የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ መዋቅር እና አደረጃጀት መመሪያ

የአስቸኳይ ጊዜ 5 /2014 መመሪያ ቁጥር 1/2014

State of Emergency“የሃገርን ህልውና እና ሉዐላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል የወጣ አዋጅ ቁጥር 5/2014”፣ አንቀጽ 7 (1)

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅም፣ ለኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ተጠሪ የሆነ በኢፌድሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም የሚመራ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ያቋቋመ ሲሆን በዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ(2) አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምርያ ዕዙ መዋቅር እና አደረጃጀት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚወሰን እንደሆነ ተመላክቷል። በዚሁ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙ መዋቅር እና አደረጃጀት እንደሚከተለው እንዲሆን ተወስኖ ይህ መመሪያ ወጥቶዋል።

1) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙ መዋቅር እና አደረጃጀት

እነዚህ መሰረት በፌደራል እና በክልል ደረጃ የአዋጁን አፈፃፀም እንዲከታተሉ ከዚህ በታች የተመላከቱት ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል፤

 1. የፌደራል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የክትትል ኮሚቴ፤
 2. የፌደራል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የፀጥታ ኮሚቴ፤
 3. የክልል’ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ኮሚቴ፤

2) ተጠሪነት

ከዚህ በላይ የተመለከቱት ኮሚቴዎች ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው። ኮሚቴዎቹ የስራ አፈፃጸማቸውን አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በየጊዜው ሪፖርት ያቀርባሉ።

3) የኮሜቴዎቹ ሃላፊነት

በፌደራል እና በክልል ደረጃ የአዋጁን አፈፃፀም እንዲከታተሉ የተቁቋሙት ኮሜቴዎች ሃላፊነት እንደሚከተለው ይሆናል፤

ሀ) የፌደራል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የክትትል ኮሚቴ ሃላፊነት፤

 1. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ጋር በተገናኘ ያሉ የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲ እና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን ማስተባበር እና መከታተል፤
 2. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አላማ ለማሳካት የሚሰሩ የህዝብ አደረጃጀት እና እንቅስቃሴ ስራዎችን ማስተባበር እና መከታተል፤
 3. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ጋር በተገናኘ የሚኖሩ የህዝብ ቅሬታዎች ምላሽ እንዲያገኙ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ፤
 4. በሽብርተኛው ቡድን የተፈናቀሉ እና ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያገኙበትን መንገድ ማሳለጥ፤
ተጨማሪ ያንብቡ:  አየርመንገድ 216 ሰራተኞችን ከሥራ አባረረ!

ለ) የፌደራል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የፀጥታ ኮሚቴ ሃላፊነት፤

በዚህ መመሪያ የክልል አስቸኳይ ጊዜ ኮሚቴዎችን የተመለከቱት ድንጋጌዎች ለአዲስ አበባ እና ለድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደርም ያገለግላሉ።

1) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የቀን ተቀን አፈፃፀም በፌደራል ደረጃ መምራት፣ ማስተባበር እና መከታተል፤

2) በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገጉ ክልከላዎች እና ግዴታዎችን ተፈጻሚነት ማረጋገጥ፤

3) ሁሉንም ፀጥታ፣ የደህንነት እና የህግ አስከባሪ አካላት በተቀናጀ ሁኔታ እንዲንቀሳቀሱ ማስቻል፤

4) ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሳካት አስፈላጊ የሆኑ ኦፕሬሽኖችን በቅንጅት ማቀድ እና ተግባራዊ ማድረግ፤

ሐ) የክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ኮሚቴ ሃላፊነት

1) በዞን፣ በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅሙ ግብረሃይሎችን ማቋቋም፤

2) በክልል ደረጃ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ጋር በተገናኘ ያሉ የፖለቲካ እና የህዝብ ግንኙነንት ስራዎችን ማስተባበር እና መከታተል፤

3) በክልል ደረጃ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አላማ ለማሳካት የሚሰሩ የህዝብ አደረጃጀት እና እንቅስቃሴ ስራዎችን ማስተባበር እና መከታተል፤

4) በክልል ደረጃ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም ጋር በተገናኘ የሚኖሩ የህዝብ ቅሬታዎች ምላሽ እንዲያገኙ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ፤

5) በክልል ደረጃ በሽብርተኛው ቡድን የተፈናቀሉ እና ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያገኙበትን መንገድ ማሳለጥ፤

6) ከፌደራል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የፀጥታ ኮሚቴ ጋር በተናበበብ መንገድ በክልሉ የፀጥታ ማስክበር ስራዎችን መምራት፣ ማስተባበር እና መከታተል፤

4) የኮሚቴዎች ስብጥር

በፌደራል እና በክልል ደረጃ የአዋጁን አፈፃፀም እንዲከታተሉ የተቋቋሙት ኮሚቴዎች ስብጥር እንደሚከተለው ይሆናል፤

ሀ) የፌደራሌ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የክትትል ኮሚቴ

ተጨማሪ ያንብቡ:  የህወሃት ድራማ ተዋናኞች ሆይ! እጃችሁን ከወልቃይት ላይ አንሱ !

