“ድንገት አመሻሹ ላይ ነው ዕቃችሁን ይዛችሁ ውጡ የተባልነው” የባልደራስ አመራር

122621556 66856c9e b8d6 4ef7 a46e daacbe0d1ace.jpgየባልደራስ ከፍተኛ አመራር የሆኑትና በቂሊንጦ ከአቶ እስክንድር ነጋ ጋር ታስረው የነበሩት የፓርቲው የድርጅት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በዛሬው ዕለት ከምሽቱ 12፡30 አካባቢ የማረሚያ ቤቱ ሠራተኞች ድንገት መጥተው ከማረሚያ ቤቱ እንዲወጡ እንደነገሯቸው አስስረድተዋል።

“ድንገት አመሻሽ ላይ መጥተው ዕቃችሁን ይዛችሁ ውጡ አሉን፤ ያው እቃችንን ይዘን ወጣን። ምንም የምናውቀው ነገር የለም” በማለት አቶ ስንታየሁ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንደወጡ በስልክ ለቢቢሲ ተናግረዋል።  አቶ ስንታየሁን በስልክ ባገኘበት ወቅት ከቂሊንጦ ማረሚያ ወጥተው ከአቶ እስክንድር ጋር ከማረሚያ ቤቱ አቅራቢያ ወደሚገኝ ቤተ ክርስቲያን እያመሩ እንደሆነም ገልጸዋል። “በዋናነት የተፈታነው በአምላክ ኃይል ነው፤ እውነት ነው ያሸነፈው፤ የሕዝብ ትግል፣ የሕዝብ እንባ ነው ያሸነፈው” ብለዋል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.