አማራ የተሰጠውን ዕድል እንደማያበላሽ ተስፋ አደርጋለሁ!! – አምባቸው ዓለሙ (ከደሴ)

(13.12.13) ዕድሜ ለአማራ ጠላቶች አማራ በደሙና በአጥንቱ እንዲሁም ለዘመናት ላቡን አንጠፍጥፎ ባፈራው ጥሪቱ መሠረታዊ ትምህርት እየቀሰመ ነው፡፡ ሰይጣን ይሁን እግዚአብሔር ማንኛቸው እንደሆኑ ባላውቅም የሚከተሉትን ዐረመኔ መምህራን ልከውለት አማራ  በጥሩ ሁኔታ ኮርሱን እየተከታተለ ነው፤ ስለሆነም ከዚህ ውድ ዋጋ ከፍሎ ከተማረበት የልዩ ዲግሪ ምርቃት በኋላ አማራ እንኳን ለራሱ ለአፍሪካም የሚበቃ ዕውቀትና ጥበብ እንደሚሸምትና ከአሁን በኋላ አንድም ቀጣፊና አጭበርባሪ እንደማያታልለው በበኩሌ እተማመናለሁ፡፡ በዚህ ትምህርት ራሱን ያውቃል፤ ምን እንደተደረገበትና ምን እየተደረገበት እንደሆነም ምሥጢሩን ይረዳል፡፡ አንድነቱን አስጠብቆ መብትና ግዴታውንም አውቆ ኅልውናውን ያስጠብቃል፡፡ ከሌሎችም ይማራል፡፡ መምህራኑ ጎበዞች ናቸው፡፡ ደከመኝ ታከተኝን በጭራሽ አያውቁም፡፡ በተለይ ባለፉት ዐርባና ሃምሣ ዓመታት ትምህርቱን ከንድፈ ሃሳብ ደረጃ አውጥተው ወደተግባር ካዞሩት ወዲህ አማራ አቅሉን እስኪስት ድረስ በተሞክሮ ሠርቶ የማሳያ የርቀትም ሆነ የመደበኛ ትምህርት እሣሩን እያሳዩት ይገኛሉ፡፡ ከሣህል በረሃ እስከ ዐርባ ጉጉ፣ ከአሰቦት ገዳም እስከመተከል፣ ከሆሮ ጉደሩ እስከ ንፋስ መውጫ …. የፈሰሰው የአማራ ደምና የወደመው ንብረት ለምለው ነገር ቋሚ ምሥክሮች ናቸው፡፡

መምህር አንድ – ብአዴን፡፡ ይህ ከላስቲክና ከጥቂት ጅማቶች የተሠራ ድርጅት አማራን በልቶ አይጠግብም፡፡ ሥራው ለላኪዎቹ ተንበርክኮ አማራን ማስፈጀትና የአማራ የሆነን ሀብትና ንብረት እያዘረፈ ወይም እንዲቃጠል ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ ማራቆት እንደመሆኑ እሱን አይንኩት እንጂ ዐርባና ሃምሣ ሚሊዮን አማራ በአንድ አዳር ተቀቅሎ ቢገነተር ጉዳዩ አይደለም፡፡ የዚህ ድርጅት አባላት አብዛኞቹ የዘር ሐረጋቸው ሲፈተሸና ቢፈተሸ ከትግሬና ከኦሮሞ አያልፉም፡፡ ስለሆነም “ዘር ከልጓም ይስባል” እንዲሉ ነውና እነዚህ ሆዳሞች ለተወለዱበትና ላደጉበት አካባቢ ሳይሆን በሆዳቸውና በዘራቸው ለቆረቡበት የማያውቁት አካባቢ ተሸጠው አማራን ባወጣ እየቸበቸቡት ይገኛሉ፡፡ ከበረከት ስምዖን እስከ አገኘሁ ተሻገር ያሉት የወያኔ አጋሰሶች አሁንም ድረስ አማራ ላይ እንደልባቸው እየተጸዳዱበት ናቸው፡፡ ይህን ዕኩይ ተግባራቸውን ለመሸፈን ማታ ማታ አረቂ ቤት እየመሸጉ በስካር እንደሚወላገዱ ይነገራል – ከዋናቸው ጀምሮ፡፡ አንድም ሰው የሌለበት ይህ የወያኔና የኦነግ አሽከር ድርጅት በቅርቡ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ እንደሚፈጸም ውስጥ ዐዋቂዎች ሲያንሾካሽኩ የሰማሁ መሰለኝ፡፡ ባደረገው!!

መምህር ሁለት፡፡ ሕወሓትና የትግራይ አብዛኛው ሕዝብ በአጠቃላይ፡፡ ማንም የሚያውቀውን የአደባባይ እውነት በመናገር ጊዜ አላባክንም፡፡

መምህር ሦስት፡፡ ኦሮሙማ፡፡ በአቢይና በሽመልስ አብዲሣ የሚመራው ኦሮሙማ ቡድን አማራን ከምድረ ገጽ ካላጠፋ በሀሰት ትርክት ጭንቅላቱ ውስጥ ለዘመናት የተሰነቀረው ቁጭቱና ንዴቱ የሚበርድለት አይመስልም፡፡ ይህንን ሕዝብ ገሃድ መግረፍ ከጀመረ ሦስት ዓመት አለፈው፡፡ ለብዙዎች የሚመስለው አቢይ በጦርነት ብቻ አማራን እያጠፋ እንደሆነ ነው፡፡ ግን አይደለም፡፡ አቢይ አማራን እያጠፋ ያለው በተለያዩ ዐውደ ውጊያዎች ከፌዴራሉም፣ ከክልሉም፣ ከሌሎች ክልሎችም ነው፡፡  አማራ የሆነ ሰው በአሁኑ ወቅት በየትም ሥፍራ መኖር አይፈቀድለትም፡፡ ሌላውን እንተወውና “አቢይ ከየት አባቱ ያገኘኛል” ብሎ ደብረ ታቦርና ወልዲያ ተገልሎ ይኖር የነበረ ዜጋ አሁን ያለበትን ሁኔታ ስትሰሙ በርግጥም አማራ ካልሞተ በሰላም መኖር እንደማይችልና እርሱን ካልገደሉም የኅሊና ዕረፍት የሌላቸው ወገኖች  በብዛት መኖራቸውን ትረዳላችሁ፡፡ ስለሆነም አማራ ከየመሥሪያ ቤቱ እየተባረረ በምትኩ ከየት መጡ የማይባሉ የኦሮሞ ነገድ አባላት ካላንዳች ሀፍረት በገልጽ እየተመደቡበት ነው፡፡ ወያኔን የሚያስመሰግን የዘረኝነት ሥርዓት እየተዘረጋ ነው፡፡ አቢይ ሰዎችን የሚያፈዝና የሚያደነግዝበት አንዳች መተት እንዳለው ስንናገር ማንም አላመነንም፡፡ እነዳንኤል ክብረት አሁን ምን እንደሚሉ ለመስማት እጓጓለሁ፡፡ እንዲያውም ሰሞኑንማ እነታማኝ በየነም ለይቶላቸው ወደ ፀረ አማራው ካምፕ እየገቡ ነው፡፡ ጊዜ መስትዋት ነው፡፡ የአቢይ ፈረሶች እነአንዳርጋቸው ጽቤና እነነአምን ዘለቀ (ሀዘን ላይ በመሆኑ አለቃቸውን መጥቀስ አልፈለግሁም) ምድረ ኢትዮጵያዊ ነኝ ባይን ሁሉ በአንዳች ምትሃት እየጎተቱ ወደ አጋንንቱ የአቢይ ጎራ እየጨመሯቸው ነው፡፡ እውነትም ሊነጋ ሲል ይጨልማል፡፡ ግን የዚህ ሆድ የሚሉት ነገር ስፋት ስንቱን ያሳያል!

መምህር አራት፡፡ ሱዳኖች፡፡ ከአቢይ ጋር የተመሳጠረችው ሰሜን ሱዳን የአማራን መሬት ከያዘች ሰነበተች – የአማራን ብቻም ሳይሆን የኢትዮጵያን፡፡ ጉድ ነው፡፡ ይህች እንደዐረብ ሀገር የምትቆጠር ሀገር ዛሬ ነፍስ ዐውቃ የሰው ሀገር መያዟ የነገሮችን ወደ ፍጻሜ ማምራት ይጠቁማል የሚሉ አሉ፡፡ ለማንኛውም አማራን መፈናፈኛ ለማሳጣት ያቀደው አቢይ ሱዳንንም ደቡብ ሱዳንንም ዝግጁ አድርጓቸዋል፡፡

መምህር አምስት፡፡ አሻድሊ ሀሰን (ቤንሻንጉል ጉሙዝ)፡፡ ይህ ሰው የኦነግ/ኦህዲድ አባልና እንዲያስተዳድር በወያኔና በኦነግ የተሰጠውን ክልል ለነአቢይ መጠቀሚያ በማድረግ ይታወቃል፡፡ ይህን ክልል የሚፈነጩበት የነአቢይ ኦነግ ሸኔና ወያኔ ናቸው፡፡ ሸኔና ኦነግ – ለነገሩ አንድ ናቸው – በሸመልስና አቢይ ትዕዛዝ በቅርቡ ምን ዓይነት ክስተት እንደሚፈጥሩ እናያለን – ግን ግን ልጆች ስለሆኑ መስሏቸው እንጂ ለነሱም አይበጅም፡፡ የሚጠብቁት የወያኔን ግስጋሴና ከርሱ ቀጥሎ ከነአቢይ የሚሰጣቸውን ስውርና ጥብቅ ትዕዛዝ ነው፡፡

መምህር ስድስት፡፡ ግብጽና ሌሎች ዐረብ ሀገራት፡፡ አማራን ማጥፋት ኢትዮጵያን እንደማጥፋትና የአባይን ውኃ ጨምሮ ከኢትዮጵያ የሚገኘውን ማንኛውንም ነገር እንደልብ ማግኘት እንደሆነ የሚያምኑት የዐረብ ሀገራት በግብጽ አጋፋሪነት እየሠሩት ያለው ጉድ ቢጻፍ ስንክሣር ይወጣዋል፡፡ የምታውቁት ስለሆነ ልተወው፡፡ ግን ይህች ሀገር ትልቅ በጀት መድባ በሁሉም ረገድ ኢትዮጵያን ለማጥፋት መነሳቷን መርሳት አይገባም፡፡ አሁን ወዳለንበት ዝብርቅርቅ ያለ ሁኔታ የገባነውም በዚህችው ሀገር ጦስ ነው፡፡ ዋና ሽብልቅ ነች – ከፋፋይ፡፡

መምህር ሰባት፡፡ አሜሪካና አጋሮቿ፡፡ እነዚህ ወገኖች ኢትዮጵያን እንደሚጠሉ ግልጽ ነው፡፡ የአሁኑን አያድርገውና ኢትዮጵያ ደግሞ ካለአማራ አትታሰብም፡፡ ምንም እንኳን አማራ ላለፉት ጥቂት አሠርት ዓመታት ከአመራሩ ገለል ቢልም እነዚህ ወገኖች የአማራን ኢትዮጵያዊነት እንደሚፈሩት አንበሣ አፉን ክፍቶ እንኳ ወደነሱ ቢሮጥ አይፈሩትም፡፡ ይቅርታ አድርጉልኝና አማራ ምን ዓይነት ግርማ ሞገስ እንዳለው አላውቅም፡፡ ሞቶም እንኳ ቢሆን የሚበረግጉ ወያኔዎችና ኦህዲዶች ማለትም አሜሪካውያንና አውሮፓውያን እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ በውነት በዚህ ደረጃ መፈራት መታደል ነው፡፡ ይሁንና አንዳንድ መታደሎች መርገምትንም በማስከተላቸው ይመስላል ይህ መታደሉ ለወደፊቱ ሳይጠቅመው እንደማይቀር መገመቱ የእያንዳንዳችን የግል ጉዳይ ሆኖ ለአሁኑ ግን አማራን እጅግ እየጎዳው ነው፡፡ ያሳዝናል፡፡

