የአማራ ክልል ልዩ ሀይል እና የኤርትራ ሰራዊት ድንበራቸውን ዘግተው ፤ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ቆመዋል !

፦ ሁሉም ባንኳች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም ፤ እንደሚባለውም መንግስት ብሮችን ቀድሞ አሽሽቶዋል
፦ ህዝቡም ይህን በመስማቱ ባንኮች ላይ እያንዣበበ ነው ።
፦ሁሉም የሸቀጥ እቃዎች በሚባል ደረጃ ቀድመው እጃቸው ላይ ብር በነበራቸው ሰዎች ተገዝተዋል ፣ የተቀሩትንም ሁሉም ነጋዴዎች ሸሽገዋቸዋል ።
፦ የእርዳታ ምግቦች ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ተዘርፈዋል
፦ የአማራ ክልል ልዩ ሀይል እና የኤርትራ ሰራዊት ድንበራቸውን ዘግተው ፤ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ቆመዋል
፦ መሃል ትግራይ ላይ የነበረው የመንግስት ጦር ከየከተማው እየወጣ አመቺ የሚለው ቦታ ላይ ሰፍሮዋል
፦ የየብስና እና የአየር በረራ ተቋርጦዋል
፦ መብራት ፣ ውሃ ፣ ነዳጅ ሁሉም አገልግሎት ቁመዋል ።

በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር የተሰጠ መግለጫ
~
በኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት እና በአምባገነኑ ህወሃት መካከል የነበረው አለመግባባት ወደ ጦርነት አምርቶ ጦርነቱ ከሰባት ወራት በላይ እንደቆየ ይታወቃል።
በጦርነቱ ያልታጠቁ ንፁኀን ህዝቦችን ጨምሮ በርካታ ወገኖች ለአካል ጉዳትና ለሞት ሰለባ ሁነዋል፤ የአገር ሀብትና ንብረትም ወድሟል።እንደ አማራ ሕዝብ በዚህ ጦርነት ያገኘነው ትርፍ በህወሃት በተፈፀመ መንግስታዊ ወረራ ተወስደው የነበሩ ርስቶቻችንን በአማራ ልዩ ሀይል፣ፋኖ እና ሚሊሻ ከፍተኛ መስዕዋትነት ማስመለሳችን ነው።
በ21/10/2013 ዓ/ም ከሰዓት ጀምሮ የተኩስ አቁም ስምምነት ተጠየቀ እና የመከላከያ ሰራዊት ቦታውን ለቆ ወጣ ፤ ህወሃት መቀሌን ተቆጣጠረ የሚሉ ዜናዎች ተሰምተዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ እንደ አማራ ነገ ምን ሊመጣ እንደሚችል አርቆ ማየት፣ ዙሪያ ገባውን በተጠንቀቅ መጠበቅ እና በሁሉም መስክ አፀፋ ለመስጠት መዘጋጀት ያስፈልጋል። የአማራ አንቂዎች የጦርነቱ አሸናፊዎች ነን ከአላስፈላጊ ትንተናዎች እንቆጠብ። ከዚህ በፊት ከነበረው የባሰ ችግር ሊመጣ ይችላል። ስለዚህ ህዝባችን በአንድነት ቁሞ አካባቢውን በተጠንቀቅ እንዲጠብቅ በያለንበት መሬት ላይ ስራ እንስራ።
መታወቅ ያለበት የማዕከላዊ መንግስት ከህወሃት ጋር ቢደራደርም ባይደራደርም እኛ አማራዎች ግን ርስቶቻችንን በማስመለስ ጦርነቱን አሸንፈናል። ከጦርነቱም አትርፈናል። በጦርነቱ ያስመለስናቸውን ግዛቶችን ለመንጠቅ የሚሞክር ማንኛውንም አይነት እንቅስቃሴ ከተፈጠረ ተፈጥሯዊ ራስን የመጠበቅ መብታችንን ተጠቅመን የሚመጣውን ሀይል ሁሉ መመከት እንዳለብን ለመላው የአማራ ህዝብ፣ የአማራ ልዩ ሀይል፣ ፋኖ እና የአማራ ሚሊሻ ማሳሰብ እንወዳለን።
ተጨማሪ ያንብቡ:  የግብጹ ባንዲራና የጥላቻው መዝሙር (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

1 Comment

  1. የአማራ ህዝብ በእግዚአብሄር ላይና በራሱ ጠንካራ ክንድ መብቱን ያሰከብራል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share