ፋኖ ሩሲያ ይዝመት፡ የአብርሃም ሃኒባልን ታሪክ ይድገም

መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com

ያገራትንና ግንኙነት በተመለከተ፣ ‹‹ቋሚ ጥቅም እንጅ ቋሚ ወዳጅ ወይም ቋሚ ጠላት የለም›› (There are no permanent enemies, and no permanent friends, only permanent interests) የሚል አባባል አለ፡፡  ባለመታደል ግን ይህ አባባል ለኢትዮጵያ አይሠራም፡፡  ኢትዮጵያ መሠረታዊና ዘላለሚዊ የሆነች ጠላች አለቻት፡፡ ይህችም ጠላት ገብጽ፣ ወይም አሜሪቃ፣ ወይም ፈረንሳይ ወይም ጣልያን አይደለችም፡፡  ስኮተትላንድም፣ ሰሜን አይርላንድም፣ ዌልስም አይደለችም፡፡  ይህች የኢትዮጵያ መሠረታዊና ዘላለማዊ ጠላት፣ እንግሊዝ የምትባል መሠሪ አገር ናት፡፡

ኢትዮጵያን በተመለከተ የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሙሉ በሙሉ የተመሠረተው በሚከተለው የሮማን ፕሮቻዝካ (Roman Prochazka) እሳቤ ላይ ነው፡፡

“የጦቢያ አያሌ ብሔረሰቦች የነጭ ባርያ የመሆን ምርጫቸውን የነፈጓቸው መሠረታዊ ዓላማቸው በነጭ ተጽእኖ መቃብር ላይ የጥቁርን ልዕልና መገንባት የሆነው የሐበሻ መሪወች ናቸው” (The numerous tribes who inhabit the Ethiopian state are being forcibly kept from European colonialism by Abyssinian rulers whose aim is to act as champions of all black people so as to attack and destroy Western culture)

የጦቢያ ዐበይት ችግሮች (በተለይም ደግሞ ከጎጠኝነት የሚመነጩ ችግሮች) ክራቸው ቢመዘዝ፣ ሂደው፣ ሂደው ጫፋቸው የሚገኘው፣ የፕሮቻዝካ ፀረጦቢያ እሳቤ የሚተገበርባቸው ዘዴወች እየተዘየዱ ለሁሉም ምዕራባዊ አገሮች ከሚሠራጩበት ከቁጥር አስር ዳውንኒግ መንገድ (Number 10 Downing Street) ነው፡፡ አሜሪቃን ጨምሮ ሁሉም ምዕራባውያን አገሮች የኢትዮጵያ ፖሊሲያቸውን የሚያረቁት፣ የምሥራቅ አፍሪቃ ጠበብቶች ናቸው በሚባሉት በመሠሪወቹ በእንግሊዞች ምክር መሠረት ነው፡፡  ባሜሪቃና በሌሎች የምዕራባውያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውስጥ የኢትዮጵያን ጉዳይ በበላይነት የሚቆጣጠሩት የአንግሊዝ ዘር ያላቸው ፀረጦቢያወች ወይም ደግሞ በነዚህ ፀረጦቢያወች የተመረዙ ባለስልጣኖች ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ፣ ሳይደግስ አይጣላምና፣ አገራችን ጦቢያ ዘላለማዊ ጠላት ብትኖራትም፣ በዚያው አንጻር ደግሞ ዘላለማዊ ወዳጅ የሆነች፣ በጭንቅ ቀን ሁልጊዜም የምትደርስላት አገር አለቻት፡፡  ይህችም የጦቢያ ዘላለማዊ ወዳጅ ሩሲያ ናት፡፡  ባድዋ ጦርነት ጊዜ የሩሲያ ቄሳር፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ እስታሊን፣ በሶማሌ ወረራ ጊዜ ብሬዥኔቭ፣ የጦቢያ ወዳጅነታቸውን በተግባር አስመስክረዋል፡፡  አሁን ላይ ደግሞ የምዕራባውያኑ ኖቤል ተሸላሚ የሆነው ጎጠኛው ዐብይ አሕመድ በምዕራባውያን እየታገዘ የጦቢያ ምሰሶ በሆኑት በአማራ ሕዝብና በተዋሕዶ ላይ የሚያወርደውን መቅጸፈት የሚቃወመው የፑቲን አስተዳደር ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ታጥቦ ጭቃ፣ አድሮ ቃሪያ - በድሉ ዋቅጅራ

ሩሲያኖች ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ደግሞ ከኢትዮጵያ ምንም ሳይጠይቁና ሳያገኙ ነው፡፡  አሜሪቃ በጦቢያ ላይ የገነባችው አንድ ነገር ቢኖር ለስለላ የምትገለገልበትን ቃኘው ጣቢያን (Kagnew Station) ብቻ ነበር፡፡  በንጉስ ኃይለ ሥላሴ በምትደዳደረው ጦቢያ ውስጥ የሚገኘውን ብቸኛውን ነዳጅ ማጣሪያ አሰብ ላይ የገነቡት ግን ኮሚኒስቶቹ ሩሲያኖች ነበሩ፡፡

መውደድ አይምሯዊ ሳይሆን ልቦናዊ ስለሆነ ምክኒያት አልባ ነው፡፡  የሚወድህ ሰው አረክለትም አላረክለትም ይወድሃል፡፡  ሩሲያም የፑሽኪንን አገር ኢትዮጵያን የምትወዳት ስለምትወዳት ብቻ ነው፡፡  የሩሲያ አምባሳደር ጥርት ያለ አማረኛ የሚናገሩ መሆናቸው ብቻ፣ ሩሲያ ስለ ኢትዮጵያ ስላላት አመለካከት ብዙ ይናገራል፡፡  በሌላ በኩል ግን መኻል አዲሳባ ላይ ብዙ ጋሻ ርስት የያዘው የእንግሊዝ ኤምባሲ፣ የኤምባሲው ሠራተኞች ኣማረኛ እንዲናገሩ ማበረታታት ይቅርና፣ የእንግሊዘኛ ትምህርት ቤት ከፍቶ ንግዱን እያጧጧፈ፣ የኢትዮጵያን ልጆች አማረኛ መናገርና ዲንጋ መወርወር ያስቀጣል እያለ በማስተማር፣ ከገዛ ሕዝባችን በሚዘርፈው በገዛ ገንዘባችን እገዛ አገራችን ላይ ያዋርደናል፣ ይልቁንም ደግሞ እንዲያዋርደን ፈቅደንለታል፡፡

ያገራቸን የጦቢያ የጭንቅ ቀን ደራሽ ሩሲያ፣ አሁን ላይ ደግሞ እሷ ራሷ በተወሰነ ደረጃ ጭንቅ ላይ ትገኛለች፡፡  ምዕራባውያን ያለ የሌለ ኃይላቸውን አሰባስበው እሷ ላይ በመረባረብ ህልውናዋን ክፉኛ እየተፈታተኑት ይገኛሉ፡፡  ስለዚህም፣ ትንሽ፣ ትልቅ ሳይባል ማናቸውም አይነት እገዛ ያስፈልጋታል፡፡ የኢትዮጵያን ወዳጅ ሩሲያን በተቻለው አቅሙ ቢያግዛት የሚወደው ደግሞ ኢትዮጵያን የሚወደው የአማራ ሕዝብ ነው፡  የአማራ ሕዝብ ደግሞ ባሁኑ ጊዜ እሱ ራሱ ጭንቅ ላይ በመሆኑ፣ ሩሲያን እምብዛም ማገዝ ባይችልም፣ ያለውን እስከወረወረ ድረስ ፈሪ አይባልም፡፡

በተለይም ደግሞ አንድ ሻለቃ ወይም ከዚያ በላይ የአማራ ፋኖ ወደ ሩሲያ ቢዘምትና አስፈላጊው ሥልጠናና መሣርያ ተሰጥቶት ዩክሬን ላይ ቢሰማራ፣ አፍሪቃን ዳግም ቅኝ መግዛት አለብን ብሎ የፎከረው የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን (Boris Johnson) በወዶ ዘማችነት ሽፋን የሚያሰማራቸውን የእንግሊዝ ወታደሮች እየገረፈ ልክ በማስገባት ለሩሲያ ከፍተኛ ውለታ ሊውልላት ይችላል፡፡  ይህ ውለታ ደግሞ የጦቢያንና የሩሲያን ወዳጅነት በደም ያስተሳስረዋል፡፡  ፋኖ ደግሞ ከሩሲያውያን የሚቀስመውን የመሣርያ አጠቃቀምና ወታደራዊ ጥበብ በመጠቀም፣ የአማራ (ስለሆነም የጦቢያ) ጠላት የሆኑትን ወያኔንና ኦነግን በቀላሉ አክስሞ የአማራን (ስለሆነም የጦቢያን) ቀጣይነት ማረጋገጥ ይችላል፡፡  የፋኖ ሩሲያ መዝመት፣ ጥቅሙ ለሩሲያ ብቻ ሳይሆን ራሱ ፋኖ ለቆመበት ዓላማም ጭምር ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኦህዴድና ስሙን የቀየረው ኢህዴን - ሰይፈ ምካኤል

ሰው ሁሉ እኩል ነው (all men are created equal) የሚል የወረቀት ሕገመንግሥት በመጻፋቸው የሚመጻደቁት ጆርጅ ዋሽንግተን (George Washington) እና ቶማስ ጀፈርሰን (Thomas Jefferson) ባሮቻቸውን ጽፈት ለመማር ሞክራችኋል በማለት ጣቶቻቸውን በሚቆርጡበት ዘመን፣  የሩሲያው ቄሣር ታላቁ ጴጥሮስ (Peter the Great) ግን፣ ኦቶማን ቱርኮች በባርነት የሸጡለትን የታላቁን ቀያኔ (poet) የእስክንድር ፑሽኪንን (Alexander Pushking) አያት፣ ኢትዮጵያዊውን አብርሐም ጴጥሮስ ሃኒባል (Abram Petrovich Hannibal) የክርስትና ልጁ (godson) አድርጎ፣ ፈረንሳይ ድረስ ልኮ በመድፈኛነት አስተምሮ በማስመረቅ (royal artillery academy of La Fere) የሩሲያ ቄሣር ጦር (Imperial Russian Army) ዋና ጀነራል (general-in-chief) አድርጎት ነበር፡፡  ፋኖወች ዩክሬን ቢዘምቱ ደግሞ፣ በጀግንነታቸው ሩሲያንም ጦቢያንም አኩርተው፣ የጦቢያን ዘላለማዊ ጠላት እንግሊዝን አሳፍረው፣ ጥቂቶቹ ፋኖወች አያታቸው አብርሐም ሃኒባል ከደረሰበት ከፍተኛ ወታደራዊ ደረጃ የማይደርሱበት ምንም ምክኒያት የለም፡፡

የጦቢያ ዘላለማዊ ጠላቶች የሆኑት ምዕራባውያን ለአማራ ሕዝብም ዘላለማዊ ጠላቶች ናቸው፣ ምክኒያቱም አማራና ጦቢያ አንድ አካል አንድ አምሳል እንደሆኑ፣ አማራ ያለ ጦቢያ፣ ጦቢያ ያለ አማራ እንደማትኖር ስለሚያውቁ ነው፡፡ ኢትዮጵያን አደረገችልኝ፣ አላደረገችልን ሳይል በኢትዮጵያዊነቷ ብቻ ከነፍሱ በላይ የሚወዳት የአማራ ሕዝብ ብቻ ነው፡፡  ሌሎቹ ግን በኢትዮጵያ ላይ ሰፍተውና ተንሰራፍተው፣ ሁሉን በጃቸው በደጃቸው አድርገው፣ በጨሳፊ (rocket) ፍጥነት ቢሊየነሮች ሁነውባት እንኳን፣ የጦቢያ ስም ሲጠራ የዘራቸው ያንዘረዝራቸዋል፣ የጦቢያን ባንዲራ ሲመለከቱ ደግሞ ዓይናቸው ደም ይለብሳል፡፡

የዩክሬን ጦርነት ምዕራባውያን ከሩሲያ ጋር የሚያደርጉት የውክልና ጦርነት (proxy war) እንጅ ከዩክሬን ብሔራዊ ጥቅም ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡  የምዕራባውያን ዓላማ ዓለምን ሙሉ በሙሉ እንዳይቆጣጠሩ እንቅፋት የሆነችባቸውን ሩሲያን ክፉኛ በማሳፈር፣ ከቻሉም ደግሞ ድምጥማጧን በማጥፋት፣ ለሌኛዋ ተገዳዳሪያቸው ለቻይና ማስፈራሪያ ማድረግ ነው፡፡  ከሩሲያ ጋር እየተዋጉ፣ ትኩረታቸው ቻይና ላይ መሆኑ በግልጽ የሚመሰክረው፣ የዩክሬን ጦርነት በዩክሬን ስም ይሁን እንጅ ለዩክሬን ሲባል አለመሆኑን ነው፡፡

