያኔ ሰበብ ህዝቡ ፍዳውን እንዲያይ አደረግከው፡፡ በብዙ መቶ ሽህ የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶችም እብሪተኛው ወያኔ ለከፈተው ጦርነት ጦስ አስደረግካቸው፡፤ በአጠቃላይ ይህንን ሁሉ ማስቆም በምትችልበት ቦታ ላይ አላግባብና ያለችሎታህ ተኮፍሰህና ሴራ እየጎነጎንክ ለህዝቡ ስደትን.መከራን. ድህነትን. በሽታን. ስቃይን. ሞትንና.እልቂትን ደግስክለት፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆንና የህዝቡ ሰቆቃና የግፉ ጽዋ ሞልቶ መፍሰስ ለአንተ ምንም ማለት አልነበረም፡፡ አሁንም ምንም ማለት እንዳልሆነ በይፋ ወጥተህ ደሰኮርክ፡፡ አቅራራህ፡፡ ቢገባህ ኖሮ በስራህ ባፈርክ ነበር፡

ይህ ሁሉ ሳይበቃህም እንደገና አሁን ላይ ደግሞ በስሌት ከወያኔ ጋር አዲስ ሽርክና ፈጥረህና አማራን ለማጥፋት ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆነህ በአማራው ላይ አለም አቀፍ ዘመቻ ከፈትክበት፡፡ በወለጋና በቤንሻንጉል፣ በሰሜንና በምእራብ ሸዋ አማራን በኦንግ ጦርና በመንግስት ሀላፊወች ጭምር አማራን የማጽዳቱ ስራ በተለይም በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ አማራን ነቅሎ ኦሮሞን የመትከሉ ተንኮልና ድብቅ ሴራ የማይታወቅ እንዳይመስልህ፡ አመንክም አላመንክም እነዚህ ሁሉ የክህደት ሴራወችህ ነቄ ተብለዋል፡፡

በከንቱ ትባዝናለህ እንጅ አገሪቱን ሆን ብለህ እንደዚህ አፈራርሰህ ሰላም አግኝቶ እንዲኖር የምትመኝለት የኦሮሙማ ስሌት ግቡን አይመታም፡፡ አይሳካም፡፡ አገሪቱም የማንም ሳትሆን ትቀራለች፡፡ አንተም ፍርድህን አግኝተህ በታሪክ አተላነት ትታወሳለህ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  መስቀልን:- ከሺሕ ዘመን ታሪካችን እና ከኢትዮጵያ ቤ/ክ አንጻር በጨረፍታ. . . በዲ/ን ተረፈ ወርቁ

3 Comments

  1. ተሳለቅ
    አቢይ አህመዴ
    አይክፋህ ተሳለቅ በእልቂት በአሳሩ
    ሙሶሎኒ፣ ሂትለር
    እንዲሁ ነብሩ
    ፈርዖንም ተሳልቋል ያኔ በዘመኑ
    አንተም በል ተሳለቅ ጽዋህ እስኪሞላ እስኪነጋ ቀኑ
    የነፍሰ ጡር አንገት እየገዘገዙ
    አማራ አሰድደው መሬት እንዲይዙ
    እየተደራጁም ትራክተር እንዲገዙ
    የምትመክራቸው በቃላት በብዙ
    ገነትን ዓልመው ገሃነም ሲጓዙ
    ፈትተህ የለቀቅከው የሲዖሉ ጭፍራ
    ሰው ማጨድ ጨርሶ እያጨደ አዝመራ
    አማረልኝ ብለህ ብትተውን በሚዲያ
    ዋጋ ትከፍላለህ ነገ ከነግ ወዲያ ።

  2. ነጥብ አንድ፦ እንደ መግቢያ መሬት ላይ ስላለው ሁኔታ፦
    ለብዙወቻችን የሁሉም ችግሮች ምንጭ መርዘኛው ወያኔ ሊመስለን ይችላል፡፡ ቢመስለንም ስህተት የለበትም፡፤ ምክንያቱም ተውሳክ የበዛበትን የወያኔ ህገ መንግስት ከማውጣት አንስቶ እስካሁን እያመረቀዘ ያለውን የዘር መርዝ በመላዋ አገሪቱ ውስጥ ዘርቶ ህዝቡን እያናከሰው ሲሆን መጨረሻ ላይ ወያኔ በህዝቡ አመጽ ተገፍቶ ወደ መቀሌ በመሄድ ትግራይ ህዝብ ጉያ ውስጥ ሌገብ ችሏል፡፤ 27 አመታት ሙሉ ከደሀዋ ኢትዮጵያ የዘረፋቸውንም ቢሊዮኖች ዶላሮች በውጭ አገራት አሽሽቶ መልሶ ኢትዮጵያን ለመጉዳት እየተጠቀመበት ነው፡፡ በአንድ ወገን ከጠያቂነትና ከወንጀለኝነት ለመዳን በየአቅጣጫውና በየፈርጁ ፈረንጅ ከመደልል አንስቶ የራሱን ሶለግ ውሾች 24 ሰአት እንዲጮሁለት እያደረገ ነው፡፡ እራሱ ወያኔ በጫረውም የእብሪት ጦርነት አያሌ ጉዳቶችን አድርሷል፡፡ስለሆነም ወያኔ ማለት ይህ ስለሆነ የሁሉም ችግር ምንጭ ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል፡፡
    ነገር ግን ህዝቡ የደም ዋጋ ከፍሎ ባመጣው ለውጥ ላይ ቁብ ያለው የኦሮሙማው ቀንደኛ መሪ አብይ አህመድ በተለይ የአማራን ህዝባዊ ሀይል እንቅስቃሴን ለማፈንና አማራን ለማስፈራራት ሲል “እኛኮ የወያኔ ግርፍ ነን” ብሎ ሲኩራራና በትህነግ ፖለቲካ ጥፍሩን ነቅሎ እንዳደገ በኩራት ሲናገር በቅርቡ ራሱ በይፋ መስክሯል፡፡ ስለሆነም ወያኔ ከወደቀ በኋላ ለተፈጠሩት የአገሪቱ ችግሮች በሙሉ ወያኔን አሁንም ተጠያቂ ማድረግ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን እንደማለት ነው፡፡ የአስተዳደር ጥበብና ክህሎት ማጣትም ይሁን ጠባብ የኦሮሙማ ተረኝነት፣ ዘረኝነትና ኢትዮጵያዊነትን አጥፍቶ አገሪቱን ኦሮማዊት የማድረጉ ከንቱ እቅድና ስውር ደባ የኦሮሙማው መሪ አብይ አህመድ የተከተለው መስመር አገሪቱን ለዚህ አሁን ላለችበት አሳዛኝ ሁኔታ ስላበቃት ቀጥተኛ ተጠያቂ ነው፡፡ ምክንያቱም ስልጣኑ በእጁ ነበረና፡፡
    ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ አሁን እውነታ ስንመለስ አዋቂ መሳይ በእውን ግን ልሙጡ ደደብና የኦሮሙማው ቀንደኛ አብይ አህመድ መላዋን እኢትዮጵያና ከሁሉም በባሰ ደረጃ ጨዋዉን የአማራ ህዝብ ቁማር እየተጫወተበት ያለው በእነ ደመቀ መኮንን፣ ተመስገን ጥሩነህና አገነሁ ተሳገር ወዘተ አይነቶቹ ሆዳም አማራ ሱመኞች እንደሆነ ወያኔም ኦነግም ድፍን የአማራ ህዝብም አሳምሮ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ነውረናው አብይ በነዚህ የችነት አጋሰሶች አሽከርነትና መሰል ተላላኪወቹ ጫንቃ ላይ ተንተልጥሎ ያለ ሰው ነው፡፡ ስለሆነም በተለይ ከሁሉም በባሰ ሁኔታ ገፈት ቀማሹ የአማራ ህዝብ ሆይ፦ ቀድመህ እነዚህን ተላላኪወች ያለርህራሄ በነጻ እርምጃህ በያሉበት አስወግድና ወደዋናወቹ ጠላቶችህ ማለትም ወያኔና ኦነግ ላይ ተባብረህ ተነሳ፡፡ ከባንዳውና የሹምባሱ ልጅ ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ በአገራችን ታሪክ እንደ አብይ በአማራ ጥላቻ የሰከረና በተረኝነት ያበደ ሰው ታይቶ አይታወቅም፡፡

    ነጥብ ሁለት፡ የአብይ አህመድ አጭር የአሁን ማንነት፦
    አብይ የሚያደርገው እያንዳንዱ ነገር በሙሉ የሚያደርሰውን ጉዳት አያዉቀውም፤ ቢያውቅም ስልጣኑን እስካስጠበቀለት ድረስ ለህዝቡና ለአገሪቱ ፈጽሞ ግድ የለውም፡፡ ምክንያቱም በልጅነቱ እናቱ ንጉስ እንደሚሆን ነግራዋለችና፡፡ በዚያ ላይ መርሳት የሌለብን አብይ አህመድ በሁሉ ኬኛ የተረኝነት የኦሮሙማ ልክፍት መለከፉን ነው፡፡ ስውር የኦሮሙማ መሪ ነው፡፡ እልም ያለ ውሸታም ብቻ ሳይሆን ፈሪ፣ ጨካኝና የወጣለት ዘረኛም ነው፡፡

    ነጥብ ሶስት፦አገር ከዚህ አልፋ እንዳትፈርስ ትንሽ ምክር ለእቡዩ አብይ አህመድ ፦
    አብይ ትንሽ እፈር!! ኢትዮጵያንና የዋሁን ህዝቧን በታሪክ አይተውት የማያውቁት መከራ ፣እልቂትና ስቃይ አደረስክባቸው፡፤ ከችሎታ ችሎታ የለህ፡፤ ከእውቀት እውቀት የለህ፡፡ ዝም ብሎ ጥራዝ ነጠቅ ነገሮችን ከዚህም ከዚያም እየቀራረምክ ያወቅህ መስሎህ ሰውንም አገሪቱንም ጎዳህ፡፡ በዙሪያህ ያሉት ደፍረው እንዳይነግሩህ አንድም እንደ አንተው ከእውቀት የጸዱ ናቸው አለበለዚያም ሆዳም አሽከሮችህ ናቸውና ሊነግሩህ አይደፍሩም፡፡ አንተ እንደ ሰው ስትመዘን ሙልጭ ያልክ ዱርየና ከእውቀት ነጻ የሆንክ ፣ቁጩ በሉ፣ አጭበርባሪና አታላይ መሆንህን የኢትዮጵያ ህዝብም፣ አለምም ፣ጢባጢቤ የሚጫወቱብህ ምእራባዊያን አለቆችህም ያወቁት የተናገሩትና የመሰከሩት ሀቅ ነው፡፡ አንተ ይህንን አታውቅም ወይንም ሌላ የቅዠት አለም ውስጥ ነው ያለሀው እንበል፡፡ እባክህ ሁሉም ይቅርና ለልጆችህና ለቤተቦችህ መሸማቀቅ ብለህ በቶሎ ስልጣኑን ለህዝባዊ ኮሚሽን አስረክበህ ገለል በል፡፤ ይህ ወንድማዊ ምክር ነው፡፡

