የጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ መልዕክት ከሳዑዲ አረቢያ እስር ቤት

ግፍ ከበዛበት ወህኒ የአክብሮት ስላምታየ ይድረሳችሁ!

እነሆ ለሁለተኛ ጊዜ ለአፍታ ያህል እድሉን አግኝቸ ወህኒ የመውረዴን እውነታ ላስረዳችሁ ግድ አለኝ ። ዛሬ አስረግጨ የምነግራችሁ ወህኒ የመውረዴ ምክንያት ሚስጥር ግምሽ እድሜየን ህግና ስርአቷን አክበሬ የኖርኩባትን የሳውዲት አረቢያን ህግ ተላልፊ አይደለም ! የስደተኛው ጉዳይ ያገባኛል በሚል የማቀርበው መረጃ ቅበላየ የማይመቻቸው ፣ ያመማቸው ከተሰረሰውና እየተሰራ ካለው ከእገታው ጀርባ ስለመኖራቸው አልጠራጠርም ። … ዛሬ በዚህ ዙሪያ ብዙ አልልም!

አላወቁትም እንጅ ክፉዎች ጠቅመውኛል ፣ ያላየሁትን እንዳይ አድርገውኛል። መንገዱ የከፋ ቢሆንም በወሰዱኝ መንገድ ተመርቸ እሰማው የነበረውን የወገኖቸ የወህኒ የከፋ ኑሮና ህመም ፣ በተቆርቋሪ ጠያቂ ማጣት ፣ በፍትህ መነፈግ እይሆኑ ያሉትን ከመስማት ማየት ማመን ነውና በአካል ማየት ችያለሁ !

ከመታሰሬ ጥቂት ቀናት በፊት በግፍ ለተደበደበው፣ ሁለት አይኑን ላጣውና ” አይሆኑ ከሚሆን ቢሞት ይሻላል “ተብሎ የፎቶ መረጃው ሳይቀር በእጀ የገባውን ወጣት ምንዱብ የወህኒ ህይወትን ተጨባጭ ታሪክ ከአይን እማኞች ቃርሜያለሁ! እሱም ያለው ከታሰርኩበት የቅርብ ርቀት ነው ። … አትጠራጠሩ አገኘውም ይሆናል !

በዚህ የጭንቅ ሰአት ከእኔና ከቤተሰቦቸ ጎን ሆናችሁ አለኝታችሁን ለገለጻችሁልን ምስጋናየ ከፍ ያለ ነው ! ዛሬ ወደ ዝርዝር ጉዳዩ አንገባም ። በላይ በመላ አለም የምትገኙ ወገኖቸ ያሳያችሁኝ ድጋፍና መቆርቆር ከጨለማው ቤት ደርሶኝ ጽናት አጎናጽፎኝ ሰንብቷል። ይህም በአረብ ሃገር ስደተኛ ዙሪያ ሳቀርነው ለነበረው መረጃ ያገኘሁት ክብርና ሞገስ ሆኖ መከራውን አስረስቶኛል: ) ምስጋናየ አይለያችሁ!

ወገኖቸ ወዳጆች ፣ ዛሬ ሰላም መሆኔን ብቻ ተረዱ ብየ እንጅ በሰፊው ስለሚሆነው አቅም በፈቀደ መጠን እናወራለን ! ዝምታው ከናፈቅኳቸው ልጆቸ ፣ ከቤተሰቦቸና ከእናንተ ጋር የሚያደርሰው መንገድ ውል እንዲይዝ የሚደረገው ሙከራ ውል እንዲይዝ የሚተጉ ወገኖችን ሂደት ላለማደናቀፍ ብቻ ለመረጋጋት ሲባል ብቻ ነው !

ተጨማሪ ያንብቡ:  በዓለም ማንኛውም ታሪክ ፤ የግለሰቦች ሚና ትልቅ ሥፍራ አለው - መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

በጨለመው የሳውዲ ወህኒም ይነጋል ፣ በንጋቱ ጮራ ታግዘን የምናወጋው የማለዳ ወግ ናፍቆኛል: ) ይህን ለማድረግ የሚከፈለውን ሁሉ ለመክፈል ደግሞ ልቤ ብርቱ ነው …

ሰላም ለሁላችሁ !

ነቢዩ ሲራክ
ከአንዱ የሳውዲ ወህኒ ቤት

6 Comments

  1. We will say No !!! to Saudi Shiber like we did at the end of last year all over Saudi embassies world wide. Saudi will be ashamed once more for their Terror/Shiber against our brave son Nebiyu Sirak. Nebiyu exposed Saudi slave masters and the Woyane slave traders. We will soon come to their embassies all over the world demanding the immediate release of our brave Son.

  2. >>>>አዎን…ታሰር!…ተበደል!..የሰማኽውን በዓይንህ ዓይተህ፣ የወገንን ሥቃይ በደልና ግፍ አንተም ደርሶብህ፣ መስክር! ተናገር!… አንዳንድ ቀበኞችም እንደመንግስት፣ እንደኀላፊ፣ እንደዜጋ፣ እንደሰው፣ ያልሰሩትን የማይሰሩትን..ችሎታም፣ ፍቃደኝነትም፣ወጋናዊነት፣ ሰብዓዊነቱም፣ የሌላቸውን ሁሉ በልጠዋቸው ተገኝተዋልና… ለበቀልም…ሞራልዎንም ለመስበር፣ ለቁርሾም…ለማሳነስም..ለማሳፈርም..የበታች ለማድረግም… ያንኑ ቆሻሻ እጅና አዕምሮአቸውን ተጠቅመው ይሆናል።

    **ይህ ካልሆነ ግን መንግስት (ካለ) በራሱ ፍቃደኝነት የተበደለው፣ የተበሳቆለው፣ የተገረፈና አጅግ እግሩ በሜንጫ በተቀነጠሰው፣ በተደፈሩ ሴት እህቶቻችን፣ በእሥርቤቱ በሚማቅቁ፣ ዛሬም ውሻ! ባርያ! ተብለው በሚዋረዱ… በእየቤቱ በተዋረድ ባርነት ቤት በተዘጋባቸው …መውጫ መግቢያው ለጠፋባቸው፣ ወይ ሀገሬ ወይ እናቴ እያሉ ለሚያነቡ ሁሉ፣ሀበገራቸው ሳይደላቸው በሰው ሀገር ይሞላል ብለው አካላቸውና ሰው መሆናቸው ለጎደለባቸው፤ በተለያየ ሕምም ተለክፈው፣ በአረመኔዎች እጅ ወድቀው ለሚማቅቁ፣ ለሚሰቃዩ፣ለሚገረፉ፣በፈላ ውሃና መርዝ ለተጠበሱ፣ ለተራቡ፣ ለተጠሙ፣ ለታረዙ ሁሉ (….) እንደግለሰብ ሳይሆን እንደመንግስት ከጎናቸው ቆመሃል ከመሃላቸው ተገኝተህ ችግርና ዋይታቸውን ዘግበሃል!.. ይበልጥኑም “ይህ አስከፊ ዘመን ከመምጣቱ በፊት የነገሩን ክፋትና መጪውን መጥፎ ሁኔታም ተንብየህ ለመፃፍህና ለማስገንዘብህ፣ ለመጮህ ፣መንግስትና የሚመለከተው አካል አስቀድሞ እንዲያስብበት፣ እንዲጠነቀቅ መፍትሔ እንዲፈጥር ፣የወጣቱ ከሀገር ፍልሰት ልቅና ኀላፊነት የጎደለው፣ የትውልድ ምክነትና ብክነት እንደሚያስከትል፣ የችግሩን ምንጭ እንዲፈተሽ፣ መንግስት የመልካም አስተዳደር፣ የትምህርትና የሥራ ፈጠራ ዕቅዱን እንዲያጤን እንዲያሻሽልና ስሕተቶችን እንዲያርም ጭምር አቶ ግሩም ተክለሃይማኖትን ጨምሮ ማሳሰባችሁን አንብበናል ሰምተናል እኛ ምሥክር ነን !!

    **”ስለዚህም የህዝብ ባለውለታ መሆንክን ያለው መንግስት ነኝ ባይ አካል አስቦበት! አምኖበት! በሰራኸው መልካም የዜግነት ገድል ተኩራርቶ ምክንያቱ ምን ይሁን ምን…በደረሰብህ ጉዳይ ቀዳሚ ደራሽ ሊሆን ይገባ ነበር።ማድረግም ግዴታና ኀላፊነቱ ነው። ግን ጉዳዩን ቀድመው ሰምተው ከጎንህ ለሆኑ ዜጎች ሁሉ ምስጋና ይድረሳቸው አሁንም ትውልድን በቅንነት በአንድንትና በመልካም የዜግነት ፍቅር ላይ ተነሳስቶ አቶ ነብዩ ሲራክን እንዲረዱ ቤተሰቦቻቸውንም እንዲያበረታቱ ማናቸውንም የህግ ምክርና ጥበቃንም ያገኙኚዘንድ እንድንተባባር ሁሉንም ሰብዓዊ ዜጎች ያለልዩነት በመልካም ሥነ-ምግባር፣ ኀላፊንት የሚሰማቸው፣ከጎጠኝነትና ዘረኝነት የፀዳ የኢትዮጵያዊነት ማንንት ያልተለያቸው የገዢው መንግስት አካላትን ጨምሮ ለዚህ ጉዳይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማየት በጉጉት ነው!!።

    **አሁንም ለግለሰቡ ጥንካሬን, ትዕግስን፣ መልካም ጤንነትና ፍትህን ያገኙ ዘንድ ሙሉ ልባምነታቸውን ይዘው እንዲቆዩ በሁሉም እምነትና ኢትዮጵያዊ ዜግነት ሰላም ለእሳቸውና ለተሰቦቻቸው ይሁን!። አሜን። በዚያች ቀውጢ ዘመን የችግር ገፋት ቀማሽ የሆኑ ከሳውዲ አረቢያ የተባረሩና በሕይውት ያሉ ሁሉ በፀሎት እዳይረሷቸው። እግዝሐብሔር ዋስ ጠበቃቸው ሆኖ ይህን የከፋ ዜና በደስታ ይለውጠው ዘንድ ዘወትር ፀሌቴ ነው። በቸር ይግጠመን ከሀገረ ከናዳ!

  3. God be with u brother.be strong and never give up,everything happen for reason. Selam for all Ethiopian lived in dark jail in Saudi Arabia and all over the world. The day has come and we see the light in the tunnel… never give up until we get freedom in our country. Peace

  4. The rumor has now become true. Journalist Nebiyu Sirak has surfaced in Saudi jail after disappearing from the public since March 4 this year. I wrote a piece regarding that last month but the diaspora media did not follow up on the tip. It was “Hiber Radio” from Las Vegas who broke the news of his being jailed last month,

    Today we heard directly from Nebiyu in one of the jails in Saudi Arabia. His letter from jail is posted on many Websites.

    This brave journalist is targeted for being the voice of our sisters and brothers in Saudi Arabia. He was in front reporting all the crimes against our women. Without him we would not have known what was going on in Saudi against Ethiopians.

    No wonder he is now jailed possibly to be deported to Ethiopia. I am asking you to share this news in our community. We need to organize a rally in front of Saudi mission/embassies soon. Our voice is very important. Silencing Nebiyu Sirak is Silencing our Sisters and Brothers !!!! Say No to Saudi Terror/Shiber !!!!

  5. The rumor has now become true. Journalist Nebiyu Sirak has surfaced in Saudi jail after disappearing from the public since March 4 this year. I wrote a piece regarding that last month but the diaspora media did not follow up on the tip. It was “Hiber Radio” from Las Vegas who broke the news of his being jailed last month,

    Today we heard directly from Nebiyu in one of the jails in Saudi Arabia. His letter from jail is posted on may Websites.

    This brave journalist is targeted for being the voice of our sisters and brothers in Saudi Arabia. He was in front reporting all the crimes against our women. Without him we would not have known what was going on in Saudi against Ethiopians.

    No wonder he is now jailed possibly to be deported to Ethiopia. I am asking you to share this news in our community. We need to organize a rally in front of Saudi mission/embassy very soon. Our voice is very important. Silencing Nebiyu Sirak is Silencing our Sisters and Brothers !!!! Say No to Saudi Terror/Shiber !!!!

  6. Dear Nebiyu Sirak,

    you are a loving and caring young Ethiopian journalist. Your articles on websites and the reports you were airing on DW broadcasting are extremely inspiring. You are a person of commitment and endurance. You are the hope and an illimunating light in the time of darkness. You are an ambassador of all Ethiopian expatriots in the middle East. When our brothers and Sisters in the whole middle East were being hunted by those beasts, you were the only voice for them. You were there when our citizens were being safocated, beaten, raped, killed, illegaly imprisoned and punished. You were the one who awared us about the victimization of Ethiopians. Since I could not have the space and time to post all the wondeful sevices and sucrifieses you provides and paid let me wind my posting with this short words! Nebiyu, we love you and you are a wonderful Ethiopian!!

Comments are closed.

Share