ይድረስ ለሻለቃ ዳዊት – ሰለሞን ሥዩም ሲያትል፣ ዋሽንግተን

የሻለቃ ዳዊት አስተያየት በጣም ያሳዝናል። ብዙ ልምድ፣ ረዥም ዕድሜ፣ እና የውትድርና ብቃት ያላቸው ሻለቃ ዳዊት በዚህ ሀገር በውስጥና በውጪ ጠላት በተከበበችበት፣ የሰዉ ስሜት በጦዞበት ክፉ ጊዜ፣ የሰከነ አስተያየት ይዘው የሚያረጋጋ የሚያበረታታ በሳል ሀሳብ ይዘዉ ኢትዮጵያ በድል አድራጊነት ፈተናዋን በምትወጣበት መንገድ ላይ ይናገራሉ ብዬ ስጠብቅ መሬት የሚነቀንቅ ሰልፍ አድርጉ፣ አማራ፣ ጉራጌ እና ኦርቶዶክስ ለአመጽ ተነሱ ብለዉ መጡ። ይባስ ብለዉ፣ እንዴት አርጎ አማራና ኦሮሞ አብሮ ይኖራል፣ እንዴት አርጎ አማራና ትግሬ አብሮ ይኖራል፣ ብለዉ በመጠየቅ አብሮ ተደጋግፎ የሚኖረውን ህዝብ የማጋጨት ፍላጎት ያለው የሚመስል ጥሪ አደረጉ። የችግር ትንተናቸዉም ላይ አፍራሽ ሚና በመጫወት ተጠያቂ ያደረጉት 1ኛ አቢይን ሲሆን 2ኛ ህዝቡን፣ ዝም ብሎ የሚያጨበጭበውን እርሳቸዉ እንደሚሉት። ኃላፊነት የጎደለው፣ ሀገር የሚያሳጣ እና ህዝብን ከህዝብ የሚያጫርስ ከፋፋይ አስተያየት ነው።

https://youtu.be/2X2UIvv6JAc

ከኢትዮጵያ መንግስት ይልቅ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለጣሉት ለአሜሪካ እና ለግብጽ በጎ አስተያየት አላቸው። ሁለቱም ኢትዮጵያ እንድትፈርስ አለመፈለጋቸዉን ይነግሩናል። አንድም ጊዜ ለዚህ ሁሉ አበሳ ኢትዮጵያን ያበቃዉን ወያኔን ሲያወግዙ አልተደመጠም። የሱዳንንም ሆነ የግብጽን ቀጥታ እና እጅ አዙር ጫና (እንደምንሰማው አስታጥቆ ተዋጊ እስከማሰረግ የደረሱትን) ሲያወግዙ አልተሰማም። የኦሮሞ ጽንፈኛ ኮርማዎች ከውስጥ እና ከውጪ ሀይሎች ጋር ሆነው የተያያዙትን በጭካኔ የተሞላ ዘግናኝ ቅስቀሳ እና ጭፍጨፋ አላነሱም።

መንግስት ፋታ አጥቶ ጥርሱን ነክሶ በተለያየ ግንባር ፍልሚያ በገጠመበት በዚህ ወሳኝ ሰዓት እርሱን አፍርሶ እርሳቸው አዘጋጅቼላችኋለሁ የሚሉት “ካውንስል” መኖሩን ያስረዱናል። ከመንግሥት ጋር የቆመዉ ከሀዲ ነው ይላሉ። የሚያስደንቅ ነው። ምን አጀንዳ ቢይዙ ነው ሻለቃ እንዲህ በርቀት ሄደዉ መስመር የለቀቁት? ይሄ ንግግራቸዉ ልዩነታቸውን እና ህመማቸውን በጉያቸው ይዘው “ተነስ፣ ታጠቅ፣ ዝመት” ጥሪ ተቀብለዉ ዛሬም እንደትላንቱ ዉድ የህይወት ዋጋ ከፍለዉ ኢትዮጵያን ከአደጋ በመታገድ ላይ ላሉት የመከላከያው እና የሚሊሻውን ወገኖቻችንን መስዋዕትነት ማርከስ መሆኑስ እንዴት አልታያቸዉ አለ? እኚህ ሰዉ በወታደሩ ቤት ዉስጥ አድገው ከፍተኛ ቦታ የደረሱ ሰው በመሆናቸው ከሌላዉ ሰዉ በተሻለ የችግሩንና የመስዋእትነቱን ክብደት ይረዳሉ ተብሎ ስለሚገመት ከርሳቸዉ የምንጠብቀው ሀሳብ ምንም ያህል ቢጎረብጥ እንኳን በዚህ ደረጃ የወረደ ይሆናል ብሎ መገመት ፈጽሞ አይቻልም ነበር።።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኮሮና "ኩሩና" እና "ይህም ያልፋል" - መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

በአብዛኛዉ አማራውን ታርጌት ያደረገዉ ይህ ሁሉ እልቂት አንዴ በኦሮሞ ጽንፈኛ፣ ሌላ ጊዜ በወያኔ፣ ከዚያም ሲተርፉ የጉሙዙ ሽፍታ ቀዮቹ እያለ እየተፈራረቁ የሚጨፈጭፉበት የጭካኔያቸዉ ምስጢር የኢትዮጵያን መንግሥት የማፍረስ አላማ ያለው መሆኑን ጀማሪ የህግ ተማሪም ሆነ ፓለቲከኛ ሊረዳዉ እየቻለ ሻለቃ በእዉነት መገንዘብ አቅቷቸው ነው ወይንስ ሳይፈልጉ ቀርተው? በምን ምክንያት? ከጥቂት አመታት በፊት አዲስ እበባ በተዘጋጀዉ የቪዥን ኢትዮጵያ ፕሮግራም ላይ የኢትዮጵያን አንድነት ለመጠበቅ ሲባል ጠ/ሚሩ ሕገ መንግሥቱን ቸል ብለዉ ፓርላማዉን በትነዉ በኃይል እንዲገዙ መክረዉ እንደነበረ ይታወሳል። ከምክርም ባለፈ ጠ/ሚሩ ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ከሀገር ስለማይበልጡ ለሚችል ሰዉ ቦታ እንዲለቁ አሳስበዉ ነበር። ከዚህ ሁሉ በሁዋላ ለምን ጠ/ሚሩ አግኝቶ አላነጋገረኝም ማለታቸዉ ግራ ያጋባል። ሻለቃ የሚሉትን ብለዉ ጨርሰዉ ነበር።

ከዚያ ጊዜ የጀመረ በተለያየ መድረክ ላይ እየቀረቡ ብዙ ማብራሪያ ሰጥተዋል። መንግሥትን በማብጠለጠል በተካኑት በርእዮት ሚዲያ፣ በኢትዮ ፫፷ እና በተወስነ ደረጃ በአባይ ሚዲያ ላይ መደበኛ ተጋባዥ እንግዳ እየሆኑ በመቅረብ በመንግሥት ላይ የሰላ ትችት ሲያቀርቡ መቆየታቸዉ ይታወቃል። ይሄ ግን ችግር አልነበረዉም። ችግሩ ከርሳቸዉ በሚጠበቅ ደረጃ ኢትዮጵያ የነበረችበትን ፈተና አለመረዳቱ ላይ ነዉ። ጠ/ሚሩ እንኳን ሀገር ቤተስባቸዉን ለማስተዳደር ምን ያህል ሲቸገሩ እንደነበረ በቅርብ ጊዜ አስረድተዉ ነበር። ወያኔ ባዶ ካዝና ባዶ ሀገር ትቶላቸዉ ነዉ ሄዶ የመሸገዉ። በሰሜን እዝ የሚገኘዉ ጠንካራዉ የሀገሪቱ መከላከያ ኃይል የታገተ በሚመስል ደረጃ እንዳይነቃነቅ ተደርጎ መቶ በመቶ አመራሩ በወያኔ ሰዎች እንደተያዘ ነዉ። ጥ/ሚሩ በምስጢር ጭምር ነበር የሀገሪቱን መከላከያ እያዋቀሩ የነበሩት። ወያኔ በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ሲከፍት ገና ተጨማሪ የዝግጅት ጊዜ ያስፈልጋቸዉ እንደነበር ያስረዱት የሚታመን ነዉ። በአደባባይ ባቀረቡት የስታትስቲክስ መረጃ መሰረት ከሰሜኑ እዝ ዉጪ የኮማንድ ፖስት እና የሜካናይዝድ ባታሊዮን አመራር መቶ በመቶ ለወያኔ ታማኝ በሆኑ አባላቱ እጅ እንደነበረ አሳይተዉ ነበር። ከዚያም ዉጪ ከመከላከያዉ ዋና መ/ቤት (ሄድ ኳርተር) ጀምሮ በተለያዩ ክፍሎች ዉስጥ እስከ ሰማንያ አምስት በመቶ ድረስ ቁልፍ የኃላፊነት ቦታዎች የተያዙት በሚታመኑት የወያኔ ሹማምንት መሆኑ ተዘግቧል። በዚህ ሁኔታ ዉስጥ የሻለቃ ምክር ውሃ የሚያነሳ ሊሆን አይችልም። ማንን የዘዉ ነዉ በጉልበት የሚገዙት፧ ስብጥሩ ኢትዮጵያን የመሰለ እምነት ሊጣልበት የሚችል የሀገር መከላከያ አልነበረም። ለዚህም በቂ መረጃ የሚሆነዉ ህወሀት አብሮ የኖረዉን የሰሜን እዝ ባልደረቦቹን በሌሊት ከቦ መረሸኑ ነዉ። ሻለቃ በፊት

ተጨማሪ ያንብቡ:  40ኛው የህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ እና “ልማታዊው ሲኖዶስ”

አልገባቸዉም ነበር ቢባል እንኳን አሁን ይሄንን ሁሉ ካዪ በኋላ እንዴት መመለስ እንዳቃታቸዉ የሚያዉቁት እርሳቸዉ ብቻ ናቸዉ።

ሌላዉ ሊሰመርበት የሚገባዉ ነገር ይሄ ሁሉ እልቂት የሚደርሰዉ መንግሥት የገዛ ህዝቡን መጨፍጨፍ ፈቅዶ ነው የሚል አንድምታ ያለዉ የተዛባዉ አረዳድ ነዉ። እንዲህ ማለቱ ህዝቡን ለመታደግ ውድ የህይወት ዋጋ የሚከፍሉትን የመከላከያ እና የሚሊሺያ አባላት ክብር የሚያጎድፍ አሳዛኝ አስተያየት ነዉ።

ከጋዜጠኛ አበበ ጋር በነበራቸዉ በዚህ ቆይታቸዉ ሻለቃ በወያኔ፣ በኦሮሞ ጽንፈኛ፣ በግብጽ፣ በሱዳን፣ ወይንም ጫናቸው በበረታው ምዕራባውያን ላይ ሳይሆን የክስ መዝገባቸዉን እያዘጋጁ ያሉት የኢትዮጵያን መንግሥት ህግ ፊት ለማቆም መሆኑን ነው የሚገልጹልን። የተሰሩ ወንጀሎችን አጣርቶ ፍትህ መጠየቅ በማንኛውም ጊዜ የተገባ ነው ብቻ ሳይሆን መቅረት የለበትም። ግን ለኢትዮጵያ ይሄ ሰዓቱ አይመስለኝም። የግድቡ ሙሊት እና ምርጫው ከመድረሱ በፊት የውስጥ እና የውጪ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ግልጽ ጦርነት በገጠሙበት በዚህ የሞት ሽረት ሰዓት ከነችግሩ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መቆም አለመቻላቸዉ ግራ የሚያጋባ ነው። በዚህ ወሳኝ ገዜ እምቢተኛ ሁኑ ብሎ ወጣቱን መቀስቀስስ እንደ ክህደት አይቆጠርም? ያዉም ከወታደር? በእኛ ዕድሜ እንኳን የምናዉቀዉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ጊዜ ታሪክስ እንዲህ ያለዉን ክህደት ይፈቅዳል?