1) አቶ ደመቀ መኮንን (የኢፌዴሪ ም/ጠ/ሚኒስትር እና የው/ጉ/ሚኒስትር) —— ሰብሳቢ

2) ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ —————–አባል

3) አቶ በለጠ ሞላ ———————— አባል

4) አቶ ቀጀላ መርዳሳ ———————አባል

5) ኢንጂነር አይሻ መሐመድ————–.አባል

6) ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ——————-አባል

7) ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ———————–አባል

8 አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን —————.አባል

9) አቶ ምትኩ ካሳ ————————-.አባል

ለ) የፌደራል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የፀጥታ ኮሚቴ

1) ጄ/ል ብርሃኑ ጁላ (የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም)—ሰብሳቢ

2) የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል. –አባል

3) የፌደራሌ ፖሉስ ኮሚሽነር ————————— አባል

4) የፍትህ ሚኒስትር—————————————–.አባል

5) የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት———————-አባል

ሐ) የክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ኮሚቴ

1) የክልልርዕሰ መስተዳደር—————————–.ሰብሳቢ

2) የክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር——————.ም/ሰብሳቢ

3) የክልል የፀጥታ እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ————-አባል

4) የክልል ፖሊስ ኮሚሽነር—————————-አባል

5) የክልል ፍትህ ቢሮ/ጠቅላይ አቃቤ ህግ —————አባል

አዲስ አበባ 24/2/2014

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ

1 Comment

 1. አስቸኳይ!!
  ደሴና ሌሎች አካባቢ እንደተፈጸመው በአዲስ አበባ እና ሌሎች አካባቢም ሌሎች አከባቢም ጥፋ ለመፈፀም በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ስለሆኑ መንግስት ከህዝቡ ጋር በመሆን ቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ የተደበቀና የታጠቁትን የመሳሪያ እና ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ሙሉ ለሙሉ ማስፈታት እና ጊዜ ሳይሰጥ እንዲያስረክቡ ማድረግ ያፈልጋል፡፡ በአስቸኳይ በየከተማው ያሉ የትህነግ እና ኦነግ ሸኔ ደጋፊዎች ተለይተው እየተመዘገቡ ያላቸውን መሳሪያ እና ድምጽ አልባ መሳሪያ ማስመዝገብ ብቻ ሳይሆን እንዲያረክቡ መደረግ አለበት፡፡ መንግስት ጠንከራ የደህንነት ስራ በመስራት ቀን ሳይሰጠው ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በሁለት ቀናት ውስጥ ከባድ ስራ መሰራ አለበት፡፡ አዲስ አባባ ከተማ ውስጥ ያሉ የትህነግ ደጋፊዎች በየመስራቤቱ ጨምሮ አጨብጭበን አዲስ አበባ ላይ ትህነግ እና ሸኔን እንቀባላለን ሲሉ የነበሩ ደጋፊዎች አሁን አልሆን ሲላቸው ለከፍተኘ ጥፋት እየተዘጋጁ ስለሆነ የነዚህ እንቀስቃሴን መንግስት በአስቸኳይ በመከታተል የደበቁትን መሳሪያ እና ገጀራ እንዲያስረክቡ ማድረግ አለበት፡፡ ህዝቡም በየአካባቢው ያሉትን በመለየት ማጋለጥ አለበት እዛው በጉያው አስቀምጦ አድፍጠው ስለተቀመጡ ሙሉ ክትትል ሊደረግባቸው ይገባል፡፡ ይልቅስ እነዚህ ጥፋት የጠማቸው አብረው ሲበሉት ከነበረ ህዝብ ጋር እስከአሁን ላጣፋት እና ህዝብ ላይ ላቀረቡት በደል ይቅር በለው በሳለም ለመኖር ቢጥሩ የተሻለ ነው፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡ ህዝብ ንቃ አፋር ላይ እንደተደረገው ቤት ለቤት አሰሳ መደረግ አለበት፡፡
  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.