አሸባሪው ህወሓት በሶስት አቅጣጫ ያሰለፈው ቡድን ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል፡- ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ

bacha debele
bacha debele

በጀነራል ምግበይ የሚመራው አርሚ አንድ ተብሎ የሚጠራው ሃይል ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን የመከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ ገልጸዋል፡፡

ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ የሰራዊቱን ግዳጅ አፈጻጸም እና ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ጁንታው ኢትዮጵያን ለመበታተን በመፈለግ የትግራይ ህፃናትን በማሰለፍ በአማራ ክልል ወረራ ፈፅሟል፤ ስልጠና ያልወሰዱ ህፃናትን ወደ ጦርነት በመማገድ ላይም ይገኛል ነው ያሉት።
በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶችን በማሰለፍ በ4 አርሚ ራሱን በማደራጀት በአማራ ክልል የሚያደርገውን ወረራ ቀጥሎበት ይገኛል።
ከነዚህ አካባቢዎች በ4 አርሚዎች ካደራጃቸው በከሃዲው ጀነራል ምግበ የሚመራ አርሚ 1 ተብሎ የሚጠራ በሁመራ አካባቢ አደርቃይ እና ማይ ፀብሪ አካባቢ ደባርቅንና ዳባትን በመቁረጥ ጎንደርን በመያዝ ከዚያ በኋላ ሁመራን ነፃ በማድረግ ከውጭ በጋለቧቸው ጌቶቻቸው የሚሰጧቸውን እርዳታ ማስገቢያ ቀዳዳ ሲፈልገ የነበረው ጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል ብለዋል።
አርሚ 1 የተባለው ይዟቸው የነበረው ከፍለ ጦሮች 1ኛ በስሩ 3 ኮሮች ያሉት ኮር 1 የሚባለው በከሃዲው ኮሎኔል ጉእሽ ገብረ የሚመራ 3 ክፍለ ጦሮች አሉት።
2ኛው ኮር 2 የሚባለው በከሃዲው ኮሎኔል ብርጋዴር ጀነራል ዘነበ የሚመራ 3 ክፍለ ጦሮች አሉት።
ኮር 3 የሚባለው በብርጋዴር ጄኔራል ወርቅ አይኑ የሚመራ 3 ክፍለ ጦሮች አሉት ያሉት ጀነራል ባጫ በአጠቃላይ 9 ክፍለ ጦሮች ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸውን ነው የገለፁት።
በመሆኑም አሸባሪው ህወሓት ወደሱዳን ለመውጣት ያቀደው ሙከራ ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡
አርሚ ሁለት የሚባለው እና በከሃዲው ሜ/ጀነራል ዮሐንስ ወ/ጊዮርጊስ የሚመራው ሃይል በጋሸና ከክምር ድንጋይ ጀምሮ በተደረገ ውጊያ ሁለቱ ክፍለጦሮች ተደምስሰውበታል፡፡
አርሚ ሦስት የሚባለው ደግሞ ከውጭ በብ/ጀነራል ፍስሃ የሚመራ እና የሰለጠነ በሽንፋ በኩል ከቅማንት ቅጥረኛ ቡድን ጋር በመተባባር ጥቃት ቢሰነዝርም ተደምስሷል የተረፈውም ወደመጣበት ተመልሷል ብለዋል፡፡
ይህ ሃይል በተለይ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ስራ ለማስተጓጎል ቢያስብም እቅዱ በጀግናው ሃይላችን ተደምስሷል ብለዋል፡፡
አሸባሪ ቡድኑ እየደረሰበት ያለው ኪሳራ በጣም ብዙ ነው ያሉት ጀነራል ባጫ በተለይ የትግራይ ወጣቶችን እያስጨረሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
EBC
ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: አዲግራት | ወልዲያ | ጎንደር | ኃይለማርያም | ጀነራል ጻድቃን | መንግስቱ ኃይለማርያም | ኦህዴድ እና ሌሎችም

4 Comments

 1. Alas! Don’t you guys feel some sense of shame when you declare as if you gained and you are gaining something new? Are you telling the people that you are accomplishing extraordinary victory because you are trying hard what you miserably lost when you abandon and left Tigray and let your former mentor, TPLF easily march to not only beyond the bordering areas of Amhara Reginal Administration but all the way down to Debere Tabor and has caused causing horrible destruction and lose of human lives? Does this make any sense of true victory of winning the war, not winning the battle (the fighting) here and there? WHO enabled the TPLF thugs to come back after you declared its total demise many months ago? Was it not and is it not because of a very embarrassing, disgraceful, and of course dangerous sabotages and hypocrisies that enabled TPLF to do what it wanted to do? Why you guys try to make your own very wicked or evil-driven game you are playing and help the people end the very miserable way of life they have gone through and keep going with no reliable means to end?

 2. ከጫት ምርቃና በኋላ የሚለፈልፈውን እውነት ብሎ መቀበል የዋህነት ነው! ከጥቂት ወራት “በፊት ዱቄት አድርገን በትነናቸዋል” ሲለን አልነበር? ባጫ የሚዋጋው ዱቄት ሃሺሹን ይሆን??

 3. ምንም ይሁን ምንም እንኳን ደስ አላችሁ የሚያሰኝ ነገር በዚህም በዚያም የለም። ወያኔ በስልጣን ጥማት ሰክሮ የትግራይን ልጆች እያታለለ በመማገድ በጦር ሜዳው ላይ የአራዊት ባህሪ እያሳዪ በዚህም በዚያም መግደልና መገደል ቆም ብሎ ላሰበ ለእልልታ አያበቃም። ሟች እኮ የትግራይ ወራሪ ሃይል ብቻ አይደለም። ሞታችን በጋራ ነው። ምንም የማያውቁ እድሜ ጠገብ ገበሬዎችን አስለፎ የሚረሽን የወያኔ አውሬ በሰፈረው መስፈሪያ ተትረፍርፎ በራሱ መከፈሉ ራሱ ያመጣው መከራ እንጂ ማንም ኢትዮጵያዊ የትግራይ ልጆችን ለመግደል ቅድመ ዝግጅት አላረገም። ያማ ቢሆን ኑሮ አፋርና አማራ አሁን የደረሰባቸው ጥቃት ባልሆነም ነበር። ሃገር አለን፤ መንግስት አለን፤ ህግ አለ ብለው በተቀመጡበት ምድር ነው ይህ ወራሪ ሃይል ታይቶ በማይታወቅ የሰው ጭካኔ ሰውን፤ ንብረትን እያወደሙ ዘረፋ ውስጥ የገቡት። በጦር ሜዳም ረገፉ፤ ገደል ገብተውም ሞቱ ሞት ያው ነው። እብድ አሳብዶ ይሞታል እንዲሉ ነው። ወያኔ እያለ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም አይኖረውም።
  በሃሳብ የዘገዪና ከወያኔ ፍርፋሬ ተቃማሽ የነበሩና ያሉ የሙታን ፓለቲከኞች ወያኔ ድንገተኛ ጦርነት በሰሜን እዝ ላይ እንደከፈተ አድርገው ሊረድ ይችላሉ። ጉዳዪ እንዲህ ነው። ወያኔ ይህን ጥቃት የከፈተው ከ 30 ዓመት ዝግጅት በህዋላ ነው። ሁሉም ነገር ወደ ትግራይ ተብሎ መቀሌ የመኪና ማምረቻ ይመስል (ለነገሩ ነበራቸው መሰል በቀን 5 አነስተኛ መኪያ የሚያምረት) የመቀሌንና የዙሪያዋን ከተሞች አጨናንቀው የነበሩት የከባድና የቀላል ጭነት መኪኖች ለጦርነቱ ዝግጅት ዋንኛ ማሳያዎች ናቸው። ለሰራዊቱ እየተባለ ከሚገባው ነዳጅ መሬት ቆፍረው በቦቴ ከደበቁት የተያዘው አንድ አካባቢ ተደብቆ የነበረው ብቻ ነው። ከጦሩ እየተሰረቁ የተደበቁ ከባድ መሳሪያዎች፤ የአየር መቃወሚያዎች፤ ስናይፕር መሳሪያዎች፤ ተተኳሽ ጥይቶችና ሌሎች ተቀጣጣይ አጥፊ ጥይቶች ሁሉ ሆን ተብሎ ከሰራዊቱ በሴራ እየተዘረፉ የተደበቁና አሁን ወያኔ አለኝ ለሚለው ሰራዊቱ ያስታጠቃቸው ናቸው።
  ከማህል ሃገር የገጠርና የከተማ የቆዬ የጦር ማከማቻ ካዝና ሁሉ ያለው የጦር መሳሪያ ተግዞ መቀሌ ለመግባቱ ተጨባጭ መረጃ አለ። ወያኔ በሌብነት ማንም አይስተካከለውም። ይህ ድርጅት እኮ ህጋዊ የሆነውን የኢትዮጵያ ብር በመቀሌ ሲያትምና ሲያባዛ የተያዘ ድርጅት ነው። በቅርቡ አንድ ከወያኔ ጋር አብሮ የተሰለፈ የቅማንት ተዋጊ ተይዞ ኪሱ ሲፈተሽ የተገኘው ገንዘብ ይህ ወያኔ በመቀሌ እያተመ ሰውን የሚያታልልበት የውሸት በር ሆኖ ይገኛል። ተያዡ በሃዘን እንዳለው ” ስንቱን ሰው በዚህ በውሸት ብር አሞኝተውት ይሆን”። መገመት ይከብዳል።
  ስለሆነም ጦርነቱ ሳይጠናቀቅ፤ በአፋርና በአማራ ከተሞች ወያኔ አሁንም እየዘረፈና እየገደለ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እየሳቃችሁ አልቅሱ ማለት ነው። መቼ የወያኔ ግባተ መሬት ሆነና። ትላንትስ ደመሰስናቸው፤ ቀበርናቸው፤ ገደል ገቡ፤ የራሳቸው መሪዎች ሞት እንዳይታወቅ አንገት ቆረጡ አልፎ ተርፎም ጠ/ሚሩ “በንፋስ የተወሰድ ድቄቶች ናቸው” አልተባልንም ነበር እንዴ? እንዴት ነው ታዲያ አፋርና ደብረታቦር ድረስ ሊገቡ የቻሉት? የኢትዮጵያ ወታደሮችና መሪዎች ዝምታን መርጠው በጦር ሜዳ ላይ የተገኘውን ድልም ሆነ ሽንፈት በመረጃ በመያዝ ወያኔ እጅ ወደ ላይ አንስቶ እስኪታሰር ወይም እስከ መጨረሻው እየተዋጋ ተዋግቶ እስኪያንቀላፋ መፋለሙ ብልህነት ይመስለኛል። ገበሬው ማረሻ በሬ እንዳያጣ እባካችሁ ከስጋ ጋር ያላችሁ ፍቅር ጭራሽ ይቅር ወይም ይቀነስ። ጦርነቱን እኮ የሰርግና ምላሽ አይነት አረጋችሁት። ምን አይነት ሰራዊት ነው ጮማ እየቆረጠ የሚዋጋ። የማይመች መንገድ። ድርቆሽና ቆሎው ይሻላል። የምናውቀውም እሱን ነው።
  ባጭሩ የቅንጫቤ የድል ወሬ ለሰራዊቱም ለህዝባችንም አይጠቅምም። ሁሉ ነገር ሲያከትም ያኔ ማቅራራት ይሻላል። አሁን ወቅቱ የፊልሚያ ነው። የትግራይ እናቶችና አባቶች የልጆቻቸው እንደ ቅጠል መርገፍን ሲረድ ከወያኔ ጋር አንገት ላንገት ተናንቀው የወያኔን ሃይሎች ለመጨረሻ ጊዜ መቃብር እንደሚያወርድአቸው አልጠራጠርም። ለአሁኑ የትግራይ ህዝብ ልክ እንደ ማህል ሃገሩ የሚነገረው ወሬና የሚዘመርለት የድል መዝሙር የተጋነነና ያለጊዜው ነው። ግን እውነት ሁለቱንም ቁልጭ አርጋ የምታሳይበት ጊዜው ቅርብ ነው። ያኔ የውሸት ቱልቱላዎች ምን ይውጣቸው ይሆን? በተደጋጋሚ እንዳልኩት ወያኔ መጠራቅቅ ውስጥ ራሱን ከቷል። ይደርሱልኛል ያላቸው ሱዳንና ግብጾችን ቲፎዞ ሆነው ቀርተዋል። የአሜሪካ ድጋፍም በአፍጋኒስታንና በሌሎች ቤት በቀል ችግሮች ተወጥሮ ተይዟል። አይ ወያኔ የጭቃ ቤት ጎጆ አቃጥሎ የሚፎክር የጨካኞች ክምችት። በእኔ እይታ መርጦና ወዶ በተለይም በዘር ፓለቲካ ሰክሮ ጦር ሜዳ የገባ ሰው እልፍ ቢሞት ግድ አይሰጠኝም። ግን ገደልን እንጂ ሞተብን የማይባልበት ወሬ ያቅለሸልሸኛል። የጄኔራሉ እና የሌሎችም የፓለቲካ ጥሩንባ ከጦርነቱ ፍጻሜ በህዋላ ቢሆን ተመልካችና አድማጭ እውነቱን ለመገንዘብ ይችል ነበር። ያ ግን ገና ጊዜ ይፈጃል። ወያኔ በቀላሉ አይሞትም። ምህረትን ለማይሻ ርህራሄ ማሳየት የራስን አንገት ለማስቆረጥ ቢለዋ ለጠላት እንደማቀበል ይቆጠራል። የአማራም ሆነ የአፋር ህዝብ ራሱን ከሞት ለመከላከል እየገደለ መሞት አለበት። ሌላ ምርጫ የለም። በቃኝ!

 4. If Nigerian ex-president Osabangoe plan and receive order from western ciuntries, US & allies to mediate and make
  reconcilation Ethiopian govt with such terrorist & rebe
  lion group it is totally a mess. You ex-president before duly determined that TPLF is a terriorist group, why now you confused abd under the direction of UN & western offucials. This is another form of colonization, you are joking
  on efforts made to fight colonization before decays. We African shall not be played just like Robots manipulated
  by them. If you elder in age at this time urge Ethiopian givt t
  o make negotiation with this tettorist group you are against interest of people and it is a shame for you, even your plan to make a meditation is totally wrong as any rational human being do not do.
  Where were you been the so called mess have been made by crimibal TPLF??? Are you taking a stake from junta, TPLF
  and so called western countries??? Instead you have to withdraw your self now, take care.
  Victory to Ethiopian Heros
  Long live to Ethiopia!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.