ታላቁ የፖለቲካ ቅሌት በኢትዮጵያ፤ ነጠብጣቦቹን ያገናኙና ምስሉን ይመልከቱ!

ፀሃፊ፡- ሰርቤሳ ከ.
ተርጓሚ፡- ሢሣይነሽ መንግሥቴ

ከሚያዚያ 2018 (እ.ኤ.አ) ቀደም ያለ ቢሆንም፣ በተለይ 2018ና 2017 ላይ በዲያስፖራው አካባቢ  የሚገኙ የኦሮሞ አክቲቪስቶች፣ ፖለቲከኞችና ሙያተኞች በርካታ ክፍት፣ ህዝባዊ ስብሰባዎችንና የኢህአዴግ አገዛዝ ውስጥ ካሉ ‹‹ህዋሶቻቸው›› ጋር ምስጢራዊ ውይይቶችን አድርገው ነበር፤ ህወሓት-መራሹ ኢህአዴግ ከተወገደ በኋላ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት የኦሮሞ የበላይነትን ማረጋገጥ እንደሚቻል የሚገልጡ ዝርዝር ስልቶችና ዕቅዶችን ለመፍጠር፡፡ ይህኛው ሃሳብ ካልተሳካ ደግሞ፣ እንዴት ‹‹ኦሮሚያ›› የተባለች አዲስ ነፃ ሃገር መፍጠር እንደሚቻል ለመምከር፡፡

ዓለም-አቀፍ የኦሮሞ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ከጥቅምት 22-23፣ 2016 ድረስ፣ ‹‹የኦሮሞ ስብሰባ ለብሔራዊ መግባባት›› በሚል መሪ ቃል፣ ለንደን – ብሪታኒያ ላይ ስብሰባ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ አትላንታ – ጆርጂያ ላይ ደግሞ፣ የመጀመሪያው የኦሮሞ አመራር ስብሰባ ተካሂዶ ነበር፤ ሁለቱ – ከበርካታ ክፍት ውይይቶችና ስብሰባዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ዝርዝር ዕቅዱ ከኢትዮጵያውያን የተሸሸገ ቢሆንም፣ በቅርብ ለሚከታተሉ ሰዎች ግን ስልቶቹ ግልፅ ነበሩ፡፡ መነሻ ዓላማቸውን በተሳካ ሁኔታ፣ መጋቢት 2019 ላይ ፈፅመዋል፡፡ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ግን ጥረታቸውን ህወሓት-መራሹን አገዛዝ ለማስወገድ የሚደረግ እንደሆነ በማሰብ፣ ችላ ብሎ ነበር፡፡

አትላንታ፣ በጥቅምት 2016 የተደረገው – የኦሮሞ አመራር ስብሰባ ላይ ዓላማዎቻቸውን ለማሳካት የሚያገለግሉ ዋና – ዋና መዋቅሮችን ለማዋቀር ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር፤ እነዚህም ላዕላይ ምክር ቤት፣ የውጭ፣ የዲፕሎማሲያዊና የሃገር ውስጥ ጉዳይ ዕዝ ሲሆኑ፣ በቁልፍ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ዲያስፖራ የኦሮሞ ልሂቃንና ፖለቲከኞች፣ እያንዳንዱን ዓላማ ለማስፈፀም ግዴታ ተጥሎባቸውም ነበር፡፡ እነዚህ ምስጢራዊ ድርጅቶች ዕቅዳቸውን ተግባር ላይ ለማዋል በርካታ ውይይቶችንና ግምገማዎችን አድርገዋል፡፡

ሁሉም – በተለይ ኢህአዴግ ውስጥ ያሉት ‹‹ህዋሶች›› – የመጀመሪያውን ዓላማ ለማሳካት ያለምንም መታከት ሰርተዋል፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ ያሉት ‹‹ህዋሶች››፣ በአሁኑ ወቅት የኦ.ዴ.ፓ መሪዎች የሆኑት፣ ከእነዚህ ቡድኖች ጋር በምስጢር እጅና ጓንት ሆነው ሰርተዋል፡፡

የኦህዴድ ባለስልጣናትንና አባላትን (የክልሉን መዋቅር የተቆጣጠሩና አስከ ገጠር መንደር ድረስ ህዝባዊ የወጣቶች ንቅናቄን (ቄሮን) ማደራጀት የሚችሉ) በመጠቀም ኢህአዴግን ከውስጥ በመቦርቦርና ሌሎች የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን – በዋናነት ብ.አ.ዴ.ንን በመጠቀም የህወሓትን ተፅዕኖ ማዳከም እንደሚቻል ደምድመዋል፡፡ ሌሎች፣ በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡ የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲዎች (እንደኦ.ፌ.ኮ ያሉ)፣ በሃገር ውስጥ የወጣቱን ንቅናቄ (ቄሮ) ስር በማስያዝ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡

በዜግነት ላይ የተመሰረቱ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችና ከብሔረተኝነት ተፅዕነ ነጣ ከሆነ ዜጋ የተመሰረተው ወገን፣ ዓላማቸውን ሊያጨናግፍ እንደሚችልና ሁለተኛው ተገዳዳሪ ከዚህ እንደሚመጣ ተረድተዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ያላቸው ፓርቲዎችን በሚጣፍጥ ቋንቋ ስለኢትዮጵያ አንድነት፣ ያለፈውን ዘመን ድንቅነትና ህወሓትን እንደዋና ሰይጣን መፋለም ለሁሉም ችግሮች መፍትሄ እንደሚያመጣ በመጎትጎት ለማባበል ጥረት አድርገዋል፡፡ ለዚህ ዓላማ መሳካት፣ የኦህዴድ ‹‹ህዋሶች›› ከብ.አ.ዴ.ን ጋር ጥምረት ፈጥረዋል – በሃገር ቤት፡፡ በዲያስፖራው ደግሞ ኦ.ዴ.ግን ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር በመቀየጥ ተጠቅመውባቸዋል፡፡

የአንድነቱን ሃይልና ሰፊውን ህዝብ ለማባበል ሲባል፣ በኦህዴድ ኦሮሞ መሪዎች በኢትዮጵያ አንድነት፣ ታሪክና የአካታችነት ስሜት ላይ ተተኩረው የተደረጉ ንግግሮች፣ የኦሮሞ ልሂቃንን አጀንዳ በውስጠ-ታዋቂነት ለማስፈፀም የተነገሩ ሲሆኑ፣ ከታላቁ ቅሌት ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚይዝ ተግባር ነው፡፡ ይህ ተግባር፣ ኦህዴድ ውስጥ የ‹‹ህዋሱ›› አባል የሆኑ ሁለት ሰዎችን ወደ ብሔራዊ መድረክ አመጣ፡፡ በውጤቱም፣ መጋቢት 2018 ላይ አንደኛውን፣ ዶ/ር አብይ አህመድን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆኑ፣ ለማ መገርሳ ደግሞ የኦሮሚያ ፕሬዝደንት (በተጨባጭ ሁኔታ፣ የኢትዮጵያ መሪ) ተደርገው ተሾሙ፡፡

ጥቅምት 2016፣ አትላንታ ላይ በተደረገው የኦሮሞ አመራር ስብሰባ ላይ የተቋቋሙት የላዕላይ ምክር ቤት፣ የውጭ፣ የዲፕሎማሲያዊና የሃገር ውስጥ ጉዳይ ዕዝ መዋቅሮች ከኢህአዴግ ‹‹ህዋሶች›› ጋር እጅና ጓንት ሆነው ሰርተዋል፤ ሚዲያውን ለመቆጣጠር፣ ህዝባዊ ንቅናቄዎችን ለማነሳሳትና ወታደራዊ ሽብር ለመፍጠር ትኩረት አድርገው፣ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስልቶች ለመተግበር ተንቀሳቅሰዋል፡፡

  1. በሚዲያ (በOMN)ና በማህበራዊ ሚዲያው – በባለግርማ ሞገሳሙና ወጣቱ ‹‹አክቲቪስት›› ጃዋር መሃመድ አማካይነት ጠንካራ የፕሮፖጋንዳ ጦርነት ማድረግ፡፡
  2. በቄሮ የተቀነባበረ የወጣቶች አመፅ በተሸሸጉ የኦህዴድ ‹‹ህዋሶች››፣ በኦ.ፌ.ኮና በሌሎች – ኢትዮጵያ ውስጥ በህጋዊ መንገድ በተመዘገቡ የኦሮሞ ፓርቲዎች መሪነት ማነሳሳት፡፡
  3. አመራሩ ላይ ያሉ የኦህዴድ ህዋሶች በኢህአዴግ ውይይት ወቅት፣ ብ.አ.ዴ.ንን እንደአጋር በመጠቀም ህወሓትን መጋፈጥና አቅሙን ማዳከም፡፡
  4. ‹‹ህዋሶቹ›› ውስጥ ያሉት የኦህዴድ መሪዎች ተልዕኳቸውን ለመሸፋፈንና በርካታ ኢትዮጵያውያንን ለማማለል ስለባለህብሯ ሃገር፣ ታሪካዊና አንድ-አድራጊ ንግግሮችን ማድረግ፡፡
  5. ወደ መሃል ሃገር፣ ኦሮሚያ ጠረፍና አዋሳኝ አካባቢዎች የታጠቁ አሸባሪዎችን (የኦነግ ወታደሮችን) ከአስመራና ከጎረቤት ሃገር አስመጥቶ በማስገባት፣ ኦሮሞ ያልሆኑትን ዜጎች ማፈናቀል፣ ከራሳቸው ‹‹ኦሮሚያ›› ማፅዳት፣ ሌሎችንም መግደልና ማሸበር፡፡ ይህ ዓላማ እነርሱ እንደሚያምኑት ለኦሮሞ ከሚገባው መሬት ላይ የሰፈሩ ኦሮሞ ያልሆኑትን ዜጎች ማፅዳት፣ ነፃ ኦሮሚያን ለመፍጠር ያግዛል፡፡
  6. በዜግነት ላይ ተመሰረቱ ብሔራዊ ንቅናቄዎችን (ለምሳሌ፡- አግ7ን) ወደ ሃገር ማስገባትና ጥምረት ፈጥረው የራሳቸውን አጀንዳ እንዲያራምዱላቸው ማድረግ፡፡
  7. የኢህአዴግ ‹‹ህዋሶች›› አንዴ ወደ ስልጣን ከመጡ፣ የኦነግ እስረኞችን መፍታት፣ የታጠቀው የኦነግ ክንፍ ኦሮሚያን እንዲቆጣጠር ማድረግ፣ ሚዲያው በኦሮሞ አጀንዳ እንዲሞላ ማድረግና መንግስታዊ ሃይላቸውንና የራሳቸው የኦነግ ሚሊሺያ፣ እንዲሁም ‹‹ቄሮ›› ተብሎ የሚጠራውን – የተሰወረ ሃይል በመጠቀም፣ በተጠና መንገድ የዜግነት ፖለቲካን ማክሰም፡፡
  8. ‹‹አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት!›› ብሎ ማወጅ፡፡ ይህንን ዓላማ በጊዜ ሂደት ሊያሳካ የሚችል ከንቲባ መሾም፡፡
  9. ኦሮሚፋ ብሔራዊ የስራ ቋንቋ ማስደረግ፡፡
  10. ኢትዮጵያን በኦሮሞ የበላይነት ስር መግዛት፤ ካልሆነም አዲስ ነፃ ‹‹ኦሮሚያ›› የተባለች ሃገር መመስረት፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰልፍና ሰደፍ፤ ዘመቻ ነቀምትና ዘመቻ ኢትዮጵያ - ከተክለሚካኤል አበበ

