ምንም ብታደርጉ ሰዎች ከማውራት አይመለሱም

ደሀ ብትሆን የመናጢ ልጅ ፤
ሀብታም ብትሆን ዶላር
ያሳበጠው ይሉሀል።
ከሴት ጋር ብትሄድ ሴሰኛ ፤
ብቻህን ብትሆን ወፈፌ ይሉሀል
☞ ብትፈጥን ቀዥቃዣ ፥ ብትዘገይ ዘገምተኛ ።
☞ ብታወራ ለፍላፊ ፥ ዝምብትል ዝጋታም ።
☞ ብትራመድ አርፎ አይቀመጥም ፥ አርፈህ ብትቀመጥ ዝፍዝፍ
☞ ብትማር አወቅሁ ባይ ፥ ባትማር የአቡጊዳ ሽፍታ ።
☞ ብትወፍር ጠብደል ፥ ብትከሳ በልቶ ማይጠረቃ ።
☞ ብትይዝ ቋጣሪ ፥ ብትለቅ መንዛሪ ። …
እንደውም አንድ የሀገራችን ተረት አለ”ባልና ሚስት አህያ እየነዱ
ሲሄዱ ተቺዎች አገኙዋቸውና ፦”እንከፎች አህያዋ ሳለች እንዴት
አይሳፈሩባትም” ሲሉ ባል ሰማና ሚስቱን ” በይ ፍጠኚና
አህያዋ ላይ ተሳፈሪ” – አላት።
ትንሽ እንደሄዱ ሌሎች ተቺዎች ፦ “ይች ባለጌ ፥ ባል በእግር
እየሄደ ሚስት በጋማ ከብት” ብለው ወረፏቸው።ባል ሚስቱን
አስወርዶ አህያዋ ወገብ ላይ ቂብ አለ ፤ትንሽ እንደተጋዙ ሌሎች
ተቺዎች አገኝዋቸው ፦ “የተረገመ ሚስቱን በእግር እያስኬደ
እሱ በአህያዋ ብለው ወረዱባቸው ።
ባልና ሚስት ድንገት ቢተዉን ብለው አህያዋ ላይ ሲፈናጠጡ
ሌሎች ተቺዎች ደም አገኙዋቸውና “ምን እንስሳ ብትሆን
ለሁለት ይከመሩባታል ግፈኞች …” የስድብ ናዳ ለቀቁባቸው ።
እንግዲህ ወዳጆቼ ፦ አህያዋን ቢሸከሙ ኖሮ ከዚህ
አይብስምን ?
ስለዚህ ሰዎች ያሉትን ይበሉ አንተ አንተነትህን ሁንና ህሊናህ
አውጥቶና አውርዶ ከተቀበለው ሀሳብ ጋር ተስማማ በመንገድህ ማመንክበት ቀጥል።
ለጮኸ ውሻ ሁላ ድንጋይ መወርወር ጊዜን ማባከን ነው፡፡
Adu
ተጨማሪ ያንብቡ:  ቴዲ አፍሮ በኢህአዴግ ለምን ይጠላል? ወይም እንደ ትልቅ አደጋ ይታያል?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share