ብታምኑም ባታምኑም አቢይ አህመድ የተላከው ለቅጣት ነው! – ምሕረት ዘገዬ

አሁን ከምሽቱ አምስት ሰዓት ነው – ውጤቱ ለታወቀው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ልንደርስ ሦስት ሌሊቶች የቀሩት የዓርብ ምሽት፡፡ ወደዚህ የንዴት ማስተንፈሻ ጽሑፍ የገባሁት ባልተቤቴ አንድ ፎርሜሽን ነግራኝ ነው – በጣም አናዳጅ ፈርሜሽን ወይም መረጃ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ከኢዮብ የበለጠ ትግስትና ከብረት የጠነከረ ጽናት ባለቤት ነው፤ ከባቢሎን የከፋ መለያየት ውስጥ የሚገኝ ሕዝብም ጭምር፡፡ የግብጽ ሴቶች ፓስቲ አሥር ሣንቲም ጨመረ ብለው ማንከሽከሻቸውን ይዘው አደባባይ በመውጣት መንግሥት ይጥላሉ እኛ አንድ ሊትር የምግብ ዘይት 130 ብር ስንገዛ ፊታችን በደስታ የተዋጠ መስሎ ከሱቆች እንወጣለን – በአሽሙር ሣቅ፡፡ የምንገርም ሕዝብና የሚገርም መንግሥት ነው ያለን፡፡ ቅጣትም እኮ ዓይነትና መልክ አለው፡፡ የኛ ይለያል፡፡

“ይሄውልህ ዛሬ ገበያ ወጥቼ…” ስትል ወጓን ጀመረች ክብርት ባለቤቴ፡፡ እኔም ይህ ዓይነቱን ነገር ለምጄዋለሁና ምን ልታረዳኝ ይሆን ዛሬ ደግሞ በሚል በጥሞና አዳምጣት ጀመር፤ ዘመኑ መቼስ በየትኛውም አቅጣጫ የመርዶ እንጂ የብሥራት አልሆነም፡፡ “ይሄውልህ ዛሬ ገበያ ወጥቼ ዛላ በርበሬ ብጠይቅ አንዱ ኪሎ 360 ብር አሉኝና ሳልገዛ መጣሁ፡፡ አንደኛ ደረጃ 360፣ ሁለተኛ ደረጃ 340፣ የመጨረሻውና እዚህ ግባ የማይባለው ምራጩ ደግሞ 300 ብር፡፡…” ስትለኝ ክው ነው ያልኩላችሁ – ጠላታችሁ ክው ይበልና፡፡

ኑሮን ተዋት፡፡ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ተደርባ ከነሱ ባልተናነሰ ሁኔታ እያሽቃነጠችብን ናት፡፡ ብል(ጽ)ግና ከመጣ ወዲህ የኑሮ ውድነቱ ሆን ተብሎ በሚመስል አኳኋን ሽቅብ እየተሽቀነጠረ ነው፡፡ አቢይ አህመድ ለቅጣት እንደመምጣቱ እኛ እህል እንቅመስ መርዝ እንጠጣ፣ ትቢያ ላይ እንረፍ ጉድጓድ ውስጥ እንተኛ … ጉዳዩ አይደለም፡፡ ይራበን ይጥማን ፣ እንሙት እንዳን የርሱ ጣጣ አይደለም – በጭራሽ አያሳስበውም፡፡ አንዳንዴ ሳስበው የሚያስተዳድረውን ሕዝብ የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ ምናልባትም ራሱን የአንደኛው የአውሮፓ ሀገር መሪ አድርጎ ሳይቆጥር አልቀረም፡፡ እኛ በርሱ ወታደሮች አንገታችን እየተቀላ እርሱ የሚገኘው አትክልት ሲተክልና መናፈሻ ሲያስጌጥ ነው፡፡ ይህ ሰው ዘረመሉ(ጂኑ) መመርመር አለበት፡፡ በደስታ የሚያለቅስ፣ በሀዘን የሚስቅ ዓይነት ግራ አጋቢ ስብዕና ያለው ነው፡፡ የሱ ዋነኛ ጭንቀት ያቺ ጦሰኛ እናቱ በሰባት ዓመቱ የነገረችው የሰባተኛ ንጉሥነት ትንቢት ናት፡፡ በህልሙም በእውኑም፣ ቆሞም ተኝቶም የሚያቃዠው የወንበሩ ጉዳይ እንጂ ሚሊዮን አማራ ታረደ፣ ሚሊዮን ዜጋ ተሰደደ፣ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ከመኖሪያው፣ ከእርሻውና ከንግዱ ተፈናቀለ ጉዳዩ አይደለም፡፡ በዚህ ሁሉ ጩኸትና ትርምስ መሀል ግና ቤተ መንግሥት ውስጥ እንዴት እንቅልፍ ይዞት እንደሚያድር ግርም ይለኛል፡፡ በዚህ ረገድ ታድሏል እላለሁ፤ እኔ ብሆን በጭንቀት እፈነዳ ነበር – ለነገሩ ለመፈንዳትም እኮ ሰው መሆንን ይጠይቃል፡፡ መላ ትኩረቱ እንደምንም አጭበርብሮ ይቺን ምርጫ እማለፉና ሥልጣኑን እመጠቅለሉ ላይ ነው፡፡ መከራ ፍዳውን የሚበላው ለዚያቺው ሥልጣን ነው፡፡ ብቻ ከጨለማው ንጉሥ የተሰጠውን ተልእኮ በሁለንተናዊ ስኬት እየተወጣ ነው፡፡ ይሉኝታ ብሎ ነገርማ በጭራሽ አልፈጠረበትም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ: አሁንስ ተስፋሽ እግዚአብሔር አይደለምን? ዶ/ር ዘለዓለም እሸቴ ይመር

እንግዲህ ልብ አድርጉ፤ በአንድ ሽህና ሁለት ሽህ የወር ደመወዝ የአራትና አምስት ብር ዕቃ አራትና አምስት መቶ ብር ተገዝቶ እንዴት ሊኖር ነው? የሥጋ ነገርማ አይነሣ፡፡ እንደሚባለው ከሆነ አንድ ኪሎ ሥጋ ከ800 እስከ 1000 ብር ደርሷል አሉ፡፡ ጥቂት ነጋዴዎችና ጥቂት ባለሥልጣኖች ነፍሰ ሥጋችንን የፊጥኝ አስረው እየተጫወቱብን ነው፡፡ ይህችን ሀገር ድራሹዋን እያጠፋ የሚገኘው አንዱና ዋናው ነገር ደግሞ ሙስና መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዘረኝነቱንና ተረኝነቱን ተታኮ የሚካሄደው ሙስና አሁን አሁን እስትንፋሳችንን ፀጥ ሊያደርግ ምንም አልቀረው፡፡ የትም ሂድ፣ የትም ግባ ጉዳይህ የሚሳካልህ በእጅህ ሄደህ እንጂ በእግርህ ከሆነ ከዘቦች አታልፍም፡፡ የሞቱት ተሻሉ፡፡ የሞቱ በለጡን፡፡ መተከልና አጣዬ በማንነታቸው ምክንያት ሰማዕት የሆኑ ወገኖቼ አስቀኑኝ – ተራየ መድረሱ ላይቀር እስከዚያው የኔም ስቃይ በዛ፡፡ የተራ ጉዳይ ነው፡፡ አቢይ እስካለ ድረስ ሁላችንም ግን ተራ በተራ እናልቃለን፡፡ በኑሮ ሆዳችን ላይ የጀመሩትን ዕርድ በሜንጫ አንገታችን ላይ ይጨርሱታል፡፡ አንድዬ ይድረስልን – በውጭ ሀገር ያላችሁ ምንኛ ታድላችኋል! በስማም! ኢትዮጵያ ሀገሬ አልመስልህ እያለችኝ ተቸገርኩ፡፡ ወዴትና በየት በኩል ልሂድ? ሰው እንዴት ሰው ባልሆነ ሰው ይተዳደራል?

