የኢትዮጲያ ፖለቲካ ሓይሎች አስላለፍ ና ውጤቱ – ሙሉቀን ገበየው

(1st January 2020)
ከሙሉቀን ገበየው

ባሁኑ ወቅት በኢትዮጲያ ያሉ የፖለቲካ ቡድኖች አሰላለፋቸው ወደፊት ሩቅ ዘመን ሳይውስድ ለጦረነትና ለብዙ ግጭት ሊያስገባ በሚስያችል ሁኔታ ላይ የሚገኝ ነው። ይህ እውነታ አስቅድሞ ካልተመከረበትና መስመር ካልያዘ ውጤቱ ለማናቸውም ሳይሆን ኪሳራና አስከፊ ይሆናል። የውጭ ሃይሎችም ይህን ልዩነት በመጠቀም የራሳቸውን ጥቅም ሊያራምዱበት ይችላሉ።

በፖለቲካ ሃይሎቹ መካከል ላለው ሲፊ የአመለካከት ልዩነት መንሴ ታሪካዊ እንዲሁም ውስጣዊና ከሃገር ውጭ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎች የራሳቸው ድርሻ አላቸው። እስካሁን ድርስ በሰላማዊ መንገድ ተቀምጠው የተውያዩበት፣ የተከራከሩበት እንዲሁም የተግባቡበት መድርክ ባለመኖሩ ልይነቱ ይብልጥ እይሰፋ የቅራኔ የጠላትነት ስሜት በተከታዮቻቸው መካከል ሊስፍን ችሏል።

ባሁኑ ወቅት ጎልቶ የሚታየው የፖለቲካ አሰላልፍንን በሁለት ዋነኛ አመልካከት ልንከፍለው የምንችለው ነው።

  1. የኢትዮጲያ የፖልቲካ ችግር የጎሳዎች መካክል ያለው የበታችና የበላይነት ታሪካዊና ወቅትዊ ክስተቶች ዋነኝ መንሴ ነው ብሎ የሚያምነው ሲሁን ይህም አመለካክት እያንዳንዱ ጎሳ ወይም ቤሂርሰብ ወይም ብሄር ራሱን በራሱ ያስተዳድር እንዲሁም እስከመገግነጠል የሚያሳችል መብት ይኑር ብሎ በዋናኝነት  በጎሳ ላይ የተመሰርተ የፊዴራል አስተዳድር በኢትዮጲያ እንዲመስርት የሚያቀነቅነው ሃይል ነው፡፤

 

  1. የኢትዮጲያ የፖለቲካ ችግር ዋነኛው የዲሞክራሲ አስተዳድር አለምኖርና የግለስቦች ሰባአዊ መብት አለመከብር ነው ብሎ በዋናኝነት የሚያምነው የፖለቲካ ሃይል ሲሆን ህዝብ የመረጠው አስትዳድር ታሪካውና ወቅታዊ ችግሮችን ይፈታል ብሎ የሚያምን ሲሆን አገራችን በጎሳና ቋንቁዋ ላይ የተመሰርት ፌዲራልዊ  አስትዳደር አላስፈላጊ ነው የሚል ነው። የተወስነው የዚህ ክፍል  በፌደርላዊ አስትዳደር የሚያምን ሲሆን ግን በጎሳና ቁንቋ ላይ የተዋቀረ መሆን የለበትም ብሎ ያምናል። ሌላው የዚሁ አስትሳስብ ክፍል ደግሞ አሃዳዊ አንድ ወጥ  መንግስት ይዋቀር የሚል ሲሆን  ቁጥራቸው ግን አንስተኛች ናቸው።

እንዚህ ሁለት አመልካከቶች ባሁኑ ዘመን ራሱን የቻለ ብዙ ተከታዮች አፍርተዋል። የጎሳ ፖለቲካ የሚያጥነጥነው ክንፍ በብዛት  ባልፉት 50  አመታት ገነው በተትርኩ ታሪክ ቀመስ ፖለቲካዊ ፕሮፓጋንዳዎች ሰልባ የሆኑ፣ እንዲሁም ስልጣን ባቋራጭ በዚህ መንግድ ይግኛል ባሉ የፖለቲካ ሊሂቃን እንዲሁም  ባልፉት  50 አመታት የነበሩ በጎሳ መካከል ያሉ  ልዪንቶችን የጭቆና ዋንኛ መግልጫዎች ናቸው ብለው ያመኑ በብዛት ከከተማ አክባቢ ራቅ ያሉና በመለስትኛ  ከተሞችና ከመሃል አገር ራቅ ባሉ ገጠርማ ያገራችን ክፍሎች በሚኖሩ ወግኖች ተክታዮች ሲኖራቸው፡ እንዚህ ወገኖች  ሌላኛውን የፖለቲካ አመለካክት ሌሎችን ድፍጥጦ የሚገዛ አንድ ወጥ አሃዳዊ መንግስት አቀንቃኞች አድርገው ይከሷቸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኛ ነገር፤ ከኔ ማእዘን፤ ክፍል 14 (ከተክለሚካኤል አበበ)

የዲሞክራሲ አስትዳድርና የሰእባዊ መብት አለመከብር ያስከትለው ችግር ነው ብልው የሚያምኑት ደግሞ ተከታዮቻቸው አብዛኛውን በዋና ከተማና ትላልቅ ከተሞች ያሉ፤ በብዛት ካንድ በላይ ጎሳ ተወላጅ በሆኑ እንዲሁም በትምህርታቸው ከፍ ያሉና በንግድ  በመንግስት ስራ እንዲሁም በተለያዩ የሞያ ዘርፍ ያሉ ወግኖች ናቸው። እንዚህ ወግኖች በጎሳ መካከል ያለው ልዩነት ዲሞክራሲያዊ ስራአት ሲመስርት ችግሩ ይፈታል ብለው የሚያምኑ ሲሆኑ አንዳንዶቹን የጎሳ ፖለቲካኞችን በጠባብነት እንዲሁም ዘርኝነት ወይም ለውጭ ሃይል ተገዢዎችና ጸረ-ኢትይጵያዊነት የሚከሷቸው አሉባቸው።

ኢትዮጲያ የብዙ ጎሳዎች፣ ቋንቋ፣ እምነት ባህልና ትሁፊት  ያሉባት አገር ናት። በዘመናት በነግስታቱ የሃይል እርምጃና እንዲሁም በተለያዩ ጎሳዎችና እምነቶች መካከል በነበረ ድርድርና ስምምነት የቆየች፤ ግዛቱዋ ሲስፋና ሲጥብ የኖርች ታሪካዊ አገር ናት።  የክርስትና እምነት በተለይም የእስልምና እምንት መስፋፍትን ተከትሎ ብዙ ታሪካዊ ፋይዳ የተካናውኑ ቢሆኑም ባለፉት 200 አመታት ደግሞ የአውሮፓውያንና የኮሊያኒስቶች የአፍሪካን መቀራመት ሩጫ በኢትዮጲያና ባካባቢው ባሉ ግዛቶች ያስከትለው ተጽኖ  አሁን ለሚታየው ልዩንቶች ያሳደረው ተፅኖ ትልቅ ነው።

ዘመናዊ ኢትዮጲያን የመሰረቱት ዳግምዊ ሚኒሊክ አስትዋጾ ደግሞ  በተለያዩ የህብረተሰባችን ክፍል የተለያየ እንዲሁም የሚቃረን አመለካክትን ፈጥሯል። በጀግንነትና የዘመናዊነት ፋና ወጊ አድርጎ የሚያይቸው ህብረትሰብ ክፍል እንዳለ ሁሉ ሌለው ደግሞ ባረመኔነትና በክፋት የሚመልከታቸው ወገን አለ። ይህ አመልካክት ብቻ ሆኖ የቀር ሳይሆን ያንዳድን ፖለቲካ ሃይሎችን አሰላለፍ መስመር እስክማስያዝ ድርስ ዘልቋል።

በኢትዮጲያ ያሉ ወገኖች ሁሉ የሚያግባብቸውና የሚያቅራርብችው ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ እምንታዊ እንዲሁም በጋራ ጠላቶቻችውን መምክታቸው እውንታ  እጅግ የሚያስተሳስርቸው ሲሆን  ጎልቶ የሚነግርው የተጋነን ልዩነትቸውን ካልተመክረበትና ካልተዋያዩበት  የጋራ እሴታችውና በአንድ አገር መሆናቸውን ሊንደው ይችላል።

የነበሩት አገዛዝ በሙሉ በህዝብ ፈቃድ የተመርጡ አስተዳድሮች ባለመሆናቸው ምክንያት ሁሉንም ዘዴ ተጠቅመው አገዛዝቸውን ሲያራዝሙ ኑረዋል።  አንዳንዶች እምነትን፣ ጎሳን፣ የዘር ሃርግን፣ እንድሂም በዘምናት አግዛዞች በፈጠሩት የባህል፣የቋንቋ ና የግለስብ ከፍታና ዝቅታ አድርጎ የሚያይ አምለካክትን ሁሉ እይተጠቀሙ  ህዝቡን ሲገዙና ሲጨቁኑ ኖረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በእርግጥሰ ምዕራባውያን የዓለም ህዝቦች ነፃነታችውን ቢቀዳጁና ዲሞክራሲን ቢያሰፍኑ ደስተኛ ይሆናሉ ወይ ? ዶክተር ብርሃኑ ነጋ - ትችት በፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)

ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ቦኋላ ባአለማችን ውስጥ የዚህን አይነት አገዛዝ እይጣሉ ዘመናዊ እና የህዝብ ምርጫ ያለው አስትዳድር የመሰርቱ አገራት እጅግ ተበራክተዋል። ያለመታዳል ሆኖ በኢትዮጲያ ዙፋን ላይ የተቀመጡ ወገኖች ግን ያንኑ የድሮውን ዘዴ  ዘመናዊ ካባ አስለብሰው  የጭቆና አገዛዝ ሲገዙ ቆይተዋል። ባልፍት 50 አመታት በተለይም  በቀደሙት 27 አምታት በትህነግ (ወያኔ) መራሹ መንግስት በኩል በ ኢትዮጲያዋያን ላይ የተሰራ ግፍ በወንድማምቾች መካከል ልዮነትን በማጉላትና በማናከስ ላይ የተመሰርተ አገዛዝ ስለነበር ቀድሞ የነበረው ችግር ላይ ሌላ  እሳት በመጨመሩ በትግል ያሉ የፖለቲካ አመላካከቶች ልዩንታቸው እንዲስፋና በጠላትነት እንዲታያዩ ትልቅ ድርሻ ተጫውቷል።

ከ ሚያዚያ 2018 (EC) ጀምሮ በተፈጠርው የለውጥ ሂደት በዶ/ር አብይ የሚመራው መንግስት በወሰደው እርምጃ ለመጀምርያ ግዜ በታሪካችን ሁሉም አይነት አመለካክት ያላቸው ነፍጥ ያነሱትንም   የፖለቲካ ሃይሎች ጨምሮ በአገር ውስጥ እንዲንቀሳቀሱ በመፈቀዱ ህዝቡ ሁሉንም አይነት የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳና መዘዙን ለመካፈል በቅቷል።

ምንም እንኳ በ ዶ/ር አብይ አሕመድ የሚመራው  መንግስት ስልጣን በያዘ  መጀመርያ ወራቶች የወሰዱት እርምጃዎች አብዛኛውን ወገኖቻችን ያስደሰተና  የአለም አገራትን  ያስደነቀ ቢሆንም ለውጡን ተከትሎ ሊከትሉ የሚችሉትን ውጢቶች ያልተጠኑና ዝግጅት ያልተደርግባቸው በመሆኑ ያስከተለው ጣጣ ብዙ ነው።  የለውጡን መንግስት ሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ክፍሎችን ያላካተተ በመሆኑ የተፈለገው ለውጥ ግማሽ መንግድ ላይ የቆመና እንዲንገዳግድ አድርጎታል። በይብልጥ በዋናኝነት ሊሰራ የሚገባውን ወዲፊት ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን የሚቀንስና ህዝቡን ለሰልማዊ ለውጥ እንዲሁም ትልቅ የመንፈስ ልእልና  ያድርስ የነበረውን  የቤሄራዊ የእርቅ፣ የመግባብት፣ የመነጋገር ና የአገር ምስርታ ጉባኤ ወይም ስራዎች ባለመሰራቱ  አሁን ለተከሰተው ችግርና ለወዲፊትም ሊከስቱ የሚችሉ ልዩንቶችን እንዳይቀርፍ አስችሏል። ይህ ተድርጎ ቢሆን ኖሮ   በዳይና ተበዳይ ይቀር ተባብሎ ፤ የተጓደለ ፍትህና ካሳ ተስተካክሎ በታሪክ ላይ የነበርውን ልዩንት ትቶ በወድፊቱ ላይ የሚያተኩር ስምምነት ላይ የደረሰ ንቁ ማህብረሰብ ይፈጠር ነበር።

በግንቦት ወር  2020 ይደረጋል የተባለው ምርጫ  በህዝቦችና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካክል መልካም ውይይትና መስማምት  ሳይድርግ   በቶሎ ሊድርስብን ነው። ይህ ንግግርና ስምምነት ሳይደርግ የሚከናወን ምርጫ መፍቴ ከመሆን ይልቅ ራሱን የቻለ ትልቅ ችግር ሊያመጣ ይችላል። ስለዚህም ይህ ስጋት በሁሉም ዘንድ አጽኖት ተሰጦት ወደ ውይይትና ድርድር ቶሎ ተድርጎ ስምምነት መደርስ አለብት ወይም ምርጫው መራዘም አለብት።

ተጨማሪ ያንብቡ:  “አይኼኼኼ!!!” - ቀሲስ አስተርአየ

ምንም እንኳ ቤሂራዊ አገር አቀፍ እርቅና የይቀርታው ጉባኤ የረፈደበት ቢሆንም ( የ በፊቱ በድልና ጥፋት ላይ የዶ/ር አብይ መንግስት ከመጣ ጅምሮ እጅግ ብዙ ወገኖች በ ሞት እርዛት ስድት  ደርሶባቸዋል)  በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ግን በመካከላቸው ያለውን ልዮነት ለማጥበብና ሊከትል የሚችለውን ደም አፍሳሽ ቅርሾዎችን መቀንስ ይቻላል።

የዲሞክራትክ ችግር ነው ዋንው መንሲኤ የሚለው ከፍል የሌሎቹን የወንድሞቹን በጎሳ ፖለቲካ የሚያምኑትን ተቀምጦ ብሶታቸውን መስማት፣ በታሪክ ሂደት ላይ ያሉ አተራርኮችን በመስማማታ ወይም በጨዋነት በልዩንት መስማምት ነገር ግን ታሪክን አሁኑኑ በመኖር ሳይሆን የአሁኑንና የወደፊቱን እጣ ፈንታችን ላይ አተኩሮ መነጋገርና መስማምት። በቋንቋ፣ ባህል፣እምነት በእኩልነት የሚታይበትን መንግድ መምልክት። የቡድን መብቶችን ለመንጋገርና  ለመስማማት መዘጋጀት አለበት።

የጎሳ ፖለቲካ ዋነኛ ነው ብሎ የሚያምነው ክፍል ሌሎች ወንድሞቹን የሚያቀርቡትን የዲሞክራሲ ስርአትና የግለስቦች መብት ሊያስከትል የሚችለውን ውጤትና ተባብሮ መስራት ሊያመጣስ የሚችለውን አገራዊ፣ ዜጋዊ እንዲሁም የቡድን መብትን ለመነጋገር፤ ከሌሎች አገር ልምድ ለመውስድ፤ የአገራችን ጠላቶች ልዩንታችንን  ለራስቸው ጥቅም እንዳይጠቀሙብን ለመተማመንን መዘጋጀት አለበት። በተጋነን ታሪክ ላይ የሚነገር ፕሮፓጋንዳን መተውና በእውነትኛ ታሪክዊ ሂደቶች ላይ ለመስማማት እንድሁም ልዩነትም ካለ ለመቀበል ነገር ግን ወደፊት  የበላይነትና የበታችነት እንዳይፈጠር የሚያስችል መንግስታዊ ስራአትን ለመምስርትን ለመምልክት መዘጋጀት ያስፈልጋል።

በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ  ኢትዮጲያን ራሳቸውን ባንድ ጎሳ  አጥር ውስጥ መሆን የማይፈልጉ  ወግኖች መኖርቸውን በማወቅ የነሱን መብት የሚከበርበትና እኩል ለሁሉም የሚሆን ድርሻ  ያለው ስራአትን መመልክት ያስፈልጋል።  ይሄ ቦታ ለኔ ይግባኛል በሚለው ከመጣልት ይልቅ ያን ቦታ በጋራ እንዴት ለሁሉም ተጠቃሚ ማደርግ እንደሚቻል መሰራትዊ ስምምነት ለማድረግ መዘጋጀት ያስፍልጋል።

በነዚ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ከተደርሰ ምርጫውን ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን አደጋ በእጅጉ የሚቀርፍ ስልሆነ ሁሉም የፖለቲካ ሓይሎች  በተለይም መንግስትና የምርጫ ቦርድ ይህን ዋና ነገር ቅድሚያ ሰጠተው ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ አደርጋለው።

 

2 Comments

  1. A very timely and measured assessment of our current situation. I couldn’t agree more with the writer. I think politicians who truly care about Ethiopia should come to their senses and work on a national consensus-building project that is led by non-partisan Ethiopians who can facilitate a transition to a fair election with the support of the current government. Among the names, I can think of for now include but not limited to; Professor Fikre Tolessa, Professor Mesfin W/Mariam, Professor Al-Mariam, Lt. General Tsadikan Wole Tensai & Major GeneralAbebe Teklehaiman, Professor Medhane Tadesse, Professor Gebru Tareke, Professor Bahiru Zewede, Renowned Researcher Desalegne Rahamaato, Professor Kassahun Birhanu, Ato Kibur Gena, AtoEyesuswork Zafu, Ato Girma Wake, Lt. Colonel Derartu Tulu, Major Haile Gebreselasse, Dr.Hailu Araya, Artist Aster Bedane, Artist Tewodros Kassahun, Artist Tsehaye Yohannes, Professor Mamo Muche, W/o Meaza Biru, W/tBirtukan Mideksa, Dr. Daniel Bekele, Artist Seleshi Demissie( Gash Abera Mola), Layer Abebe Worke, Professor Shibru Yedla Representatives of religions of all denominations, Community leaders and renowned elders from Oromia, Amhara, SNNPR, Tigray, Somali, Afar, Beneshangul Gumuz, Harari, Gambela regional states and Addis Ababa, and Diredawa city administrations Dr. Yayehirad Kitaw.

  2. I admire your comment it is down to earth and crucial this is what is on the ground. I keep asking my self why do we need so many opposition parties? There should be a body of respected Ethiopians or a government who will evaluate that a certain opposition party has all the requirements that fits the need of peoples concern and representation, what I see now in some of the opposition is competition or for the sake of creating a party and brag about it. When there is no a clear direction and knowledge of vision to run as a party the damage weighs the benefit for the country. I thank the late Mr. BEALU GIRMA who said in his “BOOK DERASSIW” that a daughter asked her dad when they were passing by the EMMANUEL HHOSPITAL why and who are these people and her dad said they are mentally ill and they get help there. there were also two skinny security guards and she asked why are they at the entrance? Her dad told her they are watching and securing the hospital. The daughter said the mentally sick are big and they look stronger than the guards what if the unite and break free they can not stop them. The dad said” EBDOCH” they don’t know how to unite they won’t break free.
    This is what is happening among parties who have no clue of democratic culture and who are narrow minded and who cares more to their buddies than the country.
    Ethiopia has more than 80 ethnicity and the believe by forming more than 80 which is hundred and something parties is a sign of democratic culture. This is a time bomb that will explode when they realize that they were not elected and the fact that they have opposition party will entitle them for parliament seats.
    Change is happening and ignorant and arrogant mentality will create havoc and lawless climate in the country that is why it is hard to keep order and security in the country.

    God bless Ethiopia.

    Muchfun A Kassa.

    Canada.

Comments are closed.

Share