March 7, 2022
21 mins read

ከሿሿው በኋላ ስለሚሆነው ልንገርህ ይልቁንስ – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

electionውድ አንባቢያን!

ይህችን አጭር ማስታወሻ የጻፍኩት አቢይ አህመድ ምርጫውን አሸነፍኩ ባለበት ሰሞን ነው፡፡ በዚያን የምርጫ ሰሞን ልክ እንደባሕርይ አባቱ እንደመለስ ዜናዊ ሁሉ ከሆዳምና ባዶ ጭንቅላት ካድሬዎቹ ጋር በኅቡዕ የሠራውን ሠርቶ በሚዲያ ግን ለታይታና የዋሆችን ለማሞኘት ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ነፃ እንደሚሆን በተደጋጋሚ ይወተውት ነበር፡፡ ያንንም ውትወታ ብዙ የዋህና ገራገር ሰው አምኖ ሳይቀበለው አልቀረም፡፡ በምርጫው ወቅት የተሠራውን አጠቃላይ የቁጭ በሉ ሥራ ግን ባልደራስ ፓርቲ በመረጃ በተጠናቀሩ ጥናቶቹ አጋልጧል፡፡ እንደዚያ ዓይነት ምርጫ በዓለም ሲካሄድ የመጀመሪያም የመጨረሻም ነበር ማለት ይቻላል፤ ፍጥጥ ያለ የፈጣጦች ሥራ ነበር፡፡ የአቢይ ሕጻንነትና የሚመራው የወሮበሎች ቡድን ዐይን አውጣነት ያኔ ነበር ቁልጭ ብሎ ገሃድ የወጣው፡፡ አስመራጭም፣ መራጭም፣ ተመራጭም፣ ድምፅ ቆጣሪም፣ ድምጽን ለየቲያትረኛው ተመራጭ ተብዬ ሁሉ ደልዳይም … ራሱ የአቢይ ቡድን ነበር፡፡ በኔ የምርጫ ጣቢያ ለምሣሌ ሀፍረተ ቢሱ ዲያቆን ጋንኤል ክብሪት ምንም ድምጽ ሳያገኝ በአቢይ ቡራኬ ነበር ፓርላማ እንዲገባ የተደረገው፡፡ ዐይን ዐውጣነት ከአቢይ በላይ በዩኒቨርስ የለም፡፡ ለውሸቱ ድካ የለውም፡፡ የማስመሰሉ እስስታዊ ጠባዩም እንደዚሁ ወሰን የለውም፡፡ ራሱን በራሱ ለመቃረንም የሚቀድመው የለም – በዚያ ዐመሉም በኩራት ይኮፈስበታል እንጂ አያፍርበትም፡፡ ምን ዓይነት ፍጡር እንደሆነ ለማወቅ የሚቻል አይመስለኝም፡፡ እስስት ስትለው ዕባብ ይሆንብሃል፤ ዕባብ ስትለው ሸለምጥማጥ ይሆንብሃል፤ ሸለምጥማጥ ስትለው አነር ይሆንና ዘልሎ ያንቅሃል፡፡ የኃጢኣታችንና የክፋታችን ብዛት ይህን መሳይ እስፊንክሳዊ ዐውሬ የላከብን መሆኑን ተረድተን አሁንም ከዚህ በከፋ ብዙ ሳይረፍድብን አምላካችንን በጸሎት እንለምነውና ከዚህ ዐረመኔ ይገላግለን፡፡ ምንም እንኳን በየአቅጣጫው ሲታይ – በተለይ ከሰሞኑ የዩክሬንና የራሽያ ጦርነት አኳያ – የዓለም ፍጻሜ የተቃረበ ቢመስልም ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ትንሽ እፎይታ እናገኝ ዘንድ በርትተን እንጸልይና ይህን ከሲዖል አምልጦ የመጣ አቢይ የሚባል የሣጥናኤል ልጅ እንገላገል፡፡ ለዚህም ስኬት ከተፈጥሮ ያፈነገጥን የብልሹ ምግባራት አቀንቃኞችና ትውልድ አጥፊዎች ከገባንበት አዘቅት በአፋጣኝ እንውጣ፡፡ በሰው