እነ ስብሐትን ደብረሲና ሲደርስ እነርሱ መጥተው ከሚፈቷቸው ቀድመን እንፍታቸው ያሉ ባለ ሥልጣናት ነበሩ – ጠ/ሚ ዐቢይ

እነ ስብሐትን የሕወሓት ጦር (ጁንታው) ደብረሲና ሲደርስ እነርሱ መጥተው ከሚፈቷቸው ቀድመን እንፍታቸው ያሉ ባለ ሥልጣናት ነበሩ፣ አይሆንም ነው ያልነው። ጦርነቱን ካሸነፍን በኋላ ነው መፍታት ያለብን ብለን ነው የወሰንነው።” (ጠ/ሚ ዐቢይ ለዲያስፖራው በተዘጋጀው በገበታችን አገር እንገንባ የራት ግብዣ ላይ)

(ምንሊክ ሳልሳዊ)


ሾልኮ የወጣ የጠሚ አብይና የነብይት ብርቱካን የፀሎት የትንቢትና የምክር ድምፅ ቅጂን THM ለቆታል:: ቅጂው ጠሚ አብይ ሴኩላር ሀገርን ለመምራት


ሾልኮ የወጣ የጠሚ አብይና የነብይት ብርቱካን የፀሎት የትንቢትና የምክር ድምፅ ቅጂን THM ለቆታል:: ቅጂው ጠሚ አብይ ሴኩላር ሀገርን ለመምራት

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ መንግሥት ተፈጸመ የተባለውን የአየር ድብደባ አስተባብሏል

3 Comments

  1. “የዘንድሮውን የልደት በዓል የምናከብረው የመከራችን ዘመን እያከተመ፣ የችግራችን ቋጠሮ እየተፈታ፣ የሰቆቃችን ምንጭ እየደረቀ ባለበት ወቅት ነው”
    ይህን “እፁብ ድንቅ የምሥራች” ያበሰረን ፍፁም ታማኝ አሽከሮቻቸው (አገልጋዮቸቻው) አድርገው የተጠቀሙባቸውን የቀድሞ ጌቶቻቸውን (ህወሃቶችን) የህዝብን መሪር የነፃነትና የፍትህ ሥርዓት ፍለጋ እንቅስቃሴ ተጠቅመው በማስወገድ ያንኑ ጥርሳቸውን ነቅለው ያደጉበትን ወንጀለኛ ሥርዓት ግን ብልፅግና በሚል ተራ የማታለያ ስያሜ ሰይመው ይበልጥ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ያስቀጠሉትን ሸፍጠኛና ሴረኛ ኦህዴድ መራሽ ብልፅግናዊያንን (ኢህአዴጋዊያንን) በመምራት ላይ የሚገኘው ጠቅላይ ሚኒስትር ነው። ይህን “እፁብ ድንቅ” ዲስኩር ከሦስት ዓመታት በላይ ከሆነውና አሁንም እየሆነ ካለው ግዙፍና እጅግ መሪር እውነታ ጋር እንኳን ማገናኘት ለማስመሰልም ፈፅሞ አይቻልም።
    ይህን አይነት የለየለት የውሸት ዲስኩር ነውር ነው ለማለት ወኔ ቢያጥረን እንኳ እጅግ አሳፋሪ የሆነ ውዳሴ አብይ ማዥጎድጎዱን እንዴት በቅጡ ለማድረግ ተሳነን? ምነው እኩያን ገዥ ቡድኖች እየተፈራረቁ ከሚቆጣጠሩት ዘመን ጠገብ የሸፍጥ፣ የሴራ፣ የክህደት፣ የመከራና የውርደት ሥርዓተ ፖለቲካ ተሞክሮ ለመማርና ለሁሉም ልጆቿ የምትሆን ዴሞክራሲያዊት አገር እውን ለማድረግ ተሳነን? ከዚህ የከፋ ትውልዳዊ ውድቀትስ አለ ወይ? ወዘተ የሚሉ መሠረታዊና ፈታኝ ጥያቄዎችን አጥብቀን እየሸሸን ስለ ሰላምና መረጋጋት ፣ ስለ እድገት ፣ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያዊነት ክብርና ኩራት መተረክ ጨርሶ ስሜት አይሰጥም።
    ለዘመናት ከተዘፈቅንበትና አሁንም ይበልጥ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ተዘፍቀን ከቀጠልንበት ሸፍጠኛ፣ ሴረኛ፣ ፈሪና ጨካኝ የኢህአዴጋዊያን ሥርዓተ ፖለቲካ አስተማማኝነትና ዘላቂነት ባለው ሁኔታ ወጥተን የሚበጀንን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን ለማድረግ ከምር የምንፈልግ ከሆነ በዚህ መጠንና ደረጃ ነው መሠረታዊውንና ፈታኙን ሃቅ መጋፈጥ ያለብን።