ከላይ የተዘረዘሩት በሙሉ ኦ.ዴ.ፓ መንግስታዊ ሃይሉን ከተቆጣጠረበት – ከመጋቢት 2018 አንስቶ አስከአሁን ድረስ እየተተገበሩ ናቸው፡፡ ጃዋር መሃመድ አንዳንዴ ምላሱ አድጦትና በስሜት ውስጥ ሆኖ የሚናገራቸውና የሚያምናቸው ነገሮች አሉ – ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታና የቃለ-መጠይቅ ዝግጅቶች ላይ፡፡ ጃዋር ከመጋቢት 2018 በፊት ከዶ/ር አብይ ጋር ግንኙነት እንደነበረው ቢናገርም፣ ተጨማሪ መረጃዎችን ‹‹ዝርዝር ኪስ ይቀዳል!›› ብሎ ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆንም፡፡

ከመጋቢት 2018 በኋላ፣ አብይና ለማ ኢትዮጵያውያንን መስማት የሚፈልጉትን ነገር በመናገርና ልባቸውን በመነካካት ላይ ቆይተዋል፤ በጎን – አሁንም የኦሮሞ ልሂቃንን ተልዕኮ ለማስፈፀም እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን የሃገራችንን ወደ ጥሩ መንገድ መግባት ተስፋ በማድረግ፣ በአሜሪካና በጀርመን ከዶክተር አብይ ጋር ውይይቶችን አድርገዋል፡፡ ዕውነታው ግን የዘውግ የበላይነትን በጉያ የሸጎጠ አዲስ ንጉስ እየመጣ መሆኑ ነው፡፡ ስለአንድነትና ሰላም ያወራሉ፡፡ መሬት ላይ ግን ሚሊዮኖችን ያፈናቅላሉ፣ ይገድላሉ፡፡ የሶማሌ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር የነበረው ምስኪኑ አብዲ ኢሌ፣ የኢትዮጵያ ሶማሊዎችንና ኦሮሞዎችን በማጋጨትና በማፈናቀል ቢከሰስም፣ የኦነግ ሰራዊትና የኦህዴድ የክልል አመራሮች ግጭቱን በመፍጠር ሂደት ውስጥ ዕኩል ድርሻ ነበራቸው፡፡ በሌላ ዕይታ፣ ሚሊዮኖች ከጌዲኦ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ፣ ከአሶሳ፣ ሌላው ቢቀር ከወለጋ፣ አዲስ አበባ ዙሪያ – ከቡራዩ፣ ከጎንደርና አሁን ደግሞ አማራ ክልል ከኬሚሴና ከሰሜን ሸዋ ተፈናቅለዋል፡፡

ከኢትዮጵያውያንና ከዓለም-አቀፉ ማህበረ-ሰብ ወይም ከመንግስታት ወይም ከምዕራቡ ሚዲያ አብይና ለማ ‹‹በዴሞክራሲያዊ እርምጃ›› ሙገሳ ማግኘታቸው ተገቢ አይደለም፡፡ አብይና ለማ እስረኞችን በመልቀቃቸው፣ ሚዲያውን በመክፈታቸውና የታገዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በመጋበዛቸው ማንን እንደሚተቅሙ ያውቃሉ፤ አቅደውም ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ሃቁ ከ85 በመቶ በላይ ተጠቃሚ ሆኑት የኦሮሞን አጀንዳ እንደተልዕኮ ያነገቡቱ ናቸው፡፡

በአብዛኛው የተለቀቁት እስረኞች የኦነግ አባላት ናቸው፡፡ ጥቂት ኦሮሞ ያልሆኑ ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ተለቅቀዋል፡፡ የሚዲያው መከፈትና የንግግር ነፃነት መፈቀድ፣ በባህረ-ሰላጤው አረቦችና በግብፅ የሚደጎመውን OMN ጥላቻንና ክፍፍል በሌሎች ላይ ይበልጥ ለመዝራት ጠቅሞታል፡፡ ሌሎቹ ያገኙት፣ ‹‹ለእነርሱ ሲዘንብላቸው፣ ለእኛ ትንሽ አካፈለን!›› ዓይነት ነው፡፡

የተከለከሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመጋበዛቸው፣ በደንብ ተጠቃሚ የሆነው ኦነግ ሲሆን፣ አረንጓዴ መብራት ስለበራለትና ድጋፍም ስለተሰጠው፣ በመላው ሃገሪቱ ትጥቁን ሳይፈታ እንደልቡ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ (ይህ በእነዚህ መሪዎች የተፈፀመ ታላቁ ዱለታና ክህደት ነው፡፡) ሌሎች ኦሮሞ ያልሆኑ የታጠቁ የፖለቲካ ቡድኖች ትጥቃቸውን ፈትተዋል፡፡ በሚልዮኖች ምስኪን ኢትዮጵያውያን ላይ በኦነግ ግፈኞች የተፈፀሙ ማፈናቀሎችንና ግድያዎችን፣ በመተባበርና በቸልታ በማለፍ ለፈፀሙት ተግባር አንድ ቀን የሚጠየቁበት ቀን መምጣቱ አይቀርም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዝግጅት! ለማን? - ቴዎድሮስ ጌታቸው

አብይ ሴት ፕሬዝደንት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ በማሳጨትና 50 በመቶው ሴት ሚኒስትሮችን በካቢኔው ውስጥ በማካተት ዓለም-አቀፉን ማህበረ-ሰብ አወናብደዋል፡፡ ሃቁ ግን ካቢኔው ውስጥ እርሱን ‹‹እሺ!›› ብለው የሚታዘዙና ለመጋፈጥም ሆነ ለመሞገት የማይቻላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ የዚህ ፅሁፍ ፀሃፊ የሴቶችን አቅም በፆታቸው ተመስርቶ ለማቃለል ባይሻም፣ ዕውነታው ግን አብይ የሚታዘዙት ጌታ መሆኑ ነው፡፡ ሃይለማርያም ህወሓትን ‹‹እኔ ከተገለለው የኢትዮጵያ ክፍል – ከወላይታ የመጣሁ፣ ከአናሳው የጴንጤ-ቆስጤ ሃይማኖት የተካተትኩ ሰው፣ ‹ህወሓት› በሚባሉ መላዕክትና አምላኮች ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ስለተሾምኩ፣ ከእኔ በላይ ማንንም አይፈልግም፡፡ ስለዚህ እነርሱን ያለምንም ይሉኝታ ማገልገል አለብኝ፡፡›› በሚል አስተሳሰብ ተንተርሶ እንዳገለገለው ዓይነት፣ በእርሳቸው የተሾሙት ሴት ሚኒስትሮቻችንም እንደዚሁ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ይዘዋል፡፡

አሁን በግልጽ ሃገሪቷን የሚመራው፣ አጀንዳ የሚቀረፀው፣ ሚዲያውንና ጦር በበላይነት የተቆጣጠረው ማን እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ቁጥር አንድ ተልዕኮ ተሳክቷል፡፡ ሁሉም ነገር በቁጥጥራቸው ስር ነው፤ ህወሓት ገለል ብሏል፣ ብ.አ.ዴ.ንን በደንብ እየተጠቀሙበት ነው፤ በማንኛውም የማህበረ-ፖለቲካ አጀንዳ የበላይ ሆነዋል እና ለሚቀጥለው ተልዕኮ መንገዳቸውን እየጠረጉ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ አስፈላጊ የሆነች ከተማ (በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊና በዓለም-አቀፋዊ ሁኔታ)ና በነዋሪዎቿ መተዳደር ያለባት ናት፡፡ አብይ የኦህዴድ ‹‹ህዋስ›› አንዱን አባል፣ አቶ ታከለ ኡማን በህገ-ወጥ መንገድ የአዲስ አበባ ከንቲባ አድርገው ሹመዋቸዋል፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ ሊያደርጉ ያልደፈሩትን፣ አብይ ለማድረግ ዳድቷቸዋል፡፡ ቅንጅት የአዲስ አበባን ምክር ቤትና የከንቲባነት ስፍራውን በ2005ቱ ምርጫ ባሸነፈበት ወቅት፣ አቶ መለስ ዜናዊ ቅንጅትን እጅግ በጣም ከተጫኑና የማይቻል ካደረጉበት በኋላ፣ ቅንጅቱ አዲስ አበባን ለመረከብ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ፡፡ አቶ መለስ የራሳቸውን ሰው በቦታው ላይ አላስቀመጡም፡፡ ኢህአዴግ በአዲስ አበባ መሸነፉን አምነው፣ አዲስ ከንቲባ ‹‹አስኪመረጥ›› ድረስ፣ ነፃ የሆነ ግለሰብ ለአጭር ጊዜ የከንቲባነቱን ስፍራ እንዲይዝ መርጠው ነበር፡፡ አብይ አሰራሮችን ጥሰው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ያልሆኑትንና የኦህዴዱን ህዋስ አቶ ታከለ ኡማ ከንቲባ አድርገዋል፡፡ የሹመቱ ጥቅም፣ አንድ ተልዕኮ ለማሳካት የታሰበበት ነው፡፡

ዓለም-አቀፋዊቷ ከተማ – አዲስ አበባ አስከቀጣዩ ምርጫ ድረስ፣ ለትልቅ ከተማና ለነዋሪዎቿ የሚመጥን ዕውቀት፣ ልምድና ጠባይ ያለው ነፃ ከንቲባ መነፈጓ ያሳዝናል፡፡ ራሳቸውን አሳምረው የማይገልጡና ልምድ የሌላቸው ወጣት፣ ብቻቸውን ትልቂቱን ከተማ እንዲመሩ በቦታው ተሰይመዋል፡፡ ተልዕኳቸውን አስከፈፀሙና ማንኛውንም ተቃውሞ (በተለይ የዜግነት ፖለቲካን) እስከአፈኑ ድረስ፣ ችግር የለባቸውም፡፡

አብይና ለማ የሚመሩት ፓርቲ፣ ኦ.ዴ.ፓ (በፊት አ.ህ.ዴ.ድ) በምስጢር፣ 2016 ላይ አዲስ አበባ የኦሮሞ ክልል እንደሆነች ቢወሰንም፣ በግላጭ ግን አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ እንደሆነች ይነገራል፡፡ አብይና ለማ በቀጥታ ሲጠየቁ፣ የሚምታታ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ የ‹‹ከተሜ ፖለቲካ፣ ዴሞግራፊና አዲስ አበባ ውስጥ አሮሞን ማስፈር›› ጉዳይ፣ ካለው ዕውነታ ጋር የሚጋጭ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ህዝቡ የኦሮሞን የበላይነት እንዲቀበል የማድረግ ጥረት ነው፡፡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ንቁ በመሆናቸው፣ የተደበቀውን ተልዕኮ በደንብ ቀድመው ተረድተውታል፡፡

የኦሮሞ ልሂቃን በአሁኑ ወቅት በእነርሱ አጀንዳ ላይ ያልጠበቁት አስደንጋችና አስፈሪ ተቃውሞን ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች እየተጋፈጡ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በታዋቂው ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ (አብይና ለማ ህወሓትን በመካከለኛ የስለላና የደህንነት ሃላፊነት እያገለገሉ በነበሩበት ወቅት፣ እርሱ 10 ጊዜ ታስሯል፡፡) መሪነት በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ አጀንዳቸውን እየተቃወሙ ነው፡፡ እርሱ እንደጅብራለታር ቋጥኝ ነው፡፡ አብይ እንደጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ሚሊዮኖች ሲፈናቀሉና ሺህዎች ሲገደሉ፣ የእርሳቸው ስልጣን ስጋት ላይ የወደቀ ሲመስላቸው፣ በሰላማዊው የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋና ‹‹ባልደራስ›› ቡድን – የከተማዋ ነዋሪዎችን ህጋዊ ፍላጎቶችን የሚያቀነቅን ቡድን ላይ – ይፋዊ ጦርነት ማወጃቸው ያስተዛዝባል፡፡ አብይ ባልተለመደና ባልተጠበቀ አኳኋን ስሜታቸው ከቁጥጥር ውጭ ሲወጣ ታይቷል፡፡ በዲያስፖራው ከታወቁና የእርሳቸውን ‹‹ለውጥ›› ከሚደግፉ ምሁራን ጥሪ ቀርቦላቸው ከእስክንድር ጋር ተገናኝቶ ለመወያየት ተስማምተው ነበር፡፡ ከዛ የተከተለው እጅግ የሚያሳፍርና ቀላል የመሰብሰብ መብቶችን የሚደፈጥጥ ሂደት ነው፡፡ መንግስታዊ ሃይላቸውን በመጠቀም፣ የፖሊስ የመሰብሰብ መብታቸውን አፍነው፣ ቆይተው ደግሞ የ‹‹ቄሮ›› ሃይላቸውን (እርሳቸው በሚያስተዳድሩት መንግስት ያልተመዘገበና መሪው በውል የማይታወቅ) ልከዋል፡፡ ይህ ለብዙ ሰው አስገራሚ ቢመስልም፣ በኦሮሞ ልሂቃን በተተለሙ ዕቅዶችና ስልቶች መሰረት የተተገበረ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:   የትግራይ ህዝብ ሆይ ፤ የሲዖል ጉዞ ይብቃህ !  - መኮንን  ሻውል  ወልደጊዮርጊስ

