አሸባሪው ሕወሃት እያደረገ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳሳሰባቸው ሳማንታ ፓወር ተናገሩ

230843668 10227829743308683 8546043337451337853 n
230843668 10227829743308683 8546043337451337853 n
በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የአሜሪካው ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩ ኤስ ኤድ) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ ዛሬ ምሽት ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም፤ ቀደም ብለው በትግራይ ክልል ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍ በተመለከተ ከሠላም ሚኒስትርና ከሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ጋር ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
በክልሉ የሚቀርበው የሰብዓዊ ድጋፍ አሁንም መፋጠን እንዳለበት ጠቁመው በዚህም ከመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ጋር መግባበት ላይ መድረሳቸውን ጠቁመዋል።
ይሁንና በዚህ የሰብዓዊ ቀውስ ወቅት አሸባሪው ሕወሃት ወደ አጎራባች ክልሎች የሚያካሂደው ወታደራዊ እንቅስቃሴ አንዳሳሰባቸው ነው ሃላፊዋ ሳማንታ ፓውር የተናገሩት።
በዚህ ሕወሃት በሚያደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴ በአማራ ክልል 150 ሺህ ሰዎች በአፋር ደግሞ 76 ሺህ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን እንዳረጋገጡ ኢዜአ ዘግቧል ።
በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የአሜሪካው ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩ ኤስ ኤድ) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር ላለፉት አራት ቀናት በሱዳን ጉብኝት አድርገዋል።
አሸባሪው የህወሃት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ በተግባር በመንቀሳቀስ በአገር መከላከከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈፀሙን ጨምሮ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ይታወቃል።
EBC
ተጨማሪ ያንብቡ:  We're not a one to saddle up and run, Bonanza

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share