March 8, 2022
16 mins read

አዲስ አበባ ሌላዋ የዘመናችን የኢትዮጵያ ወልቃይት! – ፊልጶስ

Abebe 1የአዲስ አበባ ወጣቶች እየታደኑ እየታሰሩ ነው። የአድዋን 126 የድል ቀን   በሚኒሊክ አደባባይ መከበርና የብልጽግናን ሌብነት በአደባባይ መነገር፤  ለኢሳቷ  (ESAT) የዘመናችን ጣይቱ ብጡልና ለመሰሎቿ የሚዋጥላቸው አልሆነም።  የካራ ማር 44ኛ የድል ቀንም ጠ/ሚ  አብይ አህመድ ለወጉ ”እንኳን አደረሳችሁ”  ባይሉም፤   የድሉን ቀን ለማክበር የወጡ ኢትዮጵያዊያኖችና  የባልደራስ ለእውነትኛ ዲሞክራሲ አባላት ታፍሰው ወደ እስር ቤት ተወረወሩ።  አሁንም  ”ኢትዮጵያዊ   ነው”  ያሉትንና በኢትዮጵዮጵያ ሰንደ ዓላማ   አረንጓዲ፣  ቢጫ፣ ቀይ፤ የማይደረደርውን  ሁሉ በየቤቱ እያደኑ በማሰር ላይ ናቸው።  ታዲህ ይህ   በኑጹሃን ላይ የሚደረግ ግፍና በደል  ወልቃይትን ያስታውሰናል። ወልቃይት   የወያኔ  መቃብር እንደሆነች ሁሉ፤ አዲስ አበባም ለኦሮሙማ-ብልጽግና መቀበሪያ እንደምትሆን የጎሰኝነትንና የተረኝነትን የአገዛዝ አወዳደቅ ያስተምረናል።

ከዘመናት የወያኔ ግፍና ስቆቃ በኋላ ወልቃይት አሁንም አደጋው እንደተደቀነ ቢሆንም  “ነፃ “ ወጥታለች። ወልቃይት ለዚህ ለመብቃት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ታስረዋል፣   ተገለዋል፣  ተሳደዋል፣ አካለ ስንኩል ሆነዋል፣ በጅምላ ተቀብረዋል፣ በአጠቃላይ ወያኔ በኢትዮጵያ ላይ የፈፀመው ግፍ ሁሉ በደቦ ተፈፅሞባታል። ታዲያ ወልቃይት ከወያኔ ነፃ ስትወጣ ፣ አዲስ አበባም በተመሳሳይ ሁኔታ በተረኞቹ ኦሮሙማ-ብልጽግናዎች   በዜጎቿ ላይ   ግፍ እየተፈጸመ ነው።

እንደ ወልቃይት አዲስ አበባም ተመሳሳይ ታሪክና ትርክት እያስተናገደች ነው።

ልቃይት፤  ወያኔ ትግል እንደጀመረ 1966 እስከ 1967 ድረስ ወደ ሱዳን የሚያደርገው ማንኛውም ደርሶ መልስ ጀብሃ በሚቆጣጠረው በኤርትራ ክፍለ ሃገር አድርጎ ነበር። በ1967 መጀመሪያ አካባቢ ወያኔ ከ’ርዳታ ድርጅት የዘረፈውን ቁሳቁስና የጭነት መኪናዎች ይዘው ወደ ሱዳን ለመሻገር ሲሞክሩ ጀብሃ። “ከዘረፋችሁት ሃብት ግማሹን አካፍሉኝ” አለ። ወያኔ ስግብግብ ‘’ዘራፍ!’’ አለ። ብሎም አልቀረ፥፥ የዘረፈውን ሃብት ከነመኪናዎቹ አቃጠላቼው። እናም ተከዜን ተሻግሮ ወደ ወልቃይት ፊቱን አዞረ። ቀስበቀስም አካባቢውን ተቆጣጥሮ ከሱዳን ጋር ለሚያደርግ ግንኙነት ብሎም ወያኔ ለህልውናው የደም ስር ወልቃይት ሆነች።

አዲስ አበባ ወያኔ ”አዲስ አበባን የኔ የግሌ ነች” ለማለት ምክንያት ስላልነበረው ከተማዋን አራቁቶ በልቶ ተቃውሞው ሲያስፈራው በተለይም 1997 ምርጫ በኋላ  የትላንቱን ኦህዴድ፤ የዛሬውን ኦሮሙማ- ኦነጋዊ-ብልጽግና  ከናዝሪት አውጥቶ ”አዲስ አበባ ያንተ ነች” አለው። ወያኔ የአዲስ አበባን ህዝብ ለመበቀልና አንገት ለማስደፋት  ከሄደበት መንገድ አንዱ ይህ ነበር ። በ”ርግጥ ወያኔ የአዲስ አበባን ህዝብ በተዘዋዋሪም በዘረኞቹ  የመቆጣጠሪያ ስልት መቀየሱ ነው።

ልብ እናድርግ!…፡ ወያኔ ጀበሃ በ’ኔ ግዛት አታልፍም ሲለው የሄደው ወደ ወልቃይት ነበር። የአዲስ አበባ ህዝብ የወያኔን ጸረ ኢትዮጵያዊነት ቀደሞ የተረዳ በመሆኑ፤ የሱን ወንቶ- ፈንቶ  የጎሳ ፓለቲካ “— የነካ እንጨት” ሲያደርግበት ለኦህዴድ አዲስ አበባን በእጅ መንሻ ሰጠው። ወያኔ ፈንጅ ለመቅበሩ ‘ርግጠኛ ነበር፥፥ ለምን እና እንዴት? ብለው የማይጠይቁት የኦህዴዲ ጽንፈኞች ደግሞ እንደ ትልቅ ድል ቆጥረውታል።

ወልቃይት፤ ወያኔዎች የወልቃይትን ማንነት ለማጥፋት ከግድያ ጀምሮ የትግራይ ተወላጆችን በተለያየ መንገድ ‘’ዲሞግራፊውን’’ ቀየሩት።  ከተለያዩ አካባቢዎች ህዝብን በመሰብሰብና በማስፈር   በሱዳን የተሰደዱ ስደተኞችን ከመመለስ ጀምሮ፤ ከጦሩ የተሰናበቱትን በመቶ ሺ የሚቆጠሩ እና ከተለያዮ የትግራይ ወረዳዎችን ይጨምራል። ኢኮኖሚውንም ተቆጣጠሩት። ስራ እየተመረጠ ለወያኔና መሰሎቹ ብቻ ተሰጠ። ዜጋው ከአፓርታይድ በከፋ ከምድር በታች ያለ ኢ-ሰባአዊ ሁሉ ተፈፀመበት።

አዲስ አበባ፤ የትላንቱ ኦህዴዲ የዛሬው ኦሮሙማ – ብልፅግና ‘’አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ብቻ አይደለችም፤ ኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ማግኘት ይገባታል አለ::’’ አደረጋትም ፤ ዜጎች ልፍተውና ደክመው ያስገነቡትን ቤት በማን አለብኝ ለኦሮሙማ ተከታዩች አደሉት።

የአዲስ አበባ ህዝብ በልማት ስም ቤት ንብረቱ እየፈረስ እንደ አሮጌ ቁና የትም ተወረወረ ፤በምትኩ ተረኞቹ የኦነጋዊ- ብልጽግናዎች ከየቦታው እየተጠረሩ ሁሉንም ነገር ተቆጣጠሩት፥: አዲስ አበባ ዜጎች ተወልደው ባደጉበት ባይተዋር ሆኑ። ወጣቶቹ ተምረው ስራ ማግኘትና ኑሮ መመሰረት ህልም ስለሆነባቼው መሰደድና በባዕድ አገር፡ መከራተት እጣ ፈንታቼው ሆኖ፤ ብዙዎቹ በሳአውዲ እስር ቤት የምድርን ስቃይ ሁሉ ይከፍላሉ።

የአዲስ አበባ ህዝብ በግልጽ በኢትዮጵያዊ ማንነቱና ለዘመናት በገነባው ማህበራዊ እሴት ላይ ጦርነት ታወጀበት፥፥ በወልቃይት እንደተደረገው ሁሉ በአዲስ አበባም ከሱማሌ ክልል ተፈናቀሉ የተባሉት ከግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በላይ አሰፈሩበት። ይህም አልበቃቼው፤ በአንድ ቤት ውስጥ እስክ 170 የሚደርስ መታወቂያ ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጡ የእነሱ ተወልጆች በገፍ አደሉ ”ምርጫ”  አድርገን አሸነፍን አሉ።

በወልቃይት ወያኔ እንዳደረገው ሁሉ ኦሮሙማ – ብልፅግና የከተማዋን ማንነት ለማጥፋት ከስም መቀየር ጀምሮ እስከ አዲስ ክፍለ ከተማ መፍጠር ድረስ ሄዱ። በከተመዋ የ”ነርሱን ቋንቋ የማይናገር የስራም ሆነ የኢኮኖም ተጠቃሚ መሆን እንዳይችል በመንግሥት ደረጃ መዋቅር ዝርግተው ይሰራሉ። የኦሮሚያ ፍርድ ቤት  በዋና ከተማ ላይ በማቋቋም በፍትህ ላይ ተሳለቁ።  ገዥዎቻችን በድግስና በግብዥ እየተምነሸነሹ፡ አዲሰ አበቤ ግን በችግር ” የበይ -ተመልካች’’ ሆኖ ይሰቃያል።

ወልቃይት፤ ወልቃይቶች በማንነታቸው ወያኔ ሲዘምትባቼው ጮሁ፣ ታሰሩ ፣ ተገደሉ ፣ ታገሉ ፣ በኢትዮጵያም ወያኔን የማስወገድ የትግል ፋና ወጊ ሆኑ ፣ ትግሉን አገር አቀፍ እንዲሆን ሰቆቃቼው በዓለም ዳርቻ እንዲሰማ ከፍ አድርገው ጮሁ ። ያ ትግላቼው ፍሬ አፍርቶ ዛሬ ለነፃነት በቁ።

አዲስ አበባ  አዲስ አበባሜ በማንነቱ ላይ በግልጽ ጦርነት እንደታወጀበት ሲያውቅ መታገል ጀመረ። በህዝቡ ያልተመረጠ ከንቲባ ሲሾምበት አጥብቆ ተቃወመ፥፤ ግን ወያኔዎች እንዳደረጉት ሁሉ የአዲስ አበባ ባለተረኞቹ  ኦሮሙማ – ብልጽግናዎች ሰላማዊ ታጋዮችን ከብዙ ማገላታት በኋላ ወደ ዘብጥያ አወረዷቸው።  ከአንደ አመት ተኩል  እስር በኋላ   የትኛውን  የጦር ዕዝ እንደመቱ ባናውቅም፤  የወያኔ አድራጊ-ፈጣሪና መሰሎቻቸው ሲፈቱ እነሱም ተፈቱ።

ለግዜውም ቢሆን አዲስ አበባን ታጋይ አልባ ያደረጓት መሰላቼው። ወያኔንም ወልቃይቶችን የቻለውን ያህል ገሎና አሳዶ ታጋይ አልባ ያደረጋት መስሎት ነበር። “ግን ታጋይ ይሞታል ፣ ትግል ግን አይሞትምና “ ወልቃይቶች ገና ብዙ ተጋድሎ ቢጠባቅቸውም  በነጻነት ለመኖር በቁ። የአዲስ አበባ የአሁኑ ትግል የህልውና ትግል ነው::  ለአዲስ አበባ ህልውና መከበርና ስለ ፍታዊነት በሰለጠነና በሰላማዊ የጠየቁ ዜጎችን በግፍ አስሮ ሰላም አይኖርም። የአሁኑ የግፍና የአፈሳ እስር ደግሞ ህዝብን ለመታገል የበለጠ ቆራጥ ያደርገዋል እንጅ አያንበረከከውም።

የአዲስ አበባ ህዝብ “መዲናችን የማንም ሳትሆን የሁላችን የኢትዮጵያዊያን ብሎም የአፍሪካ ነችና ‘ራስን በራስ የማስተዳደር የተፈጥሮ መብታችን አትከልክሉን ፤ ለዘመናት ከመላው ያአገሪቱ ክፍል በተውጣጡ ዜጎች የተገነባውን ማንንነት አትንኩብን! አክብሩልን! “ ፤ ከኢትዮጵያዊነይት ማማ አንወርድላችሁም!  በአረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ ዓላማችን አንደራደርም ! አለ እንጂ፣ የራሱ ያልሆነውን አልጠየቀም።

ለባለተረኛ ገዥዎቻችን የምናስተላልፈው መልእክት፤  በአሁኑ ግዜ አገራችን ከጦርነቱ ባልተናነሰ የኑሮ ውድነት እየተጠበሰው ነው።  ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ብሎ መከራና ችግሩን ሁሉ ችሎ አገሩን የሚያሰቀድመውን የአዲስ አበባ ህዝብ አትፈታተኑት። ትላንት ጎሰኝነትንና ጸረ-ኢትይጵያዊነትን እንደ ጡጦ አጥብቶ ካሳደጋችሁ ወያኔ ተማሩ።  ምንም ይሁን ምንም ኢትዮጵያዊነት ለሁላችን መደሃኒትና መዳኛችን መሆንኑ አሁንም ከወያኔ ስህተት ተማሩ ! ብለን እንመክራለን።  አዲስ አበባ ለሁላችንም ትበቃለች። አቅፋ ደግፋ ትይዘናለች።  የአዲስ አበባ  ህዝብ አብሮና ተከባብሮ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ መኖርን እንጅ፤ የአንድን ጎሳ የበላይነት የሚሸከምበት ጫንቃ የለውም። ለዚህም ነው ” አዲስ አበባ የኢትዮጵያዊነት ማሰሪያ ውል ናት!” የምንለው። ‘’አዲስ አበባን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ነው! ’’ የምንለው:: ስለዚህም ህዝብ ለታላቋ ኢትዮጵያ ሲል ቅድሚያ የሚሰጠው  የአገርና የህዝብ አንድነት ስላለ እንጅ በእናንተን የመንደርተኝነትን አገዛዝና ፓለቲካ ሊቀበል ቀርቶ መፈጠራችሁንም ባያውቅ ይመርጥ ነበር።  መገንዘብ ያለባችሁ ህዝብ ከእንናተ ከገዥዎቻችን እጅጉን በበለጠ አገሩን ያስቀድማል። እናም  ነገ-ዛሬ ሳትሉ በህገ-ወጥ መንገድ ያሰራችኋቸውን ወግኖቻችን ፍቱ።   ጨቋኝ ጎሰኛም ሆነ የነጻነት ታጋይ ከወልቃይት ይማር።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!
———-//——-ፊልጶስ

የካቲት-2014

*ይኽ  ነጻ አስተያየት  ከዚህ በፊት የወጣ ቢሆንም፤  ከወቅቱ ጋር እንዲስማማ ማስተካከያ ተደርጎልተል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop