ሕገ-ወጥ የዶላር ምንዛሪን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተሰጠ መግለጫ

/
በሀገራችን ላይ የተለያዩ ሴራዎችን ሲያካሂድ የቆየው የአሸባሪው የህወሃት ጁንታ ቡድንና ተላላኪዎቹ ፊት ለፊት ከሚያካሂዱት ሀገር የማፍረስ ሴራ ጎን ለጎን በሀገሪቱ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት እንዲፈጠርና ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲማረር የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ መሆናቸው ተደርሶበታል፡፡
በዚህ መሰረት የሽብር ቡድኑ ስልጣን ላይ በነበረባቸው አመታት በዘረጋቸው ኔትዎርኮችና ቅጥረኞች አማካኝነት ከአዲስ አበባ ቶጎ ውጫሌን፣ ሞያሌን፣ መተማንና ሌሎች የመውጫ በሮችን በመጠቀም ኮንትሮባንድ ዝውውር ላይ በመሳተፍና ዶላርን በጥቁር ገበያ እየገዛ የዶላር እጥረት እንዲከሰት ከማድረግ ባሻገር በርካታ የጥፋት ተግባራትን ሲያካሄድ የቆየ መሆኑን ቀደም ሲል በህገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ ስድስት ድርጅቶች ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ስለመሆኑ ባስተላለፍነው መረጃ ተደራሽ ማድረጋችን ይታወሳል፡፡
exchange1
ሰሞኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል ጋር በአዲስ አበባና በአንዳንድ የክልል ከተሞች ባካሄደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ለሽብር ቡድኑ የኢኮኖሚ ምንጭ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩ 117 የንግድ ድርጅቶች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ የአሸባሪው ቡድን የፋይናንስ ምንጭ እንዲደርቅ የሚያደርጉ ተግባራትን አከናውኗል፡፡
ውድ በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፡- የአሸባሪው ቡድን ከፍተኛ የገቢ ወይም የፋይናንስ ምንጭ በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የዘረጋቸውን ኔትዎርኮች በመጠቀም ዶላርን በጥቁር ገበያ በውድ ዋጋ መሰብሰብ እና የሃዋላ አገልግሎትን መጠቀም እንደሆነና ከዚህ በሚያጋብሰው ገቢም የጦር መሳሪያ ግዥን በመፈፀም ለጥፋት ተልዕኮው እንደሚጠቀምበት ፌዴራል ፖሊስና የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል በሀገር ውስጥና በውጭ ሃገርም ባካሄዱት ረጅም ጊዜ የፈጀ ጥናትና በተደረገ ምርመራና ክትትል ደርሰውበታል፡፡
በጥናቱም ኔትዎርኮቹን የመለየት ስራ የተከናወነ ሲሆን በኔትዎርኮቹ ውስጥም፡-
1. አርዓያ (የዞማ የውበት ሳሎን ባለቤት) አሜሪካ የሚኖር
2. ሳሙኤል (ሳሚ ዶላር) አሜሪካ የሚኖር
3. ጣዕመ መርከብ አሜሪካ የሚኖር
4. ሄኖክ (ዲሲ)- አሜሪካ የሚኖር
5. ሃብቶም ዶላር (ፈረንሳይ የሚኖር)
6. ኤሊያስ (ዱባይ የሚኖር)
የተባሉት ግለሰቦች የሚገኙበት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚልኩትን ዶላር አየር በአየር ግብይት በመፈፀም እንዲሁም ዶላሩን እዚያው ውጪ እንዲቀር በማድረግ ለሽብር ቡድኑ ድጋፍ የፋይናንስና የሎጀስቲክ ምንጭ በመሆን እያገለገሉ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባችኋል፡፡
በህገ-ወጥ መንገድ ዶላርን ከደቡብ አፍሪካ ወደ ኢትዮጵያ እየተላላኩ ሀገራችን ማግኘት የሚገባትን የውጭ ምንዛሬ እንድታጣ በማድረግ ረገድ፡-
1. መንግስቱ ወርቁ (እስራኤል፣ ቴል አቪቭ የሚኖር)
2. አቪ ፈጠነ (እስራኤል የሚኖር )
3. አስቴር ባልትና (ፕሪቶሪያ የምትኖር )
4. እቴነሽ (ፕሬቶሪያ የምትኖር)
5. ዮናታን ትሬዲንግ ጂፒ (ጆሃንስበርግ የሚኖር)
6. ሄኖክ ባልትና (ጆሃንስበርግ የሚኖር)
7. እሙ (ደርባን የምትኖር)
8. መሐመድ ሼክ ጀማል እና ፋሚ ሼክ ጀማል (ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ)
ግለሰቦችና ድርጅቶች እጃቸው እንዳለበት በምርመራ ስለተረጋገጠ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ብሄራዊ ኢንተርፖል እነዚህን ግለሰቦችና ድርጅቶች ለህግ ለማቅረብ ስም ዝርዝራቸውን ለአለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) ልኮ በጋራ እየሰራ ይገኛል፡፡
ስለዚህ ውድ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ይህ አሸባሪ ቡድን ለሽብር ድርጊቱ ማስፈፀሚያነት የሚጠቀመውን ገንዘብ የሚያገኘው በዚህ መንገድ መሆኑን በመገንዘብ ከዚህ ፀረ ኢትዮጵያ ቡድን ጋር ባለመተባበር ሀገር ወዳድነታችሁን እንድታስመሰክሩ እንዲሁም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት ላይ የተሰማራችሁ ዜጎች ጉዳቱ ለመላው ሀገሪቱ ነውና ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ነሐሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ተጨማሪ ያንብቡ:   ከ4ኪሎ አልወጣም አጠይቁኝ አብይ | ፕ/ር ብርሃኑ “ለአብይ ስል ወዳጄን ኢሳያስን ለመውጋት ዝግጁ ነኝ” | “ኢትዮጵያ የሚለውን ስም መስማት አንፈልግም” የአብይ ጉድ

2 Comments

  1. Though it is too late, the action is indispensable!!

    እርምጃው ቢዘገይም ተገቢ ነው፡፡ ቀድሞ ተደርጎ ቢሆን ኖሮ ስንት ጥፋትን እና የኢኮኖሚ ግሽበትን መከላከል በተቻለ ነበር፡፡

    Long live to Ethiopia!!

  2. አይ ጅምራችሁ ማለፊያ ነው። ግን ገና ይቀራችሁሃል። መቼ በአውስትራሊያ ከተሞች፤ በካናዳ፤ በአሜሪካ (ጥቂቱን ነው የነካካችሁት)፤ በኒውዝላንድ፤ በተለይም በአረብ ሃገራት ገና የሚቆፈርና የሚወጣ ጥልቅ የገንዘብ ዝውውር የወያኔ ሰንሰለት አለ። ለምሳሌ በሃገር ቤት በታላላቅ ሆቴሎች፤ በሱቆች፤ በመንግሥት መ/ቤቶ ለምሳሌ ባንኮች የባንድክ ሰራተኞችን ሳይቀር በመጠቀም፤ የትራቪል ኤጄንሲዎች፤ ቱሪስት አስመጪና አሰጎብኚዎች ሁሉ የዚህ የጥቁር ገቢያው ገንዘብ አሸጋጋሪ ኮሚሽን ተከፋዪች ናቸው። ግን ይህ ሁሉ ያው ከራሳችን ስግብግብነትም የመነጨ ነው። ህጋዊ በሆነ መንገድ እንደ ዌስተርን ዪኒየን ያሉትን እንደመጠቀም እኛ በምንልከው ገንዘብ ወያኔ ሃገርና ህዝብን ያምስበታል። አልፎ ተርፎም ኢትዮጵያን የሚያጣጥል ውሳኔ የአሜሪካን ባለስልጣኖች እንዲያስተላልፉ በላቪ ስም የእጅ አዙር ጉቦ እየሰጠ የህዝባችን የሰቆቃ ጊዜ ያራዝማል። ለምሳሌ በደቡብ ሱዳን በቀጥታ ገንዘብ በመላክ ታዋቂ ሰዎች እንዲገደሉ ይከፍላል። ከረጅም ጊዜ በፊት በዚያው ለስራ ሂዶ የተገደለው የህክምና ዶክተር ይታወሰኛል። ከዚህ አልፎ በደቡብ አፍሪቃ ሃገር ወዳድና ወያኔን ፊት ለፊት ሲፋለም የነበረውን ነብሮን እንዲገደል ያረጉት ከዚሁ በእኛ ከሚላከው ገንዘብ በመስጠት ነው። ኸረ ስንቱ ይወራል?
    አንድ ወደ 70 ዓመት የተጠጋው የድሮ የወያኔ ታጋይ አሁን አክ እንትፍ ብሎ የተፋቸው በቅርብ እንዲህ ብሎ አጫወተኝ። እኔ እንዴት ባለ ሂሳብ ነው ለዘመናት ሲጠብቃችሁ፤ ቤትና ትምህርት ቤት፤ መንገድ ሲሰራላችሁ፤ አረምና አጨዳ ሲወጣላችሁ የኖረን ሰራዊት በተኛበት የምትገሉት ስለው ዓይኑ እንባ አቅርሮ ለብዙ ደቂቃዎች ዝም ካለ በህዋላ እንዲህ አለኝ። ወንድሜ ተስፋ ወያኔ ሰዎችን በተኙበት መግደል የጀመረው አሁን አይደለም። በበረሃ የትግራይ ልጆችን ሁሉ በተመሳሳይ ሁኔታ ረሽኗል። ወያኔ ከማጎልበቱ በፊት አንድ ሃይል በትግራይ መሬት ደርግን ይቃወም ነበር። ይህ ሃይል ግን በዓላማና በፓለቲካዊ እይታ ከአሁን ወያኔ ጋር አይጣጣም። ታዲያ እንታረቅ ተባለና ሰው ተልኮ እሺ ተበሎ በሬ ታርዶ ፊሽታ ሆነ። ተበላ፤ ተጠጣ ማታ ሰው በየአገኘው አካባቢ ተኛ። ቀደም ብለው በድብቅ ባዘጋጇቸው ሃሎች በተኙበት ታራቂ ሃይሎችን በሙሉ ደመሰሷቸው። ይህ ታዲያ ከሰሜኑ እዝ አገዳደል ጋር አይመሳሰልም በማለት እንባውን አፍሶ ጸጥ አለ። እኔም የምታውቃቸው የሞቱ ሰዎች አሉ እንዴ በዚህ ግድያ ስለው አዎን ሁለት ወንድሞቼ በማለት ይባሱን ሲያለቅስ እኔንም አሳዘነኝ። እንባውን ጠራረገና እንደገና ሰለ ኢዲዪ አመራርሮች አገዳደል መናገር ሲጀመር ሲቃ ያዘው። በሥፍራው ነበርኩ። አንድ ወንዝ ውስጥ ሰውነታቸውን ይታጠቡ ነበር። ሳይታሰብ ተከባቹሃል ተባሉ። ተኩስ ተከፈተ፤ ሁሉም በዚያው በውሃው ውስጥ እንዳሉ አለቁ። ውሃው ወደ ደም ተቀየረ በማለት አጫወተኝና ከሌሎች ኑሮ ቀምስ የሆኑ ጫወታዎችን ተጫውተን ተሰነባበትን። አረመኔው ወያኔ ከራሱ በላይ ለማንም አያስብም። በውጭና በሃገር ውስጥ ከወያኔ ጋር አብረው ሲዘርፉ፤ ሲገድሉ የነበሩ የቁም ሙቶች አሁን ኢትዮጵያዊ አይደለንም ቢሉን አያስደንቅም። ሲሰርቁና የሃገሪቱን ሃብት ሲመዘብሩ ነው የእነርሱ ዜግነት። የትግራይ ህዝብም የእነርሱ የማትረፊያ ስልቻ እንጂ ለወገን ቆመው አያውቁም። አሁን ከአሜሪክ ጎን ቆሞ ሃተፍ ተፍ የሚለው ወያኔ የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም እንዲሉ ነው። አሜሪካኖች የማይታመኑ፤ በመከራ ጊዜ የሚፈረጥጡ ለመሆናቸው በሶሪያ፤ በኢራቅ፤ በሊቢያ፤ በአፍጋኒስታን የሚሆነው ማየት ብቻ በቂ ነው። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፓሊሲ “ድቄቱን አምጪው የትም ፍጭው ” ነው። ዲሞክራሲ፤ የሰው ልጆች መብት የሚባለው ሁሉ ማባበያ ነው። በመሰረቱ በአፍጋኒስታኑ ታልቫንና በሳውዲ አረቢያ መንግስት መካከል ልዪነት የለም። ግን 20 ዓመት ሙሉ የአፍጋንስታንን የመከራ ዶፍ ዞር ብሎ ያላየው የአሜሪካ ሚዲያ አሁን የነጭ ግርግር ሲታከልበት ለወሬ ፍጆታ ቀን ከሌት ይዘግቡታል። አክ እንትፍ ሊባል የሚገባው የኮሮጆ ወሬ!
    ባጭሩ ዘምባቢዌ፤ አንጎላ፤ ሞዛምቢክ፤ ካሜሩን፤ አይቬሪኮስት ወዘተ ምንም በማይረባ ነገር ሰው ከሰው እንዲላተም፤ ኢኮኖሚያቸው እንዲወድቅ የሚያደርጉት እነዚህ ሴረኞች ናቸው። በራሱ አስቦ ለህዝብና ለወገን የቆመን ብቸኛ መንግሥት አሜሪካኖች አፍሪቃ ላይ እንዲኖር አይፈልጉም። ተላላኪና እነርሱ የፈለጉትን በሃገሪቱ ውስጥ ማድረግ ከቻሉ ግን ሺ ዓመት ንገስ ነው የሚሉት። የወያኔ የስለላ መረብና አስራር ስልት፤ የገንዘብ ዝውውርና አጠቃቀም፤ ለእርዳታ የተላከውን በቢሊዪን የሚቆጠር ገንዘብ ማሸሸት ሁሉ ከአሜሪካው የስለላ መረብ አይን ያለፈ አልነበረም። ግን ሰርቀው ስለሚያበሏቸውና ዋና ተላላኪዎችና ጉዳይ አስፈጻሚዎች ስለነበሩ ዝም ተብሏል። በኤርትራ ላይ የተደረገው ማዕቀብም ከዚሁ የተላላኪ ቡድን ኡኡታ ጋር የተያያዘ ነው። ባጭሩ ወያኔ የሰሜን እዙን ለመምታት ሲያቅድ የአሜሪካው የስለላ መረብ ጠንቅቆ ያውቃል። ግን ለመንግስት መናገር አልፈለገም። በሴራው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እጃቸው ስላለበት።
    በመጨረሻም ሃገሪቱን ለማዳክም ወያኔ የዘረጋው የውጭ ምንዛሬ ዝውውር ጉዳይ በዶላር ላይ ብቻ ማተኮር የለበትም። ሌሎች የገንዘብ አይነቶች ዝውውርም ላይ ጭምር እንጂ። ለምሳሌ አንድ የኩዌቲ ዲናር ወደ 3 የአሜሪካ ዶላር ነው። ወያኔ ሂሳቡን ሲሰራ የሁሉንም ሃገር የወረቀት ገንዘቦች ጭምር እያጋጨና እያፋጨ በመሆኑ ዝርዝር ሁኔታውን መረዳት ተገቢ ይመስለኛል። እኛም ሃገር ወዳድ ነን የምንል ወገኖች በምንም ሂሳብ በጥቁር ገቢያ ማለትም ሃዋላና ሌሎች የጨለማ የገንዘብ የዝውውር መንገዶችን መጠቀም አቁመን ህጋዊ በሆነ መንገድ ብንልክ የወያኔን የገንዘብ ምንጭ ድርቆሽ ያደርገዋል። መንግስት ግን ሥራና ምርመራውን በሁሉም የሃገሪቱ ክፍል ካደረገና ከውጭ መንግስታትም ጋር በኢንተርፓል ከተረዳ ባጭር ጊዜ ውስጥ የወያኔን ዘራፊዎች የገቢ ምንጭ ማድረቅ ይቻላል። እንበርታ። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share