Hiber Radio: አንጋፋው የሜጫና ቱለማ አመራር ስንብትና ሕወሃት ሜጫና ቱለማን ለማዳከም የወሰዳቸው እርምጃዎች (ወቅታዊ ዘገባ)

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ የካቲት 9 ቀን 2006 ፕሮግራም
<...ገዢው ፓርቲ በ97 ከምርጫ በሁዋላ 130 የቅንጅት አመራሮችን አስሮ እንደቀጠለው ዛሬም በተመሳሳይ ተቃዋሚውን አስሮ ወደፊት እሄዳለሁ ማለት የሚያዋጣ አይደለም። የተቃዋሚ መሪዎችን መሪዎች ማሰር ሕዝቡ የሚያነሳውን ጥያቄ መመለስ አይደለም...እኔም እንደ እነ አቶ አስራት የካቲት 25 ፍርድ ቤት እቀርባለሁ ...>

አቶ ሀብታሙ አያሌው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዛሬ ለህብር ረሰጡት ቃለ መጠይቅ(ሙሉውን ያዳምጡት

አንጋፋው የሜጫና ቱለማ አመራር ስንብትና ሕወሃት ሜጫና ቱለማን ለማዳከም የወሰዳቸው እርምጃዎች (ወቅታዊ ዘገባ)

– ድርድር ለሕወሃት ቀልድ ቢሆንም የኦጋዴን ነጻ አውጭ በሒደቱ ተስፋ አለመቁረጡ ያስገርማል(ትንታኔ)

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

* ሁለት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ኦብነግን ተቀላቀሉ

* አቶ አስራት ከእስር ቤት ሁለተኛው ጽሑፋቸው በአዲስ ጉዳይ ትላንት ታትሞ እንዲወጣ ፈቀዱ

* መናገር ወይ መጻፍ ካልቻሉኩ በትንሹም ሆነ በትልቁ እስር ቤት ኑሮ አንድ ነው ማለታቸው ተገለጸ

* ከኢትዮጵያ ሶስት መጦ ሺሕ ሔክታር የተሰጠው የህንዱ ካራቱሪ በኬንያ ያለ የአበባ እርሻው በባንክ ተያዘበት

* የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ተወካይ ፓርቲውን ተው በሚል የግድያ ዛቻ ደረሰው

* በእስር ላይ የሚገኙት የነጻው ፕሬስ አባላት ያለ ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ተጠየቀ

* አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በአስራ አምስት ቀን የሶስት ሪኮርድ ባለቤት ሆነች

* አስቴር አወቀ አልበም ማሳተም በቃኝ ማለቷ

* ቴዲ አፍሮ ሱዳን ላይ ሙዚቃውን ሊያቀርብ

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዐቢይ አህመድ መንግስት ከትግራይ አሽባሪ ኃይሎች ጋር እንደሚደራደር መናገራቸው ተረጋገጠ
Share