March 26, 2022
2 mins read

እስክታልቁ ድረስ ስከኑ ይሉናል የአማራ ክልል ፕሬዘዳንት – መስከረም አበራ

eeeef

ከታች የምታነቡትን ንግግር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተፅፎ ቢሰጠው እንኳን በዚህ ሰውዬ ሁኔታ ተረጋግቶ አይናገረውም። ወደ ብአዴን ወንበር የሚመጣው የመጨረሻው ሰው በገዛ ህዝቡ ላይ በመዝመት የመጨረሻው የሮቦትነት ፕሮግራም የተጫነበት ዞምቢ ነው! ይህ ሰውዬ ባለንበት ወቅት ያለው የመጨረሻው Version የሮቦትነት ፕሮግራም የተጫነበት ነው! የተጫነበትን ዘርግፎ ወርዷል!!!! ሰውዬው ንብረትነቱ የገዳዮቻችን ደመኝነቱ የሁላችን ነው!!!!!!!!!ደመኛውን ከትከሻው ያላሽቀነጠረ ህዝብ እንዲህ በለቅሶ ድንኳኑ እየተደነሰበት ይኖራል !
—————————-
“መፈናቀል ሁሉም ቦታ አለ። በክልላችን እንኳን ብንወስድ ከኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን
ኦሮሞ ተፈናቅለዋል። ከጎንደር ቅማንት ተፈናቅለዋል። ቤኒሻንጉል’ም ቢሆን አማራ ብቻ ሳይሆን ጉሙዝም ተፈናቅሏል። በኦሮሚያም ኦሮሞም ተፈናቅለዋል፣ ተገድለዋል። ሁሉም ጋር ህመም አለ። የአማራውን ብቻ ነጥሎ ማስጮህ ወደ ዘላቂ መፍትሔ አይወስደንም። እባካችሁ ፅንፍ እየረገጣችሁ አማራን ከሌላው ኢትዮጵያዊ አትነጥሉት። ሕገመንግስቱ ይሻሻል እያለን ነው። በጩኸትና በፅንፈኝነት አማራን ከሌላው እየነጠለን በሕገመንግስቱ ማሻሻያ ጉዳዮች ላይ ማነው ከአማራው ጋር የሚቆመው..? አማራን ከሁሉም ጋር እያናከሰን እረፍት አየነሳነዉ ነዉ።ስለሆነም እባካችሁ አክቲቪስቱም፣ ባለስልጣናቱም እንስከን እንስከን እንስከን..! ”
https://www.facebook.com/1286795063/posts/10222036635286729/?sfnsn=mo
ዶር ይልቃል ከፋለ
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር

7 Comments

  1. ሰውየው የአማራ ልጅ ሳይሆን የአማራ እንግደ ልጅ ነው፡፤ አማራ እንደዚህ ተሰብሮ አያውቅም፡፤ ያበጠው ይፈንዳ!!!

  2. መልሱ ይህ ነው፡፡
    ብናገር ቸገረኝ ብተወው መረረኝ
    የፈለገው ይምጣ እምቢኝ አሳፈረኝ

  3. አሁን ብናገር “ምን አገባህ ዖሮሞው በኛ ጉዳይ” እንደምትሉ ስነግራችሁ ፅንፈኝነታችሁን በመተማመንና በሃዘን ነው። ብትታደሉት ኖሮ ሰውዬው የሚሉትን በቅንነት ብታዩት እስቲ እኔ- ዘመኑ እንደፈቀደው – እንደ “ውጪ” ታዛቢ ልተርጉምላቸው በራሴው አረዳድ።

    አክራርያን ሆይ!

    የዓማራው ብሶት፣ እንግልትና ስቃይ ልቤ ሳይገባ ቀርቶ አይደለም። ከኔ መንበር ሆናችሁ ቁልቁል ብታዩት ችግሩ ውስብስብ ነው። አማራውን ከኛም ውስጥ ሆነው፣ የአማራውን ጃኖ ለብሠው ፣አማራውን መስለው ፀረ-አማራ ስራ የሚሰሩም ብዙ ናቸው። ወያኔ ህዝባችንን አይደለም የጎረቤቱን የየቤተሰቡንም እርስ በርስ እንዳይተማመን አድርጎ ለብዙ አስርተዓመታት ሰብሮብን እዚሁ ድንበራችን ላይ አሁንም ቆሞ እየፎከረብን ነው። ብቻችንን ሆነን፣ ነጥለን አንፋለመው ነገር እድሜልኩን አሽመድምዶን ነጥሎ ከሁሉ አናክሶን ኖረናል። ብዙዎቻችሁ ልጆች ናችሁ፣ ብዙም አይገባችሁም። አንዳንዶችማ እንዳታስቡ አድርጓችሁ ወያኔ ውሽልሽል አድርጎ በትኗችሁዋልና እስቲ በፈጣሪ የህዝባችንን ችግር ተረዱት። በደምፍላት የሚሆን ምንም ነገር የለም። ማንንም አይጠቅምም። እኔ የህዝባችንን ሞትና እንግልት በሚዛን አስቀምጬ መለካቴ ሳይሆን እዛም ቤት ወላፈኑ አለና የጋራው ጠላታችን ትህነግ ላይ በኖ እስኪጠፋ ጥይታችንን አናባክን ” ማለታቸውስ ከሆነ? እባካችሁ እስከመቼ ተባልተን እንዘልቀዋለን? ዘይትና ፉርኖ ብርቅ ለሆነበት ህዝባችን የናንተው አንዱ ሌላውን ማዋረድ ምን ይጠቅመዋል? አንቺ መስኪ አስተዋይ ትመስይኝ ነበር። ከሁሉ ተላትመሽ ከማ ጋር ልትወያዪ ነው እንደው አወያይ ሆነሽ በሽምግልና ብትጠሪ? ደግሞስ ሰውን ሳታዋርጂ በትህትና ፈጣሪ የሰጠሺን ክህሎት ብትጠቀሚበት እንዴት ሰውዬውን በረዳሻቸው። በሉ ውረዱብኝ ተመልሼ አየዋለሁ አልዋሽም።

  4. አባዊርቱ መስከረም ከፍያለውን መምከር አትችልም የማያውቀው ነገር የለም። የሚበልጠው ስለበለጠበት ነው። እንዲህ አይነት ገለጻ ከዚህ በፊት አገኘሁ ተሻገር፣አለምነው መኮንን ሲሰጡ ሰምቻለሁ ምናልባት የራሱን ወረቀት አነሳሁ ብሎ የነሱን እንብቦ እንዳይሆን ፍራቻ አለኝ በእይነቱም በይዘትም ተመሳሳይነት አለው። ወይም ደግሞ ለአማራ ክልል ንግግር የሚዘጋጅላቸው ከጠሚኒስቴር ቢሮ ሊሆን ይችላል

    መስከረምን በተመለከተ በሀሳብ ጥራት፣በንግግር ብስለት፣ፈጥኖ በመረዳት፣አርቆ በማየት ሰልፏ ከታላላቆቹ ተርታ ነው። በምክር መልክ እነ ስዩም ተሾመን አጀግኖ እሷን ቀዝቀዝ በይ ተይ አታስቢ ለተገፋው ድምጽ አትሁኝ ማለት መልካም አይመስልም። ለአማራ ግፍ መጮህ አማራ ላይ ከደረሰው ወንጀል በላይ ለምን ወንጀል እንደሆነ ግልጽ አይደለም። ምናልባት አማራው በመስከረም ልክና ከሷም በላይ ለወገኖቹ ባለመጮሁ ይመስለኛል።

    እንዲህ ያለ መከራ በህዝብ ላይ ሲደርስ የኔ የምለውስ ላይ ቢደርስ ብሎ መገመት ይገባዋል። ጥላ የተባለውን ነገድ መጥላት የተሸከመው ሀሳብ የራሱ ሳይሆን ፕሮግራም አድርገው የላኩት አካላት ይሆናል ማለት ነው።

    ተወልደ ገረ ማርያምም ሀገር ዘርፎ ፣የዜጋ ሞራል ጥሎ፣ ከወንጀለኞች ጋር አብሮ፣ ጡረታውን እስከብሮ ተሰናብቷል እድሜ ለዶፍቶር አብይ። ነገ HR ሰልፍ ላይ ከቱባ ትግሬዎች ጋር ሲደግፍ አየዋለሁ። ፍትህ ለታምራት ነጉራ፣መሳፍንት ጥጋቡ፣ለባልደራስ አባሎች።

  5. ለመሆኑ የአማራ ክልልን መሪ የሚመርጠው ማን ነው? የአማራ ክልል ሕዝብ ወይስ የፌደራሉ መንግሥት? የክልሉ ሕዝብ ከሆነ መሽሾምና መሻር መልመድ ይኖርበታል። ፌዴራሉ የክልል መሪዎችን እንዲሾምና እንዲሽር ወይም ወደ ፌደራል ከመውሰድ መከልከል ይኖርበታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

277166764 5290928907654514 8013396154406352331 n
Previous Story

የ’ኤች አር 6600’ ረቂቅ ሕግን የሚቃወም ሰልፍ በሳን ፍራንሲስኮ ከተማ ተካሄደ

Next Story

ፋኖ ሩሲያ ይዝመት፡ የአብርሃም ሃኒባልን ታሪክ ይድገም

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop