ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY
ሚሊዮን ዘአማኑኤል
በኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ዘመን ከ2020 እስከ 2021እኤአ የኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት በ2.56 (ሁለት ነጥብ ሣምሳ ስድስት) ቢሊዮን ዶላር አሽቆልቁሏል!!! ‹‹በኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ዘመን ኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት በ2020 እኤአ ከ3.9 (ሦስት ነጥብ ዘጠኝ) የነበረ ሲሆን በ2021እኤአ 1.34 (አንድ ነጥብ ሠላሳ አራት) ቢሊዮን ዶላር አሽቆልቁሏል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ኮንፍረንስ ኦን ትሬድ አንድ ዲቨሎፕመንት፡-(The United Nations Conference on Trade and Development (UNCTAD) ድርጅት የዓለም አቀፍ ንግድ፣ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ እድገትና ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ መረጃ የሚያቀርቡ ድርጅት ነው፡፡ በዚህም መሠረት1
- በ2017 እኤአ የኢትዮጵያቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት(FDI Inward Flow )4.017 (አራት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ አጠቃላይ በሃገሪቱ ያለ የውጭ ኢንቨስትመንት ክምችት (FDI Stock) 19.097(አስራዘጠኝ ) ቢሊዮን ዩኤስ ዶላር ነበር፡፡
- በ2018 እኤአ የኢትዮጵያቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት(FDI Inward Flow )3.310 (ሦስት ነጥብ ሦስት) ቢሊዮን ዶላር ፣አጠቃላይ በሃገሪቱ ያለ የውጭ ኢንቨስትመንት ክምችት (FDI Stock) 22.407 (ሃያ ሁለት ነጥብ አራት )ቢሊዮን ዩኤስ ዶላር ነበር፡፡
- በ2019 እኤአ የኢትዮጵያቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት(FDI Inward Flow )2.516 (ሁለት ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ በሃገሪቱ ያለ የውጭ ኢንቨስትመንት ክምችት (FDI Stock) 24.923 (ሃያ አምስት ) ቢሊዮን ዩኤስ ዶላር ነበር፡፡
- በ2020 እኤአ የኢትዮጵያቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት(FDI Inward Flow )9 (ሶስት ነጥብ ዘጠኝ) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን አጠቃላይ በሃገሪቱ ያለ የውጭ ኢንቨስትመንት ክምችት (FDI Stock) 24.923 (ሃያ አምስት ) ቢሊዮን ዩኤስ ዶላር ሆኖል፡፡ መንግሥታዊው ኢትዮ ቴሌኮም 40 በመቶ የአገልግሎት ሽያጭ 850 ሚሊዮን ዶላር ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት እድገት ዋነኛ ምክንያት ነበር፡፡ Ethiopia Attracts $3.9 billion FDI in 2020/21 Fiscal Year August 19, 2021– Foreign Direct Investment (FDI) inflow into Ethiopia reached 3.9 billion US dollars in the recently concluded 2020/21 fiscal year, says country’s investment commission. 3
“The sale of the first private telecom license, however, has been the main factor,” said Henok Solomon, Communication Director of the EIC. A Global Partnership for Ethiopia, a consortium of telecom companies, won a telecom service licence offering a $850 million bid.
The amount seem within a reaching distance as the government pushes ahead with its two major plans to liberalize the telecommunication sector this year – selling a 40 percent stake in the state-controlled telecom firm, Ethio Telecom, and a second telecom operator licence to foreign companies.
- በ2021 እኤአ የኢትዮጵያቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት (FDI Inward Flow )34 (አንድ ነጥብ ሠላሳ አራት) ቢሊዮን ዶላር ሆኖል፡፡ Ethiopia has attracted $1.34 billion foreign direct investment (FDI) during the first five months of the current budget year of Ethiopia started July 8, 2021. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ሌሊሴ ነሚ መረጃውን ለዲያስፖራው ህብረተስብ ገልፀዋል፡፡ 4
የኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ከ2017 ወደ 2018እኢአ በ707 ሚሊዮን ዶላር ቀነሰ፣ ከ2018እኢአ ወደ 2019እኤአ በ794 ሚሊዮን ዶላር ቀነሰ፣ ከ2019 እስከ 2020እኤአ በ1.384 ቢሊዮን ዶላር እድገት አሳየ፣ ከ2020 እሰከ 2021 እኤአ በ2.56 ቢሊዮን ዶላር አሽቌልቁሎል፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ ይህን የኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ሁኔታ በግልፅ ለፓርላማው አላስረዱም፡፡
በኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ዘመን ኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ከ3.9 (ከሦስት ነጥብ ዘጠኝ) ቢሊዮን ዶላር 1.34 (አንድ ነጥብ ሠታሳ አራት) ቢሊዮን ዶላር በመውረድ የ2.56 (የሁለት ነጥብ ሳምሳ ስድስት) ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማሽቌልቁሉን በገሃድ አልመሰከሩም፡፡
የኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ዳግም ለማንሰራራትም የብዙ አመታት ጥረት ይጠይቃል፡፡ የውጭ ኢንቨስተሮች በሃገሪቱ በተከሰተ ጦርነት የደህንነትና የፀጥታ ሁኔታ የውጭ ኢንቨስተሮችን ያለው የጦርነት ሁኔታ ሊስባቸው አይችልም፡፡ በትግራይ ፣ በአማራና አፋር ክልሎች የተቀጣተለ የጦርነት እሳት ብዙ የሰውና የቁስ ውድመትን አስከትሎል፡፡ የመሠረተ ልማቶች ወድመዋል፣ የጤናና የትምህርት ተቆማት ወድመዋል፣ የቴሌ፣ የመብራት እንዲሁም የውኃ ተቆማት ወድመዋል፣
በተለይ በትግራይ፣ በአማራና አፋር ክልሎች ኢንቨስትመንት በማውደም ሆቴሎች በማቃጠል፣ ፋብሪካዎች በማንደድ፣ እርሻ ቦታዎች በማጋየት፣ መንገድ በመዝጋት፣ የዘርና የኃይማኖት ጭፍጨፋ (ጆኖሳይድ) በመከናወኑ የተነሳ የውጭ ኢንቨስተሮችና የሃገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ክልሉን ለቀው ወተዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት በሃገሪቱ የ2.56 (የሁለት ነጥብ ሳምሳ ስድስት) ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በማሽቌልቁሉ የተነሳ
የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸው የነበሩ ሠራተኞች ሠራ አጥ ሆነዋል፡፡ በጦርነቱ ምክንያት ብዙ ፋብሪካዎች ወድመዋል ብዙ ሽህ ሠራተኞች ከሥራ ገበታቸው ተፈናቅለው ይገኛሉ፡፡ ብዙ ትምህርትቤቶች ተቃጥለዋል ብዙ ሽህ መምህራን ከሥራቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ብዙ የጤና ተቆማቶች ወድመዋል በዛም የተነሳ ብዙ ሽህ የጤና ባለሙያዎች ከሥራ ገበታቸው ተለይተዋል፡፡
ከጦርነቱ በፊት በኦሮሚያ ክልል መንግሥት (ኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ፣ ጅማ፣ አርሲ፣ ባሌ፣) ንብረትና ኃብታቸው ለወደመ ኢንቨስተሮች ካሳ እንደማይከፍል አስታውቆል፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኢንቨስተሮቹን ንብረት ማስጠበቅ ተስኖታል፣ የፖሊስ ኃይሉና መከላከያ ሠራዊቱ ደሞዝ ተቆርጦለት፣ ቀለብ ተሰፍሮለት የሚኖረው በኢንቨስተሮቹ ታክስና ግብር በሚሠበሰበው ገንዘብ መሆኑን የኦሮሞ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ብልፅግና ፓርቲ ሹማምንትና ካድሬዎች ሊረዱት አልቻሉም፡፡ በኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ዶክተር ዐብይ አህመድ ተረኛና ዘረኛ መንግስት፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ካድሬ ሽመልስ አብዲሳ፣ የመዐድኑ የወርቁ ጌታ ታከለ ኡማ፣ የአዲስ አበባ የመሬቷ እመቤት አዳነች አቤቤ፣ የወለጋ ነፃ አውጭው ሽፍታ የወለጋ ኦሮሞችን በስብዓዊ ጋሻነት ይዞ አማሮች፣ ኦሮሞዎች የሚያርድ ኦነግ ሸኔ ሽፍታ ጃል መሮ፣ የመከላከያው ምክትል ኤታማጆር ሾም ብርሃኑ ጁላ፤ በምድረ ኦሮሚያ የሃገር ውስጥ ኢንቨስተሮችን ኃብትና ንብረት በማውደም ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ሠርተዋል፡፡ የኦሮሚያን ኢንቨስትመንትን በሻሸመኔ፣ ጅማ፣ አርሲ ፣ ባሌ ንብረት ያወደሙ፣ በግፍ ዜጎች ያረዱ ካድሬዎች፣ የኦሮሞ ህዝብን ሥራ አጥ አድርገዋል፣ አብሮቸው ከሚኖረው ህዝብ ጋር አጋጭተዋል፣ በሁሉም ተጠያቂው ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ መሠረት በ2019/20 እኤአ በኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት ወደ 600 (ስድስት መቶ) ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አሽቆልቁሏል፡፡ በ2018/19 እኤአ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍስት 2.5 (ሁለት ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ ከነበረው የኢንቨስትመንት ፍስት ዝቅተኛ ሆኖ ተመዝግቦል፤ ለመቀነሱም ዋናዎቹ ምክንያቶች የቅንጅት ስራ አለመኖር፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ በሃገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት እንደሆኑ ተጠቅሶል፡፡ የኢንቨስትመንት ባለስልጣን በሃገሪቱ የደህንነትና የፀጥታ ሁኔታ በተፈጠረው አለመረጋጋት የብዙ ኢንቨስተሮች ንብረትና ኃብት መጋየትና መውደም በመከተሉ የውጭ ኢንቨስትመንት መቀነስና የኢኮኖሚ ልምሻ አስከትሎ አልፎል፡፡
በ2019/20 እኤአ በኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት ማሽቆልቆል የተነሳ 40000 (አርባ ሽህ) ሠራተኞች ብቻ የሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ ሲሆኑ የውጭ ኢንቨስትመንት መቀነስ ያስከተለው አሉታዊ ተፅዕኖ በሠራተኞች ቅጥር መቀነስ ጋር ሊንጸባረቅ ችሎል፡፡ በ2018/19 እኤአ ለ115000 (መቶ አስራምስት) ሽህ ሰዎች አዲስ የሥራ ዕድል በመዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች (ኢንቨስተሮች) ተፈጥሮላቸው ነበር፡፡ ሃገሪቱ በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት አምስት ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት የሚያደርጉ ኢንቨስተሮች ለመሳብና ለመቶ አስራ ስምንት ሽህ ሰዎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር በበጀት አመቱ መጨረሻ ድረስ አቅደው ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ባሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አሥር መንግሥት ሠራሽና ስድስት የግሉ ዘርፍ ስሪት የኢንዱስትሪ ዞኖች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በውጭ ንግድ ገቢ ያስገኙት 164 (መቶ ስልሳ አራት) ሚሊዩን ዶላር ባለፈው አመት አስገኝተዋል፡፡ በዚህ አመት 340 (ሦስት መቶ አርባ) ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታስቦል፡፡
According to UNCTAD’sWorld Investment Report 2020, China was the largest investor in 2019, accounting for 60% of newly approved FDI projects, with significant investment in manufacturing and services. The other main investor countries are Saudi Arabia, the United States, India and Turkey. (UNCTAD) ድርጅት የዓለም ኢንቨስትመንት ጥናት መሠረት በ2019 እኤአ የቻይና መንግስት የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ድርሻ 60(ስልሳ) በመቶ ሲሆን በማኑፋክቸሪንግና በአገልግሎት ዘርፎች ላይ እንደሆነ ታውቆል፡፡ በቀጣይነት ደግሞ ሳውዲ አረቢያ፣ አሜሪካ፣ ህንድ፣ ቱርክ የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ይገኛሉ፡፡ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ በተረኛነትና በዘረኝነት ስሜት የሃገር ውስጥ ኢንቨስተሮችን ንብረትና ኃብት በጦርነት በማውደም ሃገሪቱን የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች እንዲሸሹ ተገደዋል እንላለን፡፡ በጦርነት ኢኮኖሚ የኢኮኖሚ እድገት ብሎ ነገር የለም !!! ምነው ጃል አብይ!!! ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አዲዬስ ኢኮኖሚክስ ካለ ሠነበተ ‹‹ቄሱም ዝም መፅሃፉም ዝም›› ሆነ በምድረ ኢትዮጵያ!!!
ምንጭ
(1)https://www.nordeatrade.com/en/explore-new-market/ethiopia/investment/Foreign direct investment (FDI) in Ethiopia
(2)https://ethiopianmonitor.com/2020/08/07/foreign-investment-in-ethiopia-drops-in-2019-20/
Foreign Investment in Ethiopia Drops in 2019/20 FY/ By Sisay Sahlu// Friday, October 30, 2020
(3) Ethiopia Attracts$3.9 billionFDI in 2020/21 Fiscal Year – Ethiopian Monitor.Aug 19, 2021
(4) Ethiopia has attracted $1.34 billion foreign direct investment (FDI) during the first five months of the current budget year of Ethiopia started July 8, 2021.