ዶ/ር አብይና ሁሉም የኦሮሞ ፖለቲከኞች አሮሚፋ ሃገራዊ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ግፊት እያሳደሩ ነው፡፡ አብይ አንድነትን፣ ሰላምንና ወንድማማችነትን በሚሰብኩበት ወቅት፣ ይህንን ሃሳብ አለሳልሰው ይናገሩታል – ህዝቡ አጀንዳውን እንዲቀበል፡፡ በሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የኦሮሞ የበላይነት አንግሰው ለመዝለቅ ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች በኦሮምኛ በማውራትና ኦሮሚፋን በመጠቀም ደስ ይሰኛሉ፤ አብዛኛው የቋንቋው ተናጋሪዎች ያሉበት አካባቢ የሚኖሩ፣ ለምሳሌ፡- ኦሮሚያ ክልል፡፡ ግን በሌላ መንገድ ጭቆናን ይፈጥራል፡፡ ለምን ሶማሊኛ፣ ትግርኛ፣ ሲዳምኛ…ወዘተ ብሔራዊ ቋንቋ አይደረጉም?…

የዜግነት ፖለቲካን የሚያራምዱ ፓርቲዎችን በተሳካ መንገድ አዳክመው ከአጀንዳ ውጭ አድርገዋቸዋል፡፡ በቀላሉ ሰነጣጥቀዋቸዋል፡፡ ዕውቁ አርበኞች ግንቦት7 (አግ7) በቀላሉ ትጥቅ ፈትቷል፡፡ (ኦነግ ግን ትጥቅ አልፈታም፡፡) የአግ7 መሪዎችን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች መብት የሚታገለውን – እስክንድር ነጋን ለመምታት ተጠቅመውባቸዋል፡፡ በሚያሳዝን አጋጣሚ፣ ምስኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተሞኝቶ እስክንድርን ተቃውሟል፤ በርካታ የመቅረብ ዕድሎችን በሚያገኝበት ኢሳት ላይ ሳይሆን በኦሮሞ ሚዲያ ቀርቦ፡፡

ጓዶች፣ ሁሉንም ነጠብጣቦች በመስመር አገናኟቸውና ትልቁን ምስል ተመልከቱ፤ ራሳችሁ ድምዳሜ ላም ድረሱ፡፡ ኢትዮጵያ በግዙፍ አደጋ ውስጥ ነች፡፡ ሃገሪቱ በኦሮሞ የበላይነት በሚያምን የኦሮሞ ልሂቅ ቁጥጥር ስር ናት፡፡ የዜግነት ፖለቲካ ለመሞት እያጣጣረ ነው፡፡ አብይ ሁሉንም ባለድርሻዎችን ያካተተ የሽግግር መንግስት ለማቋቋም አልፈለገም፤ ተልዕኳቸው ይከሽፍባቸዋልና፡፡ በሃገር ውስጥ ዋነኛው አጀንዳ የዘውግ ፖለቲካ ሲሆን፣ በፊታውራሪ ጃዋርና በሚዲያው – OMN በኩል፣ ስልጣን ላይ ካሉት ሰዎች ጋር በቅንጅት እየተነዛ ነው፡፡

የኦሮሞ ወንድሞቻችን ስልጣን ላይ ስለወጡ አይደለም የምንቃወመው፤ ነገር ግን ሰዎቹ ኦሮሞን የበላይነትና ሃገራችንን የመበታተን አጀንዳ ይዘው መጥተዋል፡፡ ያቀዱትን በሙሉ ተመልከቱ፣ ተግባራዊ እያደረጉት ነው፡፡ህወሓት ለ27 ዓመታት ያህል በእንዲህ ዓይነት አጀንዳ ሲመራ ቆይቶ፣ አሁን ደግሞ፣ በተመሳሳይ አስተሳሰብ ለተቃኘ አገዛዝ እየተዘጋጀን ነው፤ ሃገራችንን ሊበታትን ለሚችል፡፡ ኢትዮጵያ ሁሉንም በህግ ፊት ዕኩል የሚደርግ የዜግነት ፖለቲካ ያስፈልጋታል፡፡

ኢትዮ-ሶማሌ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ አፋር፣ ጋምቤላና ቤንሻንጉል የሚገኑ ወገኖች ጭንቀት ላይ ናቸው፤ በኦሮሞ ልሂቃን ተስፋፊ አጀንዳ ምክንያት በቀጣይ ማንን እንደሚጨፈጭፍ በማሰብ፡፡ የሚበቃቸውን ያህል፣ ‹‹ኢትዮጵያዊነት፣ ትምክህተኛ፣ የምኒልክ ሰፋሪ›› በሚሉት ወገን ላይ ግፍ ፈጽመዋል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘውግ፣ ፆታ፣ ዕድሜ፣ ችሎታ፣ ሃይማኖት፣ የፖለቲካ አተያይ ሳነጣጥለው፣ ያንዣበበውን አደጋ፣ እንዲሁም ሃገሪቷን ከዚህ ሌሎችን የበላይ ከሚያደርግና ሃገራችንን ሊበታትን ከሚችል ሰይጣናዊ አጀንዳ መታደግ አለበት፡፡

