ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማን ምክር ጠየቃቸው? – መርሐጽድቅ መኮንን አባይነህ

ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማን ምክር ጠየቃቸው?
እርሳቸው መሪያችን እንጂ አማካሪያችን ናቸው እንዴ?

ከመርሐጽድቅ መኮንን አባይነህ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም የኢ.ህ.ዴ.ሪ ህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በስድስተኛው ዙር የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዶ ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ደግሞ በዚሁ ስብሰባ ላይ ተገኝተው በአስር ዓመቱ የልማት እቅድና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለተከበሩ የምክር ቤቱ ኣባላት ገለጻ ለማድረግና በአንጻሩም ከእንደራሴዎቹ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በእለቱ ተሰይመዋል፡፡

ይሁን እንጂ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢ.ፌ.ደ.ሪ ሕገ-መንግሥት መሰረት ተጠሪ ለሆኑለት የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤትም ሆነ ለሚያስተዳድሩት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ቀጥታ በቴሌቪዥን በተላለፈው መልእክታቸው ያስደመጡን ረዥም ዲስኩር አልፏልፎ ቀልድ መሳይ ነገር የተቀላቀለበትና ያልተጠየቀ ምክር ቢጤ ጭምር የበዛበት የየኔታ ፋንታሁን አይነት ሰፊ ቃለ-ምእዳን ሆኖ ታዝበነዋል፡፡

በርግጥ ይህ አነስተኛ መጣጥፍ እንደመጫኛ የረዘመውንና ጠቅላያችን ለፓርላማው ያቀረቡትን የዚያን ሙሉ ዲስኩር ጠልቆ በዝርዝር የመተቸት አላማ የለውም፡፡

ከዚያ ይልቅ የታላቁ ምክር ቤት ስብሰባ ከመካሄዱ ጥቂት ቀናት አስቀድሞ በአማራ ክልል ተጎራባች ዞኖች፣ ማለትም በሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ብሔረ-ሰብ አስተዳደር ዘንድሮ ለዳግመኛ ተከስቶ ከነበረው ደም-አፋሳሽ ሁከትና ብጥብጥ ጋር በተያያዘ ከምክር ቤቱ እንደራሴዎች በኩል ቀርቦላቸው ለነበረው ፖለቲካ-ነክ ጥያቄ በገደምዳሜም ቢሆን በሰጡት የግብር ይውጣ ምላሽና ማብራሪያ ላይ ማተኮርን ይመርጣል፡፡

ከፍ ብሎ በተጠቀሱት የክልሉ ዞኖች ውስጥ ከአጣዬ እስከማጀቴ፣ ከሸዋ ሮቢት እስከከሚሴ በሚዘልቁት ከተሞችና ዙሪያ የገጠር ቀበሌዎች ሳይቀር በአደገኛ ሁኔታ ተስፋፍቶ ከመጋቢት 9 ቀን 2013 ዓ.ም እስከመጋቢት 13 ዓ.ም ድረስ በነበሩት ጊዜያት እንደስናይፐር፣ rpg ና መትረየስ ባሉት ከባድና የቡድን ጦር መሳሪያዎች ተደግፎ ባልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የከፋ መአት አውርዶባቸዋል፡፡

እንግዲህ ይህንኑ አስመልክቶ አቋማቸውን እንዲያብራሩና ዜጎችን ከእንዲህ ያለው ጥፋት ለመታደግ መንግሥታቸው እያሳየ ያለውን የበዛ ዳተኝነት ሀቀኛ ሆነው እንዲከላከሉ ነበር ጉዳዩ ባሳሰባቸው በአንዳንድ ንቁ የህዝብ እንደራሴዎች በኩል ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጀመሪያ የተጠየቁት፡፡

