April 29, 2021
8 mins read

ደህንነት፤ አንድነትና ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ኃላፊነቶች – በቀለ ገሠሠ (ዶ/ር)

1ኛ/         በሚከተሉት ሃቆች ላይ እንስማማ?

  • ሕዝብ በግዲያ እያለቀ ነዉ።
  • የተረፈዉ በመቶ ሺዎችና በሚሊዮኖች እየተፈናቀለ ይገኛል።
  • ጭፍጨፋዉ በአብዛኛዉ ዘርና ኃይማኖትን እየመረጠ ነዉ፤ ከፍተኛ ሰለባዎች አማራዎችና ኦርቶዶክሶች ናቸዉ። አጣዬ እንዳለች ፈረሰች። የቀረዉ ሰሜን ሸዋ በተመሳሳይ ችግር ዉስጥ ወድቋል። የወለጋዉና የመተከል ዕለታዊ እልቂቶች ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ናቸዉ፤ በተለይ የምስኪን እናቶች፤ ነፍሰጡሮች፤ አባቶች፤ ሕፃናትና ወጣቶች እጅግ አስከፊ ሰቆቃዎች።
  • በነዚህ ምክንያቶች ሕዝቡ በነቂስ በሚሊዮኖች እየወጣ ብሶቱን እያሰማ ይገኛል። ጥያቄያቸዉ ቀላል ነዉ፤ አትግደሉን፤አታፈናቅሉን ነዉ የሚሉት። የብሶት መግለጫ እንጂ ተራ ጩሄት አይደለም።
  • በትግራይ የንፁሐን ዜጎች ሰቆቃ እየተባባሰ ይገኛል።
  • በደቡብ ሰላም የለም።
  • በአፋርና በሶማሌ አካባቢዎች ግጭቶች እየተባባሱ ይገኛሉ።
  • የዉስጥ ሰላምና አንድነት ሲናጋ ለዉጪ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ያመቻል። በሰሜን ምዕራብ ድንበራችን ተደፍሮ ሕዝባችን ተፈናቅሎ ይገኛል።በታላቁ ግድባችን ግንባታ ላይ ብዙ ማስፈራሪያዎች እየደረሱን ይገኛሉ።
  • የኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል።
  • ይሄ ሁሉ ለማንም ጤናማ ዜጋ የሚጠቅም አይደለም፤ ተያይዞ መጥፋትን ይጋብዛል።

 

2ኛ/        ታዲያ ምን ማድረግ ይኖርብናል?

በመጀመሪያ እላይ የተጠቀሱ ካብድ ከባድ ችግሮች መኖራቸዉን ማመን ይጠይቃል። ምክንያቱም በግልፅ የሚታዩና የሚሰሙ ከባድ ጭፍጨፋዎችና የዘር ማጥፋት ዘመቻዎች ናቸዉ። ከዚያ በመቀጠል፤ የሚከተሉት ክፍሎች በቅደም ተከተል  ኃላፊነታቸዉን መወጣት ይጠበቅባቸዋል።

 

2.1          የመንግሥት ኃላፊነት

መንግሥት በፊት ለፊት ወጥቶ እነዚያ ችግሮች እንዳሉ ማመን ይኖርበታል። ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ብሶቱን ሲያሰማ በጥሞና ማዳመጥ ይጠበቅበታል። በወንጀለኞች ላይ እርምጃ መዉሰድ የጠበቅበታል። አደጋዎቹ በሚቀሰቀሱባቸዉ አካባቢዎች ላይ የፀጥታና የመከላከያ ኃይሎችን ቶሎ ማሰማራት ይጠበቅበታል። የተጎዱትን ማጽናናት፤ የተፈናቀሉትን ወደየሰፈሮቻቸዉ መመለስና ችግሮቹ እንዳይደገሙ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል። የሀገርን ድንበርና ሉዓላዊነት ማስጠበቅ ይኖርበታል። በአሁኑ የሀገሪቷ እጅግ አሳሳቢ የፀጥታ ሁኔታ ዉስጥ ምን ምርጫ መካሄድ ይችላል? ሰዉ ዛሬ ከአዲስ አበባ ወጥቶ ናዝረት ደርሶ በሰላም የመመለስ ዋስትና የለዉ። በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ውስጥ ተቃዋሚ የፖሊቲካ ድርጅቶች መንቀሳቀስ በማይችሉባቸዉ ቦታዎች ስለምን ምርጫ ነዉ የሚወራዉ? በፊተኛዉ ከማል በድሪ የምርጫ አፈጻጸም ዘመን እንኳን ድምጾች ይሰረቃሉ እንጂ ሰዎ እኮ በሰላም ወጥቶ መምረጥ ይችል ነበረ። ስለዚህ ቀልዶች ቢቆሙ ይሻላል። ካለፉት ከባድ ስህተቶች መማር ያስፈልጋል። ሕዝቡን ከፋፍሎ ለመግዛትና ለማናከስ የወጣዉ የወያኔ ሕገ መንግሥት መለወጥ አለበት። የወያኔ/ሸአቢያ ካድሬዎች እነ ተስፋ ገብረዓብ የረጩዋቸዉ መርዝና የዉሸት ትረካዎች መኮነን አለባቸዉ። ታሪክ ማዛባቱ መቆም አለበት። እነዚህን ተግባራት ካልፈፀሙ የመንግሥት፤ የፖሊስ ሠራዊትና የመከላከያ ኃይል መኖር ለምን አስፈለገ?

 

2.2          የተቃዋሚ የፖሊቲካ ድርጅቶች ኃላፊነት

ተቃዋሚ የፖሊቲካ ድርጅቶችም ተመሳሳይ ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል። በደርግ ዘመን ኢሕአፓና ሌሎች ሀቀኛ ዜጎች የጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት ምሥረታ ሲጠይቁ ደርግና ተለጣፊዉ መኢሶን እምቢ አሉ። እልቂት ደረሰ። እልፍ አእላፍ ወጣቶችና ከ11 በላይ የሚሆኑ መተኪያ የሌሉዋቸዉ ጄነራሎች ተረሸኑ። በመጨረሻ ደርግ በኃፍረት ወድቆ፤ ስልጣኑን ለወያኔና ሸአቢያ አስረክቦ ፈረጠጠ። ዛሬም በጭፍን ምንግሥት እየደገፉ መቀመቅ ዉስጥ እየከተቱት ያሉ ቡድኖችና ግለሰቦች ሞልተዋል። ካለፉት ስህተቶቻቸዉ አይታረሙም። ችግራቸዉ ምንድን ነዉ? የወያኔ ጥላቻ? ሕዝብ እያለቀ፤ ሀገር እየፈረሰ ፍርፋሪ ለመልቀም ነዉ? እግዚአብሔር ስለማይወድ ከስህተታቸዉ ቢታቀቡ ይሻላቸዋል። ይጠየቁበታልና።

 

3ኛ/        የሰፊዉ ሕዝብ ኃላፊነት

ዉድ ወገኖች፤ በዉሸት ትርክቶች አትታለሉ። ምኒልክ ጡት ቆራጭ አልነበሩም። በዐፄ ቴዎድሮችና በዐፄ ዮሐንስ የተጀመረዉን ሀገር መልሶ የመገንባት ጥረቶችን አከናወኑ እንጂ። ዛሬ በየሰፈሩ እየታረደ የሚገኘዉ ንፁሕ ዜጋ በገዛ ሀገሩ ጥሮ ግሮ ከመኖር በስተቀር የፈጠረዉ ምንም ኃጢያት የለም። ታዲያ ለምን ትገድሏቸዋላችሁ? እግዚአብሔር አትግደል ይላል። አላህ ሀራም ነዉ ይላል። ታዲያ ከዬት አመጥችሁት? አንድነት ይበጀናል። ካለዚያ የባሰዉ መጠፋፋት ይመጣል። የዉድ ሀገር መፍረስንም ሊያስከትል ይችላል።

ይህቺን መልእክት በሕማማት ላይ ሆኜ ስጽፍ እያዘንኩ ነዉ። ቅን አባቶቻችንና አያቶቻችን አጥንታቸዉን ከስክሰዉና ደማቸዉን አፍስሰዉ የገነቧትንና ፈጣሪ የባረካትን ሀገር አትጉዱ። ሀገሪቷ አልጠበበችም። ከራስዋም አልፋ ስንቱን ተቀብላ የምታሰፍርና የምትደግፍ ናት። እግዚአብሔር ወደ ቀድሞዉ አንድነታችን ይመልሰን። ዉሎ ሳያድር ቅን ልቦና ይስጠን።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop