ንቁ ! አትዘናጉ ! ኤች አይ ቪ -ኤድስ ዛሬም እየተስፋፋ ነው ና ! – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ዛሬ ህዳር  22/2013 ዓ/ም ነው፡፡በዓለም ደረጃ የሚታወስ የኤች አይ ቪ – ኤድስ ቀን፡፡ ይሁን እንጂ ፣ቫይረሱን በጋራ ለመከላከል የገባነውን የቀደመ ቃል ኪዳን  የምናድስበት ቀን መሆኑን ብዙዎቻችን ፈፅሞ ረስተነዋል፡፡ በእርግጥ የብዙዎቻችን አእምሮ የተወጠረው በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ላይ መሆኑ ይታወቃልና ይህንን እምብዛም ሳይታወቅ አዘናግቶ ገዳይ በሽታ ረስተነዋል፡፡ይህንን  መድሃኒት አልባ በሽታ መዘንጋታችን ባይፈረድብንም ፣ዝንጋኤአችን ግን ዋጋ እንደሚያስከፍለን ዛሬ የምንገነዘብበት ቀን ነው፡፡

ይህ ዝንጋታ ነገ ወጣቶቻችንን በመጨረስ የማየቀለበስ ዋጋ እንዳያስከፍለንም ዛሬ ነው መቃትና ቫይረሱን መዋጋት ያለብን፡፡  በቀጥታ ይህንን ደዌ ለመከላከል የተቋቋሙ ተቋማት ፣የህክምና ባለሙያዎች ና ህዝብ ቆም ብሎ በአንክሮ በማሰብ ፣ የዓለም ጤና ጥበቃ በ2030 እኤአ  የበሽተውን ተጠቂ  ወደ ዜሮ ለማምጣት ያቀደው እቅድ በእኛም አገር እንዲሳካ የበኩሉን አበርክቶ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

…ዛሬ በኮቪድ  (COVID-19 ) ሰበብ  የኤች.አይ.ቪ ወረርሽኝ ጉዞ ፍጥነቱ   ምክንያት ጨምሯል፡፡ በይበልጥም አቅመ ቢስ በሆኑ አገር ህዝቦች  ላይ አስከፊ ገፅታው በድጋሚ ሊታይ በቋፍ ላይ እነደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህንን እውነቱ የዓለም ጤና ድረጅት ዘግቧታል እኔም በህክምና ባለሙያነቴ ለኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ ተርጉሜ አቅርቤለሁ፡

እንሆ ዘገባው

በ 2019 በኤች አይ ቪ   የተያዙ 38 ሚሊዮን ሰዎች ነበሩ ፡፡ ዛሬም በኤች አይ ቪ ከተያዙ ከአምስት ሰዎች መካከል አንዱ ስለ  ህመሙ የማያውቅ ሲሆን ፣ የኤች አይ ቪ ህክምና ከሚወስዱት  3 ሰዎች መካከል አንዱ  የኤች.አይ.ቪ ህክምና አገልግሎት ችግር የጋጥመዋል፡፡ይህም የሚሆነው ፣ የምርመራ እና የመከላከያ አገልግሎቶች አቅርቦት በበቂ መጠን ባለመሰራጨቱ ነው፡፡ በተለይም ህፃናትንና ጎረምሳዎችን ይህ መሰናክል ክፉኛ ይጎዳቸዋል፡፡ በዚህ  ምክንያትም  690 000 ሰዎች በዓለማችን ከኤች ኤይ ቪ ጋር በተያያዘ ህመም ሞተዋል፡፡ 1.7 ሚሊዮን ሰዎችም  በ2019  በኤች አይ ቪ መያዛቸው ተውቋል፡፡ከ3 ሰው አንዱ ማለትም  (62%)  ወጣቶችና የመስራት አቅም ያላቸው ጎልማሶች እንደሆኑም ታውቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ራስዎን በሁለት ቦታ የማስገኘት ጥበብ

ይህ አሃዝ 2020 የዓለም ጤና ጥበቃ ዕቅድ   ከወዲሁ መክሸፉን አረጋግጧል፡፡እንደምታውቁት በ2020  ” 90-90-90”ን ለመተግበር እቅድ ተይዞ ነበር፡፡   ይህንንም ለመተግበር አገራት ሲንቀሳቀሱም ነበር፡፡ ይህ የ2020 እቅድ      በዓለም ላይ የሚኖሩ. 90% ሰዎች  ከኤች አይ ቪ ጋር እንዴት በጤንነት ለመኖር እንደሚቻል የተገነዘቡ እንዲሆኑ ማስተማርና ማብቃት፡፡ በዓለም ላይ የሚኖሩ 90% ሰዎች  የኤች አይ ቪ ኤድስ ህሙማንን የኤች አይ ቪ ኤድስን ቫይረስ መግቻ መድሃኒት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ፡፡90 % ደግሞ መድሃኒቱን በመውሰዳቸው በሰውነታቸው ውስጥ የሚገኘው ቫይረስ እጅግ ቀንሶ እንዲገኝ  ያልተቋረጠ ሥራ መስራት፡፡ 90% of people living with HIV are aware of their status; 90% of people diagnosed with HIV are receiving treatment; and 90% of all people receiving treatment have achieved viral suppression. የሚል እቅድ ነበረ፡፡

ይህ አልተሳካም፡፡እናም ይህንን አደገኛ መዘናጋት ለመቀልበስና ቫይረሱን ለመዋጋት  አለም አቀፍ ትብብር ያስፈልጋል፡፡ ተገቢውን የመከላከል ሥራ ለመስራት ዓለም አቀፍ ትብብር ያሻል፡፡ በሚል መንፈስ፣ በአዲስ ጉልበት አገራት በቫይረሱ ላይ እዲዘምቱ የአለም ጤና ድርጅት በዛሬው እለት ጠይቋል፡፡እኔም ለወገኔ ኤች አይ ቪ ዛሬም አለ፡፡እባካችሁ ንቁ፡፡ አትዘናጉ፡፡መዘናጋት   ውድ ህይወታችንን ከመንጠቁም በላይ አገራችንን የሰው ሃብት ደሃ ያደርጋታል ፡፡በማለት በትህትና አሳስባችኋለሁ፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share