April 3, 2014
17 mins read

Health: ሰዎች ለፍቅረኞቻቸው ታማኝ የማይሆኑበት ምስጢር

ሊሊ ሞገስ

ትዳር የሚመሰርቱት ምን አይነት ፍቅረኞች ናቸው?

ጥንዶች በሶስት የተለያዩ መንገዶች ጥምረት በመፍጠር ወደ ትዳር እንደሚያመሩ ይታመናል፡፡ መጀመሪያው ጥንዶችን የሚያጣምራቸው በመሀላቸው የሚፈጠር ቅፅበታዊ ፍቅር ነው፡፡ በቅፅበታዊ ፍቅር የተለከፉ ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ ማንነታቸውን ዘንግተው በአዕምሯቸው ሳሆን በስሜታቸው መንቀሳቀስ ይጀምራሉ፡፡ ማመዛዘን የሚባለው ነገር ጨርሶ ይጠፋባቸዋል፡፡ በእንዲህ አይነቱ ጊዜዊ ስሜት ውስጥ እያሉ የተጋቡ ጥንዶች ብዙ ጊዜ ትዳራቸው የሚቆየው ቅፅበታዊው ስሜታቸው አብሯቸው እስከሚቆይ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ጥንዶቹ በመጀመሪያ ወደ ትዳር ሲያመሩ ወደፊት ስለሚገጥማቸው ችግርም ሆነ ስለኑሯቸው ምንም አይነት ቅድመ ዝግጅት አያደርጉም፡፡ ትዳር የሚመሰርቱት እርስ በርሳቸው በሚገባ ሳይተዋወቁ ነው፡፡ ትዳር ከመሰረቱ በኋላ የአንደኛውን ፍላጎትና ስሜት ሌላኛው ስለማይረዳው በመሀከላቸው አለመግባባት ይፈጠራል፡፡ ቀስ በቀስም በመሀከላቸው ያለው ልዩነት ይታያቸዋል፡፡ ልዩነታቸው እየሰፋ ሲመጣ በመሀከላቸው ክፍተት ይፈጠራል፡፡ በመጨረሻም ክፍተቱ እየሰፋ ሲመጣ አብሮነታቸው ትርጉም ያጣና ይለያያሉ፡፡

ጥንዶች ወደ ትዳር የሚያመሩበት ሁለተኛው መንገድ፣ መስፈርት በማውጣት ነው፡፡ እነኚህ ጥንዶች በቅድሚያ ለትዳር የሚፈልጉትን ሰው በመስፈርት ወስነው ያስቀምጡታል፡፡ መስፈርታቸው ብዙ ጊዜ ገንዘብን፣ ውበትን፣ እውቀትንና ሌሎች ነገሮችን ያተኮረ ነው፡፡ የሚፈልጉትን የትዳር አጋር ማግኘት የሚገባቸውን ጊዜም በቀን ገደብ ወስነው ያስቀምጣሉ፡፡ በእንዲህ አይነት መልኩ ትዳር የመሰረቱ ጥንዶች ብዙ ጊዜ ትዳራቸው ዘለቄታ አይኖረውም፡፡ ምክንያቱም ትዳር ከመመስረታቸው በፊት ትልቅ ቦታ ሰጥተው ለማግኘት ሲቋምጡለት የነበረውን ነገር ሲያገኙት ከግምታቸው በጣም ዝቅ ይልባቸዋል፡፡ የተመኙት ነገር ቀድሞ እንዳገዘፉት የሚገዝፉ አለመሆኑን ይረዳሉ፡፡ ለምሳሌ፡- አንዲት ሴት ማግባት ያለባት ባል ሀብታም መሆን እንዳለበት ወስና ሀብታም ባል ካገባች በኋላ በርቀት ስትመኘው የነበረውን ሀብት (ገንዘብ/ስታገኘው) ትርጉም ላይሰጣት ይችላል፡፡ ሀብቱን መስፈርት አድርጋ ካገባችው ሰው ጋር የምትኖረው ኑሮም ባዶ ይሆንባታል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ አንድ ወንድ ማግባት ያለበት ሴት ውብ መሆን እንዳለባት አምኖ ውብ ሴት ለማግኘት ሲንከራተት ከቆየ በኋላ በመጨረሻ ውብ የሚላት ሴት አጋጥማው ሲያገባት ለውበቷ በፊት የሰጠው ግምት ያንስበታል፡፡ ከተጋቡ በኋላ ውበቷ ለእሱ ምን እንደሚያደርግለትም መጤቅ ሊጀምር ይችላል፡፡ ለጥያቄው አጥጋቢ መልስ ሲያጣ ደግሞ ምኞቱ ሁሉ ከንቱ እንደነበር ይሰማዋል፡፡ በእንዲህ አይነት መንገድ የተሳሰሩ ጥንዶች ቀስ በቀስ በጋራ የመሰረቱት ትዳር ትርጉም ላይሰጣቸውና በዚህም የተነሳ ሊለያዩ ይችላሉ፡፡

ጥንዶች ወደ ትዳር የሚያመሩበት ሶስተኛው መንገድ በመሀከላቸው እርስ በርስ መግባባት መላመድ ሲፈጠር ነው፡፡ በእንዲህ አይነት መንገድ ተግባብተው ትዳር የሚመሰርቱ ሰዎች በመሀከላቸው የተፈጠረው መቀረረብና መግባባት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዳበረና እየተጠናከረ የሚመጣ ነው፡፡ እነኚህ ጥንዶች በመጀመሪያ እንዲጣመሩ ያደረጋቸውን ነገር ለይተው አያውቁት፡፡ ሁል ጊዜ የማያውቁት ውስጣዊ ስሜታቸው እንዲፈላለጉ ያደርጋቸዋል፡፡ በትዳር ከተጣመሩ በኋላም አብሮ መሆናቸው ትርጉም የለሽ አይሆንባቸውም፡፡ በመሀከላቸው በተፈጠሩ በእንዲህ አይነቱ ስሜት የተጋቡ ጥንዶች ግንኙነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለና እየተጠናከረ የሚመጣ ነው፡፡ ብዙዎቹ የስነ ልቦና ጠበብት ለረጅም ጊዜ በትዳራቸው ደስተኛ ሆነው አብረው ለመዝለቅ የሚችሉት ተፈጥሯዊ የሆነው ውስጣዊ ስሜታቸው በፈጠረባቸው መቀራረብ የሚጋቡ ጥንዶች መሆናቸው አስታውቀዋል፡፡

ሰዎች ለፍቅረኞቻቸው ታማኝ የማይሆኑበት ምስጢር

እንደ አብዛኞቻችን ባህልና እምነት የሰው ልጅ የህይወት አጋሩን በመፈለግ ጉዞ ውስጥ እያለ ወዲህ ወዲያ ማየቱና ማማረጡ ባይቀርም፣ ካገባ በኋላ ግን መሰብሰቡ ግድ ነው፡፡ አጋሬ ያሉትንና የወደዱትን ሰው ትቶ ወደ ሌላ ማለቱ ሁላችንንም የሚያስቆጣ ተግባር ቢሆንም ከፍቅር ጓደኛዎ ጋር ከጋቻ በፊት የሚያሳልፉት የፍቅር ህይወትና በትዳር ውስጥ እያሉ የሚኖርዎት ህይወት አንድ አይሆንም፡፡ ትዳር ውስጥ እያሉ ጥንዶችን የሚያቆራኛቸው ፍቅራቸው ብቻ ሳይሆን ሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች ናቸው፡፡ እነዚህን ጥንዶች ለረዥም ጊዜ አስተሳስሮ የሚያቆያቸው ምክንያት የቤተሰብ ኃላፊነት፣ መስዋዕትነትና አንዳቸው ከሌላቸው የሚቀበሉትና የሚሰጡት ጥቅም ነው፡፡ በተጨማሪም በትዳር ውስጥ የልጅ መፈጠር ጥንዶችን ከምንጊዜውም በበለጠ የሚያቀራርባቸውና የሚያስተሳስራቸው ክስተት ነው፡፡ ነገር ግን እንደዚህ በከፍተኛ ኃላፊነት የተሳሰሩ ባለትዳሮች እንዲሁም በሚያስቀና ፍቅር ውስጥ ያሉ ጥንዶች እንኳን ለፍቅረኞቻቸው ታማኝ የማይሆኑበት አጋጣሚ በጣም ሰፊ ነው፡፡ ‹‹ካለ አንተ መኖር አልችልም!››፣ ‹‹ህይወት ለኔ አንቺ ብቻ ነሽ!›› የሚባባሉ ፍቅረኛሞች እንኳን በማይታሰብ ሁኔታ ታማኝነታቸውን ሲያጡ እናያለን፡፡ አንድ ሰው ለፍቅረኛው ታማኝ ሳይሆን ሲቀር ህብረተሰቡ ለዛ የሚያስቀምጠው የተለያየ ምክንያት ቢኖርም ሳይንስ ግን የራሱ ትንታኔ አለው፡፡
አንድ ጥናት እንደሚለው የሰው ልጅ በህይወቱ ታማኝ ሆነም አልሆነ ተፈጥሯዊ የሆነው የአካል አቀማመጡ ከመታመን ይልቅ ወደ አለመታመን ያስጠጋዋል፡፡ የወንድ ልጅ የዘር ፍሬ በአማካይ ከጠቅላላው የሰውነቱ ክብደት 0.08 በመቶ ሲሆን ከጎሬላ ጋር ሲወዳደር አራት እጥፍ ነው፡፡ ይሄም የሚያሳየው የሰው ልጅ ለመራባት ከሚያስፈልገው የሰው ፍሬ በላይ እንደሚያመርት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የተሳካ በሚመስል ፍቅርና ትዳር ውስጥ እንኳን የመወስለት አጋጣሚዎች ይከሰታሉ፡፡ ባልም ለሚስቱ፣ ሚስትም ለባሏ ያላቸው ፍቅር እያቃጠላቸው ለምን ወደ ሌላ ሰው እንደሄዱ እንኳን ምክንያቱ ሳይገባቸው ይቀራል፡፡ እንደነዚህ አይነቶቹን ጥንዶች ያጣመራቸው ከፍተኛ የሆነ ተፈጥሯዊ ስሜት ወደ ሌላ እንዳይሄዱ የሚያደርጋቸው ምንም ምክንያት የለም፡፡

