የሶማሊያ መንግስት ጦር ባለፉት 48 ሰዓታት በመካከለኛው ሸበሌ ግዛት ባካሄድኩት ዘመቻ 28 የአልሸባብ ፅንፈኛ ቡድን ታጣቂዎች ገደልኩ አለ፡

ጥር 21፣ 2014
ጦሩ ጽንኞችን የማፅዳት ዘመቻውን ያካሄደው በባላድ ከተማ አቅራቢያ እንደሆነ የቱርኩ አናዱሉ ፅፏል፡፡
ባላድ ከመዲናዋ በስተሰሜን በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ እና ወታደራዊ ጠቀሜታዋ የጎላ ከተማ እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡
ጦሩ በባላድ አቅራቢያ ባካሄደው ዘመቻ 28 የፅንፈኛውን ቡድን ታጣቂዎች ከመግደሉም በተጨማሪ ምሽጋቸውን ማውደሙም ተሰምቷል፡፡
አልሸባብ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የጦር መላውን ወደ አጥፍቶ መጥፋት እና ወደ ድንገት ደራሽ ጥቃት ማዞሩ ይነገራል፡፡
በአፍሪካ ህብረት (አሚሶም) የሚደገፈው የሶማሊያ መንግስት ጦር ከፅንፈኛው ቡድን ጋር ሲዋጋ በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡
የኔነህ ከበደ/ ሸገር
ተጨማሪ ያንብቡ:  የጋምቤላን መሬት የተቀራመተው የህንዱ ካራቱሪ የንግድ ባንክን 62 ሚሊዮን ብር ዕዳን መክፈል ተስኖታል

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share