    አዎ! በስሜታዊነት የፖለቲካ ትኩሳት በመገንፈልና በመቀዝቀዝ ንፁሃን ነፃነትና ፍትህ ፈላጊ ወገኖች ለእሥር፣ ለግድያ፣ ለቁም ሰቆቃ፣ ለመፈናቀል ፣ ለርሃብና ለበሽታ እንዲዳርጉ እያደረግን ስለ አገርና ስለ ወገን ወዳድነት የምንተርከው ትርክት ጨርሶ ስሜት አይሰጥምና ተገቢውን የጋራ መፍትሄ አምጠን መውለድ ያለብን ነገና ከነገ ወዲያ ሳይሆን ዛሬ ነው።
    ያም መፍትሄ ኢህአዴግ ሠራሹን ሥርዓት እንደ ሥርዓት አስወግዶ በእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ የሽግግር ወይም የመሰናዶ ጊዜ መንግሥት ወይም በምንስማማበት ሌላ ስያሜ በሚጠራ አካል በመተካት እንጅ ለዘመናት በፖለቲካ ወለድ ወንጀል የተጨማለቀውን ሥርዓታቸውን “ተሃድሶ” በሚል ርካሽ የፖለቲካ ጨዋታ ለማስቀጠል ሲሉ የበለጠ ግፍና መከራ በማስከተል ላይ በሚገኙ የኢህአዴግ ውላጆች መሪነት ፈፅሞ ሊሆን አይችልም። እንዲሆን መፍቀድም የመከራንና የባርነትን ሥርዓት ማራዘም ነው የሚሆነው።
    ከወራዳ የአገልጋይነት ፖለቲካ መላቀቅ ጨርሶ ባልሆነላቸው እና እንደ ደመ ነፍስ እንስሳት ከርሳቸው እስካልጎደለባቸው ድረስ እንወክለዋለን የሚሉት የአማራ ማህበረሰብ መከራና ውርደት ጨርሶ የማይሰማቸው ብአዴን ተብየዎች ህወሃት “ከዛሬ ጀምሮ ብአዴን ትሰኛላችሁ” ሲላቸው አሜን ብለው እንደተቀበሉት ሁሉ ዛሬም የተረኞች ገዥ ቡድን ኦህዴድ /ኦሮሙማ “ከዛሬ ጀምሮ የአማራ ብልፅግና ትሰኞላችሁ” ሲላቸው በደስታ ተቀብለው ጥርሳቸውን ነቅለው ያደጉበት ወንጀለኛ ሥርዓት እድሜው እንዲራዘም የማድረጋቸው መሪር እውነት ህሊናውን የማያቆስለው እውነተኛ ነፃነትና ፍትህ ፈላጊ የአገሬ ሰው የሚኖር አይመስለኝም። የትናንት ጌቶቻቸው (ህወሃቶች) ለጎሳ/ለቋንቋ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማር አልመቻቸው ያለውን የአማራ ማህበረሰብ በባላንጣነት ፈርጀው ሲያጠቁትና ሲያስጠቁት በማስፈፀሚያ መሣሪያነት ሲያገለግሉ የነበሩት እነዚህ ተዋርዶ አዋራጅ ብአዴናዊያን ይኸውና ዛሬም ተረኛው የኦህዴድ/ኦሮሙማ ገዥ ቡድን ክልሌ በሚለው ብቻ ሳይሆን የአማራ ተብሎ በተከለለ ክልል ውስጥ የሚገኘውን ይህንኑ ማህበረሰብ መግለፅ ለሚያስቸግር መከራና ውርደት ይዳርገው ዘንድ በዚያው በለመዱት የማስፈፀሚያ መሣሪያነት ቀጥለዋል ።
    አዎ! በእውነት ስለ እውነት መነጋገርና ተገቢውን የጋራ መፍትሄ አምጠን መውለድ ካለብን በዚህ ደረጃ ነው መናገርና መነጋገር ያለብን።
    በተረኛ ኦህዴዳዊያን (ኦሮሙማዊያን) የበላይነት የሚመሩት ኢህአዴጋዊያን የሠሩት እጅግ አስከፊ ፖለቲካ ወለድ ወንጀል ቢወገድና እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን ቢሆን እጣ ፈንታቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ባሰቡት ቁጥር ስለሚያቃዣቸው የሚፈፅሙት ወንጀል በአይነትና በመጠን እጅግ አስከፊ እየሆነ ቀጥሏል።
    እናም መሠረታዊውንና ፈታኙን የእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለውጥ የቤት ሥራ አጥብቀን እየሸሸን በመርመጥመጥ (በመንደፋደፍ) ላይ የምንገኘው መሠረታዊና ፈታኝ ጥያቄዎችን በአግባቡና በወቅቱ ለመመለስ ባለመቻላችን ምክንያት ከሚያሰቃየን የህመም ስቃይ ጋር ሆኗል። ከምንገኝበት አስከፊና አጠቃላይ ቀውስ ወጥተን የሚበጀንን ሥርዓት እውን ማድረግ ካለብን ይህንን የገንዛ ራሳችን ውድቀት ውጤት የሆነ መሪር ሃቅ ከምር በመቀበል እንደ ሰውና እንደ ዜጋ ተከባብረንና ተከብረን የምንኖርባትን ኢትዮጵያ እውን ማድረግ ይኖርብናል።
    ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዴሞክራሲያዊ አርበኝነት ፀንቶ ከዘመናት የድንቁርና እና የመከራ አገዛዝ ሊገላግለው የሚችል ድርጅታዊ ሃይል እውን ማድረግ ያልተሳካለትን መከረኛ ህዝብ ለሸፍጥና ለሴራ የፖለቲካ ጨዋታ ባሰለጠነው አንደበቱ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ትረክትን እያደበላለቀ አደገኛውን የፖለቲካ ቁማር መቆመሩን ያቆም ዘንድ በግልፅና በቀጥታ ሊነገረውና በቃህ ሊባል ይገባዋል ።
    አዎ! የእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በእውን የምንፈልግ ከሆነ በዚህ ደረጃ ነው መናገርና መነገገር ያለብን።
    ይህ የኢህአዴግ ውላጅ ጠቅላይ ሚኒስትር የተጠቀመባቸውንና እየተጠቀመባቸው ያሉትን እጅግ አሳሳችና ግልብ ስሜትን ኮርኳሪ ቃላትና ሃረጋት በመከረኛዋ ምድር (ኢትዮጵያ) ላይ ከሆነውና እየሆነ ካለው ግዙፍና እጅግ መሪር እውነታ አንፃር ከምር ማስተዋል ለሚፈልግና ለሚችል ነፃነትና ፍትህ ፈላጊ የአገሬ ሰው ከበቂ በላይ ግልፅና ግልፅ ነውና ከምር በቃህ መባል ይኖርበታል ። የመማር እድሉ የተነፈገውን አብዛኛውን የአገሬ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ተምሬያለሁና ተመራምሬያለሁ የሚለውን የህብረተሰብ ክፍልም ምን ያህል መሳቂያና መሳለቂያ እንዳደረገውና እያደረገው እንደሆነ የማይገነዘብ የአገሬ ሰው ዴሞክራሲንና ዴሞክራሲያዊት አገርን መመኘቱ ቅዠት እንጅ እውነት ሊሆን ከቶ አይችልም ።
    ይህ በሸፍጠኝነትና በሴረኝነት ፖለቲካ ሰብዕና እና በአደገኛ የሥልጣንና የግል ዝና ፍቅር የተለከፈ ጠቅላይ ሚኒስትር አያሌ ንፁሃን ዜጎች ከሦስት ዓመታት በላይ የገንዛ አገራቸው ምድረ ሲኦል ስትሆንባቸው በይፋ ወጥቶ “አዝናለሁ” ለማለት አለመፈለጉ አልበቃ ብሎት አሁን ደግሞ ገና እውነተኛና ዘላቂ ድል ጨርሶ በሌለበት እና ይልቁንም የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማሩ ይበልጥ በደራበት (አደገኛ የምን ታመጣላችሁ ፖለቲካ በጦዘበት) መሪር ሃቅ ውስጥ “ታሪካዊ ድል አጎናፅፊያችኋለሁና ደስ ይበላችሁ” ሲለን ህሊናውን ጨርሶ አይጎረብጠውም። ።
    የቀድሞ አለቆቻቸውን (ህወሃቶችን) ዶግ አመድ እንዳደረጓቸው ከነገሩን በኋላ ሠራዊቱ ትግራይን ለቆ እንዲወጣ የማድረጋቸው እጅግ አሳፋሪ ድራማ አልበቃ ብሎ መንገድ እየጠረጉና የጦር መሣሪያ እያስረከቡ እስከ ሰሜን ሸዋ (የቤተ መንግሥት በር) ድረስ እንዲደርስ ያደረጉ ሸፍጠኛና ሴረኛ የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ አራማጅ ወታደራዊ መኮንኖችን እስከ ፊልድ ማርሻልነት በደረሰ ሹመትና ሽልማት ሲያንበሸብሽ ለምና እንዴት ብሎ ሳይጠይቅ እልልታውን የሚያቀልጥ ወይም በተሸናፊነት ስሜት የሚቆዝም ትውልድ እንዴትና በየት በኩል ዴሞክራሲያዊት አገርን እውን ሊያደርግ እንደሚችል ሲያስቡት በእጅጉ ይከብዳል።
    የገጠመንና እየገጠመን ያለውን አጠቃላይ ማለትም ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ሞራላዊ፣ ሥነ ምግባራዊ፣ እና መንፈሳዊ ቀውስ በዚህ መጠንና ደረጃ ካልተጋፈጥነው በስተቀር ከዘመን ጠገቡ የመከራና የውርደት አዙሪት ፈፅሞ መውጫ አይኖረንም።
    ይህ ትውልድ በመንበረ ሥልጣን ላይ እየተፈራረቁ ለማታለያነት (ለማጨበርበሪያነት) ባሰለጠኑት ብእራቸውና አንደበታቸው ግልብ ስሜቱን እየኮረኮሩ የፖለቲካ ቁማራቸው መጫወቻ ያደረጉትንና እያደረጉት ያሉትን እኩያን ገዥ ቡድኖች “ከዚህ በላይ ትግሥት ከደመ ነፍስ እንስሳት በታች መዋል ነውና በቃኝ! እናንተም በቃችሁ” ብሎ ከመጋፈጥ ይልቅ ከግዙፉና መሪሩ እውነታ እየሸሸ እና ለገንዛ እራሱ ውድቀት የሰብብ ድሪቶ እየደረተ የመቀጠሉን ክፉ ልክፍት ነገ ሳይሆን ዛሬውኑ ማረም ይኖርበታል።
    በእውነት ስለ እውነት እንነጋገር ካልን ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው በተለመደው የፖለቲካ ቅጥፈት አንደበቱ መከረኛውን ህዝብ መሳለቂያ ማድረጉ አልበቃ ብሎት የክርስቶስን የልደት በዓል ለእርካሽና አስከፊ የፖለቲካ ቁማር ማድመቂያነት ሲያውለው ጨርሶ ህሊናውን የማይኮሰኩሰው ፣ የማይቆጣ እና እምቢ ለማለት የተሳነው ትውልድ እንኳን ዴሞክራሲያዊት የሆነች ከነመከራውና ከነውርደቱ የሚኖርባት (መኖር ከተባለ) አገር ባይኖረው ምን ይገርማል?
    ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚወስደንን መንገድ በመሳት ተመልሰን ለዘመናት ከመጣንበት የቀውስና የውድቀት አዙሪት ውስጥ ይበልጥ አስከፊ በሆነ ሁኔታ እንደምንዘፈቅ ግልፅና ግልፅ የሆነው ከዛሬ አራት ዓመታት በፊት እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እውን ለማድረግ የግድ ከሚሉ መሠረታዊና ፈታኝ ጥያቄዎች እየሸሸን ለሸፍጠኛ፣ሴረኛ፣ ፈሪና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች እራሳችንን አሳልፈን የሰጠን እለት ነው።
    አዎ! ይኸውና ዛሬም የነገን ተስፋ ትክክልኛነትና ዘላቂነት ባለው አስተሳሰብና ቁመና እውን ከማድረግ ይልቅ የኦህዴድ የበላይነትና የብአዴን ተብየዎች አሽከርነት (ወራዳነት) እያስከተለ ስላለው እጅግ አስከፊ የህመም ስሜት (chronically horrible symptoms of illness) የትንታኔ ድሪቶ ከመደረት ክፉ ልማድ ሰብረን ለመውጣት በሚያስችል የተግባር ውሎ ላይ ለመገኘት ትርጉም ባለው ሁኔታ አልተሳካልንም።
