የኦሮሞ ዘር ወይም ብሄር ከጥንቱ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ከሚኖሩ ጥንታዊያን ኩሽቲክ ነገዶች ከአፋርና መሰሎቹ አንዱ መሆኑን ጥናቶች በማረጋገጥ ላይ ናቸው ፡፡የአፋር ህዝብ ከማንም በላይ ቀዳሚው የኢትዮጲያ ብሄር ወይም ዘር ለመሆኑ አርኬዎሎጂና ታሪክ የመሰክሩትን ያህል የኦሮሞም ታሪክ እንደዚሁ ጥንታዊ ነው፡፡
ከዚህ በተረፈ በመካከለኛው ዘመን ከሶማሌ የመጣው ሃገራችን ኢትዮጲያን ከከፍታ ያወረደ የፈረሰው የአህመድ ግራኝን ወራር መሪ ኑርን በምስራቁ የሃገራችን ክፍል ድል ያደረገው የኦሮሞ ጀግና ሰራዊት ተመሳሳዩን ድል በአድዋ ለአፍሪካና ለመላው ጥቁር ህዝብ ኩራት የሆነውን ሰራዊቱን ያዋጣ በሁለተኛው የአለም ጦርነትም አብዲሳ አጋን የመስለ ድንቅ ጀግና ያፈራ ህዝብ ያልተነገረ ታሪኩን በታሪክ ዋቢነት ሊጠቀስ የሚገባ ታሪኩን ከይልማደሬሳ የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጲያ ታሪክ ላይ መመልከት ይቻላል::
የኢትዮጲያ ህዝቦች ትግል በተቀጣጠለበት የስድሳ ስድስቱ ትግል የገባር ህዝቦችን ትግል ይመራ የነበረው ኢጭአት(የኢትዮጲያ ጭቁኖች አብዮታዊ) ትግል ከመሩት አንዱ ባሮ ቱምሳ የመንግስቱ ሃይለማርያም ደጋፊ የነበረና በመንግስቱ የግል ታሪክ ላይ የተሞገሰው የጀመረው ኦነግ በኦሮሞዎች ልብ ውስጥ ምንጊዜም የማይጠፋ ነው፡፡ሆኖም ግን በትግል ስህተት ኦነግ ለኦሮሞ ብቻ በመቆሙና ኢትዮጵያ የአማራ ፈጠራ ናት በሚል ትርክት በጥላቻ መሳቱን የቀድሞው መስራች መሪዎቹ ሌንጮ ለታ በከፊል ሌንጮ ባቲ ሙሉ በሙሉ በቅርቡ የዘከሩት ይገኛል፡፡በዚያ የትግል ወቅት የወለጋው ባሮ ቱምሳ ኢጭአትን ለአሰፋ ጫቦ ትቶ ኦነግን ሲመስረት ወንድሙ ፓስተር ጉዲና በመካነኢየሱስ መሪ ሆኖ ሲተባበር የመካነኢየሱስ መሪዎች የንጉሱ አማች አቶ አማኑኤል አብርሃም እንደተቃወሙት የጫቱ ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋቢሳ በቅርቡ የተናገረው ማስረጃ ሲሆን የቀድሞ ደራሲያን ማህበር መሪ አቶ አማረ ማሞ ከጉራጌ ብሄር የሆኑን ይህን ለደራሲያን ዘግበው ነበር፡፡
ባሮ ቱምሳ ባሌ ለትግል በሄደበት ወቅት ባሌ ላይ የኦነግ ጦር የገደለው በሃይማኖቱ የተለየ በመሆኑና በጎሳ ልዩነት መሆኑን ዶር መረራ በኣንድ ወቅት” መስተዋት ቤት ያለ ድንጋይ መወርወር የለበትም” በሚል በጻፉት መጣጥፍ ላይ ገልጸዋል:: የነዮሃንስ (ሌንጮ) ለታን “ቀን ቀን የሚሽን አገልጋይ ማታ ማታ የኦነግ ኮማንደር” ሲሉ ገልጸዋቸው ነበር::ፓስተር ጉዲና ከወንድሙ ባሮ ሞተ በኋላ ትግሉን በከተማ ማስተባበር ሲቀጥል እነሌንጮ ለታ ‘ሜዳ’ በሚሉት በሽምቅ ውጊያ ትግሉን ያቆም ዘንድ በደርግ በአውሮፓ ሚሲዮን ተጠሪዎች ፊት ሲጠየቅ እምቢ በማለቱ በራስ ካሳ ግቢ በተመሳሳይ መልኩ የጎጃም ሰዎችን ብቻ መሰቀል በማሳለም በርቱ ብለዋል በሚል ደርግ ከከሰሳቸው ጳጳሱ ቴዎፍሎስ ጋር ታስሮ ተገድለዋል፡፡የቀድሞ አየር ሃይል አዛዥና በስዊዲን አምባሳደር የነበሩት ጄነራል ታዬ ጥላሁን ጉዲና ቱምሳ በኦነግ አስተባባሪነቱ በደርግ ሲታሰር ይፈታ ዘንድ ብዙ ቢጥሩም የደህንነት ሃላፊው ጄነራል ተስፋዬ ወልደስላሴ ባለበት ጉዲና ቱምሳ በኦነግ አደራጅነት መስራቱን ማመኑና ይቅርታ መጠየቅ ያለመፈለጉን ዛሬ በሃገር ቤት በህይወት ያሉት ጄነራል ታዬ የሚመስክሩት ነው::
በሃገራችን ብዙሃን የሆነውና ከሌሎቹ ብሄሮች ወይም ዘሮች ጋር እጅግ የተደባለቀው ኦሮሞ ባለፉት መንግስታት ማንነቱ ባህሉ ቋንቋው እንዳያድግ በጥላቻ ቃል ጋላ በሚል ስም ሲጥላላ የኖረ ተገቢ ትግል በተገቢ መንገድ ባለመሄዱ ዋናውና ግንድ ተብሎ የሚጠራው የህዝብ ክፍል ያላስፈላጊ የመገንጠል ጥያቄ በሚያራምዱና ኢትዮጲያን በሚጠሉ መሪዎች ላለፉት ሰላሳ አመታት ሲመራ ቆይቶ ነበር፡፡ በወያኔ በኦሮሞ ስም ከተደራጀ ኦህዲድ ፓርቲ ኢትዮጲያዊነትን ለመጀመሪያ ጊዜ በማሰማት የብዙዎችን በተለይም በቁጥር ከማንም ዘር ብሄር በላይ የሆኑትን ድብልቆቹንና ኢትዮጲያዊነትን በሚያራምዱ ልብ ውስጥ በመግባት ትግሉን ለአንድ አመት ያህል በመምራት አያሌ ድንቅ ድሎች ተገኘተዋል አፋኝ የወያኔ መዋቅሮች ተሰባብረዋል የመናገርና የመጻፍ መብቶች ተገኝተዋል ለዚህም የለማና አብይ ቲም ወይም ቡድን ሊመሰገን ይገባዋል፡፡
ሆኖም ግን ከጥንቱም ከወያኔና ከሻቢያ ጋር ኢትዮጲያዊነትን የማጥፋት ሴራ ያቀናብር በነበረው ኦነግ መስሪ ድርጊት ሲፋቅ ኦነግ ነው የሚባለው ኦህዲድ አክራሪ አንጃዎቹ በነአዲሱ አረጋና መሰሎቹ የድብልቅ ህዝቦች ከተማ የሆነችውን የጥንቷን ፊንፊኔ አዲስ አበባ ከተማን የኦሮሞ ብሄር ወይም ዘር ንብረት ነች የሚለውን ኢፍትሃዊ ጥያቄ በማራገብ በዲሞግራፊ ስም ለማ መገርሳ ባደረገው ስብሰባ ላይ ‘ታከለ ኡማ በሚዲያ የማይነገር ብዙ እየተባበርን ነው’ የሚለውን ሚስጥር ከዘረገፈ ወዲህ በተጨማሪም ለማ መገረሳ ያንን ንግግሩን ለማስተባባል በጠራው ስብሰባ ላይ “ሿሿ አናድርግም” በማለት በፌዝ መልክ ንግግሩ የኦፕዲኦን ስውር አላማ በማሳየት ላይ ናቸው፡፡ የአዲስ አበባ ህዝብ ያለው የፌደራል ህግና አለምአቅፍ ሜትሮፖሊታን ትልልቅ ከተሞች አሰራርን ባልተከተለ የራሱን ማስተዳደር መብቱን ኦፒዲዎች በመርገጥ ላይ ሲሆኑ ለዚህ የሚታገለውን እስክንድር ነጋና ባልደረቦቹን በማዋከብ በማጥላላት ዘመቻ ላይ ናቸው፡፡
ከዚህ ቀድም ብሎ በቡራዩ የተደረገውን የኦነግ አክራሪዎች ጭፍፍጨፋ የተቃወሙ የአዲስ አባባ ወጣቶችና የህግ ባለሙያዎች በአብይ እህመድ መንግስት ሲታሰሩ ‘በሃይማኖት ጉዳይ የሚናገረንን በሜንጫ ሰይፍ እንመታዋላን’ ያለ ጃዋር መሃመድ ብሶበት ለፍተው ኮንደሚኖ ቤት የሰሩ የሁሉም ዘር ተወላጆች እንዳይረከቡ ‘ደም ይፈሳል አይገቡም’ ብሎ ከነጀሌዎቹ የዛተውን ለህግ ከማቅረብ ይልቅ በሰላም የሚታገልውን እስክንድርን በጦርነት ቅስቀሳ የወነጀለው አብይ አህመድና የዲሞግራፊ ባለቀመር ለማ መገርሳ የኢትዮጲያዊነት እወጃ ልፈፋ ብቻ በመሆኑ ጥያቄ ውስጥ ሲገባ ይህን የተቃወሙ በሳል የአሜሪካ ምሁራንና ታላቆች ለዶ/ር አብይ የማሳሰቢያ ደብዳቤ መላካቸው ይታወሳል፡፡
የኢትዮጲያ ኦሮሞ በሃገሪቱ ብዙሃን ብሄር ወይም ዘር ሆኖ በኬንያ አናሳ ቁጥር ካለው ተመሳሳይ የኦሮሞ ብሄር ወይም ዘር ያነሰ የመብትና ስልጣን ክፍፍሉን በተቢ መንገድ ማስፈጸም ሲገባ በኦፒዲኦ ጽንፈኞች በኦነግ የውስጥ አርበኞች ጫና የሚካሄደው እኩይ ሴራ ለኦሮሞም ሆነ ለሌላው ብሄርና ዘር የማይጠቅም ይሆናል:: ይህንን የተሳሳተ የትግል አካሄድ ሁሉም ዜጋ በተለይ የኦሮሞ ምሁራንና ወጣቶች ሃርሞሳ ኦሮሚያ (የኦሮሞ ተሃድሶ) በሚሉት ትግል ሊፋለሙት የሚገባ ነው፡፡
ደርግ ሲወድቅ ሃገር ቤት የገባው የኦነግ አመራር ከወያኔ ጋር ሃገሪቱን የሚያፍረስ የጎሳ ፌደራል ያዋቀሩ ሲሆን ከዚያ ስርአት ያልተጠበቁ ለማ መገርሳና እበይ አህመድ የጀመሩት ያልተጠበቀ የኢትዮጲያዊነት ትግል በልዩ ሁኔታ ቀጥሎ የብዙሃኑን ድጋፍ አግኝቶ ለዚህ ቢደርስም በዚህ ጠማማ ህገመንግስትና በክፋት በወያኔ በተቀናበረ አካባቢን ሳይሆን ዘርን ባማከለ “ልዩ ጥቅም” የአዲስ ፊንፊኔ ባለቤትነት የተነሳ የዶር አብይ ለውጥ መስቀለኛ መንገድ ላይ ሲሆን የሃገሪቱ ብዙሃን ሆኖ ብዙ ድሎችን ከሌሎች ብሄርና ዘሮች ጋር ከአድዋ ጀምሮ ያስመዘገበው የኦሮሞ አመራርም ጥያቄ ውስጥ ነው:: ፈጣሪ ይህንን ወደበጎ በመለወጥ ሃገራችን በፊውዳል መሳፍንትና በጨካኝ ወራሪ የኦቶማን ኢምፓየትር ሎሌ ሶማሌው ግራኝ አህመድ ከመውደቋ በፊት ከነበረችበት የታላላቅ ጥንታዊ ሃገሮች ከፍታ ኢትዮጲያን ይመልሳት ዘንድ ጸሎቴና ምኞቴ ነው፡፡