April 30, 2021
6 mins read

የቱ ነው ኦሮሞ? – መስፍን አረጋ

መንደርደርያ

ያማራ ሐለወት አደጋ ላይ ወድቆ
እየተቀበረ በማሽን ተዝቆ፣
ጽንፈኛ ኦሮሞ ጉቱም ሆነ ዋቆ
ይቀየማል ብሎ ማውራት ተጠንቅቆ
ትርፉ መዋረድ ነው ፈሪ አስብሎ አስንቆ፡፡

እየየም የሚባል ነውና ሲደላ
እየተሰየፉ እርጉዝና ጨቅላ
እየተቃጠሉ ሕጻናት በጅምላ
እየተሰደደ ሕዝብ በጠቅላላ
ትሕትና በቃ ከንግዲህ በኋላ፡፡

በግፍ ተጨፍጭሮ ተከምሮ ሬሳ
የቀረው ተደርጎ ገርባና ሞጋሳ
ካገር የጠፋበት አስራ ሰባት ጎሳ
የኦሮሞ መስፋፋት የሉባ ጠባሳ፣
ወጣቱ እንዲያውቀው መቸም እንዳይረሳ
ቀን በቀን ይነገር ደጋግሞ ይወሳ፡፡

ኦነግ ቄሮን ሲግት ያኖሌን ፈጠራ
የሉባን ጭፍጨፋ ማለት አይወራ፣
ሜዳውን በመተው ላባዱላ ሤራ
ኦነግን አድርጎ ይበልጥ ጠንካራ
ትርፎ ማባባስ ነው ያማራን መከራ፡፡

በኦነግ እሳቤ ያማራ ሕዝብ አሁን
በድኑን ብአዴን አሰልፎ በጎን
ሃያ ሰባት ዓመት እያዘነበ ዲን
ስለቀጠቀጠው የትግሬ አምባገነን
ተዳክሟል በማለት እንደ ግራኝ ዘመን፣
የሉባን ወረራ ጀምሮ እንዳዲስ
ሌሎቹን ጎሳወች ባጠፋበት ቅያስ
አማራን ጨፍጭፎ ዘሩን በመጨረስ
ተነስቷል ሊስፋፋ እስከ ጣና ድረስ፡፡

የኦነግ ሠራዊት የቆጡን ለማውረድ አጣየ ሲመጣ
መገንዘብ አለበት የብብቱን ነቀምት ሊችል እንደሚያጣ፡፡

በሱማሌ ጅራፍ ከባሌ ሲነዳ
ግራኝ በከፈተው የውሻ ቀዳዳ
ገብቶ ሲንሰራፋ ገዳ ከሰው ጓዳ፣
መሆኑን ረስቶ ራሱ እንግዳ
ቤተኛውን አለው እንግዳ የገዳ፡፡

ግራኝ እያጸዳ ወደፊት ሲያመራ
እሱ ተከትሎ የከብቶቹን ጭራ
የቀሩትን ሰወች ጨርሶ በካራ
የሰፈረበትን የአማራን ስፍራ፣
ፊንፊኔ፣ ጉለሌ ብሎ ስለጠራ
የግሌ ነው ብሎ አለቅጥ ተኩራራ
አማራ ይውጣ አለ ካማራ በራራ፡፡

ጎጃሜ ሲመጣ ወደ አዲስ አበባ
እኔ ካልፈቀድኩኝ አይችልም ሊገባ
እስከማለት ድረስ በጥጋብ ጠነባ፡፡

አማራ እንደሚለው በድንቅ ተረቱ
ብዙ ቢዘገይም ቢሞላም ሺ ዓመቱ
ርሰት ይመለሳል ለሕግ ባለቤቱ፡፡

አሩሲና ከፋ፣ ወሎና ወለጋ
ፋኖ ከፍሎላቸው ብዙ የደም ዋጋ
ቀን ሲወጣላቸው ጨለማው ሲነጋ
በቀድሞ ስማቸው ይለብሳሉ ጸጋ፡፡

የቱ ነው ኦሮሞ?
ዜናሁ ለጋላን አንብቦ ባርምሞ
ለማጠናከሪያ የብሩስን ደግሞ
የኦሮሞን ታሪክ ያጠና ገምግሞ፣
የሚከተለውን በእርግጥ ደምድሞ
መናገር ይችላል አደባባይ ቁሞ፡፡