4 Comments

  1. አይ ጉድ ምሕረት ዘገዬ እንዲያው መኮነን ዘገዬ ብትለው አይሻልምን? እኔ እንደሚገባኝ የአንድ ሀገር መሪ በየቤቱ እይዞረ ቤት እያንኳኳ ምን በላትሁ፤ጠጣችሁ
    የት ተኛችሁ እያለ የሚጠይቅ አይመስለኝም። ነገር ግን አንተ እየነገርከን ያለው የሀገሪቱ መሪ በየቤቱ እይዞረ መቀመጫችንን ካላጠበ ነው። ይገርማል ያንተን የገማ እና ግም እሬብ አንተው ራስህ እጥብ ወይም የምትኖርበት የነጫጭባ ህገር መንግሥት እንዲያሳጥብልህ በወልፌር ማመልከቻ እንደለመድከው ማመልከቻህን አስገባ።ምክንያቱም ነጻ አስተያየትህ እንደ ጉሽ ጠላ የደፈረስ ነው።የታሪክህ መጀመሪያ ከባለቤትህ ጋር የዛላ በርበሬ ዋጋ 360 ብር መሆኑን አወራሃን ነው። ይህም ኗሪነትህ እትዮጵያ መሆኑ ነው። ቀጥለህ ደግሞ ” እንደሚባለው ከሆን የአንድ ኪሎ ስጋ ዋጋ ከ800 እስከ 1000 ብር ደርሶአል አሉ በለህ እየነገርከን ነው። ይህ ደግም ኗሪነትህ ዲያስፓራ መሆኑ ነው። በመሆኑም የደፈረሰ ጉሽ ጠላ ለመጠጣት እንደሚያስቸግር ሁሉ የጻፍከውም ተመሳሳይ ቅጥፈት፤ውሸት በኪሱ ስለሆነ መኮነን ዘገዬ ተብለሃል። በተጨማሪ ጠ/ሚኒስቱርሩ ለህዝቡ እንደማያስብ ግድ እንደሌለው እና ለራሱ የሥልጣን ዘመን መራዘም እንደሚጨነቅ ቤተ መንግሥት ሆኖ እንዴት እንቅልፍ ይዞት እንደሚያድር መገረምህን ሲሆን አንት ብትሆን ኖር ግን በጭንቀት እንደምትፈነዳ ነገርከን።እንዲሁም ለመፈንዳት ሰው መሆንን ይጠይቃልም አልከን።በመሆኑም ለመፈንዳት ሰው ለመሆን ሞክር ስልህም በወልፌር ካርድ እና በልመና ዝርክት ከርስህን ከመሙላት ሰው ሁን ከዚያም ከርስህን በቀስም ንፋስ ሙላ በቀላሉ መፈንዳት ትችላለሕ። ምርጫው እንደሆነ ዛሪ ይለያል። ስምህን ስታነብ ጠበቅ አድርገው። መኮነን ዘገየን ማለቴ ነው።

    • አምባው በቀለ የተባለው የአቢይ ውሽማ ስለሬብ ንጽህና አጠባበቅ ግሩም ሌክቸር ሠጥቶናል። ሁሉም ሰው ልምዱንና ሙያውን እንዲህ በግልጽ ቢያካፍል ሀገራችን የት በደረሠች!

  2. እንዲህ አይነት ከራሱ ጋር የተጣላ ሰውን ፖስት ባትፖስቱ ይመረጣል! Look some of the expressions that show …
    ♦ “ያቺ ጦሰኛ እናቱ…”
    ♦ “አቢይ እስካለ ድረስ ሁላችንም ግን ተራ በተራ እናልቃለን፡፡ በኑሮ ሆዳችን ላይ የጀመሩትን ዕርድ በሜንጫ አንገታችን ላይ ይጨርሱታል፡፡ አንድዬ ይድረስልን – በውጭ ሀገር ያላችሁ ምንኛ ታድላችኋል! በስማም! ኢትዮጵያ ሀገሬ አልመስልህ እያለችኝ ተቸገርኩ፡፡ ወዴትና በየት በኩል ልሂድ? ሰው እንዴት ሰው ባልሆነ ሰው ይተዳደራል?”

    ይህ ፀሃፊ በፍጥነት ወደ አእምሮ ህክምና ካልተወሰደ ምን አለ በሉኝ ልብሱን ይጥላል (አሁንም ጥሏል!)

  3. What a nasty comment that comes out from a dead and empty mind! Isn’t there a sort of moderation from the habesha.com’s side? This is really immoral to entertain such out of culture comments, I mean uncultured people are not fit to didactic exchange of ideas. Their negative side outweighs their positive one. What can one learn from this so called Ambaw Bekele, for example. Only dirt is coming out of its spoiled brain. He or she could use this forum for educative purposes instead of spreading vulgarism. I hope the site will consider such ugly and non-educative comments. Insults and badmouthing will never take us anywhere, sirs.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share