ክፋቱ ምንድን ነዉ…? – ማላጂ

በኢትዮጵያ ጭንቅ ቀን ደርሶ ጋሻ እና መሸሻ የሚሆነዉን ህዝብ እና የህዝብ ልጂ  ከጭለማ እና ባርነት መዉጣት መባቻ ጀግኞችን አስቀድሞ ማጥላላት የኢትዮጵያ ፖለቲካ አዳፋ መገለጫ ሆኗል፡፡

በኢትጣሊያ ፪ ኛ ወረራ የነፃነት ማግስት ባንዳ እና የከዳ የሚሾምበት የሚሸለምበት  የቅርብ ጊዜ ዕዉነት ሆኖ ለአገር አንድነት እና ለህዝብ ነፃነት የህይወት እና የደም ዋጋ የለፈሉት በራሱ በነበረዉ ስርዓት መካድ እና መገለል ደርሶባቸዋል፡፡ ዛሬ ከአንድ ክፍለ ዘመን በኋላ በኢትዮጵያ እና አማራ ጠል አራማጆች በኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዓላዊነት ፣በኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት እና በዓማራ ብሄራዊ መብት፣ ተፈጥሯዊ ማንነት እና ነፃነት ላይ አደጋ የነበሩት እና ያሉት ፍላጎታቸዉ የታሪክ እና ስልጣን ሽሚያ፣ ክዳት እና ከእኔ በላይ ለሳር  የግብታዊነት አስተሳሰብ ሲንፀባረቅ  ይስተዋላል፡፡

በኢትዮጵያ ብሄራዊ ክህደት እና በዓማራ ህዝብ ላይ ጅምላ ግድያ ፣ ማፈናቀል ፣ ማግለል…..ወዘተ ለ ፴ ዓመታት በላይ ለደረሰባቸዉ መከራ ከአስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ( ግንቦት ፳ ቀን) ጀምሮ የህልዉና እና የነፃነት ትግል በዓማራ እና በዕዉነተኛ ኢትዮጵያዉያን  ሀ ..ሁ…ሂ….  መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

ከጥቅምት ፳፬ ቀን ሁለት ሽ አስራ ሶስት  በኢትዮጵያ እና ዓማራ ህዝብ ላይ ክህደት፣ ስደት፣ ሞት እና ወረራ ተካሂዶ ለደረሰበት ጉዳት እና ጉዳቱን በሴራ እና ታስቦበት ስለመሆኑ የጦርነቱ ጅምር እና አሁን ላይ ያለዉ ዕዉነታ ተጨባጭ ዕዉነታ ነዉ ፡፡

ጦርነት እያለ ጦርነት አለቀ …..እንደ አመድ ቦነነ ….ተብሎ…..ሌላ ጁንታ …..እናዳይኖር…..የዓማራን ልዩ ኃይል ፣ ህዝብ፣ ህዝባዊ ኃይል(ፋኖ)….የከፈለዉን መስዋዕትነት ማሳነስ የተዘመረዉ…..የተሸረበዉ ክህደት…..የተሰበከዉ ገና ታህሳስ 2013 ዓ.ም. መሆኑን መረሳት ሠዉ አለመሆን ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰበር | እነ ምሬ ወዳጆ ትጥቅ ፈተዋል ወይስ አልፈቱም? | የአማራ ሕዝባዊ እንቢተኝነቱ ምን ላይ ደረሰ? | 13 April 2023 | ETHIO 251 MEDIA

ሆኖም እንደ ጉም በነነ የተባለዉ የትግሬ  ወራሪ ፣መዝባሪ  እና መሰሪ ጠላት   ስምንት ወር ሳይቆይ ሙሉ ዝግጂት አድርጎ የኢትዮጵያን ህዝብ በተለይም የኣማራ እና የአፋር ህዝብ እጂ እና ዕግሩ ታስሮ ጠላት ያሻዉን እንዲያደርግ የሚጠበቀዉን ሞት እና ዉርደት እንዲያስተናግድ ሆኗል፡፡

እዚህ ጋ የዓማራም ሆነ የአፋር ህዝብ ተጋድሎ  ራስን ከሞት እና ከጥፋት የመታደግ ብቻ ሳይሆን የአገርን አንድነት ለማስቀጠል በአንድያ ነፍሱ እና በፈሰሰ ደም እና በተከሰከሰ አጥንት  ታላቅ ዋጋ በትልቅ እና ድንቅ ታሪክ ተጋድሏል፡፡

ዕኮ በዚህ ፪ኛ  ወረራ እና ጥቃት ካደረገዉ ብሄራዊ አስተዋፅዖ  በጦርነት ዉስጥ ሆኖ በሞት እና በህይወት ያለ ህዝብ በህሄራዊ ከብሩን እና ጥቅሙን ባጣበት ማግስት በአንድ ዓመት ዉስጥ ሁለት ጊዜ  ዉለታ ቢስ እና አመድ አፋሽ ሲሆን በህመም ላይ ህመም ቢሰማዉ ምኑ ላይ ነዉ ክፋቱ፡፡

ሌላ ጁንታ  እንይኖር  በተባለ  ዓመት ሳይሞላ የድል አጥቢያ አርበኝነት …….የድል ሽሚያ…. ትንቢት አይሉት ስጋት ጮኸቴን ቀሙኝ ንግግር በተሰማ ማግስት  የድል ሽሚያ፣ የተከዳን ስሜት እነ ይገባናል …. ሌላ ምኞት   ከእዉነት ጋር የተጣላ  አስተሳሰብ መስማታችን እኛም ደንግጠናል ፡፡

ለመደንገጣችን ብዙ ቢሆንም ጦርነት እያ ድህረ ጦርነት ስጋት ማለት ምኞት መሆኑ ጦርነቱ እንዲቀጥል የመመኘት አስተሳሰብ ከመሆኑ በላይ ሳይቀድሙኝ ልቅደም  ጊዜ የማይመጥን ከፍተኛ የድል፣ የታሪክ፣ እና የማይገባን እና የራስ የስራ ዉጤት ያልሆነን ዉጤት ለራስ እና ለመሰሎች ለማድረግ  የስስት እና የአድር ባይነት ሽሚያ እና ክህደት የመኖሩን የሚያሳይ ነዉ ፡፡

ቢያንስ በኢትዮጵያ የዘመናት የሉዓላዊነት እና አንድነት ግዛት የማስጠበቅ ትልቁን ድርሻ የነበረዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ማስታወስ እና ማወደስ ባንችል በዚህ አንድ ዓመት የሆነዉን ለማጠየቅ እና ለማድነቅ አለመፈለግ  ከዚህ በላይ ክህደት፣ የድል እና የታሪክ ሽሚያ እና ቅሚያ( ይገባኛል) ምን ይሁን ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአፋርን ሕዝብ ወኃ ጠማው

ይህ በአገራችን ያለዉ ዕዉነት አንድ የቆየ አገራዊ አበባል ያስታዉሰናል …..አንድ የበግ ዕረኛ ዞትር የአካባቢዉን ህዝብ ማስጨነቅ ያስደስተዋል እንዲያዉም የመንደሩ ህዝብ በህብረት እና በአንድነት በማህበራዊ ፣ በታሪካዊ፣ በባህል… በመተሳሰብ እና በመገናዘብ ሲኖር የእርሱን ህልዉና የሚያጣ የሚመስለዉ ነበር ፡፡ እናም በየዕለቱ ቀበሮ መጣ በጎችን ሊበላ ነዉ ድረሱልኝ ባይ ሆኗል፡፡

ይህ ሟርተኛ እና ነዉረኛ እረኛ  የፈጠራ ጥሪ መሆኑን ያወቀዉ ማህበረሰብ ከዕለታት አንድ ቀን የቀበሮ መንጋ ሲከበዉ በመጮህ ድረሱልኝ ቢል ልማዱ ነዉ በማለት ህዝቡ የአሞራ ጮኸት አድርጎት ኖሯል በጎች በቀበሮዎች በአንድ ዕለት አለቁ …..፡፡

ወደ ወቅቱ ስንመጣ ከምናየዉ እና ከሆነዉ ይልቅ የማይታየዉ እና የሆነዉን ቀርቶ ያልሆነዉን ፣ የሚሆነዉን ትቶ የማይሆነዉን …..ሲነገረን ዘመናት ስላለፉ …. አሁን የብልጣብልጥ ዕረኞች ጩኸት….. የገደል ማሚቴ ከመሆን ዉጭ ዕዉነተኛ የችግር ጊዜ ደራሾችን የዕረኛዉ  ደጀኖች እና ፊታዉራሪዎችን ዕምነት ማጣት እንዳያስከትል ሁሉም የራሱ እና የአገሩ ጉዳይ የሚያሳስበዉ ኢትዮጵያዊ ዕዉነተኛዉን ዕረኛ ከሀሰተኛዉ ሊለይ እና ሊከተል  ይገባል፡፡

በኢትዮጵያ  ታሪክ ዕዉነተኛ የህዝብ ልጆች ባደረጉት መራር ትግል እና ታግድሎ መንጠቅ ( ሽሚያ፣ ክዳት እና ስስት/ይገባኛል ባይነት )ታሪክ በዘዉድ ስርዓት  በዕዉነተኛ የ፭ ዓመታት የነፃነት አርበኞች ፤ ድህረ ዘዉድ ስርዓት  በኮሎኔል አጥናፉ አባተ እና መንግስቱ ኃ/ማርያም፣ በድህረ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት ዉድቀት(1983 ዓ.ም) የበአዴን አመራር እና ታጋይ እና የዓማራ ህዝብ  ፣ በድህረ 2010 ( መጋቢት24 ) የኢትዮጵያ ህዝብ የለዉጥ ዕንቅስቃሴ ….. ምን እንደሆነ እና እነማን ሽሚያ፣ ቅሚያ እና ይገባኛል ባይ  ክህደት እንደፈፀሙ ማየት ዛሬ ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ከገጠሟቸዉ የታሪክ ፣ድል  ሽሚያ እና መከዳት በአንድም ወይም በሌላ ይመሳሰላሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አቡሽ ዘለቀ (አውጡት ከፓርላማው) - New Ethiopian Music 2022

ለአለፉት ፴ ድፍን ዓመታት በኢትዮጵያ እና ህዝቧ በተለይም በዓማራ ህዝብ ላይ የታሪክ፣ የባህል፣ የዜግነት ፣ የማንነት እና ኢትዮጵያዊነት ላይ ሽሚያ፣ ቅሚያ እና የአገር እና የታሪክ ባለቤትነት ላይ ያልተካሄደ እና ማይካሄድ ክህደት ከነበር እና ካለ እርሱ እኔ ነኝ ይበል፡፡ ያኔ ሠዉ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ማንቱን ይነግረዋል ፤ያዉቃል፡፡ በድፍኑ ተጨፈኑ ላሞኛችሁ የሶስተኛ ዓለም ፖለቲካ ለብሄራዊ ዕድገት ሆነ ለዜጎች ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚፈይደዉ አይኖርም፡፡

በቁም ያለ በጎ  ተግባር እና ምግባር ሀዉልት እንዲቆምላቸዉ የሚመኙ የሚፃፍ ታሪክ የሌለቸዉ ወይም የሚነገር ታሪክ መስራት የማይችሉ በጥላቻ እና በዝቅተኝነት ደዌ የታሰሩ ናቸዉ ፡፡

ለዕዉነተኛ ብሄራዊ አንድነት እና አንድነት ከሁሉም በፊት ዕዉነተኛ ህልዉና እና ነፃነት መረጋገጥ አለባቸዉ ፡፡ ያንጊዜ ድልም ፤ታሪክም ሆነ ዘላለማዊ ስም ለባለቤቱ ትዉልድ እና ታሪክ ይዘክራል፡፡

የሆነዉ ሆኖ   ኢትዮጵያ አገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ ፣

የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ ………..ዛሬ ቢባል ምኑ ነዉ ክፋቱ ?

የበሬን ዉለታ ወሰደዉ ፈረሱ ፣

ከኋላ ተነስቶ ከፊት በመድረሱ ፣

ዕዉነትን አፈር ለብሳ  ዉሸት እና ክህደት በሴራ ሲነሱ  ፡፡

ጦርነት እያለ  ሠላም አለወይ፣

የጀመርነዉ ሁሉ ሲናድ እየታየ እንደ አፈር ክምር ፤ እንደተካበ  ዕምቦይ ፣

ዕምየ እናት አገር ከሚናገር በቀር ሰሚ ጠፋ ወይ ፡፡

 

አንድነት ኃይል ነዉ

ማላጂ


 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share