በባህር ዳር ከተማ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ እድምታ (በገዛኸኝ አበበ ኖርዌይ )

እባካችው እናንተ የፖለቲካ መሪዎች አንድ ሆናችው ሕዝቡን ለለውጥ አነሳሱት

ይቼን ን አጠር ያለች ጹሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ በትናትናው እለት የካቲት 16 2006 ዓመተ ምህረት የአማራ ክልል በሆነችው በባህር ዳር ከተማ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ (አንድነት) ፓርቲ እና መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በቅርቡ የብአዴን/ኢህአዴግ ዋና ፀሐፊ እና የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ አለምነው መኮንን የአማርን ሕዝብ በማዋረደ እና በማናናቅ በአማራ ሕዝብ ላይ የተናገሩትን ስነ ምግባር የጎደለው ንግግራቸውን በመቃወም የጠሩትን በደማቅ ፣ ደስ በሚል እና በሚያኮራ ሁኔታ የተጠናቀቀውን ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በቪዲዩ ከተመለከትኩኝ በኋላ ነው::

ይህ በትናትናው እለት ተካሂዱ በነበረው የሰላማዊ ተቃውሞ ሰልፍ ላይ የባህር ዳር ከተማ ሕዝብ በተለይም ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ሆ ብሎ በነቂስ በመውጣት እልህና ወኔ በተሞላበት ትህይንት ማንነቱን በገሀድ ያስመሰከረበት የተቃውሞ ሰልፍ እንደነበር ተመልክቻለው:: ወጣቱ ትውልድ ላይ ቁጭት ፣ ንዴት፣ እልህ እና ወኔ ይታይበታል የወያኔ የጭቆና እና የዘረኝነት አገዛዝ አማሮታል፣ ለውጥንም እንደሚፈልግ በአደባባይ በመጮህ እየተናገረ ይገኛል:: የመለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ምሬት እና ብሶት ኢህአዲግ እና የኢትዮጵያ ሕዝብን ሆድ እና ጀርባ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል:: ሕዝቡም ከምሬቱ እና ከብሶቱ ብዛት የተነሳ ወኔን እና ድፍረትን በተላበሰ መንገድ ነበር የተቃውሞ ድምጹን ሲያሰማ የዋለው ::

ሕዝቡ በነቂስ ወቶ በድፍረት የተቃውሞ ድምጹን እንዲያሰማ የአንድነት እና የመኢአድ አባላትም ሆነ አመራሮች በአንድነት በመሆን የሰሩት ስራ የሚያስመሰግናቸው እና የሚያኮራ ተግባር ሲሆን ለሌሏቹም የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ትምህርት ሊሆን ይገባል እላላው :: የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥን ይፈልጋል::ስለዚህም ለለውጥ እና ለትግል የሚያነሳሳው ቀስቃሽ አመራርን ይፈልጋል ::ይህን ለውጥ የናፈቀውን እና ነፃነት የናፈቀውን ሕዝብ ለለውጥ ትግል ማነሳሳት የተቀዋሚ ፓርቲ ድርጅቶች ተግባር እና ኀላፊነት መሆን ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል :: የተቃዋሚ የፖለቲካ ፖርቲ ድርጅቶች አንድ ሀሳብ ይዘው በአንድ ራዕይ እና ትግል ወያኔን ለመጣል እና ከስልጣኑ ለማስወገድ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችንም ሆነ ማንኛውንም የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ቢተባበሩ እና ሕዝቡን ቢያነሳሱት ለውጥን ናፋቂው የኢትዮጵያ ሕዝብ በምንም ሁኔታ ውስጥ በማለፍን እና ትግሉ የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ባገኛው አጋጣሟ ሁሉ ቆራጥቱን እያሳየ እና እያስመሰከረ ይገኛል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  አካፋን አካፋ ብሎ ለመጥራት የመቸገር የፖለቲካ ባህል – ጠገናው ጎሹ

ይህንንም የወያኔ ካድሬዎችም ሆነ ባለስልጣኖች ጠንቅቀው የሚያቁት እና አሳሳቢ ጉዳይ የሆነባቸው ይመስለኛል :: ለዚህም ነው በተለያየ መንገድ በሕዝቡ ላይ የአካልም ሆነ የስነልቦና ጥቃት እያደረሱ የሚገኙት በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለው የአካልም ሆነ የስነልቦና ጥቃትእንዳለ ሆኖ ወያኔዎች ወጣቱን ለመከፋፈል በተለያየ ጥቅማጥቅም በማታለለ ለመያዝ እየሞከሩ ይገኛሉ:: ነገር ግን ለሆድ እና ለጥቅማ ጥቅም አልገዛም፣ ለወያኔም ካድሬዎች አላጎበድድም የሚለውን ወገን፤ የዚያ ድርጅት አባል የዚህ ድርጅት ደጋፊ እያለ ተለጣፊ ስም በመስጠት ከትምህርት፤ ከስራ እያፈናቀሉት፤ እያሰሩት፤ እያንገላታቱ ያሉት። ወያኔዎች ምክንያትን እየፈጠሩ ወጣቱን በግፍ በመግደልና በማሰር ትውልዱ በፍርሀት እንዲርድና ከትግል ራሱን እንዲያገል ለማድረግ እና የራሳቸውን የስልጣን ዘመን ቋይታቸውን ማስረዘሚያ አማራጭ መንገድ ማሰር፣ መግደል እና ሕዝብን ማወከብ ነው ብለው ያምናሉ::

ለዚህም ነው ማንኛውም የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎች እንዳይሳኩ እና ሕዝብ ተሳትፎ እና እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ወያኔዎች ሕዝብን የሚያዋክቡት እና የሚያስሩት ሰሞኑንም የባህር ዳሩ የተቃውሙ ሰልፍ በሚገባ እንዳይካሄድ እና ሕዝቡም ወጥቶ በሰልፉ ላይ እንዳይገኝ ለማድረግ የወያኔ ካድሬዎች እና የወያኔ ቅጥረኛ ፖሊሶች የባህር ዳር ከተማን ሕዝብ ሲያስፈራሩ፣ ሲረብሹ እና ሲያውኩ እንደነበር መረጃዎች ጠቁመዋል :: ነገር ግን የወያኔ ወከባ ያልረበሸው የበባህር ዳር ከተማ የሚኖረው የአማራው ሕዝብ ፍርሃትን በመስበር የኢትዮጵያን ስም እየጠራ እና እያወደሰ ዘረኛውን እና አንባገነኑን ፋሽስቱን የወያኔን ኢአዲግን መንግስት እና ባለስልጣናቶችን በድፍረት ሲያወግዝ እና ሲያዋርዳቸው ማየት በቂ እና ኩራት ነው እያልኩኝ ለባህር ዳር ከተማና በአካባቢው ለሚኖረው ሕዝብ ምስጋናዪን አቀርባለው :: በባህር ዳር ከተማ የተደረገውን እልህ እና ወኔ የተሞላበትን አጠር ያለች የተቃውሞ ሰልፍ ቪዲዮ ይመልከቱ :

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም ሕመም እና መድኃኒቱ (በፍቃዱ ኃይሉ)

1 Comment

  1. What a move! What a Demonstration it is! I am proud of being from a peaceful, nationalist and brave people of Ethiopia. A great initiative so far! People is always genuine and frankly. This is the very opportunity for Ethiopian gov’t and ANDM to take action against the bareminded Alemnew M.by respecting and genuine action and demonstration against his hate speech which is a crime and violence as per the Law .Simple verbalizing on Nations-Nationalities Equality is pitfall unless Action is taken on Haters and their nasty /stinging speech. This is very Test /EXAMS/ provided to & faced by the Gov’t. Long live Ethiopia and its People.

Comments are closed.

Share