    ዘመናትን ያስቆጠረውንና ህይወትን ጨምሮ ከፍተኛ ዋጋ የተከፈለበትን የመሠረታዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሽግግር እና ምሥረታ ጥያቄን የሸፍጠኛ፣ ሴረኛ፣ ፈሪና ጨካኝ የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኞች የሥልጣነ መንበር የበላይነት ሽኩቻ ከወለደው የማታለያ ተሃድሶ (highly deceptive reform) ለይተን ለማየት ወይም ለመረዳት አለመፈለጋችን ወይም አለመቻላችን ያስከፈለንና እያስከፈለን ያለውን ዋጋ ለመግለፅ በእጅጉ አስቸጋሪ እየሆነብን ቀጥሏል። ለዚህ እውነትነት ደግሞ መሬት ላይ ካለው ግዙፍና መሪር እውነታ በላይ የሚነግረን ሌላ ዋቢ አያስፈልገንም።
    ከሥርዓት ለውጥ ጥያቄ ክፉኛ በመንሸራተታችን በኢህአዴጋዊው ሥርዓት ውስጥ ጥርሳቸውን ነቅለው ያደጉና በፖለቲካ ወለድ ወንጀል የተዘፈቁ ፖለቲከኞች (ካድሬዎች) እራሳቸውን ብልፅግና በሚል የማታለያ ስያሜ ሰይመው እና ለግልብብ ስሜት የሚመቹ (የሚስማሙ) ቃላትን ባሰለጠኑት የማታለያ አንደበታቸው እየደረደሩ ወይም እየደሰኮሩ “ታሪክ ሠሪ የለውጥ ሃይሎች ነንና በመደመር ፍልስፍና እየተጠመቃችሁ ተከተሉን” ሲሉን ለምንና እንዴት? እናንተ እነማን ናችሁ? ወዘተ ብለን ለመጠየቅና በፅዕናት ለመሞገት (ለመታገል) አለመድፈራችን ሳያንስ እንዲያውም ይባስ ብለን “ከሰማየ ሰማያት የተላካችሁልን ሙሴዎች” በሚል የሸፍጣቸውና የሴራቸው ሰለባነታችንን አረጋገጥንላቸው።
    መሬት ላይ ከሆነውና እየሆነ ካለው ግዙፍና አስከፊ ተሞክሮ ሲሆን በፍጥነት ካልሆነ ደግሞ ዘግይቶም ቢሆን በመማር እየገደሉ ፣ እያጋደሉና አገር እያፈረሱ “እኛ ከሌለን እንተላለቃለን እና አገርም ይፈርሳል” ሲሉን ለምንና እንዴት? አሁንስ ምን እያደጋችሁ ነው? ለዓመታት ሥራ ላይ ያዋላችሁትንና አገር አፍራሽ የሆነውን ሥርዓታችሁን ባስቀጠላችሁበት መሪር እውነት ውስጥ ስለ ምን አይነት ለውጥ ነው የምታወሩት (የምትሰብኩት)? ብለን ከምር ለመጠየቅ (ለመሞገት) አለመቻላችን ወይም አለመድፈራችን በእጅጉ ያሳዝናል ወይም ያሳፍራል። ቀድሞውንም በሥልጣን የበላይነት ተረኝነት ጥያቄ የተጣሉትና ከሁለት የተከፈሉት ኢህአዴጋዊያን (ህወሃት እና ኦህዴድ/ብልፅግና) ያካሄዱትንና እያካሄዱት ያለውን አስከፊ የሥልጣን የበላይነት ሽኩቻ ጦርነት በዴሞክራሲያዊ ለውጥ ፈላጊዎችና በፀረ ዴሞክራሲሲያዊ ለውጥ ቡድኖች ወይም በአገር ገንቢዎችና በአገር አፍራሽ ሃይሎች መካከል የተደረገና የሚደረግ ጦርነት እንደሆነ አድርገን የምናይበት እይታ ፍርሃት ወይንም አድርባይነት ከተጫነው ህሊና እንጅ ከገሃዱ ዓለም የኢትዮጵያ ፖለቲካ እውነታ የሚመነጭ አይደለም።
    ሸፍጠኛ ፣ሴረኛ፣ ፈሪና ጨካኝ በሆኑ ኢህአዴጋዊያን /ብልፅግናዊያን እና በተለይ ደግሞ የኦህዴድ (ብልፅግና) መሪ በሆነው ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ “እንኳን የተቃውሞ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ግልፅና ቀጥተኛ የሆነ ትችት የሚተቹ ወገኖችን አገር አፍራሾች ወይም ከአገር አፍራሽ ሃይሎች ጋር የሚተባበሩ ናቸው ” በሚል እጅግ የወረደ ትርክት የመተረካችን ፣ መዝሙር የመዘመራችን ፣ ተውኔት የመተወናችን ፣ ቅኔ የመቀኘታችን፣ ስብከት የመስበካችን ፣ የጎዳና ላይ ትእይት የማካሄዳችን ፣ የእርግማን ናዳ የማውረዳችን እጅግ አሳፋሪ ሁኔታ እየመረረንም ቢሆን ነገ ሳይሆን አሁንኑ ማረም ግድ ይለናል።
    በሚዛናዊ ህሊናቸው ፀንተው እኩይ ሥራንና ሠሪዎቹን የሚተቹና የሚታገሉ ወገኖች የእሥርና የእንግልት ሰለባዎች ሲሆኑ “እሰይ ይበለው/ይበላት” የምንልበትን እጅግ ሰነፍና ጨካኝ የፖለቲካ አስተሳሰብ ከምር ቆም ብለን ለመፈተሽ በሚያችል ሁኔታ ውስጥ አይደለንም ። መቸም የገንዛ ራሳችንን ፈታኝና መሪር እውነታ አጥብቀን እየሸሸን በየራሳችን የቅዠት ዓለም ውስጥ ራሳችንን መሸንገል (ማታለል) ክፉ ልማድ ሆኖብን ነው እንጅ ከዚህ የከፋ አሳዛኝ የፖለቲካና የሞራል ድህነት የለም።
    እውነተኛ ነፃነት፣ ፍትህ፣ እኩልነት፣ አብሮነት፣ ሰላምና እድገት እውን ይሆኑ ዘንድ የግድ የሚሉ መሠረታዊና ፈታኝ ጥያቄዎችን የሰበብ ድሪቶ እየደረቱ አጥብቆ በመሸሽ በሸፍጠኛ፣ ሴረኛ፣ ፈሪና ጨካኝ የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ገዥ ቡድኖች እና የዚህ ክፉ የፖለቲካ አስተሳሰብ ልክፍተኞች በሆኑ ፖለቲከኞች ላይ ግልፅና ቀጥተኛ ትችት ለመሰንዘር “ጊዜው አሁን አይደለም” የሚል ምሁር ፣ ተራኪ፣ዘማሪ፣ ዘፋኝ ፣ተዋናይ፣ ሰባኪ፣ ትእይንተኛ፣ አክቲቪስት፣ ቅኔ አውራጅ ፣ ገጣሚ፣ ተራጋሚ ወይም እሰይ ይበለው/ይበላት ባይ ቁጥሩ ቀላል ያልሆነበትን የፖለቲካ አዙሪት ሰብረን ለመውጣት ብቸኛው መንገድ መሠረታዊና ፈታኝ ጥያቄዎችን በመጋፈጥ የሚበጀውን የጋራ መፍትሄ አምጦ መውለድ ነው። እጅግ አደገኛ ከሆነው የኢህአዴጋዊያን/ብልፅግናዊያን የፖለቲካ ሥርዓት ቫይረስ ጋር እየተሻሹ ጤናማና ዴሞክራሲያዊት አገርን መናፈቅ ወይ የለየለት የፖለቲካ ድንቁርና ወይም ደግሞ እጅግ ክፉ የአድርባይነት ደዌ (ልክፍት) ነው። በመሆኑም እውነተኛ የነፃነትና የፍትህ ሥርዓት እውን መሆንን ከምር የምንፈልግ ከሆን እስከዚህ ድረስ ነው መነጋገር ወይም መሟገት ያለብን።
    ከህመም ስቃይ ለመገላገል የህመሙ አይነተኛ መንስኤ (root cause) የሆነውን የኢህአዴጋዊያን የፖለቲካ አስተሳሰብና ሥርዓት ከመርዘኛ ግሳንግሱ (ምንነቱ) ጋር ከሥሩ እንዲነቀል በማድረግ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እውን ለማድረግ ሳንችል የመቅረታችን ውድቀት በሦስት ዓመታት ውስጥ ከሩብ ምእተ ዓመቱ በከፋ ሁኔታ ዋጋ አስከፍሎናል፤ እያስከፈለንም ይገኛል። ከእራሳችን ጉዳትና ውርደት አልፎም የዓለም ማህበረሰብ መሳቂያና መሳለቂያ አድርጎናል። ከባእዳን የባርነት ቀንበር ነፃ ይወጡ ዘንድ አርአያዎች ከመሆን አልፈን የምንችለውን እገዛ ሁሉ ያደረግንላቸው የእኛው ክፍለ ዓለም (የአፍሪካ) አገሮች ሳይቀሩ ከንፈራቸውን በመምጠት “ሲያሳዝኑ” ብለውናል ወይም ተሳልቀውብናል።
    አዎ! ለዘመናት የመጣንበትንና አሁንም ለመግለፅ የሚያስቸግር ሁለንተናዊ ውድቀት እያከናነበን የቀጠለውን የኢህአዴጋዊያንን (የብልፅግናዊያንን) ሥርዓት ነፃና አሳታፊ በሆነ ሥርዓተ ሽግግር አስወግደን እውተኛ ዴሞክራሲያዊት አገርን (ኢትዮጵያን) እውን ማድረግ ካለብን በዚህ መጠንና ደረጃ ነው መናገር፣ መነጋገርና መታገል ያለብን።
    በሚያሳዝን ሁኔታ ግን አሁንም የተጠመድነው ውድቀታችን ያስከተለውን እጅግ ግዙፍና መሪር መከራና ውርደት በመተረክ እና የንድፈ ሃሳባዊ (theoretical) ትንታኔ ድሪቶ በመደረቱ ዙሪያ ነው።
    እርግጥ ነው እንኳን አገራዊውን የትኛውንም ሌላ ጉዳይ በአግባቡ መረዳትና መተንተን ለጉዳዩ መፍትሄ ፍለጋ ቢያንስ ግማሽ መንገድ የመሆኑን እውነታ አሳንሶ ማየትና ማሳየት ትክክል አይደለም። እያልኩ ያለሁት ግን ድርጊት (ተግባር) አልባ የሆነ የዲስኩርና የትንታኔ ጋጋታ ፈፅሞ የትም አያደርስም ነው።

  2. የፓለቲካ እውነት ወደ ኋላ ነው። ቆይቶ እንዲህ የተባለው እኮ እንዲህ ነበር እንባላለን። እኛ ግን ጅላጅሎች በየቀኑ የተሰጠንን የውሸት ቡና ፉት ከማለት አልፈን እንጋተዋለን። በመሰረቱ የአቶ ስብሃትና የሌሎች ፍች የውጭ እጅ የለበትም የሚለው ወሬ የተወላገደ ውሸት ነው። የመጨረሻው የፊልትማን ወደ አዲስ አበባ ጉዞ በኢትዪጵያ መንግስት የተጠራና በፍቺውና በሌሎችም ዙሪያ የመከረ እንደነበር ይገባናል። ስለዚህ ትዕዛዙ ከዋሽንግተን ለመሆኑ አያሻማም። ስለዚህ እኔም ደንግጫለሁ የሚለው ጉዳይ ተቀባይነት የለውም። የሚያሳዝነው ግን ወሎን፤ ጎንደርን፤ ሽዋንና አፋርን ለወያኔ መንጋ ጥሎ የሸሸው የመከላከያ ሃይል ምን እየሰራ እንደነበረ መገመት እጅች ይከብዳል። መንግስትና በዙሪያው ያሉ ሁሉ በወያኔ ፈጣን ጥቃትና አፍራሽ ግስጋሴ ተስፋ ቆርጠው እንደነበረ የሚያሳየው ወያኔ ደብረ ሲና ሲደርስ እነርሱ አዲስ አበባ ገብተው ከሚፈቷቸው እኛ እንፍታቸው ያሉ ባለስልጣኖች ነበሩ መባሉ ነው። ጭንቀቱ እነ ስብሃትን ማን ይፍታቸው እንጂ ወያኔ በያዛቸው ስፍራዎች የሚያደርሰው ገመና የታያቸው ብዙዎች አልነበሩም ማለት ነው። አሁን በየክልሉ አጨድናቸው፤ አባርርናቸው፤ ዳግመኛ እንዳይነሱ አርገን ደቆስናቸው የሚባለው ከእውነት የራቀ ጡርንባ ሁሉ አንድ ነገር መረዳት ይኖርበታል። ” የሸሸ/ያመለጠ ጠላት የተሸነፈ ጠላት አለመሆኑን ነው”። ወያኔ ቆሞ እየሄደ ከተንኮል ተነጥሎ ለሰው ልጆች ሰላም ትጥቁን ፈትቶ፤ የትግራይ ህዝብም በመረጠው ጎዳና ይኑር ብሎ ይተዋል ብሎ መገመት ሰካራምነት ነው። ወያኔ ዳግመኛ ወረራ እንደሚፈጽም 100% እርግጠኛ ነኝ። እያደረገም ነው። ስለዚህ በአዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች አካኪ ዘራፍ ማለቱ የጠላትን ባህሪ ካለመረዳት የመነጨ ይመስላል። የኢትዮጵያ የእርስ በርስ ግጭት መሰረቱ ወያኔና የዘረጋው አፓርታይድ የፓለቲካ ስሬት ነው። በ 27 ዓመቱ አገዛዝ በሰው ልጆች ላይ የፈጸመውን በደል ዞር ብሎ ለተመነ ምን ሃይል ድርቡሾች እንደሆኑ ያሳያል። ስንቶች ናቸው አካለ ጎደሎ የሆኑ፤ የሞቱ የተሰወሩ፤ ሃብትና ንብረታቸው የተዘረፉ፤ ሚስቶቻቸውን እህቶቻቸውን የተቀሙ? ታሪክ ይቁጠረው። በወያኔ የመከራ እሳት ተጠብሶ ከዘመናት በህዋላ ከእስራት የተፈታው አቶ አንድዓለም አራጌ ” 3000 ሌሊቶች” በተሰኘው መጽሃፉ ላይ እንደሚያስነብበን አፋኙ፤ አሳሪው፤ መርማሪው፤ ቀበቶ አስፈቺው፤ ጠባቂው የትግራይ ተወላጅ ነበር። ግፍ በሰው ልጆች ላይ ለ 27 ዓመት ሲዘንብ ዝም ያሉት የትግራይ ተወላጆች ይህ የተዛባ የፓለቲካ ፈሊጥ ጊዜ እንደሚደረምሰው አለመገመታቸው በጥቅም መተሳሰራቸውን ያሳያል። አልፎ ተርፎም አሁን በተፈጠረው የእብዶች ግብግብ የትግራይ ወጣቶች እንደ እሳት ራት በወያኔ እየተገፉ ሲማገድና ሌላውን እየማገድና እየደረመሱ ሲያልቁ ድምጽ አለማሰማታቸው የትግራይ ህዝብና ወያኔ አንድ መሆናቸውን ያሳያል። ወያኔ መከራና ደም አጉራፊ ድርጅት ነው። ሰላምን አያውቃትም። የትግራይን ህዝብ ለዘመናት ሲነግድበት እንደኖረ ያለፈ ታሪካቸው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ቃል የማያልቅበት የአሁኑ ጠ/ሚርም ከዚሁ የዳቢሎስ ኮሮጆ አምልጦ የወጣ ለዘመናት ከእነርሱ ጋር የሰራ በመሆኑ አሁን ባለው “ህገ መንግስት” ላይ ተደግፎ ኢትዮጵያን ወደ አንድነትና ወደ ሰላም ማሻገር ከባድ ነው። ሌላው ቀርቶ በባንዲራ እንኳን አልተስማማንም።
    ሾልኮ የወጣ ተብሎ የተለጠፈልን የስልክ ጭውውት የሚያሳየው የእምነትን መላላትና የስመ ነብይ/ነብይነት መርከስን ነው። ይመስለኛል ይቺው ሴትና በዋይት ሃውስ ለትራንፕ ጸሎትና የወደፊት አመላካች ነገሮችን ያደረገችው። ድሮ ቀረ የወንጌሉን ቃል ይዞ ሰውን በሰውነቱ ፈርጆ ለሰማይ ቤት እንዲበቁ ማስተማር። አሁን የሚደረገው ነገር ሁሉ የመኖሪያ ብልሃት ፍለጋና የእኔንም ጋኔን አውጣልኝ ብሎ ማመልከቻ የሚያስገቡ አማኞችን ያፈራች ምድር ናት። ሲጀመር ጋኔን ብሎ ነገር የለም። ጋኔኑ እኛው ራሳችን በእህትና በወንድሞቻችን ላይ የምንፈጽመው በደል ነው። ቆም ብሎ የኢትዮጵያን የእምነት ቤቶች (እስላሙን፤ ኦርቶዶክሱንና ሌላውንም መጤ እምነቶች) ላጤነ የእኔ ካንተ ይሻላል የሚሉ እንጂ የጋራ በሆነ ሃሳብ ላይ አብሮ ለመኖር ያደርጉ የነበሩት ጥረት እየላላና ወሸት እየላሰ ተበርዟል።
    ጠ/ሚሩ እነዚህን ነብይና ነብያት ነን የሚሉ ሰዎችን ባያዳምጡና በምድር ላይ ያለውን ተጨባጭ ነገር በማጤን አመራር ቢሰጡ ፍሬማነታቸው የተሻለ ይሆናል። እኔ የስልኩን ጭውውት እንዳለ የምሰለቅጥ ሰው አይደለሁም። It can be doctored or simply fabricated by those who will always wish to keep us killing each other for endless time. ግራም ነፈሰ ቀኝ ሃገሪቱ ካለችበት የፓለቲካ አጣብቂኝ እንድትወጣ ከተፈለገ የወያኔ ሽንፈት ቀዳሜው ተግባር ነው። ወያኔ በትግራይ እያለ በምንም ሂሳብ ኢትዮጵያም ሆነች አጎራባች ሃገሮች ሰላም አይኖራቸውም። በቃኝ!

  3. The problem now is, lie #5, to cover lie#4, lie #4 to cover lie #3, lie #2 is to cover lie #1, why not the Truth at first ?, Mind you, you are talking to 120,000,000, Ethiopians minus those…all these are about Tomorrow…

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share