የወልዲያና ቆቦን ጨምሮ ከተማ ሙሉ በሙሉ ነፃ ውጥተዋል

268480882 3093264724249319 980052657627065122 nኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን አዲስ ዓመትን ሲያሳልፉ እኛ ጨለማ ውስጥ ነበርን- የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች
ኢትዮጵያዊያን ወገኖች አዲስ ዓመትን ሲያሳልፉ እኛ በጨለማ ውስጥ ነበርን ሲሉ የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።
”የእኛ አዲስ ዓመታችንና ዳግም ውልደታችን ዛሬ ነው የሚሉት ነዋሪዎቹ፣ የሽብር ቡድኑ ለዓዕምሮ የሚከብድ ወንጀል ፈጽሟልም ” ብለዋል።
የአሸባሪ ቡድኑ ወራሪ ኃይሎች በከተማዋ ሴቶችን አስገድደው በመድፈር፤ ሰላማዊ ዜጎችን በጅምላ በመጨፍጨፍና ንብረት በማውደም ግፍ መፈጸማቸውንም ነው ነዋሪዎቹ የገለጹት፡፡
የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ወልዲያና ቆቦን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎችን ከአሸባሪው ሕወሓት ወረራ ነፃ ማውጣቱ ይታወቃል።
የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች አሸባሪ ቡድኑ ወደ ከተማዋ ከገባበት እለት ጀምሮ የሰቆቃ ጊዜ እንዳሳለፉ ነው የተናገሩት፡፡
የአሸባሪ ቡድኑ ወራሪ ኃይሎች “በርካታ ወጣቶችን በአደባባይ በግፍ ገድለዋል፤ ሴቶችን በቡድን ደፍረዋል፤ የግለሰቦችን ቤት በየቀኑ እየፈተሹ ሃብት ንብረት ዘርፈዋል” ነው ያሉት ነዋሪዎቹ፡፡
የወልዲያ ሆስፒታል እና ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የጤና ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶችና የፋይናንስ ተቋማት ሙሉ በሙሉ መዘረፋቸውንም ገልጸዋል።
የሽብር ቡድኑ መንገድ ላይ የሚለምኑ ሰዎችን ሳንቲም ጭምር በመውሰድ የነውረኝነቱን ጥግ አሳይቷል ብለዋል።
ታኅሣሥ 9/2014 (ዋልታ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.