  3. አብይ አህመድ አማራ ጠል ብቻ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያንም ይጠላል፡፡ በምላሱ ግን ሚሊዮን ጊዜ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ይለናል፡፡ በተግባር ግን አይደለም፡፡ አብይ አህመድ አገሪቱ እንዲህ ስትሆን ቢወዳት ኖሮና ራሱን ባያስቀድም ኖሮ ስልጣኑንም ቢሆን ለቅቆ የተሻለና መሬት ላይ ወርዶ ዉጤት የሚያመጣ መፍትሄን ባፈላለገ ነበር፡፡
    ሰውየው የኦሮሙማ አቀንቃኝ ብቻ ሳይሆን የኦሮሙማ መሪም ነው፡፡ ኦሮሙማን አንደኛ ኢትዮጵያን እየሸከከውም ቢሆን ሁለተኛ አድርጎ ነው ያስቀመጣቸው፡፡በተግባርም የሆነው ይሄው ነው፡፡ ኦሮሙማ ደግሞ የኦሮሞ የበላይነትን ማስፈን ማለት ነው ባጭሩ፡፡
    አብይ 23 ባንኮች በኦሮሚያ በኦነግ ሲዘረፍ ቃል አልተናገረም፡፤ አብይ የአማራወች ደም በኦሮሚያ እንደጎርፍ ሲፈስ ወጥቶ አክስክሬኖቹን በዘር ነው የቆጠረው፡፤አሁንም አማራወች በየአቅጣጫው እየተወረሩ፣ እየተሰደዱና እየትገደሉ ነው፡፡ ዘረኝነት ጥንብ ናት፡፡በዘረኝነት መኮፈስ ለጊዜው ጥሩ ሊመስለው ይችላል፡፡ዘረኛ መሆን ብዙም ሳይቆይ አገርን ወደማትወጣው ቅርቃር ይከታታል፡፡አድሎ የተደረገለት ዘርም ቀንደኛ ከሆኑት የስርአቱ ሰወች በስተቀር ህዝቡ ጥቅም አይደርሰውም፡፤ ምክንያቱም ስራው የሌብነት ነዋ፡፡
    ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ለመጥራት በሚጠየፈው በመርዘኛው መለስ ዜናዊ ጊዜ እንኳን አገሪቱና ህዝቡ እንደዚህ አይነት መከራና ፍዳ አልደረሰባቸውም፡፡ በፍጹም፡፡ አብይ ግን አገሪቱን ወደኦሮሞነት ለመቀየር ውስጥ ውስጡን እየሰራ በአፉ ህዝቡን ይደልላል፡፡ የሚያውቅ መስሎ ከየምናምኑ ለቃቅሞ እየቀበጣጠረልን በተግባር ግን እውቀት የለሽና ሙሉውን ዉሸታም ብቻ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ያሳዝናል፡፡
    ለዚህ ሁሉ መስላል የሆኑት እንደ አህያ የሚጭናቸው ሆዳም የአማራ ባልስልጣናት በጫማው ስር ሆነው እንድያገለግሉት ማድረጉ ነው፡፡ በእውነት እነርሱ ባይኖሩ ኖሮ አየር ላይ ተንሳፋፊ ነበር፡፡ ይህንን ሀቅ ድፍን አገር ያውቀዋል፡፡ ወይ ለህሊናቸው አልቆሙ ወይ አለንልህ ለሚሉት ለአማራ ህዝብ አልቆሙ ህዝባቸውን በማዋረድ የጭነት አጋሰስ ሆነው ሰውየው አገሪቱንና ህዝቧን እንደፈለገ እንድጋልብ ዋና መሳሪያ ሆነውታል፡፡ ይህ ግን ከእንግዲህ አይቀጥልም፡፡
    አብይ ከወያኔ ጋር ከመጋረጃ ጀርባ ሆኖ አማራን ለመምታት የሚያደርገው ጸረ አማራ ሴራ አማራውን ይበልጥ ጠንክሮ አንድ እንድሆን አድርጎታል፡፡ለምሳሌ አንዱን ብቻ እንጥቀስ፡፤ አማራው ህዝባዊ ሀይሉን ከጫፍ እስከጫፍ በአንድ አተያይ እንድያጠነክር ረድቶታል፡፡ ከሰውየው እቅድ አኳያ በፖለቲካው በኩልም ያለው እውነታ የጨለመ ነው፡፤ በውጭ ጉልበተኛ መንግስታትና ድርጅቶች በኩል ረዣዥምና ውስብስብ የሴራ ድሮችን በመጎንጎንና በአመራ ሹመኛ ተብየወች ትከሻ ላይ ተንጠልጥሎ እያወናበዱ አገርን ለመግዛት አክሮባት መስራት ከንግዲህ ወዲያ አያስከደውም፡፡ ወቅቱ አይደለም፡፡ አክትሞበታል፡፡ ተነቅቶበታል፡፡ወቅቱ የዚህ አይነቱ የማምታቻ ፖለቲካን አያስተናግድም፡፡ የውስጥ ሆዳሞቹም ሆኑ የውጭ ጉልቤውች ከህዝቡ የመኖርና ሰላም የመሻት ፍላጎት ውጭ ስላልሆኑ መላ እየተበጀላቸው ነው፡፡
    ስለሆነም ህዝቡ ወያኔን ‘ሆ’ ብሎ እንዳባረረ ሁሉ አሁንም በዘር መናቆሩን ትቶ በቃችሁን ብሎ ወጥቶ ነጻነቱን ለማወጅ ጫፍ ደርሷል፡፡ በዘር የተከፋፈለ ህዝብ ዉጤቱ የየትኛውም ዘር የበላይ ሆኖና ሰላም አግኝቶ እንዲኖር አያደርገውም፡፤ እውነትን፣ ሀቅንና ታሪክን ያካተተ መግባባት የፈጠርን እንደሆነ ሁላችንም እንድናለን፡፡ ይህንን አካሄድ ካልተከተልን ግን አገራችን ወድቃ ትቀራለች፡፤ተረኝነት ለጊዜው ለዘረፋና ለጭፍጨፋ ይረዳ ይሆናል እንጅ ዘላቂ መፍትሄን አያመጣም፡፡
    ተዘርፎና ተጨፍጭፎ የሚኖር ህዝብ እንደሌለ ታሪክ ራሱ ምስክር ነው፡፡ የሚገባው ይግባው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share