“እነዚህ ሰዎችኮ ሠይጣኖች ናቸው!” – ዳንኤል ሽበሺ

ትክክለኛነቱ ገና ቢሆንም ሰሞኑን ከሕወሓት ጋር የድርድር ንፋስ ሽውው እያለ ነው ። ከወደ አገር ኬኒያ ።
የኔ ጥያቄ?
“እነዚህ ሰዎች ሠይጣኖች ናቸው!” በተባሉበት ሁኔታ እንዴትና በምን ቋንቋ ከሠይጣን ጋር መነጋገር እንደሚቻል ነው ግራም ቀኝም የገባኝ ። በተሰጣቸው ስያሜ መሠረት ይወራ ከተባለ ከሠይጣን ጋር የሚደራደር አንዴም ከሠይጣን ከፍ የሚል አሊያም በልኩ ያለ ሌላይኛው #ሠይጣን መሆን አለበት ። በተያያዘም ከሰይጣን ጋር የሚነጋገር ምን አይነት ሰው ነው? እንደምን ሊግባባ ይችላ? ብለን ከጠየቅንም ነውርነት ያለው አይመስለኝም ።
ቢያንስ “እነዚህ ሰዎችኮ አውሬዎች ናቸው!” ብለናቸው ቢሆን ኖሮ ለድርድርም ለንግግርም ይመቸን ነበር ። ምክንያቱም አውሬን በሂደት ማላመድ ይቻል ይሆናልና ግን ሠይጣንን እንደት?
ስለዚህ ጥያቄው በአካልም፣ በገብርም ሰዎች መሆናቸውን ክደን «ሠይጣኖች ያደረግናቸው እኛ ነን» ማለት ነውና በጊዜ ለንስሐ መዘጋጀት አለብን ። የተሳሳትን እኛ ነን ወይስ እነሱ? ብለን በሞራል ጥያቄ ራሳችንና ነፍሳችንን የምናስጨንቅበት ጊዜ ቢኖር አሁን ይመስለኛል ። ያም ሆነ ይህ …
«”ተጨባብጠን እየመጣን ነው?”»
….
በግል ስብዕናዬም፣ እንደሰላማዊ ታጋይም፣ በሃይማኖት ፣ በባህል ተጽዕኖ ውስጥ እንዳለ ሰው በድርድር፣ በንግግር፣ በውይይት፣ በይቅርታ፣ በምህረት … አምናለሁ ። እነዚህ ሁሉ እሴቶቼ ቢሆኑም ግን ለሁሉም ነገር ወግ አለው ባይ ነኝ ። የተመረጠ መንግሥት፣ የሕዝብ ውክልና ያለው ገለመለ የሚባለውን ድስኩር እንዳልሰማ ፈጣሪዬን እየተማፀንኩ፤ አንተ ጥቁር ሕዝብ ሆይ! በተለመደው ሆደ ሰፍነትህ፣ መከራ ባጎመጠው ጫንቃህ ሕወሓትን #ይቅርታ ለመጠየቅ ተዘጋጅ ። አሁንም የጠየቁትን ለመስጠት እጅህ አይሳሳ¡ ሌላ ምርጫ የለንምና ።
“ጣጣችን ጨርሰን ተጨባብጠን እየመጣን ነው?”
ቸር ያሰማን!

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ሐይማኖት ነገድ ወይም ዘር የለውም!” የኢትዮጵያውያን ማሕበር በሆላንድ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share