አሸባሪው ህወሓት በሽብር ተግባሩ በዓለም አቀፍ የአሸባሪዎች መረጃ ቋት ውስጥ የተካተተ መሆኑን ምን ያህል ያውቃሉ

tplf nazi

አሜሪካዊው ጋሪ ላ ፍሪ በአሜሪካው የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የፓርክ ኮሌጅ ዳይሬክተር፣ የወንጀል ምርምር እና የኢኖቬሽን ዳይሬክተር እንዲሁም በዓለም አቀፍ ሽብር ላይ ጥናት የሚያደርግ ተቋም መስራች የሆኑ ስመ ጥር ባለሙያ ናቸው።

በዋናነት በእኝህ ስመጥር ፕሮፌሰር እና በአሜሪካ ብሔራዊ የሽብር እና የሽብር ግብረ መልስ ጥናት ማዕከል አማካኝነት እአአ በ1970 የተመሠረተ ዓለም አቀፍ የሽብር እና ሽብርተኞች መረጃ መመዝገቢያ ቋት (GlOBAL TERRORISM DATABASE) የሚባል የመረጃ ማዕከል አለ።

ይህ የመረጃ ቋት እንደ አልቃይዳ ያሉ አሸባሪ ድርጅቶች የፈጸሟቸውን ከ200 ሺህ በላይ የሽብር ወንጅሎችን ከእነ ፈጻሚዎቻቸው መዝግቦ ይዟል።

አሸባሪው ህወሓትም የፈጸማቸው የሽብር ወንጀሎችና ራሱ ድርጅቱ በዚህ ዓለም አቀፍ የሽብር መረጃ ቋት ውስጥ ከ45 አመት በፊት ጀምሮ አሸባሪ ተብሎ ተመዝግቦ ይገኛል።

ይህ አሸባሪ ድርጅት የሽብር ተግባር መፈጸም ብዙዎች እንደሚያስቡት የአሁን ተግባሩ ሳይሆን ገና ከጅምሩ ሲፈጠር አንስቶ የተካነበት መሆኑን ይሄው ዓለም አቀፍ የመረጃ ቋት ውስጥ ተመዝግቦ ያለው መረጃ ያሳያል።

አሸባሪው ህወሓት ከስር የተያያዘው የመረጃ ቋቱ እንደሚያሳየው እአአ ከ1976 ጀምሮ በተለያዩ ንጹሀን ዜጎችና ንብረቶች ላይ ያነጣጠረ የሽብር ጥቃት ፈጽሟል።

ይህ አሸባሪ ድርጅት የፈጸማቸው የሽብር ጥቃቶች በሙሉ ኢላማ ያደረጉት ንጹሀን ዜጎችን፣ የሀይማኖት ተቋማትን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ሚዲያዎችን እና መሰል የግለሰብ ንብረቶች ላይ ነው።

አሁንም ይህ አሸባሪ ድርጅት ተመሳሳይ ወንጀል እየፈጸመ መሆኑን የሚካድ አይደለም። በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ፣ ከአንድ ሺህ በላይ ንጹሀንን የጨፈጨፈበት የማይካድራው ብሄር ተኮር ጭፍጨፋ፣ በአፋር ጋሊኮማ ያካሄደውና 107 ህጻናትን ጨምሮ ከ240 በላይ አርብቶ አደሮች የተጨፈጨፉበት እና መሰል ወንጀሎች የድርጅቱን ሽብርተኛነት ያረጋገጡ የቅርብ ጊዜ ተግባራቱ ናቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ በተቃውሞ ምክንያት ለወደሙ የኢንቨስትመንት ተቋማት ካሳ ልትከፍል መሆኑን አስታወቀች

የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ በመጣስ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሀወሓት) እና ሸኔ የሽብር ወንጀልን አላማቸው አድርገው የሚንቀሳቀሱ በመሆኑ እና የሽብር ተግባር መፈጸም የድርጅቶቹ ጠቅላላ መገለጫ በመሆኑ ሁለቱም በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ድርጅት ተብለው መፈረጃቸው ይታወቃል።

መንግስት በተደጋጋሚ ከለውጡ በኋላ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ከተፈጸሙ ግድያዎች፣ ማፈናቀሎች፣ ብሔር ተኮር ጭፍጨፋዎች ጀርባ እነዚህ ሁለት አሸባሪ ድርጅቶች እጃቸው እንዳለበት ሲገልጽ፤ እነሱም ሲያስተባብሉ ቢቆዩም ከሰሞኑ ሁለቱ አሸባሪ ድርጅቶች በጋራ አብረው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

በአሸባሪው ህወሓት የተፈጸሙና በመረጃ ቋቱ ውስጥ ተመዝገበው ያሉ የሽብር ወንጅሎችን ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው ይመልከቱ።

(ኢ.ፕ.ድ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.