“የሉባው ሠራዊት የገዳው ኦሮሞ
ሐበሻን ሲያገኘው በግራኝ ተዳክሞ
ጨለማ ተላብሶ እያረደ አጋድሞ፣
ባበሻ ምድር ላይ በያቅጣጫው ተሞ
የተንሰራፋ ነው እንደ አረማሞ፡፡”

“በጦቢያ ምድር ላይ ከጣና እስከ ጫሞ
በኦሮምኛ ቃል ያለ ተሰይሞ
ከመስፋፋት በፊት ሁሉም አስቀድሞ
አይደለም ኦሮሞ ወይም የኦሮሞ፡፡”

“በስሙ ኦሮሞ ከሆነው ሕዝብ ላይ
ዘጠና በመቶ ወይም ከዚያ በላይ
በደሙ ያይደለ ብሔሩን የረሳ
ወይ ጉዲፈቻ ነው አለያም ሞጋሳ፡፡”

አንዳርጋቸው ብሎ ቢከተል ቂጢሳ
ቂጢሳን ከማለት የኦሮሞ ጎሳ
ማለት ያመዝናል ነበረ ሞጋሳ፡፡

ከወለጋ ኗሪ አንዱን ለናሙና
ወይም ከአሩሲ አንዱን በደፈና
በመመልከት ብቻ የደሙን ወዘና
ምንም እንደሌለው ከወደ ቦረና
መናገር ይቻላል በሙሉ ልቦና፡፡

ለምሳሌ ለማ፣ ኦቦ ኦነግ ሸኔ
የኦሮሞ ችግር፣ ጥያቄ፣ ውሳኔ
ተሰጥቶኛል ያለው ተቆጥሮ ለእኔ፣
ሐረጉ ቢመዘዝ በደም ትንታኔ
የመሆን እድሉ ከረዩ ቦረኔ
እጅግ ያነሰ ነው ከመሆን ብቸኔ፡፡

ሽመልስ አብዲሳ ያልተገራው ስዱ
ነፍጠኛን ሰበርነው ሲል እንደልማዱ፣
የቦረና ውልዱ ሳለ የምጣዱ
አትንጣጣ በሉት አንተ የሰፌዱ፡፡

ዲኔግዴ፣ ጉበና ቢቂላ ወይ ባልቻ
ኦሮሞ እሚባለው በስያሜው ብቻ
አብዛኛው ቢታይ በደም መመልከቻ
ወላጆቹ ታርደው በሜንጫ ዘመቻ
የተለወጠ ነው ወደ ጉዲፈቻ፡፡

ጉዲፈቻ ደግሞ በመሆኑ ገርባ
ከገርባ በስተቀር ሌላ እንዳያገባ
ስለሚከለከል በገዳ ድነባ
ደሙ የለበትም ጠብታ የሉባ፡፡

ኦሮሞን ስናየው በዚህ ረገድ ዓይን
መሆን ይቅርና የጦቢያ ብዙሃን
እጅግ ያነሰ ነው ከሁሉም ሕዳጣን፡፡

ከጦቢያ ብሔሮች እኔ በመነጠል
ካልፈጠርኩኝ ካለ የኦሮሞ ክልል
ባሌም አይገባው ላሥር ሳይከፈል፡፡

በስሙ ቢባልም ኤጀርሳ፣ ኤለሞ
በደሙ ያልሆነ ሐበሻና ጋሞ
እንዲሁም ወላይታ፣ ሐድያ ሲዳሞ
እስኪ ተናገሩ የቱ ነው ኦሮሞ?

መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop

Don't Miss

 የዐብይ አሕመድ መሰወርና የወያኔ ፕሮፓጋንዳ – መስፍን አረጋ

አብናቶቻችን (አባቶቻችንና እናቶቻችን) እንደሚሉት፣ ዳር ሲደፈር መኻል ዳር ይሆናል፡፡   በዚህም