የሕወሓት ወራሪ ኃይል ወደ ወልቃይት 9 ጊዜ መድፍ ተኮሰ።

debreየትግሬ ወራሪ ኃይል ሰሞኑን በወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምትና አበርገሌ በኩል ለማጥቃት ተዘጋጅቶ ሰንብቷል። ትናንት ወደ ወልቃይት 9 ጊዜ መድፍ ተኩሷል። በአበርገሌ ተደጋጋሚ ትንኮሳ አድርጓል። ዋና አላማው የሱዳንን ኮሪደር ማስከፈት ሆኖ ለጊዜው ለማጥቃት ሁለት የቅርብ ምክንያቶችን ይዟል። የመጀመርያው ሰሞነኛው የበዓል ሁኔታ ነው። በበዓሉ ሰሞን መዘናጋት ስለሚኖር አጠቃለሁ ብሎ በመቶ ሺህ የሚቆጠር መንጋ አሰልፏል።

ሁለተኛው የጀፍሪ ፌልትማን መምጣት ነው። የአሜሪካው መልዕክተኛ ወደ አዲስ አበባ ይመጣል በመባሉ የትግሬ ወራሪ ለወረራ እየተራወጠ ነው። ያስፈጀውን አስፈጅቶ የሆነ ቦታ ይዞ ለመደራደርያ አቅም ማግኘት ነው። ድርድርን ለማጥቂያ የሚጠቀሙበት መሆኑን ደጋግመው ተናግረዋል። ለዛም ቢሆን ግን “ይህን ይዛችኋል ልቀቁ” ተብለው መደራደርያ ይፈልጋሉ። ስለሆነም ፌልትማን ሲመጣ የሆነ ነገር ይዘን መጠበቅ አለብን ብለው ለወረራ ተዘጋጅተዋል።

በተደጋጋሚ መዘናጋት ዋጋ አስከፍሏል። እነሱ ሁሌም ለመውረር እንዳሰቡ ነው። ሁሌም። ሁሌም ሕልውናን ለመጠበቅ መዘጋጀት ነው መፍትሄው።

በዓሉ መከበሩ በጣም ጥሩ ነው። ግን የፀጥታ ኃይሉ፣ የወታደራዊና ፖለቲካ አመራሩ ዳንኪራ የሚያበዛበት መሆን የለበትም። በዓሉ ያልፋል። ከርሞ ይመጣል። ሕልውናህን ዛሬ ከነጠቁህ ነጠቁህ ነው!

Getachew Shiferaw

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.