በእነ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የክስ መዝገብ ፍርድ ቤት የቀረቡ 21 ተከሳሾች የጠየቁት የዋስትና መብት ውድቅ ተደረገ

debre1
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት በእነ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የክስ መዝገብ ፍርድ ቤት የቀረቡ 21 ተከሳሾች የጠየቁትን የዋስትና መብት ውድቅ አደረገ፡፡
ችሎቱ በእነ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል የክስ መዝገብ ለዛሬ ይዞት በነበረው ቀጠሮ ላይ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡
በደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል የክስ መዝገብ 58 ግለሰቦች እና አራት ድርጅቶች በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው ይታወሳል፡፡ከእነዚህ መካከል ነሐሴ 11 ቀን 2013 ዓ.ም በነበረው ችሎት ከተከሳሾቹ 21ዱ በአካል ቀርበው ክስ የተነበበላቸው ሲሆን የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸውም አመልክተዋል፡፡
በተከሾቹ ላይ የተመሰረተባቸው ክስ ዋስትና የሚያስከለክል በመሆኑ ዐቃቤ ሕግ የተለያዩ ዝርዝር ሀሳቦችን በማንሳት መከራከሩም መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ችሎቱ በሁለቱ ወገኖች ክርክር ላይ ለዛሬ ትዕዛዝ ለመስጠት በያዘው ቀጠሮ መሰረት ተከሳሾች ችሎት መምጣት ሳይጠበቅባቸው በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሆነው ትዕዛዙን እንዲጠብቁ በማለት ነበር ችሎቱ ለዛሬ የቀጠረው፡፡
ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገኖች የዋስትና ጥያቄ ክርክር መርምሮ ዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል፡፡
የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በማረሚያ ቤት በኩል ለተከሳሾች እንዲደርሳቸው ሲል ችሎቱ አዟል፡፡
በችሎቱ በአካል ያልተገኙት እነ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፣ ጌታቸው ረዳ፣ ሊያ ካሳ እና ሌሎች ተከሳሾች እንዲሁም የአራቱ ድርጅቶች ተወካዮች የፌዴራል ፖሊስ ባሉበት ይዞ እንዲያቀርብ እና ውጤቱንም ለመጠባበቅ ለጥቅምት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ይታወሳል፡፡
በጥላሁን ካሣ
EBC
ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰበር ዜና – በምዕ. ወለጋ በቤተ ክርስቲያን ላይ በሚፈጸመው ግፍ ፓትርያርኩ መንግሥትን አሳሰቡ

3 Comments

  1. አገር የሚድነው እንደ እስክንድር ያሉትን ሰላማዊ ሰዎችን አስሮ ጁንታ ብሎ በመጮህ አይደለም። አብይ ከራሱ ስልጣን በላይ ለአገር እያሰበ አይደለም

  2. ቲ አውላቸው፣ ገና እስክንድር ላይ ነህ? እስክንድርማ እንደ ጽንፈኛ አክራሪ ጓዱ ጀዋር እጅ ከፍንጅ ተይዞ ታሠረ! አሁንም ገና አብን ላይ ነህ? አብን በገዛ ክልሉ በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ተሸነፈ እኮ! አልሰማህም? ስለ አገር መቸ ይሆን የሚቆጭህ?

  3. No more allegation. Do soon to evacuate this and sue mass murders soon though international communities are always and at any time doing at there favor

    .

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share