አንዳንድ ጊዜ ትዳር የጥቅም ልውውጥ ይሆናል፡፡ በትዳር ውስጥ ለፍቅረኛ ታማኝ አለመሆንን ለመረዳት በጥንዶቹ መካከል ያለውን ፍቅር መመርመር ያስፈልጋል፡፡ በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ሴትም ሆነ ወንድ አንዱ ለሌላው የሚሰጠውና የሚቀበለው ጥቅም ላይ መሰረት ያደረገ ይሆናል፡፡ ብዙ ጊዜ ሴቶች ከወንዶች የሚጠብቁት ጥቅም የገንዘብ ድጋፍ፣ እንክብካቤ፣ የጊዜ መስዋዕትነት ሲሆን ወንዶች ደግሞ እንዲሁ ከሴቶች አንዳድ የፍቅር መስዋዕትነትን፣ እንክብካቤና ፍሬያማነትን ነው፡፡ በአንድ ጥናታዊ ፅሑፍ እንደቀረበው ግማሽ በግማሽ የሚሆኑት አሜሪካውያን ሴቶችና ወንዶች በትዳር ውስጥ እያሉ ይወሰልታሉ፡፡ ለአብዛኛዎቹም ባሎች ራስ ምታት የሚሆነው በትዳር ውስጥ ያሉት ልጆች የእነሱ እንደማይሆኑ ሲያስቡ ነው፡፡ በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩትን ህፃናት ልጄ ብለው የሚታቀፉ ነገር ግን ትክክለኛ አባት ያልሆኑ ባሎች በእንግሊዝ በተደረገው ጥናት 10 በመቶ ይሆናሉ፡፡በሌላ ክልሎች ደግሞ ከአንድ እስከ 30 በመቶ ይደርሳሉ፡፡ የዲኤንኤ ምርመራ ከተደረገላቸው 1607 የስዊዘርላንድ ህፃነት ውስጥ አስራ አንዱ ልሄ ብለው ያሳደጓቸው ባሎች ትክክለኛ አባት እንዳልሆኑ ታውቋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በሚያሳዝን ሁኔታ ባሎች ለታመሙ ልጆቻቸው አካል ለመገለስ በሚሚጋጁበት ወቅት ትክክለኛ አባት አለመሆናቸውን ያውቃሉ፡፡