መምህር ስምንት፡፡ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ነአምን ዘለቀ፣ ታማኝ በየነ፣ ግንቦት ሰባት(ኢዜማ)፣ አክቲቪስቶች ለምሣሌ ሙክታሮቪች – ናትናኤል መኮንን፣ ሥዩም ተሾመና ሌሎችም፡፡ ይሄን ባልዲ ሆድ የታቀፈ ምሁር ነኝ ባይና አክቲቪስት ነኝ ባይ ሁላ ነገ ትቢያ ለሚሆን ለዚህ ጥምብ ሥጋ አድልቶ እውነትን በመቅበር ለሰባተኛው ንጉሥ አድሯል፡፡ ስለሆነም ከውጪ እስከ ሀገር ቤት ያለው “ምሁር”ና አክቲቪስት እንዲሁም ዩቲዩበር ለአቢይ ዘብ ቆሟል፡፡ እነዚህ የአቢይ ተከፋዮች አማራው ይሆነኛል ባለው አወቃቀር ተደራጅቶ ራሱን ከዘር ፍጂት እንዳይከላከል እያደረጉት ያለው ሸር የተሞላበት እንቅስቃሴ ሲታይ ሰዎቹ የለዬላቸው ደም መጣጮች መሆናቸውን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ሁሉም አማራ ላይ የሚረባረቡት ምክንያቱ ግልጽ ነው፡፡ አስመሳዩ የድርብ ድርብርብ ሰይጣናት ልዑክ አቢይ ግራኝ አህመድ ነገ አንድ ነገር ቢሆን ይህን ሁሉ ሆዳም ግሪሣ ምን እንደሚውጠው አንድዬ ይወቅ፡፡ ያ ቀን ደግሞ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አይቀርም፡፡ ሚሊዮኖችን የፈጠረ ጌታ አምላክ የንጹሓንን ደም በከንቱ አይተውም፡፡ ከዚህ ሁሉ ውጣ ውረድና መሪር የሕይወት ገጠመኝ ዕድሉን እያማረረ የሚማረው አማራና ሌላው ኢትዮጵያዊ ኅልውናውን ለማስጠበቅ ሆ ብሎ ሲነሳ እነዚህን የአጋንንት ውላጆች አያድርገኝ፡፡ የሀሰት ወሬ ሸጦ ከተራ መምህርነት ወደሚሊዮነርነት የተለወጠ አጋሰስ ሁሉ ነገ እንደዛሬው መደንፋት አይችልም፡፡ እንደጉማሬ የሚከፍተው አፉም ይዘጋል፡፡ ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር፡፡ ያን የነጻነት ቀን ለማየት ግን ብዙ ይጠበቅብናል – የመጀመሪያው ቅንነትንና ከክፋት መራቅን መሠረት ያደረገ ጸሎት ነው፡፡

አማራ ከፍ ሲል የተጠቀሱት ወገኖች በስደትና በሥራ ዝውውር ወይም ባለው የዜግነት መብት በገዛ ሀገሩ ከሚኖርበት ቀዬው ብቻም ሳይሆን ጠላቶቹ “ያንተ ክልል ነው” ብለው በሠፈሩለት አነስተኛ አካባቢም ሳይቀር እንዳይኖር የተቀናጀ ዓለም አቀፍ የዕልቂት ዘመቻ ከፍተውበታል፡፡ እንዲህም ሆኖ ራሱን እንዳይከላከል እንኳን ብዙ ደባ እየተሠራበት ነው፡፡ ሁለቱን ምናልባትም ሦስቱን ልጥቀስና ይብቃኝ፡፡

አንደኛ፡፡ ሰሞኑን በማርቆስ የአማራ ተዋጊዎች ሰለጠኑ ተባለ፡፡ እንደተመረቁ የአማራውን ትተው የዱሮውን የመከላከያ ልብስ እንዲለብሱ ተገደዱ አሉ፤ ይህ ድርጊት ያዘለውን ተንኮልና ሸር ትተነው እንዲሁ ለየዋህ ተመልካች አስቂኝም አስገራሚም ነው፡፡ ይህ ምን ማለት እንደሆነ የሌሎች ክልሎችን አልባሳት በማጤን መረዳት ይቻላል – የሌሎቹ እንደተከበረላቸው ናቸው፡፡ መሪ የሌለው አማራ ግን እስከዚህን መሣቂያና መሣለቂያ ሆኗል፡፡ የአንድ ክልል የሚሊሻም ሆነ የልዩ ኃይል የደምብ ልብስ መወሰን ያለበት በክልሉ ሆኖ ሳለ የአማራን ግን የሚወስነው ፌዴራሉ ነው – ምክንያት አማራ መሪ ስለሌለው፡፡ ከአጎብዳጅ ተላላኪዎች የዘለለ መሪም እንዳይኖረው በትኩረት እየተሠራበት ነው፡፡ የተሰጠው ልብስ ደግሞ ለጠላት ዒላማነት በቀላሉ የሚዳርግ መሆኑ ይህን ተዋጊ ኃይል ለማስጨረስ መታቀዱን ጠቋሚ ነው፡፡ አማራን ይበልጥ እያስጠቃው ያለው በውስጡ እሱን መስለው በተለያዬ እርከን ሥልጣንና ኃላፊነት የተሰጣቸው መሠሪዎች ናቸው፡፡

ሁለተኛ፡፡ የኦህዲድ ልዩ ኃይል በኢትዮጵያ ሀብት ኢትዮጵያን ለመውጋት ሲባል በአሥር ሽዎች ዶላር የሚገዛ መሣሪያ እንዲታጠቅ ሲደረግ የአማራ ልዩ ኃይል ግን የእንጨት ምርኩዝ እንኳን እንዳይዝ ተከልክሎ በባዶ እጁ እንዲዘምትና ከኋላ በሚተኮስ ከባድ መሣሪያ “ተደናግጠው ከሚሸሹ” የወያኔ ጀሌዎች እየማረከ እንዲታጠቅ ታዘዘ፡፡ ይህ ውሳኔ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዓለም አቀፍ ክስተት ነውና የምትችሉ ወገኖች ለዚያ “ጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ” ለሚባለው ድርጅት ንገሩና ይመዝገብ፡፡ ይህን ያደረጉ ሤረኞች በዛ ቢባል በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ዋጋቸውን እንደሚያገኙ ግን በኅያው እግዚአብሔር ስም እምልላችኋለሁ – መማል ባይቻልምና ለአሁን ብቻ እንደልይት ጉዳይ ተቆጥሮ ቢፈቀድልኝ፡፡ እናም እንዲህም ይደረጋልና ይህን ግፍና በደል ለመላው ኢትዮጵያውያን አሳውቁ – ባልጠፋ መሣሪያ አማራን ለማስጨረስ ታስቦ ለተጎነጎነ ደባና ተንኮል ስኬት ሲባል ብቻ  እስካፍንጫው የታጠቀ ጦር ጋር በባዶ እጅ እንዲፋለም ማድረግ ከየትኛውም ዘመን ወንጀሎች ሁሉ እጅግ የከፋ ነው፡፡ የነሆድ አምላኩ ብአዴናውያንን ሸርና ከጠላት ጋር የመተባበር ሤራም ግልጽ አድርጉ፡፡ ወገንም ይንቃና በኅቡዕ ይደራጅ፡፡

ሦስተኛ፡፡ ፌዴራል ተብዬው ከመነሻው ጀምሮ ዱቄት የተባለችውን ወያኔ ስንቅና ትጥቅ አሟልቶ ወደ አማራ የሚያዘምተው፣ አማራን እንዳይዋጋ ሽባ የሚያደርገው፣ የአማራን ከተሞች የትግሬ ተምችና አንበጣ እንዲረመርማቸው መንገድ የሚያመቻቸው፣ አማራ ሊሸንፍ ሲል ኃይለኛ ተዋጊዎችን ስንቅና ትጥቅ በመንሣት እያስወጣ አራትና አምስት ጥይት ባለው ኋላ ቀር መሣሪያ ገበሬዎችን እያሰለፈ የአማራን ሕዝብ የሚያስፈጀው፣ የአማራ አካባቢዎች በከባድ መሣሪያ እንዲመቱና ንጹሓን ገበሬዎች ከነቤተሰባቸው እንዲያልቁ ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥረው፣ የኑሮ ውድነቱን ሰማየ ሰማያት እየሰቀለ በከተሞች ሳይቀር ዜጎች በኑሮ ውድነት እሳት እንዲገረፉ የሚያደርገው፣ የፌዴራል መንግሥቱን ሀብትና ንብረት እንዲሁም የሥልጣንና የኃላፊነት ቦታዎች ለአንድ ነገድ ብቻ በመስጠት ሀገሪቱን በኬኛ ፖለቲካ እያመሳት የሚገኘው … ብዔል ዘቡላዊው የአቢይ አህመድ የአንድ ሰው መንግሥት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህን ድርጊቱን ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተብዬውም ያውቃል፡፡ ግን በዚህ ሊቀ ሣጥናኤል ሰውዬ ይበልጥ እየተጎዳና ዘሩም እየጠፋ የሚገኘው ያው የፈረደበት አማራ በመሆኑና እሱም በነሱ ዒላማ ውስጥ ገብቶ ለዕልቂትና ውድመት የተዘጋጀ ሕዝብ በመሆኑ ሌላው ይቅርና በአማራ ክልል በሚካሄደው ጦርነት ለነቢቢሲ ዝምብም የሞተ አልመሰላቸውም፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ የኬንያ መሪ የማንትስ ኬንያታ ውሻ መኪና ገጭቷት ብትሞት የነአልጀዚራና ሲኤንኤን የዜና መክፈቻ ዋና ዜና እንደማይሆን ሁሉ በኛ ሀገር በብዙ ሽዎች የሚቆጠር የትግሬና የአማራ ሬሣ እዚህና እዚያ ተረፍርፎ እየታየና የዐውሬ መፈንጫ ሆኖ ሳለ ግን ምንም ዓይነት የዜና ሽፋን አይሰጡትም፤ እግዜር በቶሎ ፍርዱን ይስጣቸው፡፡ ሰለጠኑ ይባላሉ እንጂ ከመሰይጠን አላለፉም፤ በሀብትና በቴክኖሎጂ ማደግ አእምሮን ካልሳለውና ወደ እውነት ካላቀረበ ዓለም የምትፎክርበት የዘመናችን ምጡቅ ሥልጣኔ በአፍንጫ ይውጣ፡፡ አንድ ሰው ነጭ ሲሞት አዝኖ፣ ጥቁር ሲሞት ስቆ የሚያልፍ ከሆነ ያ ሰው ሰው ሳይሆን ከቀሪዎቹ እንስሳትም ያነሰ ቅል ራስ ነው፡፡ ዝኆን ወገኑን አልቅሶ በሚቀብርባት ዓለም፣ ውሾች አዝነውና ተክዘው ወገናቸውን አፈር በሚያለብሱባት ምድር የሰው ልጅ በጎሣና በነገድ፣ በሃይማኖትና በቀለም እየተለያዬ እንዲህ መዋረዱ ባንድ በኩል የዓለምን ፍጻሜ አመላካች ነው፡፡ አሜሪካንንና አውሮፓውያንን  በሩዋንዳና በሌሎች ሀገሮች እናውቃቸዋለን፡፡ የንቀታቸውና የትዕዕቢታቸው ብዛት ደግሞ አንድ ዕልቂት ካለፈ በኋላ “እናውቅ ነበር” ይሉሃል – እነሱ ያቀናበሩትን የዘር ፍጂት ቀድመው እንደሚያውቁት በዘወርዋራ ሲገልጹልህ፡፡ ትዕቢታቸው ትዕቢት አይደለም፡፡ ግን ለነሱም የተዘጋጀ ቅጣት ስላለ በዚህች ምድር ማንም በማንም ስቃይ ተደስቶ አይቀርም፡፡ ሁሉም የዘራውን ያጭዳል፤ ሁሉም ለሰው በቆፈረው ጉድጓድ ቀድሞ ይገባል፡፡ አዲስ ነገር የለም – ችግሩ አንዱ ካንዱ ያለመማሩ ድንቁርና ቤቱን ሠርቶብን እየተጫወተብን መገኘቱ ነው፡፡ በቃኝ እባክህን …. እንዲያስችለኝና ዝም ብዬ እንድቀመጥ በፈጠራችሁ ጸልዩልኝማ …..

2 Comments

  1. ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሃርነትን ሳይሆን ባርነትን በምድራችን ካስፋፋ ወዲህ ህዝባችን ቀና ብሎ ከአፍንጫ በራቀ ምልክታ ሃገሬና ወገኔ የሚለውን እምነትና ቆራጥነት ለመፋቅ ያላሰለሰ ሴራ ሰርቷል በመስራትም ላይ ይገኛል። ለዚህ ማሳያው የኦሮሞ ሃይሎች አሁን በጭንቅ ውስጥ ካለፈው አውዳሚ ሃይል ጋር ተለጣፊና ተላላኪ ሆነው መስራታቸው ነው። እንዴት በ 27 ዓመቱ የመከራ ዘመን በወያኔ እየተለቀሙ የተገደሉት፤ አካላቸው የጎደለው፤ ሌላው ቢቀር የእውቁ ከያኔ የሴራ ግድያ የወያኔን አጥፊነትና ለኦሮሞ ህዝብ የመከራ ሸክም መሆኑን መረዳት ይከብዳል። የሱዳንና የግብጽ ተላላኪ መሆን ለጊዜው ቂጣ መግዣ ያስገኝ ይሆናል እንጂ ታኝኮ ከመተፋት አያድንም። የወያኔን አረመኔነት አሁንም አልገባኝም የሚል ሰሜን ወሎ፤ ደቡብና ስሜን ጎንደር በቅርብ ጊዜ የፈጸማቸውን ኢሰብአዊ በደሎች በሥፍራ ሂዶ መመልከት ብቻ በቂ ነው። ጤነኛ ጭንቅላት ያለው ከአማራ ጋር የሚያወራርደው ሂሳብ አለኝ ብሎ በይፋ አይናገርም። አልፎ ተርፎም ኢትዮጵያን ሲኦል ቢሆን እንከታታለን ብሎ መደንፋት ምን ያህል ወያኔ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚል የሙት ፍልስፍና እንደሚከተል አስረግጦ ያሳያል።
    አሁን ግን ጊዜው ተቀይሯል። የአማራ ህዝብ ሆ ብሎ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ተነስቷል። መዋጋት አይችልም። ሰነፍ ነው እኛ ያልነውን የሚፈጽም ተላላኪ አድርገነዋል። አማራና የኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያንን ዳግመኛ እንዳይነሱ ቀብረናቸዋል ይሉን የነበሩ የወያኔ ቁንጮዎች ግማሾቹ ማረፊያ ቤት፤ ቀሪዎቹ በድር በገደል ነፍሴ አውጪኝ ሲሉ የቀሩት ደግሞ ያለፍትሃት ዳግመኛ ላይነቁ አንቀላፍተዋል። ዛሬ በቁም ሃገርና ወገን የሚያሸብሩትም ያለምንም ጥርጥር ግባተ መሬታቸው አይቀሬ ነው። እስከዚያው ህዝባችን ያርዳሉ፤ ያሸብራሉ፤ ይዘርፋሉ፤ መንደርና ከተሞችን ያቃጥላሉ። ይህ ሁሉ ድርጊታቸው ተስፋ መቁረጣቸውን ያመላክታል። ግን አድር ባይ አማራ ወይም ቅማንት ወይም ሌላ ከወያኔ ጎን ሆነህ ዛሬ ህዝብህን የምታስጨርስ ተላምጦ ጣፋጭነቱ እንዳለቀ የሸንኮራ አገዳ ወያኔ ይተፋቹሃል። የአማራና የእነርሱ ወገን ያለሆነ ሰው ላይ ጥላቻቸው አጥንታቸው ድረስ ዘልቆ የገባ በሽታ በመሆኑ ከተገለገሉብህ በህዋላ ይረሽኑሃል። ልብ ያለው ጊዜ እያለ ተፋልሞ መሞት ነው። ሞት እንደሆነ በዚህም በዚያም አይቀሬ ነው።
    ከሁሉ በላይ ለእኔ እንቆቅልሽ የሆነብኝ ነገር የህግ ማስከበር ዘመቻው እንዴት ወደ ህልውና ዘመቻ እንደተቀየረ ነው። አለቁ፤ ገደል ገቡ፤ አየር ሃይሉ ደመሰሳቸው ወዘተ ስንባል የነበረው ውሸት ነበር ማለት ነው? እንዴት 600 ኪ.ሜትር ከመቀሌ ርቆ ወጥቶ ወያኔ በንፋስ መውጫና በደብረ ታቦር አካባቢ ሰውን አቅጣጫ የለሽ በሆነ የመድፍና የቀላል መሳሪያዎች ድምጽ ማሸበር ቻለ? አሁንም ረሸናቸው፤ ገደልናቸው፤ ደመሰስናቸው፤ ተቆረጡ፤ ተከበቡ አትበሉን ወሬአችሁ ሰልችቶናል። ሥራችሁን በልባችሁ ሥሩ። ለሽርፍራፊ ሳንቲም ሲባል በየድህረ ገጽ የሌለና ቅንጣት እውነት ያለበት ወሬ የምታናፍሱ ከተግባራችሁ ተቆጠቡ። እናንተ ሳንቲም ስትቆጥሩ ወያኔ ወሬአችሁን እንደ መረጃ ተጠቅሞ ህዝባችን እያጎሳቆለና እየገደለ ነው። በሌላ በኩል ለዘመናት በአማራና በሌሎች ክልሎች አብረው ሲኖሩ የነበሩ የወያኔ ድላ አቀባዪችና የውስጥ ድጋፍ ሰጭዎች በማያወላዳ መረጃ በተደገፈ መልኩ አይቀጡ ቅጣት ሊሰጣቸው ይገባል። እነዚህ ሃይሎች በልዪ ልዪ ተቋማት ውስጥ ወያኔ ሆን ብሎ ያስቀመጣቸው ሃይሎች ናቸው። ይህ ሲባል በጦር ሜዳ ላይም ሆነ በከተማ የወያኔ ደጋፊዎችና የውስጥ ጀሌዎች የደቦ ፍርድ ይሰጣቸው ማለት አይደለም። ይህ በጭራሽ ሊደርግ አይገባም። በተጣራ መረጃ ሰው አውቆት ህግን ተከትሎ ጠበቃ ቁሞላቸው መፈጸም አለበት። ያ ካልሆነ ከወያኔ አስራር የሚለየው የቱ ላይ ነው? እነርሱ ቤት ዘግተው አይደል እንዴ ሴትና ወንድን ያጋዪት? ግን በህግ መዳኘት ለአሁንም ሆነ ለመጪው ትውልድ ትምህርት ይሰጣልና ነው። ውጊያውን ቀልብሶ ወደ ኋላ በመመለስ ውጊያው ትግራይ ውስጥ እንዲሆንና ወያኔን በናፈቀውና ይወደናል በሚለው ህዝብ መሃል መቃብሩን ምሶ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመቅበር የትግራይን ህዝብ ዳግም ነጻ በማውጣት በሃገሪቱ ላይ በውጭና በውስጥ ሃይሎች በወያኔ መሪነት የተሽረበውን ሴራ መቀልበስ ይገባል። የኢትዮጵያ ጠላት የሱዳንም መንግስት ነው። እነርሱ ናቸው ዛሬም ትላንትናም አይዞአችሁ እያሉ የኢትዮጵያን ህልውና ከግብጽ በተሰጣቸው ትዕዛዝ የሚያናኩሩን። ለዚህ መረጃው ከስደተኞች መጠለያ ጣቢያ እየተመለመሉ ለውትድርና ስልጠና በገዳሪፍና በሌሎች የሱዳን ግዛቶች በግብጽ ወታደራዊ መኮንኖችና በወያኔ ሃይሎች የሚሰለጥኑትን ለመረጃ ማቅረብ ይቻላል። ስንቶች ናቸው ሂድ ተብለው በመንገድ በውሃ ጥምና በውጊያ ላይ የሞቱና የተማረኩት? ቤቱ ይቁጠረው!
    ባጭሩ አማራ ክዳር ድንበር በመነሳት ወራሪውን የትግሬ መንጋ ከምድሩ ማስወጣት አለበት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው የጨለማና የመከራ የወያኔ አገዛዝ ተጠያቂው ወያኔ ሳይሆን አሁን በዝምታ የቆመ አማራ ሁሉ ነው። ትላንት በመርዝ፤ በሚያመክን መርፌ፤ በመኪና በመግጨት፤ የሰው ብልት ላይ ውሃ በማንጠልጠልና በማምከን፤ ሴቶችና ወንዶችን በምድፈር፤ ከሥራ በማባረር፤ የሃገሪቱን ሰራዊት የደርግ ሰራዊት በማለት በመበተን፤ ኸረ ስንቱ ግፍ ይወራ። የሃገሪቱ ታዋቂ ሰዎች ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በውጭና በሃገር ውስጥ የተገደሉት ደም ዛሬም ይጮሃል። የፕ/ር አስራት ደም ይጮሃል። እውቅ የሃገሪቱ ከያኔዎችና ጸሃፊዎች ምሁራን ደም ይጮሃል። ወያኔ ናዚ ነው። ወያኔ ሞሶሎኒ ነው። ዋ የትግራይ ህዝብ እነዚህን ጉዶች እስከ መቼ ነው ጉያው ደብቆ የሚይዘው? በግልጽና በ ህቡዕ በመደራጀት የትግራይ ህዝብ ወያኔን በያለበት እያደኑ መግደል ለአሁን እና ሊመጣ ላለው መሰረት ነው። ወያኔ ለራሱ ጥቅም አብሮነታችን ያፈረሰ ድርቡሽ ነው። አይኑ እያየ እላዪ ላይ አፈር የሚመለስበት ጊዜው አሁን ነው። ወያኔ ለማንም የማይጠቅም ሰካራም የረገጠው ጣሳ ነው። በቃኝ!

  2. basic typographic correction in the sentence – አማራ ሊሸንፍ ሲል ኃይለኛ ተዋጊዎችን … it should have been ሊያሸንፍ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.