ዩክሬን የተጎዳቸው ያልታደለች የጦር ሜዳ በመሆኗ ነው፡፡  ምናልባትም ደግሞ የኑክሌር አርማጌዶን ልትሆን ትችላለች፡፡  ለዚህ ደግሞ ዩክሬናውያን ከማንም በላይ መውቀስ ያለባቸው ዜሌንስኪ (Zelensky) የሚባለውን የራሳቸውን ቧልተኛ መሪ ነው፡፡  ይህ ሩሲያጠል (russophobic) ግለሰብ፣ የኑክሌር ትራጀዲን ከቲቪ ኮሜዲ መለየት የማይችል፣ በቤቱ ውስጥ ያለው ነጻነት ጎረቤቱን ለማስሸበር ቀርቶ ለመረበሽ መብት እንደማይሰጠው ያልተረዳ፣ ለኪውባ (Cuba) የሠራው ለዩክሬን መሥራት እንዳለበት የማያውቅ ወይም እንዲያውቅ ያልተደረገ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ምዕራባውያን እንደ ትልቅ ጀግና እየቆጠሩት፣ ዘረኛው ዊንሰተን ቸርችል (Winston Churchill) በየቦታው እየተዘዋወረ ቱልቱላውን ይነፋ እንደነበረው፣ እሱንም ቱልቱላውን እያስነፉት ከፍተኛ አድናቆት እስከቸሩት ድረስ፣ ዩክሬኖች ጨርሰው ቢያልቁ ግድ የሌለው አረመኔ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:   ለቤት ቀጋ ለውጭ አልጋ - አገሬ አዲስ   

ነገሮችን ሳሰላስላቸው የዩክሬኑ ዜሌንስኪ እና የጦቢያው ዐብይ አሕመድ በተወሰነ ደረጃ ይመሳሰሉብኛል፡፡  በመጀመርያ ደረጃ ሁለቱም አጭበርባሪ ተውነቴኞች ናቸው፡፡  የዜሌንሰኪ ዓላማ ለዩክሬን የቆመ መስሎ ዮክሬኖችን እና ሩሲያኖችን በማጨፋጨፍ ምድሩን ባድማ አድርጎ የስላቮችን አገር የምዕራባውያን የርሻ መሬት (lebensraum) በማድረግ የነ ሂትለርን ምኞት ማሳካት ነው፡፡  የኑክሌር ጦርነት እንዲቀሰቀስ የሚቋምጠውም በዚሁ ምክኒያት ነው፡፡  የዐብይ አሕመድ ዓላማ ደግሞ አንዴ ከትግሬ ጋር፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከአማራ ጋር የወገነ እየመሰለ፣ በአማራና በትግሬ መካከል እሳት እየለኮሰና እያቀጣጠለ፣ አማራና ትግሬን እርስ በርስ አጫርሶና አወዳድሞ፣ የአማራና የትግሬን ምድር ባድማ በማድረግ የኦሮሞን አጼጌ (Oromo Empire) በመላው ጦቢያ ላይ መመሥረት ነው፡፡

ዩክሬኖችን ከሩሲያኖች ጋር እንዲያጨፋጭፍ ዜሌንስኪን በገፍ የሚያስታጥቁት ምዕራባውያን፣ ዘወር ብለው ደግሞ ዩክሬኖች ላይ የዘር ጭፍጨፋ ተፈጸመ በማለት የአዞ እንባ እያለቀሱ፣ የሩሲያ ጦር የበላይ አዛዥ የሆነውን ፑቲንን የጦር ወንጀለኛ (war criminal) ብለው በይፋ ከሰውታል፡፡  በዚህ እሳቤያቸው መሠረት ትግራይ ላይ ተፈጽመዋል ብለው በሰፊው ለሚያስወሯቸው ወንጀሎች የመጀመርያው ተጠያቂ ማድረግ የነበረባቸው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የሆነውን ዐብይ አሕመድን ነበር፡፡  ዐብይ አሕመድ ግን መለስ ዜናዊን የተካ፣ መለስ ዜናዊን በሚያስንቅ ሁኔታ አማራን የሚነክስላቸው ውሻቸው ነው፡፡  በአማራ ሕዝብ ላይ በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ስለተፈጸሙት፣ በማስረጃ የተደገፉ፣ ሊካዱ የማይችሉ ጭፍጨፋወች ትንፍሽ ሳይሉ፣ ትግራይ ላይ ተፈጸሙ ስለተባሉ ማስረጃ ስለሌላቸው ወንጀሎች አለመጠን የሚጮኹት፣ ፋኖን በጦር ወንጀለኝነት ፈረጀው በማጥፋት፣ የአማራን ሕዝብ ለወያኔና ለኦነግ ጭራቆች አሳልፎ ለመስጠት ነው፡፡  ስለዚህም ፋኖ ምዕራባውያንን ዩክሬይን ላይ መዋጋት ያለበት፣ ለሩሲያ ሲል ብቻ ሳይሆን፣ ለራሱም ሕልውና ጭምር ነው፡፡

