ሰበር ዜናው ስብሐት ነጋ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ዓባይ ዘውዱ፣ አባዲ ዘሙ፣ ሙሉ ገ/እግዚአብሔር፣ ኪሮስ ሐጎስ፣ ጃዋር ሞሐመድና በእሱ ክስ ስር ያሉ ተከሳሾች በሙሉ መፈታታቸውን ገልጿል!!!
ልብ በሉ የእነኝህ ወንጀለኞች ወንጀል ከዘር ማጥፋት ጥቃት እስከ ሀገርን ያራቆተ ዝርፊያ መሆኑን ልብ በሉ፡፡ ይሄ ወንጀል ደግሞ በየትኛውም ሕግ ምሕረትም ሆነ ይቅርታ የሚያሰጥ አለመሆኑንም ልብ በሉ!!! እነ እስክንድርን ተዋቸው ያለ ወንጀላቸው ለማባያ የታሰሩ ናቸውና!!!
ያኔ ትዕይንቱን እውነት ለማስመሰል እነ አቦይ ስብሐት እንዲያ ተጎሳቁለው በመታየት “በቁጥጥር ስር ዋሉ!” በተባለ ጊዜ ምን ነበረ ያልኩህ ወገኔ????
ለእነ አቦይ ስብሐት ምሕረት ተደረገ ማለት ለእነ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ለእነ ደብረጽዮን ወዘተረፈም ምሕረት ተደረገ ማለት እንደሆነ መረዳት ካልቻላቹህ ፖለቲካ አይገባቹህም ማለት ነው!!!
እነ አቦይ ስብሐት በዚህ ፀረ ሕዝብ ጦርነትም ሆነ በመላ የወያኔ ሠላሳ ዓመት የሥልጣን ዘመን ወያኔ ከዘር ማጥፋት ወንጀል እስከ የሀገርን ካዝና ያራቆተ ዝርፊያ ለፈጸመው ወንጀልና ግፍ ሁሉ የነበራቸው ሚናና ተሳትፎ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ በሠላሳ ዓመቱ የወያኔ ወንጀልና አረመኔያዊ ግፍ የተሞላ የሥልጣን ዘመን ሌሎቹ ለስሙ ሥልጣን ላይ ይቀመጡ እንጅ ወሳኞቹና አራጊ ፈጣሪዎቹ እነ አቦይ ስብሐት መሆናቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው!!! ሌሎቹ ከእነ አቦይ ስብሐት የሚያንሱ ናቸው!!!
አሁን ሕዝቡ መጠየቅ ያለበት ጥያቄ “እንዲህ ሕግ ተጥሶ ለሚፈቱት ነገር ‘ሕግን የማስከበር ጦርነት!’ በሚል ሀገሪቱ ወይም ሕዝቡ ይሄንን ሁሉ እልቂትና ውድመት ማስተናገዱና ዋጋ መክፈሉ ለምን አስፈለገ ታዲያ???” ብሎ መጠየቅ አለበት!!!
እኔ ግን “ሕግን የማስከበር ጦርነት!” የሚባለው ነገር ውሸት ወይም ሽፋን መሆኑንና “ዓላማው አማራን ለመፍጀት፣ ሀብት ንብረቱን ለመዝረፍና ለማውደም ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በማሰብ የውሸታቸውን ለሁለት ተቧድነው የሚያደርጉት የውሸት ጦርነት ነው!” ብየ ደጋግሜ ተናግሬያለሁ!!!
ይሄው አሁን “ሕግን ለማስከበር!” በሚል ሽፋን የተደረገው ጦርነት ሕግን ሳያስከብር እንኳንና ያልተያዙት ሊያዙ ይቅርና “ተያዙ!” የተባሉትም ሕግ ተጥሶ ተለቀው ጉዳዩን በዚህ መልኩ ለመቋጨት ከመፈለጉ የጦርነቱ ዓላማ እኔ ስለው የነበረው መሆኑን ቁልጭ አድርጎ አረጋግጧል!!!
በየትም ሀገር ቢሆን ይቅርታና ምሕረት እንዲሁም እርቅ ከፍትሕ በፊት ተፈጽሞ አያውቅም፡፡ ምክንያቱም ከፍትሕ በፊት የሚደረግ ምሕረት እንዲሁም እርቅ አኪያሔዱ የሕግ አሠራርን የተከተለ ስላልሆነ ነው፡፡ አሁን እንግዲህ ፍትሕ ሳይሰጥ ምሕረት መደረጉ ሌላው እኔ “ድራማ ነው!” ስለው የነበረው እውነት መሆኑን የሚያረጋግጥ ጉዳይ ነው!!! ይሄኛው ጉዳይ ደግሞ ጨርሶ ምሕረት ወይም ይቅርታ የሚያሰጥ አለመሆኑን አትርሱ!!!
አገዛዙ ይሄንን ያደረገው በአሜሪካ ጫና ለማስመሰል ፌልት ማን አዲስ አበባ ባለበት ሰዓት ይሄንን አድርጓል!!!
ድራማው የሦስትዮሽ መሆኑን ደጋግሜ እንደነገርኳቹህ ታስታውሳላቹህ አይደል??? ስንት ጊዜ ነው “እነ አሜሪካ ማዕቀብ የሚጥሉትና ጫናዎችን የሚያደርጉት ከአገዛዙ ጋር እየተማከሩና እየተስማሙ ነው፡፡ ማዕቀቡና ጫናው የእውነት ወይም መንግሥት ተብየውን ለመጉዳት ታስቦ የሚደረግ እንዳይመስላቹህ፡፡ ታርጌታቸው ወይም ኢላማቸው ሕዝቡ ነው፡፡ የማዕቀቡና የጫናው ዓላማም ሕዝቡ እንዲቸገር በማድረግ ከወያኔ ጋር የሚደረገውን ስምምነት ሳይወድ በግዱ ‘ይሁን!’ ብሎ እንዲቀበል ለማድረግ ነው፡፡ ምክንያቱም ወያኔ/ኢሕአዴግ እየተወነብን ያለውን ድራማ መቋጨት በፈለገ ጊዜ እርቅ አድርገው የተስማሙ በማስመሰል ድራማውን ለመቋጨት ስለሚፈልጉ እንዲህ ለማድረግ ሲሞክሩ ጦርነቱ የእውነት የሚመስለው ሕዝቡ ይሄንን ፍትሕን የረገጠ እርምጃ አጥብቆ ስለሚቃወም በማዕቀቡና በጫናው በሚፈጠሩበት ችግሮች ተንበርክኮ የድራማውን እርቅ ተገዶ እንዲቀበል ለማድረግ ነው!” ብየ ስንት ጊዜ ነው የነገርኳቹህ???
አሁን ታዲያ የልባቸውን ሲሠሩ ቆይተው ሲያበቁ በዚህ ሴራቸውና አሻጥራቸው የጨፈጨፉትን ሕዝብ “ለሀገር የከፈለው ዋጋ ነው፡፡ በሽግግር ፍትሕ ተጠቃሚ እንዲሆን ይደረጋል!” ብሎ ማለት በዘር ማጥፋት ጭፍጨፋቸው በአረመኔያዊ ግፍ የተጨፈጨፉ ወገኖቻችንን ደጋግሞ መግደልና ነፍሳቸውን እረፍት መንሣት አይደለም ወይ ወገኖቸ??? የት አግኝተውትስ ነው ይሄንን የፈጁትን ሕዝብ የሽግግር ጊዜ ፍትሕ ተጠቃሚ የሚያደርጉት??? በዚህ ደረጃ ነው እንግዲህ የናቁንና እያላገጡብን ያሉት!!!
እነሱ ምን ያድርጉ ሁሌም አረመኔያዊ ግፋቸውን አሜን ብሎ የሚቀበል ሕዝብ እያለላቸው ለምን ብለው ይጨነቁ??? ለማንስ ብለው ያስቡ??? ማንንስ ፈርተው ከአረመኔያዊ ግፋቸው ይታቀቡ???