እንደእውነቱ ከሆነ ጠቅላዩን በጥያቄ ያፋጠጧቸው እንደሌላው ጊዜ በሌላ ክልል ውስጥ ብቻ ሳይሆን በራሱ በአማራ ክልል ውስጥ ለሰሚም ሆነ ለተመልካች ፍጹም በሚዘገንን ሁኔታ የኦ.ነ.ግን ሰንደቅ አላማ አንግበው ሲንቀሳቀሱ በታዩ ታጣቂዎች እርምጃ በአማራው ብሔር አባላት ላይ የተካሄደው ዘርና ሀይማኖት-ተኮር ጭፍጨፋ ክፉኛ ያስቆጣቸውና ያበሳጫቸው እንደራሴዎች ብቻ አልነበሩም፡፡ በተቃራኒው ከመካከላቸው ከአጣዬ እስከከሚሴ የዘለቀውን አውዳሚ ጥቃት የፈጸመውም ሆነ ያቀነባበረው ከርቀት የመጣ ሌላ ሀይል ሳይሆን ኦሮሞ-ጠልና ጸረ-እስልምና የሆነው የአማራ ልዩ ሐይል በመሆኑ ከሁሉም ነገር በፊት ይኸው ሐይል ከኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ዞን ጠቅልሎ ይውጣልን በማለት ሁከትና ግርግሩን ከሀይማኖትና ከብሔር ጽንፈኝነት ጋር በማስታከክ አደናጋሪ ጩኸት ያሰሙም ይገኙባቸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጃዋር ነበር የሚለው፣ አሁን ግን የኦሮሞ ተማሪዎችም ደገሙት - ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት (ናኦሚን በጋሻዉ)

ይሁን እንጂ በትልቁ ፓርላማ ዘንድ ከተሰማባቸው የሰላ ሂስና ከተደመጡባቸው ጠንካራ አስተያየቶች አኳያ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ረዥም ዲስኩር ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በችግሩ ዙሪያ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሠጡት ምላሽና ማብራሪያም ቢሆን ያን ያህል አሳማኝና ውሃ የሚቋጥር ሆኖ አልተገኘም፡፡

ይባስ ብለው ጠቅላያችን በዚያ መድረክ ከውሳኔ ሰጪነት ይልቅ የአሸማጋይነት ዝንባሌ ተስተውሎባቸዋል፡፡ እንዲያውም ረብ-የለሽ ካድሬዎቻቸውን አምርረው ከመገሰጽና ከመካከላቸው እልቂቱን ሳያነሳሱ እንዳልቀሩ በሚገባ የተጠረጠሩትን ኦሮሞ-ዘራሽ ጽንፈኞች በኀላፊነት ከመጠየቅ ታቅበው አማራና ኦሮሞ በማሕበረ-ሰብ ደረጃ የተጋጨና ቀድሞውኑ ተጻራሪ ጥቅሞች ያሉት ይመስል እንደእርሳቸው አነጋገር ደጋጎቹ የሰሜን ሸዋ አማሮች አብረዋቸው በፍቅርና በወንድማማችነት ከኖሩት ከዎሎ ኦሮሞዎች ጋር ጎራ ለይተው መገዳደላቸውን እንዲያቆሙ ሊመክሩ ሲዳዳቸው በአንክሮ አስተውለናል፡፡

ለነገሩ እርሳቸው እኮ ድሮውንም ቢሆን መሪያችን እንጂ አማካሪያችን አልነበሩም፣ አይደሉምም፡፡

እንግዲህ የያኔዎቹ የወርሀ-መጋቢት ሰለባዎች በከባድ መሳሪያ ተደግፎ የተፈጸመው ዳግም የጥይት እሩምታ ካደረሰባቸው ቀውስ ገና በቅጡ ሳያገግሙ ነበር አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ፣ ማለትም ከሚያዚያ 6 ቀን 2013 ዓ.ም አንስቶ አሸባሪው ቡድን ከመቸውም ጊዜ ይበልጥ በመታጠቅና በመደራጀት ወደነዚሁ የፈረደባቸው የሰሜን ሸዋ አካባቢዎች በመመለስ እንደአጣዬ፣ ካራ ቆሬ፣ ማጀቴ፣ ቆሪ ሜዳ፣ አንጾኪያ፣ ሸዋ ሮቢት ያሉትን ከተሞችና በዙሪያቸው የሚገኙትን በርካታ የገጠር ቀበሌዎች ለሶስተኛ ጊዜ ያጠቃው፡፡ ቡድኑ በዚህ ጥቃት ሠላማዊ ዜጎችን በጠራራ ፀሃይ አርዷል፤ የመኖሪያም ሆነ የአምልኮ ቤቶቻቸውንና የንግድ ተቋሞቻቸውን በእሳት አጋይቷል፤ መሰረታዊ የእለት ተለት መገልገያዎቻቸውን ጨምሮ በላብና በጥረታቸው ደክመው ያፈሩትንና ያጠራቀሙትን ሀብትና ንብረት ያለአንዳች ሀይ ባይ አውድሟል፡፡

በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ የወረደው ይህ ድንገተኛ መከራ የአማራ ክልልንም ሆነ የፌደራል መንግሥቱን የፖሊስና የመከላከያ ሀይሎች ሳይቀር በብርቱ እስከመገዳደር የደረሰ ነበር፡፡ በዚያ ድንገት ለዜጎች ደህንነት ዋስትና ይሆናሉ ተብለው የተገመቱ የፖሊስና የመከላከያ አባላት አሸባሪው ቡድን ለጥፋት ካሰማራቸው ወራሪዎች ጋር ሲነጻጸር በመረጃ፣ በትጥቅም ሆነ በድርጅት አቅም አንሰው በመገኘታቸው ከሠላማዊው ህዝብ ጋር እኩል ተጠቅተዋል፣ ተጨፍጭፈዋልም፡፡

ከጅምላ ጥቃቱና ከግድያው ለመትረፍ የቻለው የየከተሞቹ ነዋሪ ከወረራው የተነሳ ከየሚኖርበት ቀዬ ተፈናቅሎ እስከመሃል ሜዳ፣ ደብረ-ሲናና ደብረ-ብርሃን ከተሞች ድረስ በእግሩ ተጉዞ ለመሰደድ ተገዷል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ረዥም ርቀት ለመሄድ የተሳናቸው ነፍሰጡር ሴቶች፣ ህጻናትን በጀርባቸው ያዘሉ እናቶች፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ደግሞ ከአቅም ማነስ የተነሳ በየመንገዱ ወድቀው ቀርተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጥለሽ - ከመርሐጽድቅ መኮንን አባይነህ

እንደሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር መግለጫ ከሆነ ለሶስተኛ ጊዜ በተፈጸመው በዚህ የታጣቂው ቡድን ወረራ የተፈናቀለውና እግሬ-አውጪኝ በማለት ወደተለያዩ ስፍራዎች የተበተነው ህዝበ-አዳም ቁጥሩ በጠቅላላው እስከ250 ሺህ ይደርሳል ነው የሚባለው፡፡

በተለይ በኤፍራታና ግድም ወረዳ ተደጋጋሚ የጥቃት በትር ያለርህራሄ ያረፈባቸው የአጣዬና የካራ ቆሬ ከተሞች ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ በእሳት ቃጠሎው ወድመዋል፡፡ የግልም ሆኑ የመንግሥት ተቋማት ተዘርፈዋል፣ ተቃጥለዋልም፡፡ የሕግ ታራሚዎች መጠለያ የሆነው የአጣዬ ማረሚያ ቤት ሳይቀር በሀይል ተሰብሮ እስረኞች ራሳቸውን ፈትተው እንዲወጡና ኀላፊነት በጎደለው አኳኋን እንዲያመልጡ ተደርጓል፡፡ ይህ እንግዲህ ለሠላማዊው ሕብረተ-ሰብ ደህንነት ምን ያህል አደገኛና አስፈሪ ኩነት እንደሆነ ለመገመት አያዳግትም፡፡

ለነገሩ እኮ አጎራባች ከሆነው ከኦሮምያ ክልል እየተንደረደሩና ይልቁንም በራሱ በአማራ ክልል ውስጥ በታቀፈው የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ አስተዳደር አንዳንድ ወረዳዎችና ቀበሌዎች እየመሸጉ ሲሰለጥኑ ይቆዩና አሳቻ ጊዜ እየፈለጉ አድብተው በመውጣት የአማራውን ማሕበረ-ሰብ አባላት መርጠው በምልልስ የሚያጠቁት ወሮበሎች እርምጃ ለአካባቢው ያን ያህል እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ በኦሮሞ ነጻነት ስም እንንቀሳቀሳለን የሚሉት አክራሪና ጽንፈኛ ብሔረተኞች ለዘመናት ጸንቶ የዘለቀውን የአማራና የኦሮሞ ማሕበረ-ሰቦች አብሮ የመኖር እሴት አብዝቶ በሚገዳደርና ክፉኛ በሚያጠለሽ መንገድ ዜጎችን በማንነታቸው ላይ አተኩረው ሲገድሉ፣ ሲያቆስሉና ሲያፈናቅሉ ቆይተዋል፡፡

ለምሳሌ የአጣዬና አካባቢው ነዋሪ ህዝባችን በሚያዚያ ወር 2011 ኣ.ም ተመሳሳይ ወረራ ተፈጽሞበት እንደነበር አንዘነጋውም፡፡ በርግጥ ያንን ድፍረት የተመላበት የግፍ ወረራ የከፋ ጥፋት ከማድረሱ አስቀድሞ በተፋጠነ እርምጃ በመቀልበሱና አማጽያኑን በመጡበት አካኋን አሳፍሮ በመመለሱ ረገድ አፈሩ ይቅለላቸውና የወቅቱ የአማራ ክልል ሠላምና ደህንነት ቢሮ ኀላፊና የታማኝ ጓዶቻቸው ቁልፍ ሚና ተጠቃሽና አይተኬ ነበር፡፡

እንግዲህ እንደቀደምት ጥቃቶች ሁሉ ሰሞነኛው ወረራም እስካሁን ድረስ ትክክለኛ ባለቤቱ በይፋ አይታወቅም፡፡ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የክልሉ ባለሥልጣናት የኦ.ነ.ግ ሸኔ ታጣቂዎች እያሉ ነው አዘውትረው የሚጠሯቸው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በስም ከመጥራት በመቆጠብ አሸባሪውን ቡድን አንድ ጊዜ የጥፋት ሀይል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጠላት፣ በሚሰኝ ቅጽል እየለዋወጡ ሲጠሩት እንሰማለን፡፡

በዚህ ረገድ ኦፊሴላዊ ያልሆነ የአፈንጋጪነት ዝንባሌ የሚታይበት የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ አስተዳደር ብቻ ከእንዲህ ያለው የተዥጎረጎረ ፍረጃና አጠራር የለሁበትም ሲል ራሱን ወደአማጽያኑ ጎራ ለማስጠጋት የመረጠ ሆኖ እናየዋለን፡፡ አህመድ ሀሰን የተባሉት የብሔረ-ሰብ ዞኑ ዋና አስተዳዳሪ በዚያን ሰሞን ወደሚዲያ ብቅ ብለው እኔ በበኩሌ ኦ.ነ.ግ ሸኔ የተሰኘ ታጣቂ ቡድን አላስጠለልኩም፣ እንዲያ የሚባል ቡድንም አላውቅም፣ ይህ የፈጠራ ወሬ ነው፣  ሲሉ ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ መደመጣቸው የዚህ ማሳያ ይመስላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ያልታሰረው ማን ነው?? (ከአንተነህ መርዕድ)

ይህ ሁሉ ሲሆን ታዲያ የፌደራሉ መንግሥት ጀሮዬን ይድፈነው በማለት ሊምልና ሊገዘት እስኪዳዳው ድረስ ስለሁከቱ ጨርሶ የሰማ እንኳን አይመስልም፡፡ አገር ቀውጢ ሆኖ ከተሞች እንደጧፍ ከነደዱ በኋላ ብቅ ብሎ እባካችሁን ተረጋጉ በማለት በመከላከያና በሠላም ሚኒስቴሮቹ አማካኝነት የጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ አይነት መግለጫዎችን አዥጎድጉዶልናል፡፡

መከላከያውስ ከዚህም አልፎ ከደብረ-ሲና እስከኮምቦልቻ የሚዘልቅ የኮማንድ ፖስት ቀጣና ዘርግቶልናል፡፡ ይህንን እንዲያደርግለት የአማራ ክልል መንግሥት አስቀድሞ ይጠይቀው አይጠይቀው በርግጥ በይፋ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡

ኦ.ነ.ግና በስሙ የሚጠራው ኦ.ነ.ግ ሸኔ ምንና ምን ናቸው?

ለዘመናት በደፈጣ ተዋጊነት ተሰማርቶና በመንግሥት በኩል ደግሞ በአሸባሪነት ተፈርጆ ከቆየ በኋላ ከለውጡ ማግስት በሠላማዊ መንገድ ለመታገል እንደወሰነና ወደሀገር ቤት እንደገባ አጥብቆ ሲወተውት የሚሰማው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦ.ነ.ግ) ተፈጥሯዊ ውላጁ ከሚመስለውና ‘ኦ.ነ.ግ ሸኔ’ እየተባለ ከሚጠራው ከዚህ የአመጽና የወንጀል ቡድን ጋር አንዳች ትስስር የለኝም ሲል ነው በየጊዜው ሲሚልና ሲገዘት የምንታዘበው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ትክክለኛው መጠሪያዬ መንግሥት እንደሚለው ‘ኦ.ነ.ግ ሸኔ’ ሳይሆን ‘የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሰራዊት’ ነው ሲል በህቡእ ከመሸገበት ስፍራ ሆኖ በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛውን አገልግሎት በስልክ ያገኘው ኩምሳ ድሪባ ዎለጋ ውስጥ ማንነትን መሰረት በማድረግ በንጹሃን የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ያለማቋረጥ እየተፈጸመ ላለው ጥቃት ተጠያቂው እኔ ሳልሆን ራሱ መንግሥት ነው በማለት አምርሮ ይከሳል፡፡

