የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባው ሶስት የውሳኔ ሃሳቦችን መርምሮ አፅድቋል

Parlama የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባው ሶስት የውሳኔ ሃሳቦችን መርምሮ አፅድቋል
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው ሶስት የውሳኔ ሃሳቦችን መርምሮ አጽድቋል፡፡
የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀት ተግባርና ኃላፊነት ለመወሰን የቀረበወን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ የውሳኔ ሃሳብ ቁጥር 3/2014 አድርጎ በ15 ድምጸ ታቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽቋል፡፡
በተመሳሳይ የቋሚ ኮሚቴዎች ዕጩ አመራርና አባላት ምደባ አስመለክቶ የቀረበወን የውሳኔ ሀሳብ ላይ በመወያየት የውሳኔ ቁጥር 4/20014 ሆኖ ፀድቋል።
በዚህ መሰረት፤
1. ዲማ ነገዎ( ዶ/ር) …………. የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
2. ወ/ሮ ዕጸገነት መንግስቱ……ሕግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
3. አቶ ሶሎሞን ላሌ…….የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
4. ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ…….የጤና፣ ማሕበራዊ ልማት፣ ባህልና ሰፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
5. ነገሪ ሌንጮ ( ዶ/ር) …………..የሰው ሃብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
6. ወ/ሮ ፈቲያ አሕመድ ………ውሃ ፣ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
7. አማረች ባካሎ (ዶ/ር)………የኢንዱስትሪና ማእድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
8. ወ/ሮ አሻ ያያ…………….የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
9. ወ/ሮ ሸዊት ሸንካ………..የከተማ ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
10. አቶ ደሳለኝ ወዳጆ……………የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
11. አቶ ክርስቲያን ታደለ………. የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነዋል።
በሌላ በኩል የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የውሳኔ ሀሳብ ቁጥር 2/2014 ሆኖ የፀደቀ ሲሆን የምክር ቤቱ አፈጉባኤ፣ ምክትል አፈ ጉባኤው፣ የፓርቲ ተጠሪዎችን ጨምሮ በአፈ ጉባኤው የሚመራ ኮሚቴ እንደሚደራጅ በተደነገገው መሰረት 11 አባላት ያሉት ነው ተብሏል።
አባላቱም ከተለያዩ ፓርቲዎችና ከግል ተወዳዳሪዎች የተካተቱበት መሆኑን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢህን ጠብቅ203c የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባው ሶስት የውሳኔ ሃሳቦችን መርምሮ አፅድቋል
ወደ ግንባር ዝመት203c የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባው ሶስት የውሳኔ ሃሳቦችን መርምሮ አፅድቋል
ሠራዊቱን ደግፍ203c የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባው ሶስት የውሳኔ ሃሳቦችን መርምሮ አፅድቋል
****************
(ኢ ፕ ድ)

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.