ሊተገበሩ የማይችሉና ህወሓት በጦርነቱ ለመቀጠል ፍላጎት እንዳለዉ አመላካች መሆናቸውን ምሁራን አመለከቱ

የትግራይ መከላከያ ሠራዊት የተባለዉ ኃይል ለተኩስ አቁም ሰምምነት አቀረበቻቸው ከተባለዉ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል እንዳንዶቹ ሊተገበሩ የማይችሉና ህወሓት በጦርነቱ ለመቀጠል ፍላጎት እንዳለዉ አመላካች መሆናቸውን ምሁራን አመለከቱ፡፡

የትግራይ መከላከያ ሠራዊት የተባለዉ ኃይል ለተኩስ አቁም ሰምምነት አቀረበቻቸው ከተባለዉ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል እንዳንዶቹ ሊተገበሩ የማይችሉና ህወሓት በጦርነቱ ለመቀጠል ፍላጎት እንዳለዉ አመላካች መሆናቸውን ምሁራን አመለከቱ፡፡ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የአማራ ማንነት ይጠየቅባቸው የነበሩ አካባቢዎች አማራነታቸው የተረጋገጠና ፋይሉ የተዘጋ ጉዳይ ነው ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

ከትግራይ መንግስት የተሰጠ በተባለው መግለጫ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሃት) ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ሰባት ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጧል፡፡ ከቅድመ ሁኔታዎች መካከል አንዱ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አሁን ከያዛቸው አካባቢዎች ወጥቶ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ወደነበረበት ቦታ ይመለስ የሚል ነው፡፡

ይህን ቅድመሁኔታ በተመለከተ አስተያየታቸውን የሰጡን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌደራሊዝምና ሰብአዊ መብት ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ፣ ቅድመ ሁኔታው የማይተገበር ነው ይላሉ፡፡

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምህር ቻላቸው ታረቀኝም የዶ/ር ሲሳይን ሀሳብ ይጋራሉ፡፡

ሌለኛው ቅድመ ሁኔታ አሁን ስልጣን ላይ  ያሉት የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች በጥፋታቸው ልክ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከቀረቡ መሆኑን ያትታል፡፡

ዶ/ር ሲሳይ ይህ አስቂኝ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰትተዋል፡፡

እንደ አቶ ቻላቸው ታረቀኝ ጉዳዩ የማይሳካ እንደሆነ ጠቁመው ፍርድ ቤት መሄድ ካለበትስ ማነው መሄድ ያለበት? ሲሉ ጠይቀዋል::

ህወሓት የመደራደር ፍላጎት የሌለው ስለመሆኑ የማይተገበር ቅድመ ሁኔታ ማቅረቡ አንዱ ማሳያ እንደሆነ አቶ ቻላቸው አብራርተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Sport: በኖርዌይ ሊግ አመርቂ ውጤት እያሳየ ያለው አሚን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ይጫወት ይሆን?

የሰብዓዊ እርዳታና መሰረታዊ አገልግሎት ተቋማት በአስቸኳ ስራ መጀመር እንዳለባቸው የጠቆሙት ምሁራኑ፣ ለስራው የሚመደቡ ባለሙያዎች ደህንነት ግን ሌላ ፈተና እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገርን ጠቅሶ እንደዘገበው የወልቃይት፤ የጠገዴ፤ የጠለምትና የራያ አማራነት የተረጋገጠና የተዘጋ ፋይል  ነው፡፡

ዓለምነው መኮንን

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ/ DW

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.