ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሶስት አገራት ላይ የጉዞ እገዳ ጣለች

ዴልታ የተሰኘው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በ85 አገራት ተሰራጭቷል

ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሶስት አገራት ተጓዦች ላይ የጉዞ እገዳ ጣለች።

ሳውዲ አዳዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች መብዛታቸውን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ቬትናም እና ከተባበሩት አረብ ኢምሬት የሚነሱ መንገደኞች ወደ አገሯ እንዳይገቡ መወሰኗን ገልጻለች።

አገሪቱ ከዚህ በተጨማሪም ዜጎቿ ወደ ሶስቱ አገራት እንዳይበሩም የከለከለች ሲሆን እገዳው ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚል መተላለፉ ተገልጿል።

የበረራ እገዳው ከነገ ጀምሮ የሚተገበር ሲሆን የሳውዲ ዜግነት ያላቸው ዜጎች እገዳው ከተላለፈባቸው አገራት የሚመጡ መንገደኞች ግን ለ14 ቀን በለይቶ ማቆያ ከቆዩ በኋላ እና ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ ወደ መኖሪያ ቤታቸው መግባት ይችላሉ ተብሏል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ዴልታ የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ከታየ በኋላ አሁን ላይ በ85 አገራት መሰራጨቱን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያስረዳል።

በተያያዘ ዜና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩኤኢ) ከአዳዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች ጋር በተያያዘ ዜጎቿ ወደ 14 የአፍሪካ ሃገራት እና የደቡብ እስያ ሃገራት እንዳይጓዙ ከልክላለች፡፡

ዩኤኢ ዜጎቿ ወደ ሃገራቱ መጓዝ ብቻም ሳይሆን ከሃገራቱ እንዳይገቡም ነው የከለከለችው፡፡

በእገዳው ከታካተቱ ሃገራት ስምንቱ አፍሪካዊ ናቸው፡፡

ደቡብ አፍሪካ፣ ናሚቢያ፣ ኡጋንዳ፣ ዲ.አር ኮንጎ፣ዛምቢያ፣ ሴራሊዮን፣ ላይቤሪያ እና ናይጄሪያ ይገኙበታል፡፡

ህንድ፣ ፓኪስታን፣ ባንግላዴሽ፣ ኔፓል፣ ስሪ ላንካ እና ቬትናም ደግሞ እገዳው ከተጣለባቸው የደቡብ እስያ ሃገራት ናቸው፡፡

እገዳው በህንድ፣ ፓኪስታን፣ ባንግላዴሽ እና ስሪ ላንካ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ሃምሌ 21 ድረስ እንደሚቆይ ዘ ናሽናል ዘግቧል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  መስታወት-ቀውሱ እንዴት ይቀልበስ?-የዶ/ር ዮናስ ብሩ ማኒፌስቶ Mengizem media

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share