የካርታ ጨዋታ (ዘ-ጌርሣም)

የካርታ ጨዋታ አምና ተጀመረ
ጆከሩን በወለድ እያሰባጠረ
ሁሉንም በአንድ ዙር ሊልፈው ሞከረ
በአንድ ጊዜ ለመክበር ቁጭ ብሎ እያደረ
ብሩን በዶንያ ያግዘው ጀመረ

የካርታ ጨዋታ መዘዙ ብዙ ነው
መጀመሪያ ብሽቀት ሲቆይ መጫረስ ነው

ኑሮ አልሆንህ ቢለው የፈረንጅ አገሩ
የካርታ ሊቸንሳ ከፈተ በአገሩ

መበላቱን ሲያውቀው ምን ያስፐውዘዋል
ባይሆን የለመደው ገበጣው ይሻላል
የሚያከስብ መስሎት ቂልም ይሯሯጣል
ያጫዋቹን ተንኮል ማወቅ ተስኖታል

የካርታው ጨዋታ የአንድ ዓመት ስልጠና
በሚላኖው ምሩቅ በእሳቱ ተበላ
የሚላኖው ካርታ አገራችን ገብቶ
ሊያጣልዝ ተነስቷል ከፋፍሎ በጉቶ
ዋ ! መጨረሻው ይህ የካርታ ቁማር
ትዳርን አፍርሶ እንዳያደርግ እርር
ወልዶ ልጅ መተካት ሳለ ደጉ ነገር
ሳይሻል አይቀርም የጉግስ ጨዋታ
ለመግዛት ከሆነ ፈሪው እንዲረታ
የካርታው አጫዋች ሁሉን ይሞክራል
መች በዚህ አቁሞ በእምነትም ጀምሯል
የካርታው ጨዋታ እጅግ በመድራቱ
ሊበላው ወስኗል እስከ ቀለበቱ
አምና በጀመረው ከፍ ብሎ ከአንገቱ
ዘሃር የቆመለት መስሎ ስለታየው
የራሱን ጨምድዶ ለጎረቤት ናኘው
ነገ እሱ ሲበላ ከዚያ ላያገኘው
ሻጥር የበዛበት የካርታ ጨዋታው
ተሎ ካልተገታ መዘዙ ብዙ ነው
የአጫዋቹ ፊሽካ በአስቸኳይ ያስቁመው
የሚላኖ ካርታ ለጣሊያኖቹ ነው
ኢትዮጵያ ከገባ ዳግመኛ ቅሌት ነው
ይህን ያለጤነ ውርድ ለራሴ ነው
1991-05-30

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.