የህወሀትን ጣረሞት ተከትሎ ዶላር 65 ብር ገብቷል፣ መቀልበስ ግን አንችላለን

ህወሀት ጣረሞት ላይ ናት ፡፡ አጎራባች የአማራና የአፋር ክልልሎችን እየወረረች ፣ ድንበሯን እያሰፋች ያለችን ድርጅት ጣረሞት ላይናት ማለት ትርጉሙ አያቦ ( paradox) ሊሆን እንደሚችል ግልጽ ነው፡፡ እውነቱ ግን ይሄንን ይመስላል፡፡
ዶላር ለምን ጨመረ
1. ከመቼውም ግዜ በላይ፣ የህወሀት በዝርፊያ የደለቡ ባለሀብቶች ፣ በየሀገሩ ያላቸውን ንብረት እየሸጡ ወደ ውጭ እየወጡ ነው፡፡ ይሄ የተሸጠ ብርንም በዶላር ለመቀየር በቀረበላቸው ዋጋ ዶላር እየገዙ ነው፡፡
2. አዲሱ መንግስት በይፋ ስልጣን ከመያዙና ካቤኔ ከማቋቋሙ በፊት መንግስትን መገዳደርን ካልቻልን፣ ጉዳያችን ያበቃል ብለው የሰጉት የህወሀት አዋጊዎች በተቻለ መጠን መሳርያ እንዲገባላቸው አባላቶቻቸውን እየተማጸኑ መሆኑ ያደባባይ ሚስጥር ከሆነ ሰንብቷል፡፡ መሳርያ ደግሞ በዶላር እንጂ በብር ስለማይገዛ፣ ያላቸውን ብር ሁሉ ወደ ዶላር ቅየራ ላይ ናቸው፡፡
3. ሀገሪቷን በውጊያ ሳይሆን በኤኮኖሚ ማሸመድመድን ግብ አድርጎ የተነሳው ሌላኛው የህወሀት የሽብር ብርጌድ ፣ ብር እጀግ እየወረደ ስለሚመጣ ፣ ያላችሁን ብር ወደ ዶላር ቀይራችሁ በዶላር ካልያዛችሁ፣ የኢትዮጵያ ባለህብቶች በሙሉ ኪሳራ ውስጥ ትገባላችሁ የሚል ሰፊ ቅስቀሳ እያካሄደ ነው፡፡ በርካታ ባለሀብቶችም በዚሁ የሽብር ዜና በመደንገጥ ብራቸውን ወደ ዶላር ቅየራ ላይ ናቸው፡፡
4. በዚህና መሰል ምክንያት ፣ ዶላር ፍላጎቱ በመጨመሩ፣ ዛሬ ላይ ምንዛሪው 65 ብር ገብቷል፡፡
5. የዶላር የዝርፊያ አቀነባባሪዎች የባንክ ማናጀሮች መሆናቸው ደግሞ ያሳምማል፡፡ ኤል ሲ ለመክፈት በሀጋዊ መንገድ የሄዱ ነጋዴዎች፣ ዶላር የሚያገኙት ለባክንክ ስዎች በድርድር ኮሚሽን ከፍለው መሆኑ ያደባባይ ሀቅ ነው፡፡ ሁሉም ሀላፊዎች በዚህ ነውር ተወቃሽ ባይሆኑም፣ ባንኮች ውስጥ ያለው ሕገ ወጥ የዶላር ሽያጭ አንዱ ምክንያት መሆኑ ግን መጠቀስ አለበት
ችግሩ የት ላይ ነው?
ኢትዮጵያ ዶላር የምታገኝባቸው መንገዶች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ፣ ከኤክስፖርት፣ ከርዳታ ወይ ደግሞ ከሬሚታንስ ወይም ደግሞ ከውጭ ከሚመጣ ኢንቨስትመንት ነው፡፡
በንጽጽር ሲታይ፣ ለመቆጣጣር ያስቸገረውና ፣ ለጥቁር ገብያ ምቹ የሆነው የዶላር ምንጭ ግን ፣ ከውጭ ሀገር ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን የሚላከው ነው፡፡ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ፣ ውጭ ሀገር ያለው ዳያስፖራ፣ ዶላር አላላክ ላይ በሚያሳያው የጥንቃቄ ጉድለት ፣ ሀገር ውስጥ የሚኖረውን ሕዝብ በኑሮ ውድነት እያሰቃየው ነው፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዪት፣ ውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ በዓመት ከአራት እስከ ስምንት ቢሊዮን ዶላር ወደ ሀገሩ ይልካል፡፡ ከዚህ ሀብት ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገባው ሩቡ እንኳን አይሆንም፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ ዶላር የሚጠለፈው በኢትዮጵያ ጠላቶችና ኢትዮጵያን ለማፍረስ በሚፈልጉ አካላት ነው፡፡ ይህን አመቻችቶ የሚሰጠው ደግሞ ዲያስፖራው ነው፡፡ አሁንም ሁሉም ዳያስፖራ ተወቃሽ ባይሆንም፡፡
የዶላር የሌብነት ሰንሰለት
በሚደንቅ ሁኔታ፣ የዶላር በብር ትልቅ ንግድ የሚካሄደው ዱባይና ቻይና ላይ ነው፡፡ የዶላር ብር ምንዛሬ ከሚወሰንባቸው ሀገራት አንዷ ዱባይ ናት፡፡
ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ብትጠይቁ፣ እቃ የሚያስመጣው ከባንክ በሚያገኘው ዶላር ብቻ አይደለም፡፡ የባንኮች የዶላር አሰጣጥ ግልጽ ያልሆነና ከፍተኛ ሙስና ያለበት በመሆኑ፣ በርካታ ነጋዴዎች ዶላር በብር ለመግዛት የሚሄዱት ዱባይና ቻይና ነው፡፡ ዱባይ ላይ ይሄንን የሚሰራ ትልቅ ቢሮ አለ፡፡
ሂደቱ ይሄንን ይመስላል
ህወሀት ፣ ስልጣን ላይ እያለች ህልሟ፣ ኢትዮጵያን መቶ አመት መግዛት ነበር፡፡ ለዛም ይሆን ዘንድ፣ ብዙ ጀሌዎቿን በውጭ ሀገር አሰማርታለች፡፡ አንዱና ዋነኛ የትኩረት ኢላማቸው የነበረው፣ የዶላር ንግድ ነው፡፡
አሜሪካ ውስጥ፣ ዶላር የሚያስተላልፉ ሱቆችን ብትመለከቱ፣ አብዛኞቹ በህወሀት ሰዎች የተያዙ ናቸው፡፡ እነዚህ የሱቅ ባለቤቶች ጀርባ ታሪካቸውን ስትመረምሩ ደግሞ፣ ከስደተኛ ካምፕ ኤርትራዊ ነን ብለው የመጡና፣ በሱዳን በኩል አሜሪካ በገቡ የህወህት ጀሌዎች የሚዘወሩ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ስቴት ያሉትን ብር ላኪዎች ተመራመሩና “ ለምን “ ብለን እንጠይቅ
ደድቢቶች፣ አሜሪካን በተዋወቁ ማግስት የመጀመርያ ስራቸው ፣ የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ መክፈትና፣ “ ዶላር እንልካለን “ የሚል ማስታወቂያ እዛው ሱቅ ውስጥ መለጠፍ ነው፡፡ የሸቀጥ ሱቋ ሽፋን ናት፡፡ ዋናው ስራ የዶላር ንግዱ ነው፡፡
ዳያስፖራ ፣ ለፍቶ ያገኛትን ዶላር የተሻለ ምንዛሬ አገኘሁ ብሎ በነዚህ ሱቆች አማካኝነት ይልካል፡፡ ብዙው ሰው፣ የጥቁር ገበያው ምንዛሬ ትልቅ በመሆኑ፣ ብዙው ዳያስፖራ በዚህ ግዜያዊ ያልተገባ ጥቅም ተታሎ ይልካል፡፡ መረዳዳት ባሕላችን ስለሆነ፣ እጅግ ብዙ ዳያስፖራ ብለዘመድ ላዝማዱ ይልካል፡፡ ሀገር ውስጥ በዝርፊያ የተሰበሰበው ብር እየወጣ ፣ ለተላከላቸው ወገኖች በየባንክ አካውንታቸው ይገባል፡፡
ይሄ የተሰበሰበ ዶላር ነው እንግዲህ ዱባይ ላይ በጨረታ የሚሸጠው፡፡ ኢትዩጵያውያን ፣ መረዳዳት ባህላችን ስለሆነ፣ በተለይም ደግሞ በበዓል ወቅት ከፍተኛ ገንዘብ ስለሚላክ፣ እነዚህ የጥቁር ገበያ ጌቶች፣ የተጠየቁትን ያህል ዶላር ለኢትዮጵያ ነጋዴ ለማቅረብ አይቸገሩም፡፡የኢትዮጵያ ነጋዴ ደግሞ፣ ወረፋ ጠብቆ ኤልሲን መጠበቅ ስለሚረዝምበት፣ አማራጭ አድርጎ የሚወስደው እነዚህን ድርጅቶች ነው፡፡ ሌቦቹም፣ ከፈለጉ፣ ዶላርን ዋጋውን እጅግ አንረው፣ የሀገር ውስጡን ኑሮ ሰማይ ማድረስ ይችላሉ፡፡ ዶላር ሲጨምር፣ የሸቀጥ ዋጋም አብሮ ይጨምራል፡፡
ባለፉት ሶስት ዓመታት የታየው የዶላር መናርም አንዱና ትልቁ ምንጭ ይሄ ውጊያ ነው፡፡ ህወሀት ጦር ሰብቃ ኢትዮጵያን በወታደር እየወጋች እንዳለችው ሁሉ፣ በኤኮኖሚውም ዶላርን ተንተርሳ፣ ከላይ በጠቀስኩት መንገድ ኢትዮጵያን እየወጋች ነው፡፡ የሚያሳዝነው ግን ብዙዎቻችን ዲያስፖራዎች ሳናውቀው ለሀገራችን መፍረስ ተባባሪ መሆናችን ነው፡፡
ከውጭ የሚላከውን ዶላር፣ ህወሀት ኪስ ውስጥ ማስገባቱን ትተን በቀጥታ በህጋዊው መንገድ መላክ ብንችል፤ ለኑሮ ውድነት መቀነስ አስተዋጾ ከማድረጋችን በላይ፣ የህወሀትንም ክንፍ እንሰብረው ነበር፡፡
የመንግስት ያለህ፣ የሕዝብ ያለህ
1. Currency Transaction Report
ጥቁር ገበያ parallel market ነው ብለን የምንተወው ጉዳይ አይደለም፡፡ የሀገርን ማሽመድመጃ ድምጽ አልባ መሳርያ ነው፡፡ ይህን ጥቁር ገበያ የመዋጋት ተቀዳሚ ሥራ የመንግስት ነው፡፡ የጥቁር ገበያ ጌቶች ፣ ብሩን ኢትዮጵያ የሚያደርሱት፣ በባንኮች አማካኝነት ነው፡፡ እንዴት መንግስት ይሄንን መቆጣጠር ያቅተዋል? በየቀኑ ከግለሰብም ሆነ ከቢዝነስ አካውንቶች የሚወጡና የሚላኩ ብሮችን በቀላሉ ትራክ ማድረግ ይቻላል፡፡ ግለሰብም ከሆነ ማሕበራዊ ዋስትና ቁጥርን(Social security number) ፣ ድርጅትም ከሆነ ታክስ አይዲ ቁጥርን ( Tx ID Number) በመጠቀም በካሽ የሚወጡና የሚገቡ ትራንዛክሽኖችን ማወቅ ቀላል ነው፡፡ ለምሳሌ አሜሪካ ውስጥ ፣ ማንም ሰው በቀን ከአስር ሺህ ብር በላይ በካሽ የሚያወጣ ወይም የሚልክ ከሆነ፣ ባንኮች ያንን ግለሰብ ወይም ድርጅት ለመንግስት የደህንነት ተቋም የማሳወቅ ግዴት አለባቸው፡፡ ይህን ሲያሳውቁ፣ ገንዘቡን ገቢ ወይም ወጭ ያደረገው ማን እንደሆነ፣ ቤኒፊሻል ኦውነሩ( beneficial Owner) ማን እንደሆነ ዝርዝር ማቅረብ ግዲታ አለባቸው፡፡ ይሄንን ተላልፎ የተገኘ ባንክ ግን ላይሰንሱን እስከ መሰረዝ( Revoking License and business operation) የሚደረስ ቅጣት ይጣልበታል፡፡ ኢትዮጵያ ይሄንን አሰራራ መተግበር ለምን አቃተ?
2. CIP/ CDD/ KYC/KPC
ሌላኛው ዓለም በሙሉ የሚጠቀምበት አሰራር፣ Due diligence, Know your Customer ወዘተ ናቸው፡፡ አሜሪካ ውስጥ ያሉ ባንኮች በሙሉ ደምበኞቻቸውን የማወ, ለደህንነት አካላት የማሳወቅና የተጠራጠሩትን ደምበኛ ሪፖርት የማድረግ ግዴታና መብት አለባቸው፡፡ የባንኮች ስራ ገንዘብ መቀበልና ማበደር ብቻ አይደለም፡፡ ያንድ ሀገር ኤኮኖሚ the most liquid asset ገንዘብ ነው፡፡ በሀገራት ደረጃም ከፍተኛ ውጊያ ያለው ገንዘብ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ባንኮች የሀገርን የገንዘብ ደህንነት የመጠቅ ግዴታ አለባቸው፡፡ አካውንት ካለመክፈት ጀምሮ እስከ የደምበኛን የገንዘብ ምንጭ ማውቅ ድረስ ያለውን ያጠቃልላል፡፡ እንዴት ነው ፣ ባንኮች ከውጭ የሚላክ ብርን በየግለሰብ አካውንት የሚልኩት ሰዎች ማወቅ የሚያቅታቸው? በየትኛውም ሀገር የባንክ ግዴታ ነው፡፡ ከውጭ የሚላኩ ብሮችን በየከስተመሩ አካውንት የሚልኩ ሰዎችን አነፍነፈው እንዲይዙ ለባንኮች መመርያ መውረድ አለበት
3. Asset control/ List based and company-based sanction
አሜሪካ፣ በየዓመቱ የምታወጣው የንግድ ግንኙነት እቀባ ሊስት አለ፡፡ Office of Foreign Asset Control ( OFAC) የአሜሪካ ባንኮች ገንዘብ መላላክ የማይችሉባቸውን ሀገራት ያሳውቃል፡፡ ተላልፎ የተገኘ፣ ቅጣቱ እጅግ ከባድና በሀገር ክህደት የሚያስጠይቅ ስለሆነ። ባንኮችን የሚያንቀጠቅጣቸው ኦዲት ይሄ ነው፡፡ አሜሪካ በግለሰብና በካምፓኒ ደረጃ የግ ንኙነት ማዕቀብና ክልከላ ያደረገችባቸውን ግለሰቦችና ድርጅቶች በየግዜው ለባንኮች ታሳውቃለች፡፡ ይሄን ተላልፎ የተገኘ ባንክ ፣ ግጭቱ ከሀገሪቱ ደህንነት ጋር ስለሆነ መዘዙ ከባድ ነው፡፡ አሜሪካ ብቻ ሳትሆን ዓለም የሚሰራበት አሰራር ነው፡፡
ኢትዮጵያ ፣ በሀገር ደረጃ የዶላር እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ልታግድ የሚገባት ካምፓኒዎች አሉ፡፡ አሜሪካ ውስጥ ዶላር የሚልኩት ካምፓኒዎች፣ ሱቆችና ግለሰቦች ይታወቃሉ፡፡ ከነዚህ ድርጅቶች ጋር ንክኪ ያላቸውን ግለሰቦችንም ሆነ ድርጅቶች በስም ጠርቶ የንግድ እቀባ ማቀጅ መብቱ ነው፡፡ ( List based sanction)
ይሄ ዱባይ እና ቻይና ያሉትን ድርጅቶች ይጨምራል፡፡ ይሄን ተላልፎ በነሱ የሚላከውን ፣ ወይም ከነሱ ጋር ንክኪ ባላቸው ሰዎች የሚተላለፈውን ገንዘብ (freeze) ማድረግ ይቻላል፡፡መንግስት ይሄን ለማድረግ እጁን ምን ያዘው?
4. ግለሰባዊ ተጠያቂነት
መንግስት በጥቁር ገበያ(Black Market) ገንዘብ የሚልኩ ኢትዮጵያውያንን ፣ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከል ይችላል፡፡ በጥቁር ገበያ ገንዘብ መላክ መብት አይደለም፡፡ It is money laundering. It is terrorist financing. It is illegal ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ደግሞ ወንጀል ነው፡፡ ከውጭ ገንዘብ የሚላክላቸውን ቤተሰቦች አካውንት በማነፍነፍ፣ ላኪዎቹን ፓስፖርት ባለማደስ፣ ቢጫ ወረቀት ባለመስጠት፣ ተቀባዮቹ ጋር ከሚደርሰውም ብር በመቁረጥ ፣ ጥቁር ገበያን መከላከል ሕጋዊ ሥራ ነው፡፡ ምክንያቱም፣ በጥቁር ገበያ ምንዛሪ ፣ የሀገር ኤኮኖሚ አደጋ ውስጥ እየገባ ነው፡፡ ኑሮ በከፍተኛ ደረጃ እየናረ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሀገር ላይ የሚሰራ ከባድ ወንጀል ነው፡፡
5. አስመጭዎችን መቅጣት
ማንም ነጋዴ ዶላርን ማግኘት ያለበት፣ በሕጋዊ መልኩ ከባንኮች ነው፡፡ በሌላ ካልታወቀ ምንጭ ዶላር አግኝተው ሸቀጥ የሚያስገቡ ነጋዴዎችን፣ ለመቀጣጫ ንብረታቸውን መውረስ፣ ኤልሲአቸውን መከልከል አንዱ መፍትሄ ነው፡፡ በመቶ ሚሊዪን የሚቆጠር ሕዝብ በኑሮ ውድነት ከሚሰቃይ፣ ጥቂት ሕገ ወጥ ነጋዴዎችን መቅጣት ጽድቅ ነው፡፡
ውጭሀገር ላለን ወገኖች ሁሉ
ለንትሽ ብር ትርፍ ብለን ለምን ሀገራችንን እንገላለን? ለምን ያንን ድሃ ሕዝባችንን በኑሮ ውድነት እንቀጣዋለን? በሕገ ወጥ መልኩ የምንልከው ገንዘብ አንዱ የኑሮ ውድነቱ ምክንያት ስለሆነ፣ እባካችሁ ገንዘባችንን በሕጋዊ ድርጅቶች ብቻ እንላክ
መንግስት ሆይ፣
በኑሮ ውድነት የተማረረ ሕዝብ ማዕበል ሆኖ ወጥቶ የሚበላህ አንተኑ ነው፡፡ ያ ክፉ ቀን እንዲመጣ ነው፣ ሰዎቹ ተግተው ዶላር ላይ እየሰሩ ያሉት፡፡ ለራስህ ስልት እውቅበት
ተጨማሪ ያንብቡ:  የአሸባሪውን ቡድን አከርካሪ የሰበረው መከላከያ ሃይል የትኛውንም ጠላት መደምሰስ የሚችልበት አቅም ገንብቷል- ጀነራል አበባው ታደሰ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share