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

7 Comments

  1. Mesfin thank you for your taking your time relentlessly sending articles to waken up the sleeping Ethiopians. As you said it Russians do not need any thing in turn only to help Ethiopia. I thought Abyi will use this opportunity to side Russians sadly he is telling his followers to stop “No More”. There are million citizens who will listen your advice.

  2. መስፍን አረጋ፦ያቀረብከው ትንታኔ ምንም ውሸትና ማገነን የሌለበት ሙሉውን እውነት ነው፡፤ አብይ አህመድ በሰው አምሳል የተፈጠረ ቁሞ የሚሄድ ሰይጣን ነው፡፡ ሰወች እንዳያልቁ ማድረግ ይችል በነበረበት አቅምና ቁመና ላይ ሆኖ እርሱ ግን አስቦና ሆን ብሎ ብዙ ንጹሀን እንዲያልቁ አድርጓል፡፡ለዚሁ ዘግናኝ ስራወቹ ለጊዜው ይመስለዋል እንጅ ከተጠያቂነት አያመልጥም፡፡
    እንዳልከው ራሽያ ለኢትዮጵያ የሰራችው የአሰብ ወደብ የነዳጅ ማጣሪያን ብቻ ሳይሆን በወቅቱ ታላቅ የነበረውን የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታልንና እንደገናም በቴክኒክ ስልጠና ረገድ በአገሪቱ በወቅቱ ብቸኛ የነበረውን የባህር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኢንስቲትዩትን ለኢትዮጵያ ሰርታ አስረክባለች፡፡
    አብይ አህመድ ኢትዮጵያዊነትን ገድሎ ኦሮማዊነትን በመላው አገር ለመትከል እያደረገ ያለው ሴራ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ ወያኔ 27 አመት የወሰደበትን ዘረፋና ዘረኝነት ተረኛው ኦሮሙማ እጅግ በከረፋና በከፋ መልኩ በታላቅ ፍጥነት በ27 ወራቶች በብዙ እጥፍ አሳድጎ ፈጽሞታል፡፡ አብይ የአማራውን ህዝብ በተለየ መልኩ ለመጉዳት በአዲስ መልኩ ያዘጋጃቸው ሴራወች፣ የጭፍጨፋ እቅዶችና አማራን አዋርዶና አራቁቶ የማመናመን ዘመቻው በሆዳም የአማራ ሹመኞች በኩል ታግዞ ወደተግባር ይቀየር ዘንድ ሴራው ተጀምሯል፡፤ ፋኖን ትጥቅ ማስፈታት፣ መምታትና ቀጥሎም ልዩ ሀይሉን አፍርሶ የወልቃይትና ራያ የአማራ መሬቶችን በአለቆቹ በታዘዘው መሰረት ለወያኔ ያለምንም ተቀናቃኝ በገጸ በረከትነት ለማበርከት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
    ይህ በእንዲህ እያለ አማራው ሰማዩ ተድፍቶበትና የሚያስተዳድሩትም የአብይ ተላላኪወች በሆኑበት በዚህ ወቅት ከራሽያ ጎን የሚሰለፍ የአማራ ሀይል ለመላክ ምሰቡ አግባብ ቢሆንም የሚቻል ግን አይደለም፡፡

  3. ato mesfin you wrote there are no permanent friends neither enemis bt interest……….cool down you don’t make saense at all

  4. Abiy is enemy of Amhara but friend of Amhara lihiqan (amhara elites). Amhara elites don’t bother if entire amhara elites die except their family, red raw meat and langano awash park

  5. ሊሂቃነ አምሓራ ለራሳቹህ የሥልጣንና የመሬት ወረራ ጥቅሞች ስትሉ አማራ ሆይ ተነሥ ፥ተደፍረሃል፥ተወረሃል፥ተደራጅ ታጠቅ አልም ወርውር ተኩሥ ጨፍጭፍ እያላቹ በአራት ማዕዘን ከሚኖሩና ከሚጎራበቱት ሕዝቦች ጋር ጦር አታሣብቁት፥፥የዩክሬን ሕዝብ ጠላት የሆነው ራሺያን በኢኮኖሚ የማድከም ና የማንበርከክ ዓላማ ያላቸው የምዕራባውያዩን ዓላማ ለማሣካት የሚሠራ የራሳቸው መሪ ቮለድሚር ዘለንስኪ ነው ብለሃል፥፥በአራት ማዕዘን ከሚኖሩ ጎረቤቶቹ ጋር አምሓራን ደም እንዲቃባና ልጆቹ በሥጋትና በሀዘን እንዲኖር የዳረጉት የአማራ ሕዝብ ጠላትም የሆኑት የገዛ መሪዎቹ የብልፅግና ና የሻቢያ አሸርጋጆች ና አሽቃባጮች ልሂቃነ አምሓራ መሆናቸውን አሥረግጠን እንነግርሃለን ፥፥ ፥እውነታው ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሓን ዕልቂትን ያስከተለ ምክንያት የሆነው ከራሺያ ለአቢይ አሕመድ መንግሥት የተበረከተው የጅምላ ዕልቂት መሣሪያ ድጋፍ እስከ መቼውም ቢሆን አይዘነጋም ፥፥ይህ ዘመናዊ የዕልቂት መሣሪያ የብዙዎችን ክቡር ሕይወት አጥፍቷል፥ከአንድ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ከመኖሪያ ቤታቸው አዛብቷቸዋል፥ ለረጅም ዓመታት በብዙ ዉጣ ውረድ በእንባና በላብ ፍሰት የተገኝን ሀብትና ንብረት በደቂቃዎች ዶግ አመድ አድርጓል፥፥ስለሆነም በሕዝባችን ዕልቂት የማንኛቸውም ቢሆን አስተዋፅዖ የሚዘነጋ አይደለም፥፥በሁለት ሳምንት ውሥጥ ፑቲን የጦር ወንጀለኛ ብለው የፈረጁ የምዕራባውያኑ መሪዎች ለአሥራ ሰባት ወራት የዘለቀ እና ከአንድ ሚሊዮን ያላነሰ ሕዝብ ያለቀበት የእርስ በርስ ጦርነትን በዋናነት የመራውን እና ሕዝባችንን የጨፈጨፈ ና ያስጨፈጨፈ አቢይ አሕመድን የጦር ወንጀለኛ ብሎ ለመጥራት እንደተሳናቸው እየታየ ነው፥፥ የአማራ ልሂቃን ራሳችሁን ነጻ ለማውጣት አቢይን በመኮነን ብቻ የምትወጡት ምስቹ ተሆነ ተሳስታችሗል፥፥

  6. “ፋኖ ሩሲያ ይዝመት፡ የአብርሃም ሃኒባልን ታሪክ ይድገም?” ኡኡቴ ጉራ ነው ገበርዲን።
    ኢትዮጵያ የራሽያን ውለታ ትመልስ ምን የሚሉት መጃጃል ነው?
    ባረጀ መፈክር የዘመኑን ፖለቲካ እና የአገሮችን ፈቃድ ለመፈጸም ማሰብ የግ ንዛቤ ጉድለት ነው።
    መስፍኔ የሮማን ፕሮቻዝካ (Roman Prochazka) መጽሐፍ ስትደጋግም ብዙ ጊዜ ሆኖሃል።
    (በነገራችን ላይ፣ ፕሮሃዝካ ነው)።

  7. Alem,
    You are cheap! You have to fight ideas not letters.
    Your comment above shows how low your persona is!!!
    The butcher Abiy Ahmed has to be ashamed of you paying for such a lazy and nonsense person like you!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share