በማኮብኮብ ላይ በነበረ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር አውሮፕላን ላይ የተንጠላጠሉ 7 ሰዎች ወድቀው ሕይወታቸው ማለፉን የዩናይትድስቴትስ ባለስልጣናት አስታወቁ

በአፍጋኒስታን ታሊባን የካቡልን ከተማ ከተቆጣጠረ በኋላ በካቡል ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከሀገር ለመውጣት በማኮብኮብ ላይ በነበረ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር አውሮፕላን ላይ የተንጠላጠሉ 7 ሰዎች ወድቀው ሕይወታቸው ማለፉን የዩናይትድስቴትስ ባለስልጣናት አስታወቁ።
44
44
ዛሬ ከረፋዱ ጀምሮ ሟቾችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በማኮብኮብ ላይ ያለ ግዙፉን የዩናትድ ስቴትስ ሰው ጫኝ የጦር አውሮፕላን ሲንጠላጠሉ በማህበራዊ የመገናኛ አውታሮች ላይ በስፋት ሲሰራጭ ውሏል። ሟቾች አውሮፕላኑ በመንደርደር ላይ ሳለ እንዲሁም የተወሰኑት ደግሞ አውሮፕላኑ ተነስቶ መብረር ከጀመረ በኋላ ከአውሮፕላኑ ወድቀው ይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።
ታሊባን ትናንት እሁድ ከተጠበቀው ጊዜ አስቀድሞ መዲናዋ ካቡል መግባቱን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ዜጎች የታሊባንን የበቀል እርምጃ በመስጋት ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ሲተሙ ታይተዋል። በምዕራባውያን የሰለጠኑ ወታደሮች እና ሌሎች ባለሞያዎች የዩናይትድ ስቴትስ ጦር አፍጋኒስታንን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ ተፍረክርከዋል አልያም ተበትነዋል ነው የተባለው ። የአፍጋኒስታን የሲቪል አቪዬሽን መስሪያ ቤት ተጨማሪ መመርያ እስኪመጣ ድረስ በማለት የመንገደኞች መገልገያ መስመር መዝጋታቸው የከፋው አደጋ እንዲፈጠር ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል።

DW
ተጨማሪ ያንብቡ:  Sderot’s Hagit Yaso Captures Top Prize in “Israeli Idol”

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.