ስልጣን ላይ ያሉት ወገኖች ከህወሓትና መሪዎቻቸው በመማር፣ ሃገሪቱ ወደማትወጣው አዙሪት አይገፏት፡፡ ለህዝብ የሚሰብኩትን ይሁኑ፣ ድብቅ አጀንዳ አያራምዱ፡፡

 

የተጠቀምንባቸው ምህፃረ-ቃላት  

አግ7፡ አርበኞች ግንቦት 7

ብ.አ.ዴ.ን፡ ብሄረ-አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ

ቅንጅት፡ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ

ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር

ኦ.ዴ.ግ፡ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር

ኦ.ዴ.ፓ፡ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

ኦ.ፌ.ኮ፡ የኦሮሞ ፌድራላዊ ኮንግረስ

ኦ.ነ.ግ፡ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር

ኦ.ህ.ዴ.ድ፡ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲዊ ድርጅት

ህ.ወ.ሓ.ት፡ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር

5 Comments

  1. እንዲህ አይነት ምንም ጥናትና ምርምር የሌለበትና በመረጃ ያልተደገፈ ግልብ የጥላቻጽሁፍ ነዉ አገር ዉስጥ እያጨራረሰን ያለዉ- ዘሃበሻም መጠንቀቅ አለባችሁ- የታከለ ኡማ ምክር ቤት ህጋዊ አይደለም ያለዉ እስክንድር ነጋ እሱ እራሱ በተራዉ የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ብሎ በጎን ህጋዊ ያልሆነ አካል ሲያቋቁም ለምንድነዉ ትክክል የሚሆነዉ? ወይስ እስክንድር በተከታታይ ስለታሰረ እሱ ሁሌም ልክ ነዉ? ይህንን ተረት ተረት እየለጠፋችሁ ሰዉ አታፋጁ- ፖለቲካ ዳያስፖራ ዉስጥና አገር ቤት በጣም ይለያያል

  2. ህወሓት-መራሹ ኢህአዴግ ከተወገደ በኋላ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት የኦሮሞ የበላይነትን ማረጋገጥ እንደሚቻል የሚገልጡ ዝርዝር ስልቶችና ዕቅዶችን ለመፍጠር፡፡ ይህኛው ሃሳብ ካልተሳካ ደግሞ፣ እንዴት ‹‹ኦሮሚያ›› የተባለች አዲስ ነፃ ሃገር መፍጠር እንደሚቻል ለመምከር፡፡
    Who told you that? could you justify?

    ኦሮሞ ያልሆኑትን ዜጎች ማፈናቀል፣ ከራሳቸው ‹‹ኦሮሚያ›› ማፅዳት፣ ሌሎችንም መግደልና ማሸበር፡፡
    Oromos are deacinated from somali and benishangul régions. you are only teling the un truth.

    በአብዛኛው የተለቀቁት እስረኞች የኦነግ አባላት ናቸው፡፡
    You are right. more than 85 percent of prisoners were Oromos. thats why Siye Abraha toled us ethiopian prisons speak Afan Oromo.

    ጥቂት ኦሮሞ ያልሆኑ ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ተለቅቀዋል፡፡
    who rest in prison??? Are you stil there? or are you in locked at your homme?

    የሚዲያው መከፈትና የንግግር ነፃነት መፈቀድ፣ በባህረ-ሰላጤው አረቦችና በግብፅ የሚደጎመውን OMN ጥላቻንና ክፍፍል በሌሎች ላይ ይበልጥ ለመዝራት ጠቅሞታል፡፡
    No you are lying. the Israeli sponssored ESAT also has benefited this opportunity. You can ask the falasha man (Tamagn )

    አብይ ሴት ፕሬዝደንት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ በማሳጨትና 50 በመቶው ሴት ሚኒስትሮችን በካቢኔው ውስጥ በማካተት ዓለም-አቀፉን ማህበረ-ሰብ አወናብደዋል፡፡
    oooooohh. you belive that wowen are created for kichin and bed. Is that?

    አብይ የኦህዴድ ‹‹ህዋስ›› አንዱን አባል፣ አቶ ታከለ ኡማን በህገ-ወጥ መንገድ የአዲስ አበባ ከንቲባ አድርገው ሹመዋቸዋል፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ ሊያደርጉ ያልደፈሩትን፣ አብይ ለማድረግ ዳድቷቸዋል፡፡
    Dont you remember that Meles brought Arkebe from Heven/ Mekele to govern Finfine. Takele is from Sebeta.

    I stop here reading your garbeg. You finish it pleace. Oh Pleace don’t write again.

  3. “አብይና ለማ እስረኞችን በመልቀቃቸው … ከ85 በመቶ በላይ ተጠቃሚ ሆኑት የኦሮሞን አጀንዳ እንደተልዕኮ ያነገቡቱ ናቸው፡፡” አይ የጉድ ሃገር! እስር ቤቱ ኦሮሚኛ ይናገራል በተባለበት ሃገር፣ ከእስር የተለቀቁት አብዛኞቹ ኦሮሞ መሆናቸውም ያስቀናል!!