ጋዜጠኛው አበበም ሻለቃ ያዘጋጁልን “ካውንስል” ምን እንደሆነ መጠየቅ ስለሚገባዉ ይሄንን አጣርቶ እንደሚያመጣልን ተስፋ አደርጋለሁ። ነገር ግን አበበ በዩቲዩብ ላይ የጫነዉን ቪዲዮ “ሻለቃ ዳዊት ውልደጊዮርጊስ ሃቁን አፈረጡት” ከሚለዉ፣ “ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በሀቅ ፈረጡ” ቢለን ለእዉነት የቀረበ ይሆን ነበር። ስለቃላት ምርጫዬ ትልቅ ይቅርታ እጠይቃለሁ። በአበበ በኩል ፕሮግራሙ ሲጀመርም ሆነ በየመሀሉ የሰልፉን ቪዲዮ እያስገባ፣ የሺመልስን አፍ እላፊ እያቀረበ፣ መንግስትን መኮነን እና ከፋፋይ መልዕክቶችም መደጋገማቸዉ አስፈላጊ የነበረ አይመስለኝም። ጉዳት አለዉ። እንዲህ ያለዉ አቀራረብ በዚህ ቁርጥ ሰዓት የስሜታዊዉን ወጣት ስነልቡና ሰልቦ ትጥቅ ከማስፈታት እና ሀገሪቱን ከመጉዳት ያለፈ ፋይዳ የለዉም። በአማራው ወገናችን ላይ አላባራ ብሎ በተደጋጋሚ የሚደርሰው ጭፍጨፋ ምስጢሩ በርግጥ የአማራ ጥላቻ ነው ወይንስ ይህንን ክቡር ህዝብ አስቆጥቶ ከወገኑ በማባላት መንግሥትን ከተቻለ ለመጣል እና በካዉንስሉ መተካት፣ ካልሆነ በድርድር (በምርጫ ሳይሆን) ቦታ ለመያዝ የሚፈልጉት ሀይሎች ሴራ ነው? ይሄ ቡድን ህወሀትን እና ደጋፊዎቹን፣ የኦሮሞ ጽንፈኞችንን (ምናልባትም የሀይማኖት አጀንዳም የያዙትን ይጨምራል) እና የግድቡን ሥራ ማስተጓጎል የሚፈልጉትን አጥፊ የዉጪ ሀይሎች አንድ ላይ አምጥቷል። ይሄ በዉይይቱ አልተነሳም። ከነዚህ ባላነሰ ሁኔታ በየደረጃው ባሉ የመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ ተሰግስገው የተሳካ ምርጫ ከተደረገ ቦታ የለንም በሚል ስጋት ከእኩይ ቡድኖች ጋር የተሰለፉት ደካማ ኃይሎችም ለመንግሥት ተጨማሪ ፈተና መሆናቸውም ፈጽሞ አልተነሳም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  መስቀልን:- ከሺሕ ዘመን ታሪካችን እና ከኢትዮጵያ ቤ/ክ አንጻር በጨረፍታ. . . በዲ/ን ተረፈ ወርቁ

ሻለቃም ሆነ አበበ ይህንን የተዛባ አስተያየት እና ያልተገባ ቅስቀሳ አስተካክለው ሚዛናዊ ዘገባ እንዲያቀርቡ በአክብሮት እጠይቃለሁ።

ሰለሞን ሥዩም
ሲያትል፣ ዋሽንግተን

https://zehabesha.info/amharic/archives/116782

 

https://amharic.zehabesha.com/explainer-why-ethiopias-federal-system-is-deeply-flawed/

 

11 Comments

  1. ሰለሞን፣ የ አማራው ህዝብ ዕልቂት ግድ የሚልህ አይመስለኝም። ሙሉ በ ሙሉ ባይሆንም የ ሻለቃ ዳዊትን ቃለ ምልልስ ከ አበበ በለው ጋር ተመልክቼዋለሁ። ዋና መልዕክታቸው የነበረው አቢይ ለ አማራ ህዝብ ዕልቂት ምክንያት ና አስፈጻሚ መሆኑን ነው። አማራ እየተፈጀ ያለው በ ኦሮሙማ መስፋፋት ዕቅድ ምክንያት ነው። ለ መሆኑ ሰሜን ኦሮሚያ ብለው ያወጡት ካርታ እስከ ትግራይ እንደሚደርስ ታውቃለህ? አማራ እየታረደ ያለው መሬቱን ለ መቀማት ባወጡት ዕቅድ ምክንያት እንጂ የ ውጪ ጠላት የሚባለው ሽፋን ነው። አላማቸው አማራን፣ ቤኒሻንጉልን፣ ደቡብን፣ ጋምቤላን እና አፋርን የ እነሱ ማድረግ ነው። በ አማራ ላይ የከፋ ነው እንጂ የሚዋሰኑዋቸው ክልሎችን ሁሉ እየወጉ እና እየገደሉ ነው። ለመሆኑ ለምን ይመስልሃል 34 ዙር ልዩ ሃይል ያሰለጠኑት? በተቃራኒው አማራን ለምን አሰለጠናችሁ ብሎ ገደላቸው።
    አቢይ ለ ኢትዮጵያ የሚያስብ ከሆነ ወደ 300፣000 የሚጠጋ ልዩ ሃይሉን ተጠቅሞ ሱዳንን ከ እትዮጵያ ምድር አያስወጣም? አቢይ ያለውን ሰምተሃል? የሚፈልጉትን እያልናቸው የምንፈልገውን እንሰራለን ነው ያለው። ከ እንደዚህ አይነት መሪ ምንም አይነት ነገር ለ ኢትዮጵያዊያን አይጠበቅም።

  2. Solomon Seyoum,

    Playing game on Amara blood! Aka Solomon does not care about the millions of Amaras massacred since Gragn Abiy Ahmad came. Amaras take a note of aka Solomon Seyoum. I tell you take a note of him! Graziani is better than this devil.

  3. አቶ ሰለሞን
    “ብዙ ልምድ፣ ረዥም ዕድሜ፣ እና የውትድርና ብቃት ያላቸው ሻለቃ ዳዊት” ታልክ ተክቡር ሻለቃ ዳዊት መማር እንጅ ምን በአማራ ሬሳ መሳለቅ ያስፈልጋል?

    እናንተ ሰዎች በሞቶ ሺዎች ያለቀን አማራ ሕዝብ እንደ ጉንዳን ነው የምታዩት ልበል? ያንተ አይነቱ ሰይጣን አስትያየት ያላሸፈተ ምን ያሸፍታል?

    ጣልያን የእርጉዝ ሆድ ቀዶ የኣማራ ዘር አጥፍቷል ወይ? የሚያሳብድ ነገር እኮ ነው የጣፍከው! እሁሁሁሁ! አቃጠልከኝ! ሲያል ያላችሁ አማሮች ይኸንን ሰውየ ታውቁታላችሁን?

    • Mulu,
      እውሸት ነው አልተቃጠልክም። አባላሁዋቸው፣ አለቆቼ የሰጡኝ የእሳት እና ጭድ ፕሮጄክቴ ሰራ ብለህ ጮቤ እየረገጥክ ነው:።
      ማንነትህን “ሞቶ ሺዎች” ስትል ነው አሳልፈህ የሰጠኸው።

      በአማራው ደም መነገድ ይብቃ!

      • አቶ ሰለሞን ከጠበኩትም በላይ ጅል ነህ!