ስቃይ የምንደሰት ወገኖች ሰው ሰው ለመሽተት እንሞክር፡፡ መጥፎ አጋጣሚን ለትርፍ አንጠቀምበት፡፡ ነገ ጥምቡን ለሚጥል የምግብ ዘይት – ለምሣሌ – ቀድመን ባስገባነው ዘይትና ሌላ ሸቀጥ ስንጥቅ በማትረፍ ምስኪን ወገኖቻችንን ለመከራ አንዳርጋቸው፡፡ የምንሠራው ሁሉ – ደግም ሆነ ክፉ – ወደራሳችን እንደሚዞር ደግሞ እንመን፡፡ ሃይማኖት እንኳን ባይኖረን ይህን የኮንፊውሸስ አባባል እንረዳ – “ሰዎች ባንተ ላይ እንዲያደርጉብህ የማትፈልገውን ነገር አንተም በነሱ ላይ አታድርግ፡፡” ትልቅ ፍልስፍና ነው – የሚሠራው ግን ሰው ነኝ ለሚል ብቻ ነው – ሰው ሆኖ ለመገኘት ለሚጥር ምድራዊ ፍጡር፤ ለአጋንንታዊ ጭፍራዎችና ለሴቴኒዝም እምነት ተከታዮች አይሠራም፡፡ በሚያልፍ ችግር የማያልፍ ጠባሳ ማኖር ትንሽነት ከመሆኑም ባሻገር ኋላ ለጸጸት ይዳርጋልና ተራ ዜጎች በቁማቸው ከሞቱት ከአቢይና አቢያውያን ተሽለን ለመገኘት እንሞክር፡፡ የዛሬ መብላት መጠጣት፣ የዛሬ መዘነጥ፣ የዛሬ በቪላና በአፓርትማ መሽሞንሞን፣ የዛሬ በቦሌና በሸጎሌ በሃመርና በቪ8 መንፈላሰስ፣ የዛሬ ድሃን ባይኔ አልይ ማለት፣ የዛሬ በድሆች ላብና ደም መክበር … ለነገ የሚያስከትለውን ፍዳና መከራ ለመገንዘብ በግድ ሦርያንና ኢራቅን ማስታወስ አይጠበቅብንም – ብልኅ ሰው የችግርን ምንነት ከሩቅ ይማራል፤ ጅል ሰው ግን በራሱ እስኪደርስ አይገባውም፡፡ እመነኝ – ሁሉም ነገር የተራ ጉዳይ ነው፤ የቀንና ምናልባትም የዕድል ጉዳይ ነው፡፡ ዛሬ በሕዝብ ስቃይ የምንደሰት ቅንጡ ሁላ ነገ ጊዜ ዘምበል ሲል የያዝነው ወርቅ ሁሉ ከአፈር አንድ ነው፤ ወርቅ ወርቅነቱ የሚለካው በብዛቱ ሳይሆን የምንጠቀምበትን ዕድልና ምቹ ሁኔታ ስናገኝ ብቻ ነው፡፡ አዎ፣ የሦርያን ሀብታሞች ጠይቁ፤ የሊቢያን ቡርዥዋዎች ጠይቁ፤ የአፍጋኒስታንን ቱጃሮች ጠይቁ፤ ምን ሩቅ አስኬደኝ – የዩክሬንን ቅንጡዎች ጠይቁ፤ የጎረስካትን ሳትውጥ ለምትሰናበትባት ጥልማሞታዊ ዓለም ብለህ ሰውን አትበድል፤ በሰው ላይም በከንቱ አትኩራራ፤ ሀብትና ሥልጣን እንዲሁም ዝናና ዕውቅና ከላይ ከሚታዘዝ በላ ወይም መቅሰፍት አያድንም፡፡ እንግዲያውስ መተሳሰብና መተዛዘን ሳይመሽና ሳይጨልም አሁንና አሁን ነውና ወደትክክለኛ ሰውነትህ ተመለስ፡፡ በጠፉ ሰዎች አትወሰድ፤ በነሱም አትቅና፤ ዋጋቸው ይሰፈርላቸዋልና፡፡ አንተ የገዛኸው አፕል አንድ ቀን አለፈው ብለህ ወዲያ ስትወረውር አጠገብህ በርሀብ እየሞተ ያለ ወገንህ አለ፡፡ ምናልባት ለዚያ ሰው መራብ ያንተ ሚናም አለበት፡፡ ለማንኛውም በዚያን ጽሑፍ ስለወደፊቱ በምናቤ ታይቶኝ ከከተብኩት የተወሰነው ገና የሚጠበቅ ቢሆንም ብዙው ግን እውን በመሆኑ ለማስታወስ ያህል ቀጥለን ለመመልከት እንሞክር፡፡