በጥንዶች መካከል እምነት አለመኖር ለትዳር ወይም ፍቅር መፋረስ ትልቅ መሰናክል ሊሆን ይችላል፡፡ስለ ፍቅር መፋረስ 100 በሚሆኑ የተለያዩ ህብረተሰቦች ላይ በተደረገው ጥናት ለትዳር መሰናክልና ለፍቅረኛሞች መለያየት ዋነኛ ምክንያት አንዳቸው ለሌላቸው ታማኝ አለመሆናቸው እንደሆነ ታውቋል፡፡ ተያይዞ በተደረገው ጥናት ሚስት ከባሏ በላይ የገቢ ምንጭ በምታገኝበት ትዳር ውስጥ ጥንዶቹ የመለያየት እድላቸው ከሌሎቹ ባለ ትዳሮች ጋር ሲነፃፀር 50 በመቶ ይጨምራል፡፡

በሰሜን አሜሪካና በሌሎቹ ሀገሮች በሚገኙ ባለትዳሮች ላይ በተደረገው ጥናት ብዙ ባለ ትዳሮች ፍቺን ቢፈልጉም ባላቸው ላይ ባላቸው ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጥገኝነት ምክንያት ፍቺን ለማከናወን የሚደፍሩት ጥቂቶች ናቸው፡፡ የሚደፍሩትም በራሳቸው መቆም የሚችሉና የኢኮኖሚ ጥገኝነት የሌለባቸው ሴቶች ናቸው፡፡ ሴቶችም ለፍቅረኛቸው ታማኝ የማይሆኑበት አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ የተደረጉት ጥናቶች እንዳሳዩት ሴቶችም እንደ ወንዶች ሁሉ በተፈጥሮ ታማኝ እንዳይሆኑ የሚያደርጓቸው ክስተት እንዳለ ነው፡፡ ይኸውም ሴቶቹ ለኛ ብቁ ወንድ ብለው ካሰቡት ወንድ ፍረቼ ማፍራትን ይመኛሉ፡፡ የሚያገቡትም ወንድ ብቁ ብለው ካስቀመጡት መስፈርት ውስጥ አንዱን ወይም ሁለቱን ቢያሟላ ሌላውን ለማሟላት ልባቸው ወደ ሌላ መሄዱ አይቀርም፡፡ ህብረተሰቡ የተስማማበት ገደብና ባህል ባይኖር ኖሮ ሴቱ ሁሉ መስፈርቱን አሟልቶ ሚዛን የደፋውን ወንድ ሁሉ ባል ያደርጉ ነበር በማለት ያስቀመጠው ጥናት የደመደመው የሰው ልጅ በሰው ሰራሽ ደንብና ስርዓት ስለተያዘ እንጂ በተፈጥሮው ለፍቅረኛው ታማኝ የማያደርገው ብዙ ምክንያቶች አሉ በማለት ነው፡፡

ምንም እንኳን ለፍቅረኛ ታማኝ ሆኖ ላለመገኘት ምክንያቶች ሳይንስ የሚያስቀምጠው ትንታኔና ትርጓሜ ቢኖረውም ተፈጥሯዊ የሆኑ ስሜቶችንና ፍላጎቶችን ሁሉ ማስተናገድ አለብን ማለት አይደለም፡፡ በስሜታዊነት የሚደረግ ውሳኔና ጉዞ ሁሉ መጨረሻው መካካድ፣ ታማኝ አለመሆንና መለያየት ነው፡፡ ሳይንስ እንደሚለው ተፈጥሯችን ታማን እንዳንሆን የሚያሳድርብን ጫና ቢኖርም ያንን ተቋቁሞ ላፈቀረው እስከ መጨረሻው ታማኝ መሆን የሚችል ግን ጠንካራ ልብ ነው፡፡ ሰዎች ለፍቅረኞቻቸው ታማኝ የማይሆኑበት ተፈጥሯዊ ምክንያት ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ስነ ልቦናዊና ማህበራዊ ችግሮች እንዳሉም መዘንጋት የለበትም፡፡ ይሄንንም ችግር ከማንም በላይ መፍታት የሚችሉት ደግሞ ጥንዶቹ ናቸው፡፡ ፍቅር ማንንም ሰው የማንበርከክ ምትሃታዊ ሃይል አለው፡፡ አፍቃሪ ልቦች ደግሞ በፍቅር ህይወታቸው ውስጥ የሚያጋጥማቸውን ጋሬጣ ሁሉ የመቋቋም አቅም፣ ትዕግስትና ጥበብ አላቸው፡፡

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop