” የጥለዛ ፓለቲካ ” ፣ሥለ ፍትህ ፣ ሥለ ሠላም ሥለ ዴሞክራሲ ወዘተ ደንታ የለውም  – መኮንን ሻውል  ወልደጊዮርጊስ 

በእርግጥ ይህንን ህዝብ እናቀዋለን?
ይሄ ህዝብ ግን ጠንቅቆ ያቀናል።በምንኖርበት ቀዬ፣ሥለኛ የተሰወረ አንዳችም የለም።
በሁሉም የኢትዮጵያ ከተሞች ና የቀበሌ ገበሬ ማህበሮች ፣   በህዝብ አሥተዳደር ላይ ያሉትን  የግዢውን ፓርቲ  ሹማምንት ፣ ገበናቸው” ቢፈተሽ” የበዙት እልም ያሉ ሰርቆ አደሮችና ሆድ አደሮች  መሆናቸው እርግጥ ይሆናል።
” የሠረቀ ሁሉ ይታሠር ቢባል አዲሥ አባባ    እንኳ ለወህኒ  ቤትነት አትበቃም።”ሲባል ዘረፋው ምን ያህል መንግሥታዊ እንደሆነ ያሳብቃልና!!
   እንዲህም ይባል እንጂ ፣ዛሬም  ቀደም ሲል  የዘረፉ ፣ በየጊዜው  ከአንድ በላይ   ቀበሌ ተሹመው መሬትን  በጓሯቸው እንዳመረቱት ሽንኩርትና ቃሪያ   በተደጋጋሚ የቸበቸቡ ፣ ዛሬም የገዢው ፖርቲ  የቀበሌና የክፍለ ከተማ ሹመኞች ሆነው የሚገኙ እንዳሉ ህዝብ ያውቃል።
     እንዴት ተሾሙ ሲባል?  ” በኢህአዴግ  ድርጅት  ውሥጥ ከከፍተኛ ባለሥልጣን እሥከ ሚኒሥቴር የሥጋ ዝምድና እና የጋብቻ ዝምድና ሥላላቸው ነው። ” በማለት ከትውልድ ቦታቸው ጀምሮ ታሪካቸውን  በተሾሙበት ቀበሌ፣ክፍለ ከተማ፣ወረዳ ወዘተ ያለ ህዝብ  ይተርክልሃል።
( የዝሙት ግንኙነታቸውን ሳይቀር ሲተርክልህ፣ወዳጄ ነጻ ፕሬሥ ያለው ህዝብ ውሥጥ ነው።ትላለህ።)
    ለዚህም ይመስላል ጨረቃ ቤት  እንዲሠራ በሺ ለሚቆጠር ሰው   በተሹመበት ቀበሌ የሸጡ፣በህግ ሊጠዩቁ ይቅርና ፣ ቦታ ቀይረው ያውም በእድገት  የወረዳ ና  የክፍለ  ከተማ ሹመኛ  ለመሆን የበቁት። ( ዛሬ በዛ አካባቢ በችግሩ ሳቢያ ጎጆ ቀልሶ የሚኖረው ህዝብ የሠርቆ አደሮቹና የሆድ አደሮቹ ሰለባ ሆኖል።የበዛው የጨረቃ ቤት ነዋሪ ግን ዛሬም በላያችን ቤቱን አፍርሱ እንጂ ፣ከሰርቆ አደሮች የገዛነውን የጨረቃ ይዞታ አንለቅም ባዮች ናቸው።)
   ይህ ድርጊት ህዝብ በኢህአዴግ  ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ አድርጎታል።ህዝብ ነዋሪ ነውና  በ27  ዓመት ውሥጥ በኢህአዴግ አማካኝነት የመጡበትን ገዢዎች ሥምና ፣በጣት በሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ  በሥልጣን አለግባብ በመጠቀምና በሥርቆት   ወደ  ሚሊዮነርነትና ወደትልቅ ባለሃብትነት  መሸጋገራቸውን ይመሰክራል።
      ህዝብ  የእያንዳንዱን ባለሥልጣን  የተደላደለ ኑሮ ፤ አልጋ በአልጋ የሆነ የሠርቆ እና የሆድ አደር  ህይወት በየዕለቱ ያስተውላል።
   ዛሬ በቋንቋና በዘር መሰላል፣ በህዝብ ሥም ያለይሉንታ በመንደላቀቅና ለመንደላቀቅ በመቋመጥ ፣በደርግ ያከተመውን የብሔር ጭቆና ፣ዛሬም ከ27 ዓመት የኢሕአዴግ   ” የብሔር ብሔረሰቦች አገዛዝ በኋላ እንኳ ጭቆናው እንዳለ እንዲታሰብ በተለያየ መንገድ ከሚጥሩት መሐከል በዋነኝነት ተጠቃሾቹ እነዚህ እንደሆኑም ህዝብ  የሚያወራው የአደባባይ ምሥጢር ኑው።
     ከነዚህ በላይ ህዝቡን የሚገርመው  እና  የሚያሰገው  የሠርቆ አደርና የሆድ አደር  ፖለቲከኞች የመፀሐፍ ማጠብ ተግባር ነው።
   ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ፣ 27 ዓመት ሙሉ የኢትዮጵያ ቆራጭ፣ፈላጭ መንግሥት   ሆኖ  ፣ሥሙን ያለመቀየሩ የትግራይን ህዝብን ጭምር ገርሞት ሣለ ፣ የሌለ የዘር ጭቆና እንዳለ በመቁጠር  ሥሙን እንደ ድሮ ሽፍታ ማሥፈራራዬ በማድረግ ፣ አንዳንዶች  ጤፍ በሚቆላ አንደበታቸው በመታገዝ  ፣ ያኔ ተግባሩን የሚገልፅ ሥያሜ የተሰጠውን ፣   ዛሬ ሁሉም ነገር ተለውጦ  (ልብ በሉ ህወሓት  ከ44 ዓመት በላይ ያሥቆጠረ የነፃ አውጪ ድርጅት ሥያሜ ነው።) “ያንን የነፃ አውጪ ሥም እወደዋለሁ ። እናንተ ከሥሙ ምን አላችሁ?? ሥም ሳይሆን ተግባር ነው ወሳኙ። ”  ይሉናል። ይህ ህዝብን መናቅ እና ያለማወቅን ያለማወቅ ነው። እንኳን ህወሓት  ይቅርና ኢህአዴግም  ከላይ እሥከታች ካልተቀየረ ፣ በነፃ ምርጫ አሸንፋለሁ ብሎ እንዳያሥብ!? እውነቱን በአጭር አማርኛ ለመናገር ህዝብ ዶሮ ማታ ሰልችቶታል።
       ይህንን እውነት የኢህአዴግ ቁንጮ መሪዎችና ካድሬዎቹ አሳምረው ያውቁታል።ይሁን እንጂ   የነሱ ከርስ ካልጎደለና ምቾታቸው እሥካልተናጋ ድረስ ለማንም ለምንም ” ሃጃ ” የላቸውም።ይሁን እንጂ በጊዜ ሂደት አወዳደቃቸው እጅግ የከፋ ይሆናል። “እንደሠራ አይገልምና!!”
      ዛሬ እንዳማረባቸው ፣ በዚሁ ቁመና ነገ አይገኙም። እነዚህ በነፃ አውጪ ሥም በዙሪያቸው ጠባቂ ቀጥረው   እያሥፈራሩ የሚኖሩ፣ ነገ ያ የቀጠሩት ነፍጥ ታጣቂ  ፣ለማይረባ ሳንቲም ከነሱ ጎን መቆሙና ማሥፈራሪያ መሆኑ እጅግ አሣዝኖት የጠመንጃውን አፈሙዝ ፣ከህዝቡ ወደራሣቸው ሊያዞርና  “በነፃ አውጪነት ሥም መነገድ ይብቃ !!”ሊል ይችላል። የዛን ጋዜ “እንደ ሠራ አይገድል!!”ማለት  ምን ማለት እንደሆነ በቅጡ ይገባቸዋል።
       በመላ ኢትዮጵያ እነዚህ የነፃ አውጪነትን ሚና በጠመንጃ አፈሙዝ አሥገዳጅነት እንጫወታለን የሚሉ ፣  “ጥሬ በሚቆላ ምላሣቸው ” የዋሁን እና የለት ጉርስ የዓመት ልብሥ የሌለውን በራሳቸው ባልሆነ በሀገርና በህዝብ ሀብት እየደለሉ ፣ እንደ ፌውዳሎቹ ሰጪና ነሺ በመሆን ህዝቡ እነሱ ከሌሉ የምግብ ዋሥትና እንደሌለው በማሳየት ፣ ጌቶቼ ሺ ዓመት ንገሱልን እንዲላቸው ፣ እየጣሩ ነው። ይህ ደግሞ ከቶም የሚሆን አይደለም። የልመና ሥንዴ ና አፈና  ለዛሬ የሚሰራ እንጂ የህዝቡን ” እሥከ ሙቼ በምፅዋት ? ”  የሚለውን የውሥጡን የኩሩ ህዝብ  ጥያቄ በዘላቂነት የሚፈታ አይሆንም።   ዛሬ እነዚህ ነፃ አውጪ ነን ባዮች እየተጫወቱ ያሉት ፣የህፃናቶች ጫዋታ ነው።የኳሥ አበደች ጫወታ።ፖለቲካቸውም የኳሥ አበደች—“የጥለዛ ፖለቲካ ነው”
   ይሄ የኳስ አበደች ፖለቲካ ነው።ይሄ ጥለዛ ነው።ይሄ ፍፁም መረንነት ነው።የሜዳ ወሰንም ሆኑ ዋና ዳኛ  ወይም መስመር፣ዳኞችም የሌሉበት ነው።” እኔ እወደዋለሁ።እኔ እጠላዋለሁ።በሚል የግል ሥሜት ቅኝት ፣በግል ሥሜት ተገፋፍቶ ኳሥ ጥለዛ ነውር ነው። በነፃነት የሚኖረውን ህዝብ ነፃነት ማሳጣት እና በውሥጠ ታዋቂነት “ጌቶች” መሆንን የሚያውጅ ፣  መጥፎ  የፓለቲካ  ጫዋታ ነው።
      ይህ የፓለቲካ  ጫወታ አሥቀያሚ ና በደሃው ህዝብ ላይ የመቀለድ ጫወታ ብቻ ሣይሆን ፣ ህዝብ ዘላአለም ዓለሙን ከድህነት እንዳይወጣ ፣ለሚፈልጉ ፣የኢትዮጵያንም  ብልፅግና ለማይወዱ  መሣቂያና መሣለቂያ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ቆሻሻ  ጨዋታ ነው።
     የኢትዮጵያ ህዝብ   ይህንን የኳሥ አበደ፣የጥለዛ ፖለቲካ አይቶ  ሞራል ለመስጠት ይቅርና መከሰቱ በራሱ አናዶታል። ።ጥለዛን ህፃናት እንጂ አዋቂዎች ከቶም አይመርጡትምና !!
     በመላው ኢትዮጵያ በየፈርጁ በሥራ ላይ ተሠማርቶ የድካሙን ፍሬ እየተመገበ ኑሮን ” በሰውነቱ ተከባብሮ ” የሚኖራት ዜጋ ፣ይህንን የሂትለሮችን አጥራዊ አሥተሣሠብ ነፍሱ ሥለምትጸየፈው ከቶም የዘረኞችን የኳሥ አበደች ፖለቲካ ከቶም አይደግፍም።
     የኳሥ አበደች የጥለዛ ፖለቲካ  ደጋፊዎች ፣ “ሠርቆ አደሮች ና ሆድ አደሮች ” እንጂ ፣ሠርቶ አደሮች አይደሉም። እነዚህ ሠርቆ አደሮች   በዘውግ ማሊያ አሸብርቀው፣ የሰውን ተመሳሳይነት እና አንድነት ክደው ፣ የፖለቲካውን ኳስ በየክልላቸው እያሣበዱ የሩዋንዳውን የፋሺዝም ተግባር በእኛ ሀገር እንዲደገም  አበክረው እንደሚሰሩ እያሥተዋልን  ነውና አሻጋሪው መንግሥትም ሆነ የዜግነት ፓለቲካ(የዜግነት ፓለቲካ ማለት የመደብ ፓለቲካ ነው የሚሉ አሉ።ሲትዝን እና ክላስ በየት እንደሚገናኙ ያብራሩልን።)  አራማጆች  ቆም ብለው ማሰብ ይጠበቅባቸዋል።
  ፅሑፌን በዚህ ግጥም እቋጫለሁ።
ተናገር ኢትዮጵያዊው
ተናገር አንተ ኩሩ
አንተ እኮነህ ጥንትም
የአለም መምህሩ።
ይወቁ ፣ይረዱ
ከታሪክህ ይማሩ።
“በቅኝ ያለመገዛትህ
ነው ወይ ?
የድህነትህ ምሥጥሩ??”
“ይገርማል!እንደዘበት
እንደው እንደዋዛ
………………………
ነፃነት መናኛ ሲሆን
በህሊና ድንዛዛ!!
በህሊና በተዘራ
የጥገኝነት አዝመራ…
ከክብሩ ይልቅ…
ድህነትን …
አጥብቆ በሚፈራ።
ባርያ ለመሆን በተዘጋጀ
ስለሆድ ሠርክ በሚያወራ።
………………………
አልሰምቶም እንደሆን
ንገረው ……ሀገሬ
ለክብርህ ና ለነፃነትህ…
ማንም ሳያስገድድህ…
ተፋልመህ እንደበቃህ…
እንሆ ለዛሬ።
ባለማወቅ ቢናፍቅም
መገዛትን በፀጋ፤
አንተ ግን …ዛሬም…
በተግባር ታሳያለህ
ለክብርህ ና ለነፃነትህ
ግንባርህን ሰጥተህ
በወኔ እንደምትዋጋ!
ግና ……
ጠያቂው በውል ይገንዘብ…
መገዛት እንዳልሆነ
የሥልጣኔ ምንጩ
ባርነት እና ጭቆና እንደሆነ
ህይወትን አጨልሞ
ተስፋ አስቆራጩ።
እወቅ የሀገርህን ህዝብ
ቆም ብለህ አስብ
አስተውል
ተመልከት
በቅጡ ተረዳ
ጆሮ ካለህ ስማ፤
እንኳን እኛ …
ወንዛችን ደግነው
ባዳን የሚያበለፅግ
መግቦ የሚያኖር
ውሃም ሳያስጠማ።
ካላወቀ ይወቅ
ሰለአክሱም
ስለላሊበላ!!
ሥለ እንግዳ አክባሪው
ስለዚህ ኩሩ ህዝብ …
ቤት የእግዜር ነው ብሎ
እግር አጥቦ …
ሙክት አርዶ
“አፈር ሥሆን “እያለ
በልበ ቅንነት
ሲለግስ የኖረ …
ሳይሰስት እያበላ!!
አልሰምቶም እንደሆን
ንገረው ሀገሬ
ህይወትህን ሰጥተህ
ደምህን አፍሰህ
አጥንትህን ከስክሰህ
ንብረትህን አጥተህ
ነፃነትን ለትውልድህ
በኩራት ያወረስህ
አንተ እኮ ነህ!!!
ደግሞም ይማር
በጥልቀት ይረዳ
ሀገር ነበረች
ዓለምን የምትረዳ።
ኢትዮጵያ እንደነበረች
የሥልጣኔ አውራ
በዕውቀት ና በጥበብ
የመጠቀች…
ከፍ ብላ የምትታይ
ዝናዋ እስከምድር ዳርቻ
ከአድማስ በአሻገር የተወራ።
አልስምቶም ከሆነ
ስለጀግንነትህም ንገረው…
ስለቅርቡ ታሪክ
ስለጉንደት ጉንዳጉንዲ
ስለአንፀባራቂው ድላችን
ስለዛ ሥለአደዋ!!
ኢትዮጵያ መሆኖን
ወደር የማይገኝላት
የጥቁር ህዝብ መመኪያ
የጀግኖች ቁንጮ
የማትበገር ጀግናዋ።
አልሰምቶም እንደሆን
ይገንዘብ…
ምድረ ግብዝ
ምድረ ሞኝ…
ምድረ ተላላ፤
የሰብቅ
የሀሜት
የክፋት ደቀመዝሙር
የውሸት አበጋዝ
የውሸት ቱልቱላ።
በነጭ ያለመገዛቱን
በእኩይ መንፈስ ተረድቶ
ለነፃነት ሳይሆን
ለሆዱ አድልቶ
“አድዋ አንባላጌ
ጉንደት ጉንዳጉንዲ…”ብሎ
መናገር ሲጀምር
ካለው “ወግ ጠራቂ…”
በእሱነቱ ኮርቶ
በነጭ ሳይገዛ
በኖረ ሀገሬ…
ሥምና መስዋትነቱን
ካ-ጠ-ለ-ሸ-ው…
ጥገኛው በወሬ
አስመስክሯል ና…
አልሰምቶም እንደሆን
በግልፅ በአደባባይ
መገዛት እንዳማረው
ነፃነትን እንደጠላ
ሱሪውን አስወልቀህ
ራቁቱን ስደደው
ጎንበስ ብሎም ይጋጥ
እንደከብት ሣር ይብላ።
ሰው ሆኖ ተፈጥሮ …
በሰው ላይ ከኮራ ።
ናቡከደናፆርን ያዋረደው
ይኽ ትዕቢት ነውና!!
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
መሥከረም
2009 ዓ.ም
ተጨማሪ ያንብቡ:  ደህንነት፤ አንድነትና ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ኃላፊነቶች - በቀለ ገሠሠ (ዶ/ር)

1 Comment

  1. TPLF killed two prominent leaders of the Gambella People’s Liberation Front and took control of the Gambella People Liberation Front military Camp in Gambella, Ethiopia.

    Few years ago until the change of (TEAM LEMMA) ,won and Abiy Ahmed started leading the country, the Gambella People’s Liberation Front had many military camps in Gambella that operated to drive out TPLF land grabbers such as Azeb Mesfin out of Gambella.

    TPLF used the opportunity now at the time when one Defence Minister Aisha was being demoted and when one Ato Lemma Megersa was being promoted as the new Defence Minister of Ethiopia, TPLF used the opportunity to take it’s revenge against the Gambella People’s Liberation Front by killing two of it’s prominent leaders of the organization.

Comments are closed.

Share