        ገና ለገና “ሞቶ” አለ ብለህ ወያኔ አርገኸኝ ቁጭ አልክ፡፡ የሆሄ ግድፈት ነው ብሎ የማሰብ ሌላ መንገድ የለም ባንተ ብላሽ ጪንቅላት፡፡ እሽ አሁን መቶ አልኩልህ ወያኔ ነኝ ወይስ ወያኔ አይደለሁም፡፡ አጣዬ ሕጻናትን ያረዱትና ያሳረዱት ወያኔዎች ናቸው ለማለትም ይቃጥሃል፡፡

        አማራ በጪራቆች ታርዶ ይልቅ አንተ ሰላሳ ሁለት ጥርስህን እያሳየህ ገልፍጥ! ይኸንን በአማራ ደም የሚቀልድ የተረኞች ቱልቱላ የሚቋቋም ሲያትል አማራ የለም ማለት ነው? ወይ ነዶ!

  4. አቶ ሰለሞን፣ ስምህ እንኳን የአማራ ይመስላል። ግን የአማራ ጠላት ነህ። የአማራ ክልል ገዢዎችም የአማራ ብልፅግናዎች ተመሳሳይ ሃሳብ ይዘው ይሄው ህዝብ ያሰጨፈጭፋሉ። ዘር ማጘጥፈት ቃሉ ሲያንሰው ነው። እንዲያውም ሻለቃ ዳዊት ስነ ምግባር ስላላቸው ምክናታዊነትን በመመርኮዝ አይን ገላጭ ቃለምልልስ ነው ያደረጉት።
    ፍትህ ሲወርድ አንተና መሰሎችህ የቅጥር ሳይበርድ ወታደሮች ለፈፍርድ መቅረባችሁ አይቀሬ ነው። ይሄ ዘረኛ መንግስትም እንዲህ በ3ዓመት ያበጠው የመጥፊያውን ጊዜ እያፋጠነ ነው። ህወሓትም እንደ ብጉንጅ አብጣ ፈርጣለች።
    ሻለቃ ዳዊት ከዚህ የበለጠ ህዝቡን ማነሳሳት ነበረባቸው ።አማራ የሚድነው በሚያደርገው አመፅና በሚሰጠው መልስ ምት ነው ።ከዚህ ያነሰው ሂደት ቀልድ ነው። አሁን አማራ ሕዝባችን እየሞተ ነው ። መልሱ ተዳርሷል።

  5. ጠቅላይ ሚስትሩ ለፍርድ መቅረባቸው አይቀርም። ኢትዮጵያውያንን በቂቤ ምላሳቸው እያደነዘዙ ቢከርሙም እውነታው መሬት ላይ ፍንትው ብሎ እየታዬ ነው። እስካሁን ኢትዮጵያ ያልፈረሰችው አማራው ለእናት ሀገሩ ካለው ጥለቅ ፍቅር እንጅ እንደሚሰራው ቢሆን ነገሩ ሌላ ነበረ። ይሄኛው ትውልድ እንደዚያኛው ትውልድ ከርሳምና በኢትዮጵያዊነት ካባ ተጀቦኖ የሚያልቅ እንዳይመስልህ። ለሁላችንም ያልሆነች ሀገር ምን ልትረባን ጃል። ሚሊዮኖች ሜዳ ላይ ሲወድቁና በመቶ ሺዎች በአደባባይ እየተገደሉና እየተቃጠሉ አንዴ እንኳን ለማውራት የማይፈልግ መሪ ነው ሀገር የሚያድነው??? የቤተ መንግስት አጠር ካስጣላቸው የምናየው ይሆናል።

  6. Solomon,

    I respect your right not to agree with Shaleka Dawit. However, what should the Amhara people do if the government does not protect them? Is not it their birth right to defend themselves? Did any of the other regions in Ethiopia condemn the genocide of Amharas? Did any oromo party, ruling or in opposition, condemn the killing of Amharas by olf murderers in the bilgina party and outside??

    You just spit your hate on Ahaleka without telling us what alternatives the Amhara people have to avoid being killed by fascist olf.

  7. አቶ ሰሎሞን ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊወርጊስ ስለሰጡት አስተያየት ክብርና ማዕረጋቸውን ሣይደፍር በክብሮት ያመነበትን አስተያየት ለአንባብያን አቀረበ።እንዲሁም ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊወርጊስ በስራ ዘመናቸው ማለትም በኤርትራ ሁለተኛ ክፍለጦር ይባል በነበረው ፤በደርግ ዘመን ደግሞ የሰሜን እዝ ይባል በነበረው የክፍል ሃላፊ በነብሩበት ወቅት ፤በደርግ ቀይ ሽብር የያ ትውልድ በቀበሌ አብዮት ተባቂዎች እንደ ቅጠል በረገፈበት ወቅት የፈጸሙት እና ያስፈጸሙትን ተግባር ወደኋላ በመተው ወይም ባለማንሳት፤የእርዳታ ማስተባበሪያ ኮሚሺን በነበሩበት ወቅትም የፈጸሙት እና ያስፈጸሙትን ተግባር ባለማውሳት በአሁኑ ወቅት ሻለቃው የሰጡትን አስተያየት አቶ ሰሎሞን በመልካም ስነምግባር እንዲሁም ለመላው ህዝብ መልካም ምክር እና አስተያየቱን በሰነዘረ ስህተቱን ማረም ይገባል ብየ አምናለሁ። በመዘላለፍ ስህተትን ማረምም ሆነ መታረም የሚቻል አይመስለኝም እና እባካችሁ ይህን የሃሣብ መግለጫ መድረክ የእንካ ሰለኬንታ መድረክ አይሁን።ከላይ የተጠቀሱት የስድብ እንክብሎች ቀዳዳ ከመድፈን ይልቅ እፉኝቶችን የፈጥራልና መዘላለፉ ቀርቶ መመካከሪያ መድረክ ይሁን።

    • Mr. A. Bekele, you are worse than Solomon Seyoum, Little man, you think you are smarter than other readers and you filled out what the anti-Amara Solomon left blank to belittle the very important cause Shaleqa Dawit stands for.

      Are you guys insane? To what extent you hate Amaras and you want them perish every day? What should Amaras do other than fight back when they are massacred and buried in mass every day?

  8. ሻለቃ ዳዊት ላይ የሚካሄድ ዘመቻ ለሚጨፈጨፍ አማራ የሚጮህለት ስለሌለ የአማራን ድርጅት መሰረትኩ ያሉት ፕ/ር አስራት ላይ የጎሳ ፖለቲከኞች ያደረሱባቸውን ማዋከብ አስታወሰኝ::ፕ/ር አስራት የሃገሪቱን የመጀመሪያ የህክምና ኮሌጅ የከፈቱ የነኮፊ አናን ባልደረባ ታስረው ለሞት የበቁ ሰማእት ነበሩ::በኤርትራ ጉዳይ ምክራቸው ሰሚ አጥቶ ያ ሁሉ ወገን አለቀ ጦሱ ዛሬም አለ::በዘሩ የተነሳ ለሚታረድ አማራ ሻለቃ ዳዊት ያደረጉት ተሟጋችነትና የአብይ አህመድ ወገናዊ መንግስትን መንቀፋቸው ተገቢ ነው::
    የአጣዬ ዘግናኝ ጭፍጨፋና የከተማ መውደም ሳይከሰት አባገዳ ሰንበቶ ለጀርመን ድምጽ በዚያ የተደራጀ ሸማቂ መኖሩን ሲጠቁሙ የአብይ ጄነራሎች ብርሃኑና ጌታቸው ተሳለቁበት::ጥቆማው ቢሰማ ከተደራጀው ገዳይ እልቂት ህዝባችን ይድን ነበር::እንረዳለን::ስለሻለቃ ዳዊት የኤርትራ ጸሃፊ የመሰከረው እነሆ :-
    https://amharic.zehabesha.com/major-dawit-woldegiorgis-red-tears/

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share