አስቴር አወቀ “ካሁን በኋላ የሙዚቃ አልበም የምሰራ አይመስለኝም” አለች

/

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንግሥት በሚል የምትሞካሸው ድምጻዊት አስቴር አወቀ ካሁን በኋላ የሙዚቃ አልበም ለመሥራት ሃሳብ እንደሌላት የቅርብ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ጠቆሙ። አስቴር ለቅርብ ሰዎቿ አሁን ባለው የሲዲ ገበያ የተነሳ ሙሉ አልበም ሠርቶ ለማቅረብ የሚያበረታታ ነገር የለም ስትል ተናግራለች።

በአሁኑ ወቅት ዘፈኖች በሲዲ ከወጡ በኋላ በተለያዩ በዩቲዩብ፣ በተለያዩ ድረገጾች፣ በፍላሽ ድራይቭ፣ በአይቱን፣ በኢሜይል፣ በሳውንድ ክላውድ፣ በፌስቡክ፣ በራድዮ፣ በጎግል ድራይቭና በመሳሰሉት መካፈያ (ሼር ማድረጊያ) መንገዶች ሕዝቡ ዘፈኖቹን በነፃ ስለሚያገኛቸው የአልበም ሽያጭ እጅጉን አሽቆልቁሏል። ይህን ተከትሎም በርካታ የሙዚቃ አሳታሚዎች በከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ መውደቃቸው በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው። ይህ ብቻም ሳይሆን በሕገ ወጥ መንገድ ኮፒ አድርገው ይሸጡ የነበሩ ሰዎች ሳይቀሩ አይደለም የኦርጂናል አልበም ሥራዎች የቅጂ አልበሞች ሳይቀሩ ገበያቸው ወርዶ ገዢ እየቀነሰ ነው ሲሉ ያማርራሉ።

ዘ-ሐበሻ ከተለያዩ ምንጮች ባሰራጫቸው መረጃ በአሁኑ ወቅት ከላይ በተጠቀሱት ዘዴዎች አብዛኛው ሰው ዘፈኖቹን ስለሚያገኛቸው አልበም ገዝቶ ለመስማት ፍላጎት ያላቸውም። ይህም አርቲስቱንም ሆነ አሳታሚዎችን በ እጅጉ እየጎዳ ይገኛል።

ድምጻዊት አስቴር አውቀ በቅርቡ “እወድሃለሁ” በሚል የሠራችው አዲስ አልበም ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያስገኘላት ሲሆን በሽያጭ ደረጃ ግን ለአልበሙ የሚመጥነውን ገቢ እንዳላገኘ ድምጻዊቷ እየገለጸች ነው ያሉት የቅርብ ምንጮች ዘፈኖቿን በግሏ አሳትማ በሃገር ቤት ከተሰራጨ በኋላ በውጭው ዓለም ገና ለገበያ ሳይቀርብ ሕዝቡ በነፃ ሼር በማድረግና በኮፒ አዳምጦ እንደጨረሰው ገልጸዋል።

የአስቴር እወድሃለሁ አልበሟ በውጭው ዓለም ሽያጩ ያን ያህል ቢሆንም፤ ተደማጭነቱ ግን ከፍተኛ እንደነበር ድምጻዊቷ እየተዘዋወረች ባቀረበችው የሙዚቃ ኮንሰርቶች ላይ ታይቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሜይ 28 በሚኒሶታ የሚታየው የ"ላገባ ነው" ፊልም ተዋንያንን ተዋወቁ

“ካሁን በኋላ ሙሉ የሙዚቃ አልበም የምሠራ አይመስለኝም” ያለችው አስቴር በተለያዩ ጊዜያት ነጠላ ዜማዎችን በመሥራት በየ2 ዓመቱ ኮንሰርቶችን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በመዘዋወር ለማቅረብ ሃሳብ እንዳላት የቅርብ ሰዎቿ ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።

የሙዚቃ አልበም ሽያጭ መውረድን ተከትሎ በርካታ አርቲስቶች ሥራ ይዘው እንዳይቀርቡ ሊያደርጋቸው ይችላል የሚል ፍራቻ አለ።

በዚህ ዙሪያ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች አስተያየታችሁ ምንድን ነው?

4 Comments

  1. My beautifull old lady,its time to quit and head back to your god and church.leave this shit to the youngster,darling look your self through mirror.as much I love your great song,I believe it time to quit.love you sis.

  2. This is very saddening news. I understand her. I hope things will improve as days go by. technology should facilitate the artists accessibility and reward for their talents.Aster should instead rise to the occasionand invest to hasten the dawn of a new bright era to fellow artists. aster is a legend whom ethiopia turn to listen to. Don’t despair astu when you can be aforruner to the solution. We love aster and we can’t afford to miss her.

  3. YYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYYesssssssssssssssssss!!! it is better to die on your feet… One day all Dictaorship collaborators will be juged by Ethiopian people;and you Aster Aweke will pay blood with your friends.Until that day comes your nightmare hunting you.Because for twenty two years million people had been killed Agazi regime

  4. yeAster albumin megzat leberektu new:it is not just an ordinary cassette:it is being blessed to have it:run for it

Comments are closed.

Share