January 16, 2020
4 mins read

የትምህርትና የእምነት ተቋማት ለሴቶችና ለፖለቲካ በቂ ትኩረት አልሰጡም ተባለ

ጥር 2  ቀን 2012  ዓም በአዲስ አበባ ሆቴል ዲአፍሪክ በተካሄደ የመጽሃፍት  ባዛር ላይ በታሪክና በፖለቲካ የከፍተኛ ትምህርትና የእምነት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ሃገራዊ ሃላፊነት በአግባቡ ይወጡ ዘንድ ማሳሰቢያ ተሰጠ::

“ኢትዮጲያ  2012 መጽሃፍት ምረቃና ባዛር” ላይ የተገኙ “በሀገራችን ካሉት በጣት ከሚቆጠሩት የዩንቨርስቲ ሴት መመህራን አንዷ “የኬሚስቶች እናት” የሚባሉት  በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ዶ/ር ድርሻዬ መንበሩ በዪኒቨርስቲ  እንስት ምሁራን ትኩረት እንደማይሰጣቸው ቅሬታቸውን ገለጹ::  በዚሁ ስብሰባ ላይ ሌላው ተናጋሪ ቄስ ማርቆስ ሃደሮ በሃገራችን የሃይማኖት ሰዎች  የሚፈራረቁት መሪዎችን እየተቀበሉ ማስተጋባት ወይም መሸሽ እንጂ ለምድራዊና ሰማያዊ ሃላፊነት ያለመትጋታቸውን ገለጹ::  ለሃገራችን  ተገቢው  ፍትህ መስፈን ቤተሃይማኖቶች ትልቅ ድርሻ ስላላቸው ዘመኑን በመዋጀት የሚጠበቅባቸውን  ሃገራዊ ሃላፊነት በቅንነት ይወጡ ዘንድ ቄስ ማርቆስ መክረዋል::

ሁለቱም ተናጋሪዎች ምሁራንና የእምነት ሰዎች ለበጎ ለውጥ ምሳሌ መሆን እንደሚኖርባቸው በአጽንኦት ሲገልጹ ዶክተር ድርሻዬ ለዘመናት ባገለገሉበት የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በዚህ መሰሉ መድረክ ላይ የመናገር እድል ቀርቶ ተገቢ ትኩረት እንደተነፈጋቸው ቅሬታቸውን ለታዳሚዎቹ አሰምተዋል::

ፕሮግራሙ የተከናወነው በአሜሪካ  የኢትዮጲያ ኮሚኒቲ አስተባባሪ አደፍርስ (ኤዲ) ሃብቴ መካሻ ሁለት መጽሃፍት ምረቃና  የመጽሃፍት ባዛር  በተደረገበት ወቅት ሲሆን በስፖንሰርነት ይደግፉ ዘንድ ከተጠየቁት መሃል የምስራች ድምጽ መገናኛ ዘዴዎች ብቻ ዴሬክተሩ አቶ ገመችስ ዲዲ የመጽሃፍትን ጠቃሚነትና የእውቅት ምንጭነት በመዘርዘር ተናግረዋል:: በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ የደራሲው ወላጅ እናትና የማይጨው  አርበኛ  የወ/ሮ ልኬለለሽ በያን ባልደረባ የወሮ ጥሩነሽ ወልደአረጋይ ልጅ  ወ/ሮ ተረፈች አስፋው ልጃቸውን ለተባበሩ ደራሲያንና የሚዲያ ሰዎች ምስጋና አቅርበዋል::

ሚዛናዊ ታሪክና ፖለቲካ የአደንዛዥ እጽና የአልኮል መጠጥ ሱስ ምክሮች ሁለት መጽሃት በይፋ በተመረቁበት ፕሮግራም ከገበያ ውጭ የሆኑ ጠቃሚ መጽሀፍትን የሚሰበስቡ አቶ ብርሃኑ ጥርሳምብ ብርቅዬ መጽሃፍቶቻቸውን በማቅረብ የመጽሃፍት ፍቅራቸውንና የዘመናት የአንባቢነት ታሪካቸውን ለታዳሚዎቹ አውግተዋል::

ይህን መሰሉ የንባብብ ባህል አሳዳጊ  ፕሮግራም በሌሎችም ዘንድ በተለይ  በዳያስፖራው ኮሚኒቲ ዘንድ እንዲጎለብት ተሳታፊዎቹ አበክረው ጠይቀዋል::

በወቅታዊ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ልዩ ልዩ ጽሁፎቹን የሚያቀርበው ደራሲው አደፍርስ (ኤዲ) ቃልምልልሶች ከዚህ ቀደም በኢሳትና በአውስትራሊያ የአማርኛ ሬዲዮ  ፕሮግራሞችና በኦማሃ ሄራልድና በከተማው ቻነል ስድስት ቴሌቪዥን ቀርቧል::

የዜና ምንጭ- የኢትዮጲያ ኮሚኒቲ ኦማሃ ነብራስካ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

አማራና ትግሬ – መስፍን አረጋ

340
Next Story

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለምርጫ 2012 ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ፡፡

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop