“የማይቆነጥጡት ልጅ ሲቆጡት ያልቅሳል” ይባላል፡፡ እመለስበታለሁ፡፡
ከሰሞነኛ ጉዳዮች አንዱ አማራው በመላዋ ኢትዮጵያ የሚደርስበትን የዘመናት ግፍና በደል ማለትም መገደል፣ ከሥራና መኖሪያ መፈናቀልና ንብረት መዘረፍ እንዲሁም በቁም መቃጠል ለመቃወም በነቂስ ወጥቶ ያሳየው ፍጹም ሰላማዊ ሰልፍ ነው፡፡ እንደዚህ ያለ ሰላማዊ ሰልፍ ምናልባት አደጉ በሚሉ ሀገሮች ይታይ ይሆናል እንጂ በአፍሪካ የመጀመሪያ ሊባል የሚገባው ይመስለኛል፡፡ ይሄ ሰልፍ ደምቢዶሎ ላይ ቢሆን ኖሮ … ሆ! ምን አገባኝ ልጄ፡፡
በነዚህ የአማራ ሰልፎች በርካታ መፈክሮችና የብሶት መግለጫ ጽሑፎች ታይተዋል፡፡ ከነዚህ ሁሉ በጣም ትክክለኛ ሆኖ ያገኘሁት በኦቢኤን ጣቢያ በአባገዳዎች ሲመነዘርና ሲብጠለጠል የነበረው በርዕሴ ላይ ያስቀመጥኩት መፈክር ነው፡፡
የቃላት ስንጠቃ አያስፈልግም፡፡ ኦሮሙማ ማለት ልዩ ትርጉም እስካልተሰጠው ድረስ ሽመልስ አብዲሣና አቢይ አህመድ የሚያራምዱት በአጠቃላይ ኢትዮጵያንና በተለይ ደግሞ አማራን በቆንጨራና በሜንጫ ቆራርጦና በእሳት አንድዶ ከምድረ ገጽ የማጥፋት ዘመቻ የሚመራበት ትልቅ ፍልስፍና ነው – ከኦሮሞነትም ሆነ እኔ ከማውቀው ጤናማ ኦሮሞ ጋር ፈጽሞ አይገናኝም፤ ወዳጄ ፍቅሬ ቶሎሣና የአንድ ወቅት የሥራ ባልደረባየ ኮሎኔል ዱሬሣ ዋማ አማራን አሰልፈው አንገት ሲቀሉ ታየኝ፡፡ ጄኔራል ደምሴ ቡልቶና ጄኔራል ካሣየ ጨመዳ የአጣየን ከተማ ሲያነዱ ይታያችሁ፡፡ ጓደኛየ እሸቱ ቱራና በዝና ብቻ የማውቃት እህቴ ደራርቱ ቱሉ የአንፆኪያ ከተማን ከነኗሪዎቿ ሲያጋዩዋት ይታየን፡፡ … ስለዚህ ኦሮሙማ በደጉ ኦሮሞ ስም የሚሸቀጥበት የአቢይ አህመድ ሰይጣናዊ ፍልስፍና እንጂ ኦሮሞን የሚወክል አይደለምና በተለይ የሚዲያ አባላትና አካላት ይህን እውነት የማስረዳት ኃላፊነትና ግዴታ አለባችሁ፡፡ ይህ ፍልስፍና ከጥንቱ የኦሮሞ መስፋፋት ጋር እንኳን በምንም መንገድ የማይገናኝ ፍጹም ዲያቢሎሳዊ ፍልስፍና ነው፡፡ ኦሮሙማ በጥሬ ትርጉሙ ኦሮሞነት ቢመስልም ሃቁ ግን በኢትዮጵያችን በአሁኑ ወቅት በሰሜን ሸዋ፣ በመተከል፣ በሐረርና ድሬዳዋ፣ በወለጋ፣ በባሌ ወዘተ. ዐይኑን አግጦ የምናየው ዜጎችን በማንነታቸውና በዜግነታቸው እንዲሁም በሃይማኖታቸው ምክንያት የፌዴራሉና የኦሮምያ ክልል በሚያቀርቡለት ዘመናዊ የጦር መሣሪያና በባህላዊ ሜንጫ አማራን መጨፍጨፍ፣ ሕጻናትንና ሴቶችን በቤት ውስጥ ቆልፎ ማቃጠል፣ ሀብት ንብረትን መዝረፍና ከተማን ውደማ ማድረግ ነው፡፡ ይህ ያልወደመ ማን ይውደም ታዲያ? ይህ ፍልስፍና እንዲጠፋ ካልተዘመተ በማንና በምን ላይ ይዘመት? ኦሮሙማ የኢትዮጵያውያን የኅልውና ሥጋት እንደመሆኑ ከይውደም መፈክርም ባለፈ ሁሉም በሞረሽ ተጠራርቶ ከአሁኑም በባሰ ብዙ ጠባሳ ሣያሳርፍብን በቶሎ መደምሰስ ይኖርበታል፡፡ አለበለዚያ ማንም አይተርፍም፡፡
“ፋሽዝም ይውደም፤ ጣሊያን ትቅደም!”፤ “ናዚዝም ይውደም፤ ጀርመን ትቅደም!”፤ “ጽዮናዊነት ይውደም፤ እሥራኤል ትለምልም!” ብሎ መመኘትም ሆነ ለእውናዊነቱ መታገል ስህተቱ እምን ላይ ነው? እርግጥ ነው ለፋሽስቶች መፈክሩ የሞት መርዶ ነውና አይወዱትም ብቻ ሳይሆን አምርረው የሚፋለሙት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ አሁን የምናየው የኦሮሙማ እንቅስቃሴ የኦሮሞነት ወይም የኦሮሚያ ተብዬው ወያኔ-ሠራሽ ክልል መገለጫ እንዲሆን ካልተፈለገ በስተቀር በምንም መንገድ ኦሮሙማ ማለት ኦሮሞ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ ኦሮሞና ኦሮሙማን መለየት ያሻል፡፡ በተጠቀሰው ቲቪ ቀርበው ራሳቸውን ለትዝብት የዳረጉ አባ ገዳዎችም ይህን እውነት ካላወቁ ዘመድ አዝማድ ይምከራቸውና እንዲረዱት ይደረግ፡፡ ደግሞም ከአንድ ምንጭ እንደሰማሁት እነዚህ አባ ገዳዎች በቃላት ስንጠቃ የአማራን ሰልፎች አወገዙ እንጂ የሰልፎቹን ምክንያት ጠቅሰው ለአማራ ሕዝብ መጨፍጨፍ አንዳችም የሀዘን ስሜት አልገለጹም፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ መጨካከን አያቀባብርም፡፡ ኦሮሞና አማራ የተዋለደና ብዙ የጋራ ሕይወት ያሳለፈ፣ አሁንም እንኳን ቢሆን የላይኞቹን የተጠየፈው የታችኛው ክፍል (ሕዝቡ) በአምቻ ጋብቻ የሚተሳሰርና በዕድሩም፣ በዕቁቡም፣ በፅዋ ማኅበሩም፣ … አብሮ የሚኖር ሠርገኛ ጤፍ ነው፡፡ ወደፊትም መቼም ቢሆን አንለያይም፡፡
ወደተረቴ ልመለስና ነገሬን ልቋጭ፡፡ “የማይቆነጥጡት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል” እንዲሉ የሻዕቢያን የመቶ ዓመት የቤት ሥራ ከወያኔዎች በልዩ ብልጠት በመረከብ ተሸክመው የሚንከራፈፉት ኦሮሙማዎች (ኦሮሞዎች አላልኩም!) አማራንና ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በኢትዮጵያ ምክንያት እንዳሻቸው መግደልንና ማፈናቀልን እንደመብት ስለወሰዱት እንደምናየው ቃላትን በመሰንጠቅና በትክክለኛ አጠቃቀማቸው ለመረዳት ባመፈለግ የአማራን ሕዝብ ሰልፎች በመፈክሮች ብቻ ምን ያህል ለማጠልሸት እየተራወጡ እንደሆነ በአግራሞት እያስተዋልን ነው፡፡ ይህን ክስተት “የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ” በሚለው ብሂል መግለጽ እንችላለን፡፡ አማራ ደግሞ ለተረት – “እናቱ ወንዝ የወረደችበትና (እናቱ) የሞተችበት እኩል ያለቅሳሉ” ብለንም ነገራችንን ይበልጥ ሕይወት መስጠትም ይቻላል፡፡ እስኪ አሁን ምናቸው ተነካ? እነሱ በተረዱት መንገድ ብንወስደውስ ከመሳደብና አንገትን ከመቁረጥ የትኛው ኃጢኣት ነው የሚከፋው? “አፈር ያብላህ” ብሎ መሳደብና የእርጉዝ ሴት ሆድ ቀድዶ ጽንስን ለሟች እናት ማስታቀፍ፣ ንጹሓን ዜጎችን ቤቱ እንደሞላ ጠቅጥቆ በእሳት ማንጨርጨር ምን ምን ናቸው? በተገኘው ዱላና ዘመን ባፈራው የጦር መሣሪያ ለዐርባና ሃምሣ ዓመታት ሲቀጠቀጥ የነበረ አንድ ሰው ደብዳቢውን ወይም የደብዳቢውን አባትና እናት ድንገት በንዴት ሳት ብሎት አንዳች ክፉ ቃል ቢናገር ነገርን ሆን ብሎ በማጋነን የበዳይን እንከን በተበዳይ ትንሽ ግድፈት ሳቢያ በማጠየም የጥፋተኝነትን ሚዛን ለማስጠበቅ የሚደረግ አጉል መውተርተር ካልሆነ በስተቀር ስህተቱ እምን ላይ ነው? ይህን ስል ታዲያ እነሱ በወሰዱትም ቢወሰድ ማለቴ እንጂ አማሮች እንዲህ ያለ ቅሌት ውስጥ ለመግባት ያቺን ጦሰኛ መፈክር እንዳልጻፉ መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ፡፡ በአንዱ ሰልፍ ላይ የኦሮሚያን ባንክ እንዴት ይጠብቁ እንደነበር አላያችሁም? “አማራነት የሰውነት የውኃ ልክ ነው” ሲሉ በዚያን ሰሞን ሰምቼ “ጉረኞች!” ብዬ ስቄባቸው ነበር፡፡
ይልቁንስ አራጆች ሆይ! ለማይቀረው አርማጌዴዖን ተዘጋጁ፡፡ የእስካሁኑ መንገድ ለእናንተ ቁልቁለት ነበር፡፡ ከአሁን በኋላ ያለው መንገድ ደግሞ ለእናንተ አቀበት ሲሆን ለታራጆች ግን ቁልቁለት ነው፡፡ ትንሽ ጊዜ እንዳለቻችሁ ብደብቅ ግን እናንተ ራሳችሁም ትታዘቡኛላችሁ፡፡ በሉ ግድያውንም ቃጠሎውንም ተል ተሎ ቀጥሉ፡፡ ማንና ለምን ዓላማ እንደላካችሁ ስለምረዳና ምክር የማይመልሳችሁ የሥነ ልቦና ደዌ ሰለባ እንደሆናችሁ ስለምገነዘብ “እንዲህ አድርጉ፤ እንዲህ አታድርጉ” በሚል ምክሬን አላባክንም፡፡ ይቅናችሁ፡፡