    The other is typical conspiracy theory: “ጓዶች፣ ሁሉንም ነጠብጣቦች በመስመር አገናኟቸውና ትልቁን ምስል ተመልከቱ ! – A seven headed serpent called Oromo is overtaking Imiye Minilik’s Holy Ethiopian Empire!!”

    Your crying and whining is very entertaining! I enjoy the cry of desperation of Minilikan wanna be neo-colonialists! They lament that Ethiopia is disintegrating unless the reigns of power is not given into their grips asap! However, it reminds us (those old enough to have lived through) the cry of EPRP of “ዲሞክራሲ አሁኑኑ!” and what they subsequently unleashed and its backlash – White terror/red terror blood-letting that killed a generation! And the present outgrowth of this EPRP demon has not learnt an iota from the path of the abyss! If their wish comes true, this time it may not only kill a generation but also kill the country called Ethiopia altogether! ልብ ያለው ልብ ያድርግ!

  4. ሢሣይነሽ መንግስቴ ይህን ጠቃሚ ፅሁፍ በእማርኛ ተርጉመው ስለ አቀረቡልን እናመሰግናለን:: ብዙ መረጃዎችን እንድናውቅ ረድቶናል::

    አቶ ሰርቤሳ ከ. ይህን እጅግ ጠቃሚ ወቅታዊ መረጃ በእንግሊዘኛ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን:: በርሶ ፅሁፍ መርጃ References ሁሉ የቀርበ በመሆኑ ተአማኒነቱን ያጎለዋል:: ሢሣይነሽ በተረጎሙት ፅሁፍ ግን Refernces ቢያካቱት የትርጉሙን ፅሁፍ ይብልጥ የመረጃ ሀይሉን ያጠናክረዋል::

    ሌላው ያየሁት የትርጉም ስህተት ድግሞ የመጀመሪያው ምራፍ ላይ ያለው አመታት (2016 and 2017) ሲሆን የአማርኛው ግን (2018 እና 2017) ይላል ያም ቢስተካከል::

    ሌላው እራተኛው ምእራፍ ላይ ያለው በእንግሊዘኛው November 2016 የሚል ሲሆን የአማርኛው ግን ጥቅምት 2016 ይላል:: ህዳር 2016 በሚለው ሊታረም ይቻላል::

    ፀሀፊውንም ተርጏሚውን እናመሰግናለን::

  5. አብዮት(አብይ) ኣህመድ በተካነበት የኢንሳ መረጃ ሃላፊነት ልምድ በአዝማሪ ከማዘፈን ጀምሮ ሀራካዊ ድራማውን በመለመሉትና ባሳደጉት ወያኔዎች ላይ በማስፋፋት የጦሩን መሪ ሳሞራን በክብር በመሸኘት መከላከያውና ደህነቱን በራሱ ዘር በማደራጀት ፓርቲው ኦዲፒኦን ባለተራ ወያኔ የማድረጉን ዘመቻ ቀጥሎበታል:: ከሁሉም የሚያሳዝነው ዳውድ ኢብሳን ሊቀብሉ ከተማዋን ያጥለቀለቁ ነፍሰገዳዮች ቡራዩ የነበሩ የሌላ ብሄር ዘር ወገኖቻችንን በአስቃቂ ሁኔታ የገደሉት ለፍርድ ይቅረቡ ያሉትን ወጣቶች በረሃ መታሰር የደገፈ ቆይቶ የከተማዋ የራስን ማስተዳደር መብት ይከበር ያለውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በጦር ቅስቀሳ ሲከስ በሜንጫ የሚናገረንን እንመታለን ያለውና ለፍተው ኮንደሚኖ ቤት የሰሩ ወገኖች ቤቱን ከተረከቡ ‘ደም የፈሳል’ ያለውን ጃዋርን ለህግ ከማቅረብ በማቀፍ ለስረተኞቹ ቤት የሰጠ አብይ አህመድ የለየለት ዘረኛ አታላይ ነው::በአጣዬ ስፈረው የነበሩ የኦነግ ጦር በልዩ ሁኔታ መታጠቃቸውን አባ ገዳ ሰንበቶ የመሰከሩት ሳይረሳ በዚያ የተጨፈጨፉትን ወገኖች ሰቆቃ የሚያጣጥል የጦር ኣአዛዥ የተባለ የአብይ ሎሌ በስፍራው መንም የውጭ ሃይል የለም ብሎ ያፈጠጠውን ሃቅ ሲክድ አብይም ያንኑ ያስተጋባል:: ስለዚህ ወገን ሊነቃና ይህንን አደገኛ የአዲሱ ወያኔ የኦሆዲድ ጽንፈኞች የነታከለ ኡማ ምደባን አዲሱ አረጋ ለማ መገርሳ የዲሞግራፊውን ቀመር ሲተነትን ምስጢራቸውን የዘረገፉት ከበቂ በላይ ማስረጃ ስለሆነ በአብይና ለማ “ኢትዮጲያ ሱሴ” መደለያ ሳንዘናጋ
    ዘረኘነትን መዋጋት ይኖርበናል::

Comments are closed.

Share