 

የመጥረቢያ ልጅ መዘለፊያ ነው፡፡ ከእባብ ዕንቁላል እባብ እንጂ ዕርግብ ወይም ሌላ ፍጡር አይፈለፈልም፡፡ ሣይንስንና ሃይማኖትን እንዲሁም ባህልን መናቅ ውጤቱ የዜሮ ድምር ነው – ባዶ፡፡ ሣይንስ በዲኤንኤ የዘረመል ውርርስ ያምናል፤ ስለሆነም የዝንጀሮ ልጅ ዝንጀሮ መሆኑን አይክድም፡፡ ሃይማኖትም ብዔል ዘቡልን ብዔል ዘቡል እንደማያወጣው በግልጽ ይናገራል – የሰይጣን ልጅ የሰይጣንን ልጅ ሊቃረነው አይችልምና፡፡ ከሰይጣን የሚገኘው ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ ባህላችንም “እባብ የወጣበትን ጉድጓድ አይረሳም” ሲል የእፉኝት ልጅ እፉኝት እንጂ ሌላ ሊሆን እንደማይችል ያስረዳል፡፡ ምን አዲስ ነገር አለ? ከሕወሓት/ኢሕአዲግ ማሕጸን ደህና ሰው ይወለዳል ብለሽ የተሞኘሽ ቂላቂል ሁላ ሒሣብሽን አገኘሽ፡፡ አቢይ አህመድ እማማ ፊሽካ ቀርቶ አባባ እግዚአብሔርን ሄዶ ቢያጫውት ተፈጥሮውን አይረሳም፡፡ ማታለልና ማስመሰል የርሱ quality ነው – በእንግሊዝኛ ልንገርህ፡፡ ማጭበርበር ከልጅነቱ ጀምሮ የሰየጠነበትና የሰለጠነበት ልዩ ተሰጥዖው ነው፡፡ ገድሎ ማልቀስ፣ ራሱ አስርቦ ያዘነ መምሰል የባሕርይ ስጦታው ነው፡፡ ጃዝ ብሎ በላከው ኦነግ-ሸኔ አንድ ከተማ ሲጠፋ ርህራሄ የሌለው ዐረመኔ የሀገር ቀርቶ የቀበሌ መሪ ሊሆን እንደማይችል የማይረዳ ሰው፣ ሰው አይደለም፡፡ እናም ሰው ባልሆኑ ፍጡራን የተከበበ ዐውሬ ማንንም አይጠቅምም፡፡ ለነገሩ ከመለስና ከስብሃት ነጋ ሥር ሉጥ ሉጥ ሲል አድጎ ጥሩ ሰው ቢሆን ነበር የሚገርመው፡፡ የመለስን ስህተቶች ልቅም አድርጎ በመረዳትና በማጥናት እርሱ አሻሽሎ ነው ኢትዮጵያን መቀመቅ እየከተተ የሚገኘው፡፡ ልዩ ሰው ነው፡፡ አሁን አሁን የሚያሳዝኑኝ ያዞረባቸውን ያላወቁ እነዳንኤልን የመሰሉ ዞምቤዎች ናቸው፡፡ ዞምቤ (zombie) ማለት በአፈ ታሪኩ እንደሚነገረው ቡዳዎች በልተዋቸው ከገደሏቸውና ከተቀበሩ በኋላ ከመቃብር ወስደው እቤታቸው በመደበቅ ከእንደገና የሚስለመለም ነፍስ ዘርተውባቸው በሕይወትና በሞት መካከል በመሆን ሥራ የሚያሠሯቸው ናቸው – የማይሰሙ የማይለሙ ድንዙዛን፡፡ ዋና ተግባራቸው መታዘዝ ብቻ ነው፡፡

አቢይ ምርጫውን ሿሿ ሠርቶናል – እኔን አይጨምርም በርግጥ፤ ምክንያቱም በፊቱንም እውነተኛ ምርጫ እንደማይኖር በግሌ ለፍልፌያለሁ፤ ከጮሌ ሰው አንደበት ማር ጠብ ሊል ይችላል እንጂ ተግባሩ ዲያብሎሳዊ ነው፡፡ ብዙ ሰው ግን የዚህን አጭቤ ሰውዬ የማስመሰል ድርጊቶች በማመን ምርጫው ነፃና ፍትሃዊ እንደሚሆን ጠብቆ ነበር፡፡ ሰውዬው በመቶ ሽዎች የሚገመቱ አጋንንት ከርሱ ጋር ስለተሰለፉ ብዙ ሰው ቢወናበድ በበኩሌ አልፈርድም፡፡ ግን ማየቱ ጥሩ ነውና እንኳንስ ሰው ሂደቱን እያዬ እየተረዳ መጣ፡፡ ሰሞኑን ስታዘብ ብዙ ሰው በምርጫው ውጤት ግራ ተጋብቷል፡፡