ግራም ነፈሰ ቀኝ በልዩ ሁኔታ እስካፍንጫው ድረስ የታጠቀና የተደራጀ ነው እየተባለ የሚነገርለትና በህቡእ የሚንቀሳቀሰው ኦሮሞ-በቀል ቡድን ኦ.ነ.ግ ሸኔ የሚሰኘው ስሙ በተደጋጋሚ አየር ላይ ሲናኝ በአግራሞት መታዘባችንን ቀጥለናል፡፡ እስካሁን ድረስ ፍጹም ጉራማይሌ የሆነብንና በውል ለመረዳት የተሳነን ግን በዚሁ ቡድን ስም እየተንቀሳቀሱ የከተማም ሆነ የገጠር መንደሮችን ሲወሩና በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጭፍጨፋዎችን በተከታታይ ሲፈጽሙ፣ የሰለባዎችን ህይወት ሲቀጥፉና ንብረት ሲዘርፉ ወይም ሲያወድሙ የምናገኛቸው የጥፋት መልእክተኞች አፋን ኦሮሞ የሚናገሩና አልፏልፎም በኦ.ነ.ግ ባንዲራ አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸው ነው፡፡

እንግዲህ ጉዳዩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚመለከታቸው የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥትም ሆነ የራሱ የፌደራሉ መንግሥት የበላይ የፖለቲካ አመራሮች መፍታትና ማፍታታት የሚጠበቅባቸው ይህንን እንቆቅልሽ መሆን አለበት፡፡

የትኛውም አይነት ጥያቄ እንደየቀረበበት አውድ ከአንድ በላይ የሆኑ መልሶች ይኖሩት ይሆናል፡፡ ትክክለኛ ምላሹ ግን ምንጊዜም ቢሆን አንድና አንድ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ ለግብር ይውጣ ያህል የሚሰጥ የማስታገሻ መልስና ኀላፊነት የሚወሰድበት ምላሽ በጠባያቸው ይለያያሉና፡፡

አበቃሁ፡፡

 

 

7 Comments

  1. ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤናም የለውም ፤ የሚናገረውንም አያውቀውም። ከቦሌ መንገድ አዲስ አበባ የጠፋውን የአበባ ተክል ሲያፈላልግ ነው የነበረው ፤ አልተዘጋጀበትም ነበር ለንግግሩ። የአበባ ግቢ ያለው መኖሪያ ቤት ተሰጥቶት ስልጣኑን የሚለቅበትን ሀሳብ መምከር ያሻዋል።

  2. እኚh ሰው የአማራ ክልል ፕረዚደንት የህግ አማካሪ መሰሉኝ፤ የገዱም፤ የአምባቸውም አማካሪ ነበሩ [ካልሆኑና ከተሳሳትኩ ይቅርታ!]
    በአንድ ወቅት አንድ የኢራቅ ጋዜጠኛ በፕረዚደንት ጆርጅ ቡሽ ላይ ጫማ ወርውሮ ስቷቸው ነበር። ታዲያ ቡሽ “ምን ተሰማዎት’ ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ አሉ። “ሳዳም ሁሤን ላይ ቢሆን ይህንን እንኳን ሊአደርገው ሊያስበው አይችልም” ብለው ነበር። በተመሳሳይ ጸሃፊው በቅድሚያ “እንኳን ለዚህ አደረስዎት” ነው መባል ያለባቸው። ምክኛቱም እንደ እድሜአቸው ከሆን ብዙ መንግስታትን አይተዋል፤ በማንም ላይ ያልሞከሩትን አቢይ ላይ እየተለማመዱ ስለሆነ። ከዚህ በፊትም የአማራን ግድያ “የዘር ፍጅት” ብሎ መንግስት እንዲአውጅ ሲጎተጉቱ ነበር።
    ጥያቄው እኝህ ሰው በምን ፖርትፎሊዮ ነው የጻፉት/የሚጽፉት? የሚለው ነው። አሁንም “አማካሪ” ናቸው/አይደሉም? የአማራ ብልጽግና አባል ናቸው/አይደሉም? ሁለቱንም ካልሆኑ [ጡረታ ወጥተውም ከሆነም] መብታቸው ስለሆነ “case closed” ብ.ለን እናልፈዋለን። ሁለቱን ቀርቶ አንዱን እንኳ ከሆኑ ግን በጣም አደገኛ ነው። ከሁለቱም ቦታ ባስቸኳይ መልቀቅ/መነሳት ይኖርባቸዋል።

  3. Setete,

    Are you still the mouth piece of the “Seventh King abiy ahmed? A lot of worshippers of abiy ahmed have come to their senses during the last two weeks. I thought you would be one of them. Think about it before it is too late.

    • አይ መሰረት? አቢይ በጉልበት ይወርዳል ብለህ አስበህ ከሆነ በጣም ሞኝ ብቻ ሳትሆን ስለአሁኗ እትዮፒያ ያለህ እውቀት ከዜሮ በታች ነው ማለት ነው። ከተሰካላችሁ ማድረግ የምትችሉት የአማራን ወጣት ቀስቅሳችሁ ከተቀረው የኢትዮጵይ ብሄረሶቦች ወጣት ጋር ጦርነት ከፍቶ እትዮጲያን እንዲያፈርስ ማድረግ ነው። ሞክረው። ለቀብር እንኳ መመለሻ ሃገር አይኖርህም።
      አንድ ቀን ሃሳብ ስትሞግት አንብቤ አላውቅም። ተው የዋሁ መሰረት we are not in the same league

      • Poor and little setete,

        I realized that you have never read history, be it Ethiopian or world history. The ultimate fate of dictators is to die like gadaffi and sadam hussein. I believe, your little, liar abiy will end in a worse way. Time will show us.

  4. አይ ከድር ሰተቴ ለኦሩሙማ ካልበጁ ይወገዱ ነው ያልካቸው? ሰውየው የጻፉትን ርእሱን ነው? መነበብ ባለበትስ ልክ አንብበኸዋል? የጽሁፉ አወራረድ መደበኛ የአካዳሚክስ መስፈርትን ያሟላና አስተማሪ የሆነ ነው ቅደም ተከተሉ ይዘቱ እይታው ማጠቃለያው ለስድብ አይሆንህም እንጅ ለማይሆነው የለም። ለሰውየው ባለህ አመለካከት ብቻ ጽሁፉን ከመደብከው የሳይበር ቄሮ መሆንህ ነው እንኳን እንደሳቸው ለማስተማርያነት የተጻፈ ጽሁፍ ቀርቶ እንዳንተ ለመሳደብም ሀሳብንና መረጃን ማሰባሰብ ይጠይቃል።
    It is not at all recommended to stretch beyond your limit አንድ ቦታ የተመለከትኩ መሰለኝ ላንተ ከሰራ ላካፍልህ ብዬ ነው።የፖለቲካ ተንታኝህ ስዩም ተሾመ የፖለቲካ መሪዎችህ እነ ታየ/ሽመልሶች ከሆኑ የትምህርት ተቋምህም ድንቁ ደያስ ዩኒቨርስቲ ከሆነ አንተን ለማስተማር የምንደክምበት ምክንያት አይኖረንም በርትተህ ተሳደብ ማን ፈይሳ የተባሉት አዲሱ አምላክህ ይጠብቁህ። አደራ ጫት በልተህ ለስድብ አትሰማራ ሰላም ክረም

    • ምን ብዬ እንደ ተሳደብኩ አላወኩም። በሃሳቤ ላትስማማ ትችላለህ/ እንደፈለክም መጠምዘዝ መብትህ ነው። ነገር ግን እኔን “ተሳደብክ” ሳትል ዝም ብለህ ልትስደበኝ ስትችል ለምን በሃስት ትከሰኛለህ? በተልይ በአቢይ ጾምና በረመዳን ጊዜ ሲሆን ደግሞ ሰውን በሃስት መወንጀል ባያስቀጣም ይደብራል። ህሊናም ያቆሽሻል። ተው ግምኛ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share