“ጠላትን  መሸኘት ወይስ እንደወጣ ማስቀረት ? ” –  ማላጂ

የዘመናት የጥፋት ስምምነት የተመሰረተዉ  በጥላቻ የተወለደ የዝቅተኝነት ስሜት ዛሬ የሚነገር አይደለም ፡፡

ይህ የአንድ ክ/ዘመን ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያንን የማክሰም ሴራ እና መዳረሻ የምናወራበት ጊዜ ላይ  አይደለም የተባለ እና የተነገረ ታሪክ ነዉ ፡፡

ይህ በታሪክ እና በጊዜ የተገለፀ እና የታወቀ  የአደባባይ  ጥላቻ እና የጥፋት ዘመቻ  ላይ መደጋገም  “ለደንቆሮ  እንደ ማጨብጨብ ” ይቆጠራል  ፡፡

ዛሬ የኢትዮጵያን ህዝብ እና ንብረት ማዉደም እና ማጥፋት  በቀደሙት ዓመታት ታሪክ በማዛባት እና በማምታት ኢትዮጵያን ከምድረ ገፅ በማጥፋት እና ጥላቻቸዉን ለማስፋፋት አሁን ላይ የሚደረገዉ አጥፍቶ የማጥፋት እና የመስፋፋት ዕኩይነት በማን አለብኝነት ቀጥሏል፡፡

ብዙኃኑን የኢትዮጵያ  ህዝብ  በዘመን የክፋት  እና የመከራ ዘለመን የበደል ክምር የሚያሸክሙት  በኢትዮጵያ የዘመናት የዉስጥ  እና  ዉጭ ፣ የቅርብ እና ሩቅ ጠላት ጉዳይ አስፈጻሚነት በመሆን ሌት ተቀን ለሚኳትን ጠላት ጊዜ መስጠት እና ተራ ተባ ማለት በየትኛዉም ወገን ለአገር እና ለህዝብ የሚኖረዉን መጻዒ ጊዜ አስቀድሞ መገመት ያስፈልጋል ፡፡

በዚህ ወሳኝ ዘመን ስለ ጠላት ወዳጂ እና ጠላት የሚነገርበት ጊዜ እና ለዚህ ሊደረግ የሚደረገዉ ቅድመ ዝግጅት እና አደረጃጀት ከ1960.ዓ.ም. ጀምሮ  የብሄር ብሄረሰብ አጋጭ የጠላት መዉጊያ እና መለያያ  መርዝ በተቀመመበት ወቅት ነዉ ፡፡

ዛሬ አጥፍቶ ጠፊዉ እና ተስፋፊዉ  የሚያደርገዉን  የዘር ፍጅት፣ ማሳደድ፣ ስርቆት  እና ክህደት  ላለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት ያደረሰዉን እና እያደረሰ ያለዉን ዘመን አይሽሬ ጥፋት እና ክህደት ያላወገዘ፣ ያልጠየቀ፣ ያላሳወቀ ወይም ያልጠየቀ  ሁሉ የጠላት አጋር ወይም በአገር እና በህዝብ ላይ ለሚደርሰዉ ጥፋት ዕዉቅና አለመስጠት  ከታሪካዊ ጠላትነት የማይነጠል ስለሚሆን በጥብቅ ሊስተዋል ይገባል፡፡

ስለዚህ አገርን ከፍርሰት ለማዳን እና ትዉልድን ከሞት በመታደግ ለሚደረገዉ ህዝባዊ ተጋድሎ ስለጠላት ብቻ ሳይሆን ስለ  ጠላት  ወይም የወዳጅ ጠላት “መሀል ሠፋሪ  ” በልዩነት እና በአፅኖት  በማየት ልብ ሊባል ይገባል፡፡

ኢትዮጵያን ለማዳን ዓማራን ማዳን መሆኑን የሚጎራብጣቸዉ የኢትዮጵያዉነት ማንነት  የሚከነክናቸዉ እና የሚያቅለሸልሻዉ መኖራቸዉን ሊሰመርበት ይገባል፡፡

ሠዉ ሆይ  የጨዉ ክምር ሲናድ ሞኝ ይስቃል ፤ ብልህ ያስቃል  እንዲሉ  እንዲሁም ክርስቶስ ለስጋዉ አደላ አንዲል ታላቁ መፅሀፍ   የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያንን በተለይ ዓማራን ለዘመናት ማሳደድ እና መግደል ምቾት የሰጠዉ ወይም ያልጎራበጠዉ ኢትዮጵያን ለማዳን ለሚደረገዉ ጥረት መጠበቅ ከጭንጫ እና በረሀ  ቦታ አበባ እንደመሻት ነዉ ፡፡

ዕዉነት ለህዝብ እና ለአገር ህልዉና ለሚያሳስበዉ ሁሉ ለሚደረገዉ ህዝባዊ እና ብሄራዊ ትንቅንቅ በመንንም ዓይነት የግለሰብ እና የቡድን ቀቢፀ ተስፋ እና ከንቱ ዉዳሴ ከትግል እና ድል በኋላ በይደር ማቆየት ይጠበቃል ፡፡

ጠላትን እንደከዚህ ቀደም በመጣበት መመለስ ሳይሆን በመጣበት ማስቀረት ዉጭ የሚደረግ ትግል ጊዜያዊ ድል ከመሆን ዉጭ የኢትዮጵያን እና ህዝቧን የሞት እና የመከራ ጊዜ ማራዘም  የነጻነት እና የህልዉና ዋጋዉን መናር ይሆናል ፡፡

ስለዚህ እንደመጣ በመጣበት መሸኘት ሳይሆን በመጣበት ማስቀረት የህልዉና እና ብሄራዊ ትግል ወቅታዊ መርህ መሆን አለበት ፡፡

ወደቀ ሲባል ተሰመረ ለሚሉት ከዋና ጠላት የማይለይ በመሆኑ ጊዜ የማይሰጠዉ ብሄራዊ ትግል መሆን አለበት፡፡

ጠላትማ ምንጊዜም ጠላት ነዉ ከጥንት አስከ ዛሬ ፣

እኛን የበደለን የወዳጅ ጠላት አሶክሷኪዉ ሆኖ ተቸገርን አገሬ ፡፡

 

                                                                                                      ማላጂ

“ ድል ለኢትዮጵያ ፤ሞት ለአጥፊ እና ተስፋፊ  

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.