አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ አረፉ። ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ህመም ህክምና ሲክተሉ ቆይተው ማረፋቸውን የቤተክርሲያኒቷ ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አስታውቋል።
ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ከ1983 ጅምሮ በስደት ላይ ቆይተው፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥረት እና ሽምግልና በአገር ቤት ካለው ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር እርቅ ወርዶ ወደ አገራቸው ተመልሰው ቤትክርስቲያኒቱንና ምዕመናኖቿን ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል።
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ የቀብር ሥነስርአትን በተመለከተ የቤትክርስቲያኒቷ ቅዱስ ሲኖዶስ ተሰብስቦ የሚወስንና ለህዝብ የሚያሳውቅ መሆኑም ተገልጿል።