የአቢይን ብልግና ፓርቲ ለመምረጥ መቼም ቀን ከሌት የሚሰለፍ ጅላንፎ የለም፡፡ ጥቂት ሆዳሞችና የዘረኝነት ልክፍት የተጠናወታቸው ሆዳሞች ብልግናን እንደሚመርጡ ቢጠበቅም ይህ ሁሉ ሕዝብ ያን ሁሉ እንግልት ችሎ በብርድና በዝናብ እየተሰቃዬ ገዳዩንና አስገዳዩን የብልግና ፓርቲ ለመምረጥ እንደዚያ አይቸገርም፡፡ ኑሮውን በየደቂቃው ሽቅብ ለሚያጉን ፓርቲ ድምጹን ለመስጠት ያን ያህል ውጣ ውረድ ውስጥ መግባት የሚፈልግ ዜጋ አይኖርም፡፡ ጩልሌው አቢይ ግን ከወያኔ ጅልነትና ግትርነት ተማረና በልዩ ሥልት ምርጫዋን ገቢ አደረጋት፡፡ ይሁን፡፡ የሚጠበቅ ስለነበር ብዙ አይደንቅም፡፡

ቀጣዩ ትዕይንት ይህን ይመስላል፡፡ ጆሮ ያለው ይስማ፤ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ደግሞም አይጠራጠር፡፡

ብዙ ዜጎች ተደምመዋል፡፡ ድምፃቸው መሰረቁን አምነዋል፡፡ ብዙዎች መታለላቸውን ተገንዝበዋል፡፡ ግን እንደ97ቱ ወደ ዐመፅ አልገቡም፤አይገቡምም፡፡ አቢይ ከመለስ ተምሮ ብዙ የማስመሰልና የማጭበርበር ሥልቶችን ተግባራዊ እንዳደረገ ሁሉ ሕዝቡም ከዚያው የ97 የከሸፈ ምርጫ ተምሮ ይህንንም ምርጫ መሸወዱን በማመን ከሌላ አቅጣጫ ልዩ የትግል ሥልት እንደሚቀየስ ይገምታል – ያንን በዓይነቱ ልዩ የሆነ ሰብኣዊና መለኮታዊ የመጨረሻ አማራጭ በጉጉት ይጠብቃል፡፡ ያም ትግል በቅርብ ይጀመራል፡፡ ብዙ ጊዜም አይወስደም፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለድል ይበቃል፡፡ አቢይን ያለ ሁሉ፣ በዚህ አጭበርባሪ የተወሰደ ደንቆሮና አጋሰስ ሁሉ ጥግ ጥጉን የሚይዝበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ያኔ ጨለማው ይነጋል፡፡

የምርጫ ቦርድ ኃላፊ ሂደቱን በመገምገም ነገሮች እንደተጠበቀው አለመሄዳቸውን ታምንና አንድም ሀገር ጥላ ትኮበልላለች፤ ወደቀደመ ኑሮዋም ትመለሳለች፤ አንድም እውነትን በመካድ የታሪክ ተወቃሽ በመሆን ከአቢይ ጎን ትሰለፍና የሚደርስባትን ቅጣት ለመቀበል ዝግጁ ትሆናለች፡፡ ጎላ ያለው ግምት ግን እውነትን ተከትላ በያበጠው ይፈንዳ ራሷን ነፃ ልታወጣ እንደምትችልና እንደሚገባትም ነው፡፡ ይህች በወያኔዎች ብዙ መከራና ፍዳ የደረሰባት እንስት ከኅሊናዋ ጋር እንደማትጣላ ትልቅ ግምት አለኝ፡፡ ምርጫው ግን የራሷ ነው – ከእውነት ጋር መጋፈጥና የሕዝብን ፍቅር ማስጠበቅ  ወይም ከሃሳዊ መሲሑ ጋር ሁለት ሞት መሞት፡፡ ይህን ማስታወሻ እንዲደርሳት ብታደርጉልኝ ባለውለታየ ናችሁ፡፡

አቢይና ወዳጅ ዘመዶቹ ታሪክ የሚወረውርላቸውን መቁነን ተካፍለው ይቃመሳሉ፡፡ ለብልግና ፓርቲ እንደእህት ኩባንያ በሚቆጠረው የብርሃኑ ነጋ ኢዜማም ሆነ በብልግና ፓርቲ በራሱ ውስጥ የሚገኙ መልካም ሰዎች ከመራራው ጽዋ ሳይጎነጩ ለዘር ይተርፋሉ፤ መዳን በሥራ እንጂ በድርጅት አባልነት ብቻ እንዳልሆነ መረዳት ተገቢ ነው – በሃይማኖቱም ጭምር፡፡ ኦርቶዶክስ ስለሆንሽ ብቻ አትድኝም – ሙስሊም ወይንም ሰባተኛ ቀን ስለሆንሽም አትጠፊም – ከፈለግህ አገለባብጠው፡፡ በመቶዎች የተቧደኑት ፓርቲዎችም እንደየድርሻቸው ለዚህች ሀገር ውድመት ያበረከቱትን ድርሻ በሚመጥን መልኩ ቅጣታቸውን ይቀበላሉ፡፡ ከነሚስቱና ልጆቹ ፓርቲ መሥርቶ የሀገርን ሀብት አላግባብ በፓርቲ ስም የተቋደሰና ያባከነ ሁሉ የቀባጭ ምሱን አያጣም፡፡ ለዚህች ድሃ ሀገር ቢያንስ ሁለት ቢበዛ ሦስት ፓርቲ አነሳትና “የአባትህ አገር ሲወረር አብረህ ውረር” በሚለው የቆዬ ፈሊጥ ተመርተው በሀገር ላይ የቀለዱ ሁሉ ዋጋቸው እንደሥራቸው ይከፈላቸዋል፡፡ ዛሬ አእምሮ ጠፍቶ ሀገር እንዲህ ብትማስን ነገ ሰዎች ይፈጠራሉ፤ ያኔ እንካሣለን፤ ሰውም እንሆናለን፡፡

ኢትዮጵያን ከዚህ ሁሉ ትርምስና የዘረኝነት ቱማታ ነፃ ለማውጣት አድፍጦ የሚጠብቅ ኃይል አለ፡፡ ይህ ኃይል ማንም የሚበግረው ኃይል አይሆንም – በቅዱስ መንፈስ የሚመራና በሀገር ፍቅር የተቃጠለ ነው፡፡ የሚጠብቀው አበቅቴውን ብቻ ነው – የፈጣሪን ፊሽካ፡፡ ከዚያ በኋላ አፈ ቅቤ ልበ ጩቤውን ጨምሮ ሁሉም የሀገራችን ጠላት የማሽላ እንጀራ ይሆናል፡፡ ከውጭም ከውስጥም ሆነው ሕዝቡን የሚያባሉት መዥገሮችና አልቅቶች ሁሉ እንደጉም ይበናሉ፤ እንደጤዛም ይረግፋሉ፡፡ አሁን ግን ጊዜያቸው ስለሆነ በጊዜያቸው እንዳሻቸው ይፈነጫሉ፡፡ ብዙ የተጠመዱ ፈንጂዎችና የተቀበሩ ቦምቦች ግን አሉ፡፡ እነዚያን በማክሸፍ ረገድ ብዙ ወጪ የሚጠይቅ ሥራ አለ፡፡ በዚያም ሳቢያ ግፋፎ ግፋፎው እስኪራገፍ ወንዞችና ሐይቆች መልካቸው ይቀላል፡፡ ነፃነት የምርቃት ድግስ ወይም የሽኝት ፓርቲ አይደለምና ብዙ የንብረት ውድመትና የሕይወት ኅልፈት መከሰቱ አይቀርም፡፡ ወያኔና ኦነግ/ኦህዲድ የደገሱት የመከራ ድግስ ለእስፖንሰሯ ግብጽም ይተርፋል፡፡ ኢትዮጵያ በፈጣሪዋ ስትጎበኝ ሊያጠፏት ያሰፈሰፉ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጠላቶች ሁሉ አፍረው ይደበቃሉ፡፡

በቃኝ …

Hiber Radio Special – March 06, 2022

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop