“በእኛ እና በመላ የአማራ ህዝብ መቃብር ላይ ካልሆነ ዳግም “ተከዜን” የሚሻገር አንዳች የትህነግ አሻባሪ ቡድን አይኖርም!” ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ

በኢትዮጵያ ህዝብ ወኪሎች ፊት ቀርቦ አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀ ቡድን ጋር መንግስታዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረግ ከአሸባሪዎች አገር የማፍረስ ዓላማ እና ፍላጎት አይተናነስም። ከአሁን በሗላ በአማራ ህዝብ የህልውና ላይ ሒሳብ ለማወራረድ የሚሞክር መንግሥታዊም ይሁን አሸባር ቡድን ካለ ራሱ ይዋረዳል።
በመንግስት በኩል በቅርቡ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የትህነግ ቡድን በአገር ላይ በፈጸመው ግፍና ክደት ምክንያት የአገር መከላከያ ሰራዊት እና የአማራ ልዩ ሐይል በወሰዱት ኦፕሬሽን ከአማራ ታሪካዊ ግዛት ከሆኑት ወልቃይት ጠገዴ ፣ ጠለምትና ራያ ማጽዳት ተችሏል። በተወደሰደው እርምጃም በርካታ ጉምቱ አባላቱ ድፋቅ ተመተዋል። ላይመለሱ አሸልበዋል።
በተለይም አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሀገር ላይ ከፈጸመው ግፍ በተለየ ሁኔታ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ አማራ ህዝብ ላይ ለዘመናት ሲፈጽም የኖረው ግፍና በደል በዚህ መለስ የሚባል አይደለም። ታሪክ ይቅር የማይለው ሰባዊና ቁሳዊ በደል ፈጽሟል። ጋራ ሸንተረሮች ሁሉ ሰባዊ አጽም እንዲከማችባቸው አድርጓል።
የአማራ ህዝብ ለዘመናት ተጭኖበት ከነበረው መከራና ግፍ ለመላቀቅ ተመን የለሽ መስዕዋትነት ከፍሏል። ለነጻነቱ ሲልም በከፈልነው ዋጋ ላይ ሒሳብ ለማወራረድ የሚሞክር አካል ካለ ጠባችን ከአሸባሪ የትህነግ ቡድን ጋር ብቻ ሳይሆን ስምምነት ከፈጸመው አካል ጋር ጭምር ነው።
ምክኒያቱም በኢትዮጵያ ህዝብ ወኪሎች ፊት ቀርቦ አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀ ቡድን ጋር መንግስታዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረግ ከአሸባሪዎች አገር የማፍረስ ዓላማ እና ፍላጎት አይተናነስም!
የአማራ ህዝብ መረዳት ያለበት ነባራዊ ሀቅና እውነታ ከራሱ ታሪካዊ ግዛት ከሆኑት ወልቃይት ጠገዴ ፣ ጠለምትና ራያ ተከዜን ተሻግሮ የሚመጣ ቡድን በእኛ በመላው የአማራ ህዝብ መቃብር ላይ መሆኑን ነው።
ለአማራ ህዝብ ነጻነት ሲባል ሚሊዮን አማራዎች ተገለዋል ፣ ሚሊዮኖች ደግሞ ተፈናቅለዋል። በሚሊዮን ወገኖቹ መስዋትነት ነፃነቱን ያረጋገጠው የወልቃይት ጠገዴ ፣ ጠለምትና ራያ አማራ ህዝብ ህልውና በጋራ ትግላችን ነጻነቱን አውጀዋል። በማንም የግልና የቡድን ፍላጎት ሳይሆን ለዘመናት ተነጥቆ ታፍኖና ተጨቁኖ ከኖረበት ግፍና በደል ተላቆ አማራነቱን በአደባባይ አውጇል። የማንንም ይሁንታ አይጠይቅም ፤ አያስፈቅድም።
በእኛ እና በመላ የአማራ ህዝብ መቃብር ላይ ካልሆነ ዳግም ከእንደዚህ ቀደሙ ሁሉ “ተከዜን” የሚሻገር አንዳች የትህነግ አሻባሪ ቡድን አይኖርም። ሊኖርም አይችልም።
.
.
ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ
በአማራ ክልል የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ
ተጨማሪ ያንብቡ:  በእናትና በአባቱ አስከሬን መካከል ለተገኘው የሁለት ዓመት ህጻንና ወንድሞቹ የተለያዩ ወገኖች ድጋፍ እያደረጉላችው ነው

1 Comment

  1. ክብር ህይወታቸውን ለ ሰዉ አርበኞቻችን ይሁን። አሁንም ህይወታቸውን ሊሰዉ ለተዘጋጁት።

    አማራ በ መላ ኢትዮጵያ የሚገደለው እና የሚፈናቀለው አንዳች ወንጀል ሠርቶ ሳይሆን ተደራጅቶ እራሱን ስለ አልተከላከለ ነው። በ አንድነት ቆሞ እራሱን እስከ አላስከበረ ድረስ ዕልቂቱ እንደሚቀጥል ምንም ጥርጣሬ የለኝም ምክንያቱም መንግሥት ተብዬው ከ አሁን በፊት እንደ አስመሰከረው ምንም ሲያደርግ አልታየም። ስለዚህ ህግ በሌለበት አገር ህልውና የሚከበረው በራሱ በ ተጠቂው ህዝብ ነው። ይህ ነው የ ተፈጥሮ ህግ።
    አማራ ብዙ አደጋዎች ከፊቱ ተደቅነውብውታል። ሱዳን፣ ትግሬዎች እና ኦሮሞዎች አማራን አጥፍተው መሬቱን ለ መቀራመት ከፍተኛ ምኞት አላቸው። ስለዚህ አማራ ይህን ተረድቶ የሚመጣውን ለ መመከት መዘጋጀት አለበት።
    የ ፍትህ አምላክ ይርዳን።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share